በመቄት ወረዳ በተደረገ ውጊያ ከ25 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ!
በውጊያው፡ በአገዛዙ በኩል አራት ዲሽቃ እና ሞርተር እንዲሁም ሌሎች የቡድንና ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቀ አንድ ክ/ጦር ሰራዊት የተሰለፈ ሲሆን፡ በፋኖ በኩል ደግሞ ክንዳቸው እሳት የሚተፋ የአንድ ሻለቃ አባላት ተሰልፈው በጥቂት ኃይል ትልቅ ድል ተቀዳጅተው መዋላቸው ተነግሯል።
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ሰይድ ክ/ጦር ስር የሚገኙት ክንዱ አሻግሬ ሻለቃ አባላት ዛሬ ጥቅምት 27/2018 ዓ/ም በመቄት ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ፡ 10 የአገዛዙ ወታደሮችን ሲገድሉ ከ15 በላይ የሚሆኑትን ማቁሰላቸውን ዕዙ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
በውጊያው በአገዛዙ በኩል አራት ዲሽቃ እና ሞርተር እንዲሁም ሌሎች የቡድንና ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቀ አንድ ክ/ጦር ሰራዊት የተሰለፈ ሲሆን፡ የክንዱ አሻግሬ ሻለቃ አባላት ግን የሰራዊት ብዛት እና የመሣሪያ አይነት ብቻ ለድል እንደማያበቃ በማሳየት የአገዛዙን ኃይል አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል ነው ያለው ዕዙ ለጣቢያችን በላከው መረጃ።

🙏1
ሞት እና ዕድሜ ልክ በሚያስፈርድ ፍርድ ፤ ዕቃቤ ሕግ ፣ ሕግን በመቃረን ማስረጃ አቀረበ!
በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ አምሳ አንድ (51) የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ቀርበው ነበር።
ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምጽ ቅጂ በማስረጃነት በፍርድ ቤት አቅርቦ ፣ የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ላይ ሞት እና ዕድሜ ልክህ ለማስፈረድ ካለው ፅኑ ፍላጎት በመነሳት ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረቡ በችሎት ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ እና ክርክር ተነስቷል።
ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምጽ ቅጂ ከዚህ ቀደም ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አቅርቦ በማስረጃነት እንዲያዝለት ያቀረበውን ጥያቄ ፤ የተከሳሽ ጠበቆች ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምፅ ቅጂ በምን አግባብ ነው ?! ጠለፋውን ለማከናወን የሚያስችል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለው ወይ ?! በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ፤ ዐቃቤ ሕግ በሰጠው ምላሽ ከ2 ዓመት በፊት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አውጥቼ ነው ጠለፋውን ያደረጉት በማለት ምላሽ በመስጠቱ ጠለፋ የተደረገበት መዝገብ እንዲቀርብ በተደጋጋሚ ጊዜ ቢቀጠረም ፤ መዝገብ ጠፍቷል የሚል ምላሽ ከፍርድ ቤት ሪጅስትራል እና መዝገብ ቤት ተገልጿል ።
ይህ ከሆነ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ከፍርድ ቤት አመራሮች ጋር በመነጋገር ፤ የጠፋው መዝገብ በሕግ ወጥ መንገድ እንዲደራጅ ካስደረገ በኋላ ፣ መዝገብ ጠፍቷል ከተባለ ከ2 ዓመት ከ9 ወር በኋላ ፤ እንደ አዲስ ተደራጅቶ በመቅረብ በችሎቱ ውስጥ በተከሳሾች በኩል ከፍተኛ ውዝግብ ተቀስቅሷል ።
ይህም በመሆኑ ፤ ችሎት ከቀጣይ ቀጠሮ በኋላ ከአመራሮች ጋር በመነጋገር በፕላዝማ እንዲሆን አደርጋለሁ ። በማለት ችሎቱን ለመበተን የሞከረ ቢሆንም ፣ በተከሳሾች እና በጠበቆቻቸው በኩል በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያየት እንስጥ በሚል ችሎቱን ቢጠይቁም የቀረበው ማስረጃ ሚስጥር በመሆኑ አንስጥም የሚል ምላሽ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል ።
የተከሳሽ ጠበቆች ፤ ደንበኞቻችን ሞት እና ዕድሜ ልክ በሚያስፈርድ ፍርድ ተከሰው ክርክር እያደረግን ነው የስልክ ጠለፋ ለማድረግ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያስፈልጋል ፣ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ የተደረገ የስልክ ጠለፋ ከሕግ አግባብ ውጪ በመሆኑ ተከሳሾች ሊጠየቁበት አይገባም ፤ ዐቃቤ ሕግ እንዲያቀርብ የተጠየቀው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመሸሸግ የፈለገው በእኛ በኩል የምናቀርበው መከራከሪያ የሚደገፍ ስለሆን ነው። መዝገቡ እንዳይቀርብ የተደረገው በማለት ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል ።
የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ፤ ለችሎት ምሬት እና ብሶት ባዘለ መልኩ ፤ በአማራዊ ማንነታቸዉ እንዲሁም በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለምን ብለው በመጠየቃቸው ብቻ ፤ እየደረሰባቸው ያለው ፍርድ ገምድል አካሄድ በችሎት አምርረው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተቃውሞአቸውን አስምተዋል።
በዚህም ምክንያት ችሎት በፍትሕ ጠያቂዎች ፣የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች እና ፍትሕን በሚደፈጥጡ መካከል ፤ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ተፈጥሯል ።
ፍርድ ቤት የውዝግብ ውጥረት እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ፤ ለኅዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን ፤ከወዲሁ ችሎት በፕላዝማ እንደሚሆን እና የተከሳሾችን ፍርድ ቤት ቀርቦ የመከራከር መብት የሚጋፋ ውሳኔ ሊሰጥ እንደሚችል ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሰጥቷል ።
©ይድነቃቸው ከበደ

❤1😢1💔1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር
ሰበር የድል ዜና!!!
በመተማ ወረዳ 3ኛ ቀኑን ያስቆጠረው አውደ ውጊያ በድል እንደቀጠለ ይገኛል።
የአገዛዙ ሀይል ከምዕራብ አርማጭሆ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለጭማሪ ከቀጠናው ለመግባት ሙከራ ቢያደርግም ፣ በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ ባደረጉት ጣምራዊ ልዩ ኦፕሬሽን ከጥቅምት 25/2018 ከቀኑ 9:00 ላይ የጀመረው አውደ ውጊያ እስከ ጥቅምት 26/2018 ሙሉ ቀኑን እስከ ምሽት 12:00 ስአት ፣ መውጫ መግቢያ አጥቶ ከፍተኛ ሙትና ቁስለኛ ከማስተናገዱ ባሻገር የደረሰበትን ከፍተኛ በትር መቋቋም ሲያቅተው በማታ ስአት እግሬ አውጭኝን ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ድምጡን አጥፍቶ ከታፈነበት ቦታ ወጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሽንፈት ያላዳነውን የድረሱልኝ ታፍኛለሁ ጩኸት ለማገዝ ከመተማ የተነሳው የአገዛዙ ጥምር ሀይል አሁንም ላንተስ ማን ይዞልሀል አይነት ሌላ ያልተጠበቀ ከባድ መብረቃዊ ጥቃት በነበልባሎቹ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ተካ ብርጌድ በአርበኛ ደሴ ተገኘ ስምሪት ሰጭነት ከመተማ ወጣ ብሎ ጓንግ ከምትባል ቦታ ላይ ይህን አረመኔ አራጅ ቡድን በዛሬው እለት ጥቅምት 27/2018 ከጧት ጀምሮ አይቀጡ ቅጣት እየቀጡት ይገኛሉ።
በጥቅሉ ባለጊዜ ነኝ ባዮች የዘር ፓለቲካ አራማጆች የኦሮሙማ ስርአት አራጊ ፈጣሪዎች በየ ጊዜው በአማራ ላይ የሚዶሉቱትን ተለዋዋጭ የጥፋት ሴራ እና ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ በጭፍን ጥላቻ ህዝባችን ለመሰልቀጥ ያዘጋጁት በመከላከያ ስም የሚነግደው የስርአቱ አስፈፃሚ ከየትም መጣ ከየት ወደ ቀጠናው መግባትም ሆነ ከገባም መውጣት እንደማይችል ፣ በፋኖ ብርቱ ክንድ ከፍተኛ ሽንፈት እየደረሰበት ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ምድሩም የእግር እሳት እየሆነበት ይገኛል።
የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህ/ግ አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳሳወቀን በአሁኑ ስአት የአገዛዙ አረመኔ በየ አቅጣጫው የጭንቀት ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ለንፁሀን ህይወትና ንብረት ስጋት ሆኖ ይገኛል። አካባቢው ላይም የድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ማህበረሰቡም ሆነ የፋኖ ሀይል ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክት ማስተላለፍ እንወዳለን።
በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
ወደ መተማ ከተማ 1 አይሱዙ አስክሬንና 2 አምቡላንስ ቁስለኛ አንስቶ የወሰደ ሲሆን አውደ ውጊያው ይህን መረጃ እስካጠናቀርንበት 7:30 ድረስ እንደቀጠለ ይገኛል።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ጥቅምት 27/2018 ዓም

❤3💔1
በዝሆኖቹ መራገጥ የሚወድመው ሣሩ ነው!
(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል የገቡበት ጦርነት በክልሉ ብቻ ሳይገደብ የኤርትራን ጣልቃ ገብነት አክሎ አብዛኛውን የአማራ ክልል እና የአፋር ክልል በማቀፍ ቀላል የማይባል ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል። ይኸው ጦርነት ፕሪቶሪያ ላይ ተደረሰ በተባለ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአግባቡ ግልጽ ባልተደረገ ስምምነት ተቋጭቷል። ጦርነቱ ኦፊሴላዊ ባልሆነ ግምት የአንድ ሚሊዮን ዜጎቻችን ሕይወት እንደቀጠፈ የሚነገር ሲሆን በገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ መሠረት ደግሞ አንድ ትሪሊዬን ተኩል ያክል የንብረት ውድመት እንዳስከተለ ተነግሯል። የጦርነቱ አጀማመር እና ዳራ እንዲሁም የተቋጨበት መንገድ ሕዝባችን ያላወቀውና ታሪክ ነገ የሚገልጠው ቢኾንም በወቅቱ መቆም መቻሉና ሕዝባችን የጠመንጃ ድምጽ ከመስማት መዳኑ እንዲኹም ዕለት ዕለት የሚረግፍ ሕይወት አለመኖሩ ትልቅ እፎይታ የሰጠ ለመኾኑ የሚካድ አይደለም።
የትግራይ ክልል ጦርነት በዚህ መልኩ ከተቋጨ በኋላ ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል ይካሄድ የነበረው ጦርነት እና ኋላም በአማራ ክልል የተጀመረውና እስከ ዛሬ ድረስ አድማሱን አስፍቶ ክልሉን በሙሉ ሽፍኖ የቀጠለው ጦርነት የትግራይ ክልል ጦርነት በተቋጨበት የጠረጴዛ ዙሪያ ድርድር በገለልተኛ አገርና አደራዳሪዎች እንዲፈታ ያለማሳለስ የተደረጉ ጩኸቶች ሰሚ በማጣታቸው የእርስ በርስ ጦርነቱ መጠኑን አስፍቶ ቀጥሎ ይገኛል።
ይኽ በእንዲህ እንዳለ በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር(ሕወሓት) መካከል የቀጠለው እሰጥ አገባ ከቅርብ ጊዜያት ወዲኽ ዙሩ ከሮ በትግራይ ክልል እና አዋሳኝ የአፋር ክልል የጦርነት አደጋ አንዣብቧል። በኹሉም አቅጣጫ ዘራፍ የሚል የጦርነት አታሞ በመደለቅ ላይ ይገኛል። በአፋር ክልል የተወሰኑ ቀበሌዎች ዘልቆም በርካታ ወገናችን እንደተፈናቀለ ታዝበናል። በወልቃይትና አዋሳኝ አካባቢዎችም ተመሳሳይ ጉሰማዎች እየተስተዋሉ ነው።
እናት ፓርቲ ከዚኽ ቀደምም በተደጋጋሚ ጊዜያት እንዳሳሰበው ከዚኽ መሰል ግጭት ኢትዮጵያ አትራፊ ሳትኾን ከሳሪ እንደኾነች ለመግለጽ ይወዳል። በኹለቱም ወገን ያሉ ባለሥልጣናት የጦርነት ፉከራና ቀረርቶ ሲያሰሙ የሞቱ ድግስ እናት ጥሬ ቆርጥማ ልጄ ነገ ሰው ኾኖ ያሳልፍልኛል ብላ ተስፋ ለጣለችበት ወጣት እንጂ ከጦርነት ማግስት ምንም ያልተፈጠረ ያኽል ሻምፓኝ ለሚራጩት ባለሥልጣናትና ለጦር መሪዎቹ ብሎም ልጆቻቸው እንዳይደለ እሙን ነው። የተደቀነው መራር እውነታ ማቅ ለብሳ ዓመታት ያሳለፈች የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር እናትን ብሎም መላው ኢትዮጵያን ዳግም ማቅ የሚያስለብስ እንደኾነ ሕዝባችንም ዓለምም እየታዘበ ነው። የመጀመሪያዋ የአብሪ ጥይት ተኩስም ኃያላኑን ጭምር ጎትታ የማስገባት አቅም ያላት የማያባራ እሳት ለኩሳ የማለፍ እድል ያላት መኾኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በእንደዚህ ዓይነት የጦርነት ጠመቃ ‘ዝሆኖቹ ሲጣሉ የሚጎዳው ሣሩ ነው’ እንዲሉ ተጠቂው እና የጦርነቱ ሰለባ የሚኾነው ለዓመታት የመከራ ሕይወት እየገፋ ያለው ሕዝባችን ነው።
ስለዚኽ ፓርቲያችን፣
1. ኹሉም ወገኖች ቆም ብለው የያዙት መንገድ እንዲፈትሹና ከደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲታቀቡ፤
2. በትግራይ ክልል ወደ ግጭት እያመራ ያለውን አካሄድ ጨምሮ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እየተደረገ ያለው ጦርነት በአስቸኳይ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ድርድር እንዲፈታ ዛሬም በጥብቅ ያሳስባል።
3. ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብና መላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ወጣቶች "ጦርነት በቃን" በሚል አንድ ቃል ተቃውሟቸውን ባገኙት አጋጣሚ ኹሉ ለጠማቂዎቹ እንዲያሰሙ ጥሪ እናቀርባለን።
ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ. ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

❤2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር
ሰበር የድል ዜና!!!
በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ በተደጋጋሚ ፋኖ ድል እየቀናው የጠላት ሀይል እየተሽመደመደ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል።
በትናንትናው እለት ጥቅምት 27/2018 የአገዛዙ አገልጋይ ጡት ቆራጭ ሀይል መነሻውን ቁጥር አንድ አድርጎ ወደ አርባጅራ እየተጓዘ ባለበት ስአት አይበገሬዎቹ የበረሀ ፈርጦች የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ፋሲል ብርጌድ በአርበኛ ሳሌ ግርማ እና በአርበኛ ባንዴራው እየተመራ እንዲሁም የክ/ጦሩ አመራሮች በተሳተፉበት ስምሪት ሌላ 3ኛ ዙር ከታጉር እና ጓንግ ከተሰራው ጀብድ የቀጠለ ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት ይህንኑ ግብስብስ የብልፅግና ስርአት አስፈፃሚ የማፊያ ቡድን ከቀኑ 9:00_11:30 ክፉኛ ሲያበራዩት እንደ ተለመደው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ አርባጅራ ፈርጥጧል።
በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህ/ግ አርበኛ ግዛት አለበል እንዳሳወቀን ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ለጊዜው የደረሰን የአገዛዙ ሀይል ሙትና ቁስለኛ ከዚህ በታች ከጠቀስነው በላይ እንደሚሆን የውስጥ መረጃዎች አድርሰውናል ሲል አሳውቋል።
ሙት = 18
ቁስለኛ = 26
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ

❤1🙏1
የምኒልክ ዕዝ የስልጠና ጥሪ!
የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ከአፓርታይዱ ስርዓት ጋር ትንቅንቅ ከጀመረ ዓመታትን እንዳስቆጠረ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያወቀዉ የአደባባይ እዉነታ ነዉ።
በመሆኑም ይህን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገርስሶ ለመጣል ሰራዊታችን እና የጦር መሳሪያዎችን እያዘመንን ወደፊት እየገሰገስን ሲሆን ተጨማሪ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች እንደሚያስፈልጉን ስላመን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ ከጥቅምት 29/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳዉቃለን።
1 ) እድሜ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ /የሆናት
2 ) የአማራ ተወላጅ የሆነ / የሆነች እና በብሔርተኛነት ትግሉ ሙሉ በሙሉ ያመነ / ያመነች
3) ማንኛውንም ሃይማኖት ማክበር የሚችል /የምትችል
4 ) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ግሉል የሆነ አባልም ያልነበረ/ ያልነበረች
5 ) ስለተወለደበትና ስለሚኖርበት አካባቢ ( የትዉልድ ቦታ ) ሙሉ መረጃና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል / የምትችል
6 ) ምንም አይነት ሱስ የሌለበት
7) ከአካል ጉዳት ነጻ የሆነ / የሆነች
8 ) ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ / የሆነች
9 ) ማንበብና መፃፍ የሚችል / የምትችል
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

👍1
በምእራብ ጎንደር ቀጠና የአገዛዙ ሃይል
ንፁሃንን በየአደባባዩ እየረሸነ መሆኑ ተገለፀ::
"የውጭ ባዳንና የወስጥ ባንዳን ማጥፋት" በሚል የአገዛዙ ሃይል በየወረዳው ውይይት በሚል ቢቀመጥም ባንዳዎች ራሱ የብልፅግና አሽከሮች መሆናቸውን የሚነግራቸው ተፍቶጅ ከሰሞኑ በመተማ : ገንዳውሃና በቁአራ የራሱን ዜጋ ንፁሃንን በመጨፍጨፍ ላይ መሆኑን በአፋብኃ በላይ እዝ የቁአራ አኦሜድላ ከፍለጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አስቻለው አለባቸው ላለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ አስታውቁአል::
በተለይ በቋራ ነፍስገብያ አካባቢ ከትናንት በስትያ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በሪሁን/ጮሬ : ብርሃን ሲሳይ : ቢላል እና ስመኘው ምረቱ የተባሉት ሞተረኞችን : እንዲሁም በዛሬው እለት ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓም ደግሞ የእለት ጉርሱን ቆራሊዎ በመስራት ይተዳደር የነበረ ወጣትነት የሐሰት ስም በመስጠት ረሽኑዋቸዋል ብሏል:: ይህ ድርጊት የአገዛዙን ሽንፈትና ተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው ያለው አርበኛ አስቻለው ሁሉም በነቂስ ወጥቶ ሊታገለው ይገባል ብሏል::
በሌላ በኩል ደግሞ የተለያዩ የጫኝ አውራጅ : የመነሃሪያ ስምሪት ማህበራትና ልዩልዩ አደረጃጀቶችን እያንዳንዳቸው 5 ሰው መልምለው ለውጊያ እንድልኩ ባስገዳጅ መልኩ መታዘዛቸውንም ለማወቅ ተችሏል ያለ ሲሆን ሁሉም ራሱን ለትግል ያዘጋጅ ነው ያለው::
@አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ!

❤4
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በከባድ መሳሪያ የንፁሃን አማራዎችን ህይወት እየቀጠፈ ቅጥሏል:: በዚህም የአስራ አንድ ልጆች እናት የሆኑ አዛውንት የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል::
የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በበርካታ ቀጠናዎች ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ማለትም የሞርታር ታንክ መድፍና ቢ ኤም እንዲሁም የጄትና ድሮን ጥቃቶችን በመፈፀም ህዝብን የመጨፍጨፍ ህይወት የመቅጠፍ አካል የማጉደልና እንስሳቶችን ጨምሮ ቤትና ንብረት የማውደም ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ከሁለት ቀን በፊት ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም መነሻውን ከቆቦ ከተማ ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ አድርጎ በሚያስወነጭፈው ከባድ መሳሪያ ራያ ቆቦ አረፋ ጊዮርጊስና አርበት አካባቢ ንፁሃኖች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ከነዚህም መካከል አንዲት ወይዘሮ የማታ ይመር የተባሉ የአስራ አንድ ልጆች እናት እግራቸው ተቆርጧል:: በሌሎች በርካታ ቀጠናዎችም የንፁሃን ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በበርካታ ቀጠናዎች ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ማለትም የሞርታር ታንክ መድፍና ቢ ኤም እንዲሁም የጄትና ድሮን ጥቃቶችን በመፈፀም ህዝብን የመጨፍጨፍ ህይወት የመቅጠፍ አካል የማጉደልና እንስሳቶችን ጨምሮ ቤትና ንብረት የማውደም ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ከሁለት ቀን በፊት ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም መነሻውን ከቆቦ ከተማ ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ አድርጎ በሚያስወነጭፈው ከባድ መሳሪያ ራያ ቆቦ አረፋ ጊዮርጊስና አርበት አካባቢ ንፁሃኖች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ከነዚህም መካከል አንዲት ወይዘሮ የማታ ይመር የተባሉ የአስራ አንድ ልጆች እናት እግራቸው ተቆርጧል:: በሌሎች በርካታ ቀጠናዎችም የንፁሃን ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
❤1
አዲስ ቅዳም 💪💪💪
ዛሬ #ከአሽዋ_እስከ_አዲስ_ቅዳም ከተማ
የጦር ሜዳ መገናኛዉን ጨምሮ ክላሽ እንደቆሎ ታፍሷል‼️
በአንድ በኩል የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ሊያደርግ ያሰበዉን ዉይይት ለማስተጓጎል በሌላ በኩል ኬላ ዘርግቶ ማህበረሰባችንን ለመዝረፍ አሰፍስፎ ዛሬ ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም ከአድጓሚ ተራራ እስከ አሽዋ ተዘርግቶ የነበረዉ የብልፅግና ታጣቂ በፋኖ ሰይፍ እየተበላ በወጣበት ቀርቷል።
በዚህ እረመጧ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር
የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ እና ቁጡዎቹ የክ/ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ ሀይል በሰሩት አስደናቂ ኦፕሬሽን
የአድማ አዛዡን እና ዲሽቃ ተኳሹን ጨምሮ 22 የጠላት ታጣቂ ሲደመሰስ
_ከ29 በላዩ ቁስለኛ ሁኗል።
በምርኮ በኩልም
_23 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ
_1አንድ የጦርሜዳ መገናኛ ሬዲዮን
_5 የእጅ ቦንብ _328 የክላሽ ተተኳሽ ገቢ ተደርጓል።
አዲስ ቅዳም ከተማ የተሰገሰገዉ ሆድ አደር ካድሬ በእየጊዜዉ የሚወገድበትን በመቶወች የሚቆጠር ታጣቂ
"የድሀ ልጅ መተካት" በሚለዉ ፀረ ፍጥረት ፍልስፍናዉ ከላይ ከላይ እየተካ ስልጣኑን ለማቆየት ቢጥርም ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሩ ዉጭ ሁነዉበት መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ እየፈራረሰ ይገኛል።
አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!!
ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም
ፋኖነት አሸናፊነት‼️

❤3🙏1
ጀምበር የጠለቀችበትና ተስፋ የቆረጠው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በብሔር እና በሐይማኖት ምክንያት የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት ጊዜ ለመግዛትና ዙፋኑን ለማፅናት በበጀትና በመዋቅር የተደገፈ ስራ እየሰራ ይገኛል::
የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በፋኖ የህልውና ተጋድሎ ተንኮታኩቶ ጀምበር እየጠለቀችበት ያለ ሲሆን ይህንን ሁኔታ በኢትዮጵያውያን የእርስ በርስ ግጭት ለመቀየርና ጊዜ ለመግዛት ሐይማኖትን እና ብሔርን መሰትረት ያደረገ ግጭት ለመቀስቀስ በበጀትና በመዋቅር የተደገፈ ስራ እየሰራ እንደሆነ በርካታ ጉዳዮችን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም በተለይ አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሚንቀሳቀስበት አጠቃላይ በቤተ-አማራ ቀጠና የሃይማኖት ግጭቶች እንዲነሱና በህዝብ መጠፋፋት ዙፋኑን ለማፅናት በከፍተኛ ሁኔታ ስራ እየሰራ ያለ ሲሆን በቅርቡ ካየናቸው ተጨባጭ ምልክቶች በተጨማሪ ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ልዩ ስሙ ሮቢት አካባቢ ከባድ የጥፋት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የደህንነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል::
ስለሆነም መላው ህዝባችን ይህንን የብልፅግና አገዛዝ ፀረ-ህዝብ ድርጊትና እንቅስቃሴ በመረዳትና በመገንዘብ አንዳንድ ሁኔታዎችን ከመፈጠራቸው በፊት ተገቢውን ጥንቃቄና ክትትል በማድረግ ብሎም ችግሮች ቢፈጠሩም ድርጊቱ የፋሽስቱ አገዛዝ ተግባር መሆኑን በማወቅ ህዝባችን ሽ ዘመናትን የኖረና የተሻገረ አንድነትና አብሮነቱን ጠብቆ እንዲሄድ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን::