ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ተጨማሪ 9 (ዘጠኝ) ኦርቶዶክሳውያን መሞታቸው ታወቀ፡፡

በአርሲ ዞን በጃጅ ወረዳ፣ በሰጉሬ፣ በወሸባ፣ በተሬ አሜና እና አንጌ (ጓ) ዳቼ አካባቢ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 24 2018 ዓም በነበረው ጭፍጨፋ ታፍነው ከተወሰዱ 16 ኦርቶዶክሳውያን መካከን ዛሬ ዘጠኙን ገድለው ጥለዋቸው ተገኝተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ስድስቱ እስከአሁንም በገዳዮች እጅ ላይ ይገኛሉ፡፡
በአንድ ሳምንት ብቻ የሟቾች ቁጥር 43 ደርሷል።

ለኦሮሚያ መንግሥት፣ ለአርሲ ዞን እና ለብልጽግና ይኸ ልማታቸውና ሰላማቸው ነው፡፡
1
ሰበር ዜና!

11 የአገዛዙ አባላት ፋኖን ተቀላቅሉ!

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦርን 11 የአገዛዙ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል፣ ከእነዚህም ውስጥ 9 ሚሊሻ 2 የመከላከያ አባላት ሲሆኑ ፦
➢ 8 ክላሽ
➢1አብራራው
➢ 2 ቦንብ
➢ 300 የክላሽ ተተኳሽ
➢ 8 የወገብ ትጥቅ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል ።

   ዛሬ "ከእነበላይ አገር ጎጃም ተወልጀ በነጋ በጠባ ይከበባል ደጀ " የሚለው ስጋት የበዛበት ጎጃምኛ ዘፈን ወደጎን ተብሎ "ዙሪያ ዳር ድንበሩን አፈሩን ኩሩበት፣ አነበላይ ናቸው የተወለዱበት!" የሚለው ጎጃምኛ ወኔ ቀስቃሽ ሙዚቃ በታጋዪ ስነ ልቦና ላይ ነፍስ ዘርቶ አጥንት አለምልሞ በመጨፈር ላይ ይገኛል።

ከድርጅቱ በተቀበለው ተልዕኮ መሠረት አረንዛው ጎንቻ፤ አባይ ሸለቆ እና ሶማ ብርጌዶችን ይዞ የነበረው የ9ኛ ሳሙዔል አወቀ ክፍለጦር ወደ ግዙፋ 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለጦር በማሳደግ በቀጠናው ከፍ ብሎ አየበረረ ይገኛል።

ክፍለጦሩም በ5 አንጋፋ ሬጅመንቶች ተዋቅሮ የመጀመሪያው ምዕራፍ የፕወዛና አባላቱን በተመደቡበት ቦታ የማስገባት ስራቸውን በድል በማጠናቀቅ፣ ሁሉም ሬጅመንቶች እና አባላቱ በተመደበት ቦታ ተገኝተው ቀጠናቸውን በንቃት መከታተልና ትዕዛዝ በመጠባበበቅ ላይ መሆናቸውን የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ ፋኖ በላይነህ እናውገው አሳወቀዋል።

ለዚህ ድል መገኘትም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የ74ኛ ክ/ጦር አመራርሮች፣ ለሬጅመንት አመራሮች፣ ለሬጅመንት አባላት፣ ለወረዳዎቹ ጊዜያዊ መስተዳድር አባላት እና በጦሩ እንቅስቃሴ ወቅት ልዩ አሸኛኘት እና አቀባበል ላደረገልን እነብሴ ሳር ምድር ፣ጎንቻ ሲሶ እነሴ እና እናርጅ እናውጋ ወረዳ ማህበረሰብ፣የጎበዝ አለቃ መዋቅር እና የገበሬው ጦር በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናየን በክ/ጦሩ ስም አቀርባዋል።

   ይሄንን የአደረጃጀት ስራ በጥራትና በፍጥነት በመሰራቱ እና ድርጅቱ፣ ባለፋት ሶስት ቀናት ማለትም ከጥቅምት 25 እስከ 27/02/2018 ዓ/ም ብቻ

➦ከመርጦለማርያም .....ከተማ 7 ምኒሻ
1. እምቢያለ አየለ= ኮርያ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
2. ይርጋ እባቡ =ኮርያ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
3. ሃብታሙ ዉዱ= በደዉ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
4. አወቀ ደርጀዉ= አብራራው ከነሙሉ ትጥቁ
5. አወቀ አስናቀዉ= በደዉ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
6. እንዳለው ታደሰ = ጀሌ
7. አስናቀዉ አሻግሬ ኮፍ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ ይዘው

   ➦""ከግንደወይን ከተማ 2 ምኒሻ
1. አረጋ እንየው = ኮፍ ክላሽ
2. ታዴ እንየው= ሰሜን

➦""ከፈለገ ብርሃን ከተማ 2 የመከላከያ አባላት ከ14ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት አባላት የሆኑት
1. ክቡር አታክልት= ኮርያ ክላሽ፣የወገብ ትጥቅ፣1ቦንብ፣150 ፍሬ የክላሽ ጥይት
2. ጋሻው ገብሩ= ኮርያ ክላሽ፣የወገብ ትጥቅ፣ 1ቦንብ፣ 150 ፍሬ የክላሽ ጥይትበመያዝ በአጠቃላይ 11 የጨፍጫፊውና ሰወበላው ስርዓት በቃን በማለት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ፋኖም ለመጡት የመከላከያ እና ምኒሻ አባላት ሞቅ ያለ አቀባበል በማድረግ በድርጅቱ ትዛዝ መሰረት በፍላጎታቸው እንዲተዳደሩ ማለትም ወደፋኖ መደበኛ መዋቅር ገብተው መታገል ወይም በገበሬው ጦር ጋር በመሆን ቤተሰባቸውን እየመሩ ትግሉን መደገፍ እነደሚችሉ እድል ተሰጥቷቸዋል።

አነዚህ የምኒሻና የመከላከያ አባላትም ሳያውቁ እና በተሳሳተ አላማ ተሸውደው እስካሁን በአማራ  ህዝብ ላይ መንግስት ለሚያደረገው ዘር ማጥፈት ተግባር ተሳታፊ በመሆናቸው መላውን የአማራ ህዝብ ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን ሌላው የምኒሻ፣ አድማ ብተናና ፖሊስ አባላትም የእነሱን ፈለግ ተከትሎ ፋኖን እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገዋል ሲል የ ቴዎድሮስ እዝ የ201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ሐብታሙ የሱፍ ገልጿል።
1👍1🙏1
አርበኛ ስለሽ ከበደ

የ206ኛ ኮር  የ14ኛ፣24ኛ፣34ኛ ክፍለጦር   አደረጃጀት ተጠናቋል።

የአፋብኃ  ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ24ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት እንዲሁም የጊዜያዊ መንግስት አሰተዳደር አወቃቀር እያደራጀ ይገኛል።
በዚህም በአዲስ አደረጃጀት የ24ኛ ክፍለጦር በቀደመው አደረጃጀት ቦቅላ አባይ  ብርጌድ ፣ የስናን አባጂሜ ብርጌድ እና የደባይ ጮቄ ብርጌድ በጋራ በአንድ ሆኖ ተመስርቷል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃዎች በጊዜያዊ መንግስት አሰተዳደር   የተደራጀ  ሲሆን ለቀጣይ ለሚሰጣቸው ድርጅታዊ ስምሪትም  ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የጊዜያዊ መንግስት አሰተዳደር ፣  የሻለቃ  አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
ክፍለ ጦሩን መልሶ ለማደራጀት የተገኙ የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች 
1 አርበኛ ምናልባት ይታየው የዲያሰፖራና ውጭ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ
2 አርበኛ ሰለሺ ከበደ የቴዎድሮሰ ዕዝ ም/አደረጃጀት መምሪያ ሀላፊ

3 መቶ አለቃ እሱባለው ዋለ የቴዎድሮሰ ዕዝ የሰው ሀይል ኃላፊ እና የ206 ኮር አመራሮች በተገኙበት የአፋብኃ  ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ስር የሚገኙ የ14ኛ፣24ኛ፣34ኛ ክፍለጦር ምስረታ አጠናቋል ።
ድል ለአማራ ፋኖ!!

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
2🙏1
መርአዊ ከተማ ላይ ጥቃት ተፈፀመ!

አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ የ102ኛ ኮር አካል የሆኑት ኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ  ሻምበል መማር ጌትነት ሻለቃ አባላት መራዊ ከተማ ላይ የተሰገሰገውን የአብይ  ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ እርምጃ ተወሰደበት

በተጠና የከተማ ኦፕሬሽን በጠላት ምሽግ ላይ ከባድ የቦንብ ዝናብ በማውረድ 12  የስርዓቱ ወንበር ጠባቂ ሚሊሻና አድማ ብተና እስከወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን ከ20 በላይ ከባድና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።

በዚህ መብረቃዊ ጥቃት የመከላከያ ጦር አዛዡ በሽርፍራፊ ሰከንዶች ማምለጥ ቢችልም ሌሎች የብልፅግና ሆድ አደር ካድሪዎች ነፍሴ አውጭኝ በማለት ወደ ጦር ካምፕ ፈርጥጠውል በጥቃቱም ከፍተኛ ድንጋጤና  የጦር መረበሽ እንደተፈጠረ ለማወቅ ችለናል  በርካታ ሙትና ቁስለኞችን ህዝቡ እንዳያይ ቤት እየዞሩ በማዘጋት ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

በመጨረሻ አሁንም አልመሸም  እዳላቹህን ተጠቅማቹህ ወደ ማንነታቹህ ተመለሱ በማለት ለሚሊሻ እና አድማ ብተናወች መልክት አስተላልፈዋል።

ጥቅምት  27/2018ዓ.ም
2🙏1
በመቄት ወረዳ በተደረገ ውጊያ ከ25 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ!

በውጊያው፡ በአገዛዙ በኩል አራት ዲሽቃ እና ሞርተር እንዲሁም ሌሎች የቡድንና ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቀ አንድ ክ/ጦር ሰራዊት የተሰለፈ ሲሆን፡ በፋኖ በኩል ደግሞ ክንዳቸው እሳት የሚተፋ የአንድ ሻለቃ አባላት ተሰልፈው በጥቂት ኃይል ትልቅ ድል ተቀዳጅተው መዋላቸው ተነግሯል።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ሰይድ ክ/ጦር ስር የሚገኙት ክንዱ አሻግሬ ሻለቃ አባላት ዛሬ ጥቅምት 27/2018 ዓ/ም በመቄት ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ፡ 10 የአገዛዙ ወታደሮችን ሲገድሉ ከ15 በላይ የሚሆኑትን ማቁሰላቸውን ዕዙ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

በውጊያው በአገዛዙ በኩል አራት ዲሽቃ እና ሞርተር እንዲሁም ሌሎች የቡድንና ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቀ አንድ ክ/ጦር ሰራዊት የተሰለፈ ሲሆን፡ የክንዱ አሻግሬ ሻለቃ አባላት ግን የሰራዊት ብዛት እና የመሣሪያ አይነት ብቻ ለድል እንደማያበቃ በማሳየት የአገዛዙን ኃይል አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል ነው ያለው ዕዙ ለጣቢያችን በላከው መረጃ።
🙏1
ሞት እና ዕድሜ ልክ በሚያስፈርድ ፍርድ ፤ ዕቃቤ ሕግ ፣ ሕግን በመቃረን ማስረጃ አቀረበ!

በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ አምሳ አንድ (51) የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ቀርበው ነበር።

ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምጽ ቅጂ በማስረጃነት በፍርድ ቤት አቅርቦ ፣ የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ላይ ሞት እና ዕድሜ ልክህ ለማስፈረድ ካለው ፅኑ ፍላጎት በመነሳት ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረቡ በችሎት ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ እና ክርክር ተነስቷል።

ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምጽ ቅጂ ከዚህ ቀደም ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አቅርቦ በማስረጃነት እንዲያዝለት ያቀረበውን ጥያቄ ፤ የተከሳሽ ጠበቆች ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምፅ ቅጂ በምን አግባብ ነው ?!  ጠለፋውን ለማከናወን የሚያስችል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለው ወይ ?! በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ፤ ዐቃቤ ሕግ በሰጠው ምላሽ ከ2 ዓመት በፊት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አውጥቼ ነው ጠለፋውን ያደረጉት በማለት ምላሽ በመስጠቱ ጠለፋ የተደረገበት መዝገብ እንዲቀርብ በተደጋጋሚ ጊዜ ቢቀጠረም ፤ መዝገብ ጠፍቷል የሚል ምላሽ ከፍርድ ቤት ሪጅስትራል እና መዝገብ ቤት ተገልጿል ።

ይህ ከሆነ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ከፍርድ ቤት አመራሮች ጋር በመነጋገር ፤ የጠፋው መዝገብ በሕግ ወጥ መንገድ እንዲደራጅ ካስደረገ በኋላ ፣ መዝገብ ጠፍቷል ከተባለ ከ2 ዓመት ከ9 ወር በኋላ ፤ እንደ አዲስ ተደራጅቶ በመቅረብ በችሎቱ ውስጥ በተከሳሾች በኩል ከፍተኛ ውዝግብ ተቀስቅሷል ።

ይህም በመሆኑ ፤ ችሎት ከቀጣይ ቀጠሮ በኋላ ከአመራሮች ጋር በመነጋገር በፕላዝማ እንዲሆን አደርጋለሁ ። በማለት ችሎቱን ለመበተን የሞከረ ቢሆንም ፣ በተከሳሾች እና በጠበቆቻቸው በኩል በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያየት እንስጥ በሚል ችሎቱን ቢጠይቁም የቀረበው ማስረጃ ሚስጥር በመሆኑ አንስጥም የሚል ምላሽ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል ።

የተከሳሽ ጠበቆች ፤ ደንበኞቻችን ሞት እና ዕድሜ ልክ በሚያስፈርድ ፍርድ ተከሰው ክርክር እያደረግን ነው የስልክ ጠለፋ ለማድረግ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያስፈልጋል ፣ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ የተደረገ የስልክ ጠለፋ ከሕግ አግባብ ውጪ በመሆኑ ተከሳሾች ሊጠየቁበት አይገባም ፤ ዐቃቤ ሕግ እንዲያቀርብ የተጠየቀው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመሸሸግ የፈለገው በእኛ በኩል የምናቀርበው መከራከሪያ የሚደገፍ ስለሆን ነው።  መዝገቡ እንዳይቀርብ የተደረገው በማለት ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል ።

የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ፤ ለችሎት ምሬት እና ብሶት ባዘለ መልኩ ፤ በአማራዊ ማንነታቸዉ እንዲሁም በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለምን ብለው በመጠየቃቸው ብቻ ፤ እየደረሰባቸው ያለው ፍርድ ገምድል አካሄድ በችሎት አምርረው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተቃውሞአቸውን አስምተዋል።

በዚህም ምክንያት ችሎት በፍትሕ ጠያቂዎች ፣የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች እና ፍትሕን በሚደፈጥጡ መካከል ፤ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ተፈጥሯል ።

ፍርድ ቤት የውዝግብ ውጥረት እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ፤ ለኅዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን ፤ከወዲሁ ችሎት በፕላዝማ እንደሚሆን እና የተከሳሾችን ፍርድ ቤት ቀርቦ የመከራከር መብት የሚጋፋ ውሳኔ ሊሰጥ እንደሚችል ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሰጥቷል ።

©ይድነቃቸው ከበደ
1😢1💔1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

ሰበር የድል ዜና!!!
በመተማ ወረዳ 3ኛ ቀኑን ያስቆጠረው አውደ ውጊያ በድል እንደቀጠለ ይገኛል።

የአገዛዙ ሀይል ከምዕራብ አርማጭሆ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለጭማሪ ከቀጠናው ለመግባት ሙከራ ቢያደርግም ፣ በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ ባደረጉት ጣምራዊ ልዩ ኦፕሬሽን ከጥቅምት 25/2018 ከቀኑ 9:00 ላይ የጀመረው አውደ ውጊያ እስከ ጥቅምት 26/2018 ሙሉ ቀኑን እስከ ምሽት 12:00 ስአት ፣ መውጫ መግቢያ አጥቶ ከፍተኛ ሙትና ቁስለኛ ከማስተናገዱ ባሻገር የደረሰበትን ከፍተኛ በትር መቋቋም ሲያቅተው በማታ ስአት እግሬ አውጭኝን ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ድምጡን አጥፍቶ ከታፈነበት ቦታ ወጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሽንፈት ያላዳነውን የድረሱልኝ ታፍኛለሁ ጩኸት ለማገዝ ከመተማ የተነሳው የአገዛዙ ጥምር ሀይል አሁንም ላንተስ ማን ይዞልሀል አይነት ሌላ ያልተጠበቀ ከባድ መብረቃዊ ጥቃት በነበልባሎቹ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ተካ ብርጌድ በአርበኛ ደሴ ተገኘ ስምሪት ሰጭነት ከመተማ ወጣ ብሎ ጓንግ ከምትባል ቦታ ላይ ይህን አረመኔ አራጅ ቡድን በዛሬው እለት ጥቅምት 27/2018 ከጧት ጀምሮ አይቀጡ ቅጣት እየቀጡት ይገኛሉ።

በጥቅሉ ባለጊዜ ነኝ ባዮች የዘር ፓለቲካ አራማጆች የኦሮሙማ ስርአት አራጊ ፈጣሪዎች በየ ጊዜው በአማራ ላይ የሚዶሉቱትን ተለዋዋጭ የጥፋት ሴራ እና ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ በጭፍን ጥላቻ ህዝባችን ለመሰልቀጥ ያዘጋጁት በመከላከያ ስም የሚነግደው የስርአቱ አስፈፃሚ ከየትም መጣ ከየት ወደ ቀጠናው መግባትም ሆነ ከገባም መውጣት እንደማይችል ፣ በፋኖ ብርቱ ክንድ ከፍተኛ ሽንፈት እየደረሰበት ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ምድሩም የእግር እሳት እየሆነበት ይገኛል።

የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህ/ግ አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳሳወቀን በአሁኑ ስአት የአገዛዙ አረመኔ በየ አቅጣጫው የጭንቀት ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ለንፁሀን ህይወትና ንብረት ስጋት ሆኖ ይገኛል። አካባቢው ላይም የድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ማህበረሰቡም ሆነ የፋኖ ሀይል ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክት ማስተላለፍ እንወዳለን።

በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
ወደ መተማ ከተማ 1 አይሱዙ አስክሬንና 2 አምቡላንስ ቁስለኛ አንስቶ የወሰደ ሲሆን አውደ ውጊያው ይህን መረጃ እስካጠናቀርንበት 7:30 ድረስ እንደቀጠለ ይገኛል።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ጥቅምት 27/2018 ዓም
3💔1
በዝሆኖቹ መራገጥ የሚወድመው ሣሩ ነው!
(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል የገቡበት ጦርነት በክልሉ ብቻ ሳይገደብ የኤርትራን ጣልቃ ገብነት አክሎ አብዛኛውን የአማራ ክልል እና የአፋር ክልል በማቀፍ ቀላል የማይባል ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል። ይኸው ጦርነት ፕሪቶሪያ ላይ ተደረሰ በተባለ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአግባቡ ግልጽ ባልተደረገ ስምምነት ተቋጭቷል። ጦርነቱ ኦፊሴላዊ ባልሆነ ግምት የአንድ ሚሊዮን ዜጎቻችን ሕይወት እንደቀጠፈ የሚነገር ሲሆን በገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ መሠረት ደግሞ አንድ ትሪሊዬን ተኩል ያክል የንብረት ውድመት እንዳስከተለ ተነግሯል። የጦርነቱ አጀማመር እና ዳራ እንዲሁም የተቋጨበት መንገድ ሕዝባችን ያላወቀውና ታሪክ ነገ የሚገልጠው ቢኾንም በወቅቱ መቆም መቻሉና ሕዝባችን የጠመንጃ ድምጽ ከመስማት መዳኑ እንዲኹም ዕለት ዕለት የሚረግፍ  ሕይወት አለመኖሩ ትልቅ እፎይታ የሰጠ ለመኾኑ የሚካድ አይደለም።

የትግራይ ክልል ጦርነት በዚህ መልኩ ከተቋጨ በኋላ ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል ይካሄድ የነበረው ጦርነት እና ኋላም በአማራ ክልል የተጀመረውና እስከ ዛሬ ድረስ አድማሱን አስፍቶ ክልሉን በሙሉ ሽፍኖ የቀጠለው ጦርነት የትግራይ ክልል ጦርነት በተቋጨበት የጠረጴዛ ዙሪያ ድርድር በገለልተኛ አገርና አደራዳሪዎች እንዲፈታ ያለማሳለስ የተደረጉ ጩኸቶች ሰሚ በማጣታቸው የእርስ በርስ ጦርነቱ መጠኑን አስፍቶ ቀጥሎ ይገኛል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለ በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር(ሕወሓት) መካከል የቀጠለው እሰጥ አገባ ከቅርብ ጊዜያት ወዲኽ ዙሩ ከሮ በትግራይ ክልል እና አዋሳኝ የአፋር ክልል የጦርነት አደጋ አንዣብቧል። በኹሉም አቅጣጫ ዘራፍ የሚል የጦርነት አታሞ በመደለቅ ላይ ይገኛል። በአፋር ክልል የተወሰኑ ቀበሌዎች ዘልቆም በርካታ ወገናችን እንደተፈናቀለ ታዝበናል። በወልቃይትና አዋሳኝ  አካባቢዎችም ተመሳሳይ ጉሰማዎች እየተስተዋሉ ነው።

እናት ፓርቲ ከዚኽ ቀደምም በተደጋጋሚ ጊዜያት እንዳሳሰበው ከዚኽ መሰል ግጭት ኢትዮጵያ አትራፊ ሳትኾን ከሳሪ እንደኾነች ለመግለጽ ይወዳል። በኹለቱም ወገን ያሉ ባለሥልጣናት የጦርነት ፉከራና ቀረርቶ ሲያሰሙ የሞቱ ድግስ እናት ጥሬ ቆርጥማ ልጄ ነገ ሰው ኾኖ ያሳልፍልኛል ብላ ተስፋ ለጣለችበት ወጣት እንጂ ከጦርነት ማግስት ምንም ያልተፈጠረ ያኽል ሻምፓኝ ለሚራጩት ባለሥልጣናትና ለጦር መሪዎቹ ብሎም ልጆቻቸው እንዳይደለ እሙን ነው። የተደቀነው መራር እውነታ ማቅ ለብሳ ዓመታት ያሳለፈች የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር እናትን ብሎም መላው ኢትዮጵያን ዳግም ማቅ የሚያስለብስ እንደኾነ ሕዝባችንም ዓለምም እየታዘበ ነው። የመጀመሪያዋ የአብሪ ጥይት ተኩስም ኃያላኑን ጭምር ጎትታ የማስገባት አቅም ያላት የማያባራ እሳት ለኩሳ የማለፍ እድል ያላት መኾኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

በእንደዚህ ዓይነት የጦርነት ጠመቃ ‘ዝሆኖቹ ሲጣሉ የሚጎዳው ሣሩ ነው’ እንዲሉ ተጠቂው እና የጦርነቱ ሰለባ የሚኾነው ለዓመታት የመከራ ሕይወት እየገፋ ያለው ሕዝባችን ነው።

ስለዚኽ ፓርቲያችን፣
1. ኹሉም ወገኖች ቆም ብለው የያዙት መንገድ እንዲፈትሹና ከደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲታቀቡ፤

2. በትግራይ ክልል ወደ ግጭት እያመራ ያለውን አካሄድ ጨምሮ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እየተደረገ ያለው ጦርነት በአስቸኳይ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ድርድር እንዲፈታ ዛሬም በጥብቅ ያሳስባል።

3. ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብና መላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ወጣቶች "ጦርነት በቃን" በሚል አንድ ቃል ተቃውሟቸውን ባገኙት አጋጣሚ ኹሉ ለጠማቂዎቹ እንዲያሰሙ ጥሪ እናቀርባለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ. ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
2