ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አሳዛኝ መረጃ ከአርሲ‼️

በአርሲ የኦርቶዶክስ ግድያ አሁንም እንዳልቆመ መረጃዎች እየወጡ ቢሆንም፤ አገዛዙ በበኩሉ ይህ ግፍ በሚፈፀምበት አካባቢዎች ላይ መረጃዎች እንዳይወጡ ኔትወርክ ሲስትም እየጠፋ ይገኛል ። ለአብነትም፤ ከሰሞኑ በአርሲ የተለያዩ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን እገታና ግድያ ተፈፅሞ መረጃው እንዳይወጣ ተደርጓል ።

በአርሲ ዞን ጀጅ ወረዳ በሰጉሬ በወሸባ.... አንጎዳቼ አካባቢ በሚገኙ አካባቢዎች የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያንን፤ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ ም ድረስ ከ16 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ታፍነው ተወስደው የነበረ ሲሆን ዘጠኝ ኦርቶዶክሳውያን #ተገድለዋል ።  ሌሎቹ ሰዎች ደግሞ በገዳዮቹ  እጅ #ታፍነው ያሚገኙ ሲሆን በአርሲ በየቀኑ ኦርቶዶክሳውያን እየተገደሉ ነው ። ይህ ዜና ታፍኖ ሳይነገር የቀረ ያልተዘገበ ነው ።በጣም ብዙ ድምፆች ታፍነዋል  💔  🖤
😢2
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የግንባር መረጃዎች!

ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር እና ነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር ጥምረታዊ ድል

የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት የሆነው አማራ በታኝ(አድማ ብተና)  መነሻውን ከወረታ፣ ከአምበሳሜ እና ከሐሙሲት ከተሞች አድርጎ መዳረሻውን ''ዋንዛዬ''ን  በቅዠት አቅዶ ተንቀሳቅሶ ነበር። ነገር ግን የጠላት መረጃ ቀድሞ የደረሳቸው የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር 02 ብርጌዶች(ጣና ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ) እና ነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር ይህንን ቅጥረኛ ታጣቂ ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ  ''አውራ ተራራ'' ላይ መብረቃዊ ጥቃቴ በመፈጸም ጀምረውታል። ውጊያው አድማሱን አሥፍቶ እሥከ ወረታ ዙሪያ እና ጉማራ ከተማ ድረሥ ጠላት በአማራ ልጆች ሲመታ ውሏል።

መጀመሪያ የገባው የአገዛዙ ታጣቂ የአማራ ፋኖን ክንድ መቋቋም አቅቶት አጋዥ ኃይል ከባሕር ዳርና ከአምበሳሜ ሲያክል ውሏል። በመጨረሻም ጠላት በቁጥር ላይ ቁጥር ቢጨምርም የአማራ ፋኖን ክንድ መቋቆም ባለመቻሉ በአቅራቢያው ካሉ ከተሞች አለኝ ያለውን ጥምር ኃይል በማምጣት የነበረውን ኃይል ከቀኑ 11:30 በሙሉ ጠቅልሎ ወደ አምበሳሜና ባሕር ዳር እግሬ አውጭኝ ብሏል።

በዚህ ውጊያ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ፣ አካላዊና ሞራላዊ ኪሳራ ደርሷል። ራሱን በመከላከያ ሥም የሰየመው የአቢይ አሕመድ ታጣቂ  በ11ኛው ሠዓት በደቂቃዎች ምት 10ሩ ሲደመሰስበት 09 የሚሆኑት ቆሥለውበታል።

ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር
ጥቅምት 26/2018ዓ.ም

የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከአምበሳሜ ከተማ ወደ ሐሙሲት ከተማ በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀስ የነበረ ታጣቂ በ''አምበሶ ብርጌድ'' ''ገነት ወንዝ'' ላይ  ከቀኑ 6:00  በተወሰደ የታቀደ የደፈጣ ምት አንዱ ፓትሮል ላይ የነበሩ አካላት በሙሉ ሲደመሰሱ የነፍሥ ወከፍ መሳሪያዎችም በምርኮ ተገኝተዋል።

ጉና ክፍለ ጦር/አንዳ ቤት ብርጌድ
ጥቅምት 26/2018ዓ.ም

የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት አለኝ ያለውን ሜካናይዝድ  እና እግረኛ ኃይል በመያዝ መነሻውን ከአንዳቤቷ ወለሽ በማድረግ ወደ ገነተ ማርያም ሲንቀሳቀስ የአንዳ ቤት ብርጌድ አካል የሆነችው ረመጧ ሻለቃ 02 ጠላትን ከጠዋቱ 2:30 ጀምረው እሥከ ቀኑ 7:10 ሲያርበደብዱት ውለዋል። የአማራ ፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የፋሽሥቱ ጥምር ጦር ንጹሐን አማራ አርሶ አደሮችንና ቀሣውሥትን በጅምላ ሢገርፍና ሢያሥር ውሏል። የአርሶ አደሮችን ሰብልን ሲያወድም ቤተክርሥትያናትን ኢላማ አድርጎ በከባድ መሣሪያ ሲደበድብ ውሏል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
1🙏1
አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ በበርካታ ቀጠናወች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠነ ራሱን በሰው ሀይል እያጠናከረ ያለ ሲሆን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ በመደራጀትላይ ያለችው በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን በቀን 27/2/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁን ይታወቃል::

ይህን ሁኔታ ያየው የደሴ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና እና የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በቀን 28/2/2018 ዓ.ም በደሴ ዙሪያ ወረዳ የሚቀሳቀሰውን ፋኖ አጠፋለኩ ብሎ የመጣው የመከላከያ ሰራዊት ተብየውና የአድማ ብተና ሚኒሻና ፖሊስ ጥምር ጦር በሁለት አቅጣጫ መነሻውን ከደሴ አዲርጎ በጉጉፍቱና ከደሴ የተነሳው በአስግዶ በኩል በሁለት አቅጣጫ መቶ ፋኖ በሚቀሳቀስባቸው ቦታወች የገባው ጥምር ጦር

አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃና አዲስ ተመራቂ ሰልጣኖች በምርቃት ማግስት የመጣውን ጥምርጦር ቀድሞ መረጃው ስለደረሰን አጥትመስበሪያና እሁዲት ተብለው የሚጠሩ ቦታወችላይ ደፈጣ በመያዝ የመጣውን ጥምርጦር በላጎ ተወርዎሪ ሻለቃ ሙትና ቁስለኛ አርጎ መልሶታል በዚክም መብረቃዊይ ጥቃት ሁለት መኪና እሬሳውንና ሶስት አቡላስ ቁስለኛውን ከደሴና ኮምቦልቻ ከኩታበር ወረዳ ተጨማሪ ሀይል አምጥቶ ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ እግሬአውጭኝ ብሎ ወደ ደሴ ከተማ ተመልሶ ገብቷል::

መዳረሻችን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልወና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ህልውናችን በተባበረ ክዳችን
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
2🙏1
በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሜክሲኮ በምርመራ ስም ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ለሚገኙ አማራዎች ድምፅ እንሁናቸው!

ጠበቆች ፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት ፣ ቀይ መስቀልና ጋዜጠኞች በስፍራው ተገኝታችሁ እንድትጎበኟቸውና ድምፅ እንድትሆኗቸው ተጠይቃችኋል።

በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውና ሕክምና ተከልክለው በስቃይ ከሚገኙት በርካታ የማንነት ፣ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች መካከል ፦

1. ተመስገን አቤ፣
2. ያለም ሰው፣
3. ብሩክ እና
4. አለም የተባሉ እስረኞች ይገኙበታል።

ፍትህ ለሁሉም!

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 28/2018)
በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ እስራኤል መስፍን ፍ/ቤት ቀርበዋል ፤ ተከሳሽ ልዑል እማዩ በአንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ስለተፈፀመበት ድብደባ አቤቱታውን ለፍ/ቤት በጽሁፍ አቅርቧል ፤ ችሎቱ እንዳይናገር ከልክሎታል።  

በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ እስራኤል መስፍን ጥቅምት 26/2018 ፍ/ቤት ቀርበዋል ፤ በእለቱም ተከሳሽ ልዑል እማዩ በሚኖርበት በቂሊንጦ ማ/ቤት በአንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ጥቅምት 20/2018  ስለተፈፀመበት ድብደባ አቤቱታውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በጽሁፍ አቅርቧል።

ይሁን እንጅ ተበዳይ ልዑል እማዩ ስለ አቤቱታው በቃል ለመናገር እድሉ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ችሎቱ እንዳይናገር ከልክሎታል። 
 
መዝገቡ የተቀጠረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ቢሆንም ምስክሮችን አሟልቶ ባለመቅረቡ ተከሳሾች ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በዚህም መሰረት ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን አሟልቶ በመቅረብ ለታህሳስ 13/2018 እንዲያስመሰክር ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በመዝገቡ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው የፖለቲካ እስረኛው ልዑል እማዩ በእለቱ ለፍ/ቤቱ በጽሁፍ ካመለከተው አቤቱታ ላይ እንደገለፀው በሚኖርበት ቂሊንጦ ማ/ቤት በአንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ጥቅምት 20/2018 በዱላ እና በቦክስ ድብደባ እና የግድያ ዛቻ ተፈጽሞበታል።

በጥቃቱም አካላዊ እና የስነ ልቦናዊ ጉዳት የደረሰበት ስለመሆኑ ለችሎቱ አሳውቋል።
 
ጥቅምት 25/2018 በተጻፈ በዚሁ ደብዳቤውም ስለደረሰበት ድብደባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊዎች ተገቢ ማጣራት እንዲያደርጉ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ነው የጠየቀው።

የወንጀል ድርጊት የፈፀመው አባልም ተይዞ በሕግ ፊት ቀርቦ እንዲጠየቅለት ነው ተበዳዩ ያመለከተው። 

ልዑል ጥቅምት 21/2018 በተጻፈ ማመልከቻውም ለቂሊንጦ ማ/ቤት አስተዳደር የደረሰበትን ጥቃት አሳውቆ ፍትህ እንዲሰጠው መጠየቁም ተመላክቷል።

የቂሊንጦ ማ/ቤት በተለይም ከነሃሴ 2017 ጀምሮ ከሕግ ውጭ በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀ ነው ፤ በሕግ እስረኞችና በቤተሰቦቻቸው ላይም ከማ/ቤቱ አባላት ጋር በመሆን ሰብአዊነት የጎደለው ፍተሻ እያካሄደ ነው ፣ እስረኞችን በሌሊት እየፈተሸ ነው ፣ እያጀበ ነው ፣ በየትኛው ሕግ ነው ይህ ሊሆን የቻለው? እየተፈጠረ ላለው ችግርስ ማን ተጠያቂ ሊሆን ነው በሚል በተለይም ጥቅምት 18/2018 በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ ተከሳሾች እንዲሁም ከችሎቱም ጭምር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ አምነው ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።
 
ይኸውም ከፌደራል ፖሊስ ጋር በፍተሻ እና በእጀባ አብረው እንዲሰሩ የቃል አቅጣጫ ከበላይ እንደተሰጣቸው ጠቅሰው በፌደራል ፖሊስ ችግር ከተፈጠረ ማ/ቤቱ ኃላፊነቱን ይወስዳል ማለታቸው ይታወቃል።

©
ፋሽስቱ አገዛዝ በአንጎት ወረዳ የግለሰብ ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና እንስሳቶችን አወደመ።

ስርዓቱ የግለሰብ ባጃጅ ያቃጠለ ሲሆን፤እንስሳዎችን ደግሞ ተኩሶ ገሏቸዋል።

ጥቅምት 29/2018 ዓ/ም የፋሽስቱ ስርዓት
ከአስር በላይ ላም፤በሬና በጎች በአገዛዙ ሰራዊት ሲገድሉ፤አንድ ባጃጅ ደግሞ ሙሉ በሙሉ አቃጥለውታል።

ለብልፅግና ስርዓት የአማራ ህዝብ አይደለም እንስሳቱም፤እፅዋቱም፤ንብረቶችም ጥላት ናቸው ብሎ የዘመተባቸው ስርዓት በአንጎት ወረዳ የህዝቡን ንብረት በዛሬው እለት አውድሟል።

ባጃጆች ማንነት አላቸው፤እንስሳዎችም አማራ ናቸው። የአማራ ህዝብ ህይዎቱ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውም መውደም አለበት ብሎ የሚያስበው የበሻሻው ስብስብ አፀያፊ ድርጊት በእንስሳቶችና በተሽከርካሪ ንብረቶች ላይ ፀያፍ ድርጊት ፈፅሞባቸዋል።

መዳረሻችን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልወና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ህልውናችን በተባበረ ክዳችን
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ
ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና የምንሊክ እዝ - ወታደራዊ አዛዥ ድርሳን ብርሃኔ :
- ዋና አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጆ እና
- ፋኖ አበበ ፈንታው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ፋኖ በሰሜን ጎንደር አዳርቃይ እና ዛሬማ አካባቢ ታላቅ ድል ፈፅሟል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ  የራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር ድብ ጠለምት ተከዜ እና ጭና ክፍለጥር በጡት ቆራጩ የአብይ አህመድ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ ድል መቀዳጃታቸዉን አስታዉቀዋል።

ከጥቅምት 26/2018 ዓ.ም እስ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም ድረስ በነበረዉ እልህ አስጨራሽ አዉደዉጊያ በመደርዘን የሚቆጠር የስርአቱ አገልጋይ ሰራዊት ድል ተደርጓል።

የአገዛዙ ብልፅግና የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሶስት ክፍለጦር ሰራዊት በአዳርቃይ እና ዛሬማ ቢሰማራም አብዛኛው ሰራዊት መደምሰሱ ተገልጿል።ለአራት ተከታታይ ቀናት በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ አዉደዉጊያ ከ90 በላይ የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ 80 የነፍስወከፍ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ደግሞ ምርኮ ተደርጓል።

ጥቅምት 27 ለጥቅምት 29 አጥቢያ ሌሊቱን የድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦርን የከበበዉ የአገዛዙ ሰራዊት ከፍተኛ የሆነ ሽንፈትን አስተናግዷል።በለሊቱ በተደረገዉ አዉደዉጊያ ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሰራዊት መደምሰሱን የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ እሸቱ መለሰ ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግሯል።

አዉደዉጊያዉ ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፋኖ በርካታ ወታደራዊ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል ።በፋኖ ከፍተኛ ምት ያስተናገደዉ እና አብዛኛው ሰራዊት የተደመሰሰበት የብልፅግ ጡት ቆራጭ ሰራዊት በሰላማዊ ዜጎች ሀብት እና ንብረት ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።
የአርበኛ ታድሎ ደሴ ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ

አርበኛው፣ የትሕነግ ሕወሓት ወታደር አከርካሪ ሰባሪው፣ የፋሽሥቱ አቢይ ሸኔ ወታደር እግር እሣት፣ የጎጠኞች መድኃኒቱ፣ የአጣዬው ዘማቹ፣ (የነአሥቻለው ደሤ፣ ዘማች ሞላ፣ ዳንኤል፣ መልኬ፣ ቢሰጥ፣ አሌክሥና መላሽ) የትግል ጓዳቸው፣ የዳውንትና ጋሸና ምሽግ ደርማሽ፣ የደብረ ዘቢጡ ኮንክሪት ምሽግ አፈራራሽ፣ የአሣምነው ፅጌን አላማ ተግባሪ፣ የአጣዬው ዘማች፣ የተጎዳው አማራ የፍትሕ ዘብ፣ የራያው በላጎ ምሽግ ሰባሪ፣ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ቀኝ እጅ፣ የነበዕውቀትና ቻይና ዕውነተኛ የትግል ጓድ፣ የብአዴኖች መድኃኒት፣ የአማራ ሕዝብ ሕልውናዊ ትግልን በውል የተረዳ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ቀኝ እጅና ራዕይ ተጋሪ፣ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አባልና አብሪ ኮከብ ታጋይ ለነገደ አምሐራዊ ነጻነቱ በክብር መሥዋዕትነትን የተቀበለ ዕንቁ

ጥቅምት 28/2017ዓ.ም ከሰዓት የጠላት ጦር ከደብረ ታቦርና ከወረታ በአለም በር በኩል ከጀርባ ፋኖን ሊወጋ ተንቀሳቀሰ። የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ቃኝ ሻለቃም ለ4 ተከታታይ ሠዓታት እልህ አሥጨራሽ ውጊያ አድርገው በውሥን የአማራ ፋኖ የአቢይ መከላከያ ወደ ደብረታቦር እንዲፈረጥጥ አደረጉ።

ከደብረ ታቦር የመጣው መከላከያ ከአማራ ፋኖ ጋር ሲገጥም በሌላ አቅጣጫ አማራ በታኙ አድማ ብተና የፋኖ ቤተሰብ የሆኑ የቁም ከብቶችን(በቁጥር 23) በምን ታመጣላችሁ ወደ ደብረታቦር እየነዳቸው ነበር። በእብሪት የተወጠረውን አማራ በታኝ በትኖና 23ቱንም ከብቶች ከእገታና ከመታረድ ታድጎ በመሐል አለም በር ከተማ ወደ መዳረሻቸው እየመለሷቸው እያለ ከወረታ የመጣው የአቢይ መከላከያ ገጠማቸው።

አርበኛው ጠላቶቹን ከረፈረፈ በኋላ በጀግንነት መሥዋዕትነትን ተቀበለ። የጀግና ሞቱ ክብሩ ነውና አርበኛው ጠላትን ረፍርፎ በአማራዊ ጀግንነት በክብር ሰማዕትነትን ተቀብሏል። አሁን አንድ አርበኛ ታድሎ ደሤ በእልፍ አእላፋት ታድሎዎች ተተክቷል።

በዕውነት ሥለ ዕውነት ለመናገር ይህ ዋጋ እየተከፈለለት ያለ የአማራ ትግል በጎጠኞች እንዲቆሽሽ ለናኖ ሰከንድ ልንፈቅድላቸው አይገባም። ፀሐይ የመግባት የመውጣቷን ያክል የአማራ ትግልም እንደሚያሸንፍ ቅንጣት ታክል አንጠራጠርም፤ ፩ አምሐራ ያሸንፋል

አርበኛ ታድሎ ደሤ አማራ ሆኖ ተፈጥሮ፣ ለአማራ ታግሎ፣ አማራ ሆኖ በክብር አልፏል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ነፍሥ ሔር ወንድማለም

@ሀቅያለው አለባቸው
በአፋብኃ በላይ እዝ ሜጄር ጄኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ