ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
~ ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ  ግንባር ለፋኖ ኃይሎች የተሰጠ የአጋርነት መግለጫ!

የተከበራችሁ መላው የአፋር ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በሙሉ  እንደምታወቀው የአፋር "ኡጉጉሞ" ነፃነት ግንባር፣ የአፋር ህዝብ ክብርና ጥቅም እንዲሁም ልዑላዊነትና ድህንነት ከየትኛውም የውስጥና የውጭ ጠላት እንዲጠበቅና እንዲከበር ለበርካታ አመታት በደምና በአጥንት ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ግንባር መሆኑ ይታወቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ወደመደበኛ የትጥቅ ትግል በመሸጋገር ላይ እንዳለን ይታወቃል።

የአሁኑን ትግላችን ከዚህ ቀደሙ የተለየ ያደረገው፦

አንደኛ፡- የብልፅግና ቡድን የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለሌላ አሳልፎ ሊሰጥ በመሆኑ፤

ሁለተኛ፦ ቀይ ባህርን የኢትዮጵያ አካል እናደርጋለን በማለት የብልጽግና አገዛዝ የሚቀሰቅሰው ጦርነት፣ በይበልጥ አፋርና አፋርን ለማጋደል የተጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ፤

ሦስተኛ፡- ክልሉን በለውጥ ስም ስልጣን የተቆጣጠረውና ለ7 አመታት እየመራ የሚገኘው የብልፅግና ቡድን በማናለበኝነት የህዝብ ሀብት መበዝበዝና ጎሳን ከጎሳ በማጋጨት ወንጀል  እየፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ፤

አራተኛ፡- በአፋር መሬት ላይ ለአብይ አህመድና የአገዛዙ ፍላጎት ማስፈፀሚያ እየሰለጠኑ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች አፋርን የደም መሬት ሊያደርጉት እየሰሩ በመሆኑ፤

በእነዚህና ሌሎች የትግል መነሻ ምክንያቶች   የአፋር ህዝብ ያልተገባ የመስዋዕትነት እንዲከፍሉ ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑ የአሁኑን የትጥቅ ትግላችን የተለየ ያደርገዋል።

በአሁኑ ሰዓት በምናደርገው የተደራጀ ትግል የአብይ አህመድ ወኪል፣  አድርጎ ያስቀመጠውን የአወል አርባን አገዛዝ ከውጭም፣ ከውስጥም ሁነን እያፈረስነው እንገኛለን።

በዚህም አመርቂ ውጤቶችን አግኝተንበታል። በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው የአወል አርባን ወታደራዊ አመራሮችና ሲቭል አመራሮች እየተቀበልን እንገኛለን።

ከዚህ በፊት በመግለጫችን እንዳስታወቅነው፣ በሶማሌ ክልል እጅ አዙር መሪነትና በጂቡቲ ስፖንሰርነት፣ የተባበሩት የሶማሌ አሸባሪዎች የአፋር ህዝብ ላይ በኢሳ ሽፋን ያወጁት ወረራ ለ7 አመታት በንጹሃን ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። 

ከወትሮ በተለዬ የአፋር ህዝብ በገዛ ቤቱ እያሸበሩና እየገደሉ ቢሆንም የአፋር ህዝብ በብርቱ ክንድና በሙሉ ልብ እየመከታቸው ከራሱ አልፎ ኢትዮጲያን ከዚያድ ባሬ ህልምና ቅዠት እየታደጉ አብዛኛው አሸባሪዎችን ወደ መሬት እቀበሩ የተቀሩት ደሞ በመመከት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ማድረግ ላይ ነው።

ሕዝባችን በራሱ ትግል ክልሉን ከወራሪው ነፃ ያደረገ ቢሆንም በሚያሳዝን መልኩ ይሄንን የተባበሩት ሶማሌ ተስፋፊያን የከፈቱብን ግልፅ ወረራ የፌድራል መንግስት ወራራውን ከማስቆምና ከመከላከል በተቃራኒ የአብይ ቡድን በጂቡቲ ያለውን የሥልጣን ጥቅምና ቀጠናዊ የቡድን ፍላጎት በማስቀደም በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈፀም የተባበሩት ሶማሌ ወረራ በግልፅ እየደገፍ ይገኛል።

አፋርን በቴክኒካል ሴራና የእጅ አዙር ተፅዕኖ በማዳከም አሸባሪዎቹን ወደ አፋር ልዑላዊ ግዛት እምብርት ላይ እንዲመለስ ግፊት በማድረግ ላይ ነው። ይህ እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር ወንጀል ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወንድም የሆነውን የኤርትራ ህዝብን ለመውጋትና የሚሰለጥኑ ኃይሎች ለአፋር ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለአካባቢው የከፋ አደጋ እንደሚያመጣ ህዝባችን ያምናል።

በትላንትናው ዕለትም የአፋር ሕዝብ ይሄ ነገር መቆም እንዳለበት ተቃውሟውን በተለያዩ መንገድ ገልጿል፣ ይሄ ጉዳይም እስከ ነጻነት ድረስ የሚቀጥል መሆኑን የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ያስታውቃል።

የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ከሰሞኑ በአማራ ክልል ወሎ ግንባር በአገዛዙና በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በኩል እየተደረጉ ያሉ ውጊያዎችን በትኩረት እየተከታተለ ይገኛል።

የፋኖ ኃይሎች ከባዶ እጅ በመነሳት ዛሬ ላይ በመካናይዝድ የታገዘ መደበኛ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን ተገንዝበናል። የተሰየመው ዘመቻም ዘመቻ አደም አሊ የሚል መሆኑን፣ ዘመቻው የተሰየመለት ፋኖ፣ በትግል ላይ የተሰዋ ሙስሊም ፋኖ መሆኑንም አረጋግጠናል።

ይህ የፋኖ ኃይሎችን የአንድ ኃይማኖት ሰዎች ናቸው፣ የቀድሞውን ሥርዓት ለመመለስ ነው የሚታገሉ የሚለውን የብልጽግና አገዛዝ የሐሰት ፍረጃ፣ እንዲሁም በፍረጃው ለተሳሳቱ ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ሁኖ አግንተነዋል።

የፋኖ ኃይሎች እያደረጉ ላለው ከባድ ትግል እውቅና የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

የአማራ ሕዝብና የአፋር ሕዝብ ከትናንት እስከዛሬ በመከራም፣ በደስታም የጋራ እጣ ፈንታ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል።  አሁን ላይ በአብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት ተቀባይነት የሌለውና ለሀገር ወዳዱ የአማራ ሕዝብም ይሄ የማይገባው መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እያደረጉት ያለው ተጋድሎ ከነሱም መግለጫዎች በተደጋጋሚ እንደተረዳነው የመላው ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ነጻነት እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል።

እኛም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር በቀጣይ ከፋኖ ኃይሎች ጋር በጋራ በመታገል የአብይ አህመዱን የብልጽግና አገዛዝ ለአንዴና ከመጨረሻ ጊዜ በመጣል በእኩልነት የጋራ አገር ለመገንባት  በትብብር እንደምንሰራ ስንገልጽ በደስታ ነው።

በመጨረሻም አፋርን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ የአማራ ሕዝብን ለማውድም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መላው የአፋር ሕዝብ እንዲቃወምና እንዲያስቆም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ይጠይቃል፣ እንዲቆም እንደምንሰራ መግለጽ እንፈልጋለን።

መላው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የትግል መነሻዎቻችን ተረድቶ በሀገራችን ላይ የተደቀነው ብሄራዊ አደጋ በጋራ ትግል እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን።

ግመሎቻችን ጭምር የሚያውቋት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳትወድቅ፣ ነፃ ሀገር እንድትኖረን ለትግላችን አስፈላጊውች ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን !

ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ
🙏41
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

ሰበር የድል ዜና!!!
በመተማ ወረዳ 3ኛ ቀኑን ያስቆጠረው አውደ ውጊያ በድል እንደቀጠለ ይገኛል።

የአገዛዙ ሀይል ከምዕራብ አርማጭሆ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለጭማሪ ከቀጠናው ለመግባት ሙከራ ቢያደርግም ፣ በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ ባደረጉት ጣምራዊ ልዩ ኦፕሬሽን ከጥቅምት 25/2018 ከቀኑ 9:00 ላይ የጀመረው አውደ ውጊያ እስከ ጥቅምት 26/2018 ሙሉ ቀኑን እስከ ምሽት 12:00 ስአት ፣ መውጫ መግቢያ አጥቶ ከፍተኛ ሙትና ቁስለኛ ከማስተናገዱ ባሻገር የደረሰበትን ከፍተኛ በትር መቋቋም ሲያቅተው በማታ ስአት እግሬ አውጭኝን ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ድምጡን አጥፍቶ ከታፈነበት ቦታ ወጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሽንፈት ያላዳነውን የድረሱልኝ ታፍኛለሁ ጩኸት ለማገዝ ከመተማ የተነሳው የአገዛዙ ጥምር ሀይል አሁንም ላንተስ ማን ይዞልሀል አይነት ሌላ ያልተጠበቀ ከባድ መብረቃዊ ጥቃት በነበልባሎቹ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ተካ ብርጌድ በአርበኛ ደሴ ተገኘ ስምሪት ሰጭነት ከመተማ ወጣ ብሎ ጓንግ ከምትባል ቦታ ላይ ይህን አረመኔ አራጅ ቡድን በዛሬው እለት ጥቅምት 27/2018 ከጧት ጀምሮ አይቀጡ ቅጣት እየቀጡት ይገኛሉ።

በጥቅሉ ባለጊዜ ነኝ ባዮች የዘር ፓለቲካ አራማጆች የኦሮሙማ ስርአት አራጊ ፈጣሪዎች በየ ጊዜው በአማራ ላይ የሚዶሉቱትን ተለዋዋጭ የጥፋት ሴራ እና ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ በጭፍን ጥላቻ ህዝባችን ለመሰልቀጥ ያዘጋጁት በመከላከያ ስም የሚነግደው የስርአቱ አስፈፃሚ ከየትም መጣ ከየት ወደ ቀጠናው መግባትም ሆነ ከገባም መውጣት እንደማይችል ፣ በፋኖ ብርቱ ክንድ ከፍተኛ ሽንፈት እየደረሰበት ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ምድሩም የእግር እሳት እየሆነበት ይገኛል።

የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህ/ግ አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳሳወቀን በአሁኑ ስአት የአገዛዙ አረመኔ በየ አቅጣጫው የጭንቀት ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ለንፁሀን ህይወትና ንብረት ስጋት ሆኖ ይገኛል። አካባቢው ላይም የድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ማህበረሰቡም ሆነ የፋኖ ሀይል ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክት ማስተላለፍ እንወዳለን።

በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
ወደ መተማ ከተማ 1 አይሱዙ አስክሬንና 2 አምቡላንስ ቁስለኛ አንስቶ የወሰደ ሲሆን አውደ ውጊያው ይህን መረጃ እስካጠናቀርንበት 7:30 ድረስ እንደቀጠለ ይገኛል።
🙏2
ከደሴ አፍንጫ ስር ልዩ ኮማንዶዎች ተመረቁ!

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ስር ተወርዋሪዋ በላጎ ሻለቃ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ለወራት ያሰለጠነቻቸው ዕጩ ኮማንዶዎችን ማስመረቋን የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም ኮሮቹና በዕዙ ልዩ ዘመቻ በበርካታ ቀጠናዎች እያሰለጠነ ነባሩን ፋኖ በሰው ሃይል እያጠናከረ የህልውና ትግሉ በሚፈልገው ልክ ራሱን እየተደራጀ ይገኛል::

ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ስልጠናውን በቀላል ወጭ ነገር ግን የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እየተሰጠ የከፍተኛ እውቀትና ስነምግባር ባለቤት እያደረገ ለህልውና ትግሉ እያቀረበ ይገኛል ነው ያለው ሕዝብ ግንኙነት መምሪያው።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት ነፃ ባወጣቸው አካባቢዎች የሲቪል አስተዳደር መዋቅር ዝርጋታ መጀመሩ ተገለፀ::

የምኒልክ ዕዝ ምክትል ሰብሳቢ እና የፓለቲካ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አርበኛ ሔኖክ አዲሴ ከአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊው ከአርበኛ አበበ ቀዬ ጋር በመመካከር የሲቪል መዋቅር ስራው በቅንጅት እንድሰራ በመወሰን ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ውስጥ የሚኖረውን ህዝብ የፓለቲካ ንቃተ ህሊና ለማሳደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን የዕዙ ፓለቲካ ክንፍ ሲሰራ የአደረጃጀት ክንፉ ደግሞ የየቀበሌዎችን ሊቀመናብርት፣ የፀጥታና አስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም የማህበራዊ ሸንጎ መዋቅር የመዘርጋት ስራ መስራቱ ታውቋል::

በዚህም መሰረት በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ 012 ሚናያ ቀበሌ የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ አለልኝ ተሰማ ጭምር በተገኘበት ከህዝብ ጋር ውይይት ተደርጓል::

የውጭ ባዳ እና የሀገር ውስጥ ባንዳ በሚል ርእስ የአሸባሪው ብልጽግና ካድሬዎች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመሰብሰብ የሚሰሩትን ፕሮፓጋንዳ ለማክሸፍ ህዝብን የማንቃት ስራ ተሰርቷል:: የህልውና ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን የዳሰሰ ውይይትም ተደርጎ በተለይ አፈንግጠው በዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ፀረ ህዝቦችን አሳዶ የመያዝ ግዳጅ በስኬት ተጠናቆ ቀጠናው ከሌቦች መፅዳቱ ለህዝብ ግልጽ ተደርጓል:: የፋሽስቱ አብይ ሰራዊትም ከይዞታው ተነቅሎ የማድረግ አቅሙ ተልመሽምሾ በቡድን እየከዳ እንደሆነም ነው አርበኛ አለልኝ ተሰማ በመድረኩ ላይ ለህዝብ የገለፀው::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
3🙏1
የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠኑ ማስመረቁን አጠናክረው ቀጥለው ዛሬም ደጀን ክፍለጦር አስመርቋል::

በቅርቡ የተደራጀው የደጋው መብረቅ ኮር ሁሉም አሃዶቹ ምልምል ፋኖዎችን በእግረኛ እና በልዩ ኮማንዶ ደረጃ እያሰለጠነ እያስመረቀ ሲሆን ዛሬ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም ደግሞ ደጀን ክፍለጦር ለወራቶች የሰለጠኑ ለልዩ ተልዕኮ የሚውሉ ኮማንዶዎችን አስመርቋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም ኮሮቹና በዕዙ ልዩ ዘመቻ በበርካታ ቀጠናዎች እያሰለጠነ ነባሩን ፋኖ በሰው ሃይል እያጠናከረ የህልውና ትግሉ በሚፈልገው ልክ ራሱን እየተደራጀ ይገኛል::

ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ስልጠናውን በቀላል ወጭ ነገር ግን የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እየተሰጠ የከፍተኛ እውቀትና ስነምግባር ባለቤት እያደረገ ለህልውና ትግሉ እያቀረበ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏1
ተጨማሪ 9 (ዘጠኝ) ኦርቶዶክሳውያን መሞታቸው ታወቀ፡፡

በአርሲ ዞን በጃጅ ወረዳ፣ በሰጉሬ፣ በወሸባ፣ በተሬ አሜና እና አንጌ (ጓ) ዳቼ አካባቢ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 24 2018 ዓም በነበረው ጭፍጨፋ ታፍነው ከተወሰዱ 16 ኦርቶዶክሳውያን መካከን ዛሬ ዘጠኙን ገድለው ጥለዋቸው ተገኝተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ስድስቱ እስከአሁንም በገዳዮች እጅ ላይ ይገኛሉ፡፡
በአንድ ሳምንት ብቻ የሟቾች ቁጥር 43 ደርሷል።

ለኦሮሚያ መንግሥት፣ ለአርሲ ዞን እና ለብልጽግና ይኸ ልማታቸውና ሰላማቸው ነው፡፡
1
ሰበር ዜና!

11 የአገዛዙ አባላት ፋኖን ተቀላቅሉ!

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦርን 11 የአገዛዙ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል፣ ከእነዚህም ውስጥ 9 ሚሊሻ 2 የመከላከያ አባላት ሲሆኑ ፦
➢ 8 ክላሽ
➢1አብራራው
➢ 2 ቦንብ
➢ 300 የክላሽ ተተኳሽ
➢ 8 የወገብ ትጥቅ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል ።

   ዛሬ "ከእነበላይ አገር ጎጃም ተወልጀ በነጋ በጠባ ይከበባል ደጀ " የሚለው ስጋት የበዛበት ጎጃምኛ ዘፈን ወደጎን ተብሎ "ዙሪያ ዳር ድንበሩን አፈሩን ኩሩበት፣ አነበላይ ናቸው የተወለዱበት!" የሚለው ጎጃምኛ ወኔ ቀስቃሽ ሙዚቃ በታጋዪ ስነ ልቦና ላይ ነፍስ ዘርቶ አጥንት አለምልሞ በመጨፈር ላይ ይገኛል።

ከድርጅቱ በተቀበለው ተልዕኮ መሠረት አረንዛው ጎንቻ፤ አባይ ሸለቆ እና ሶማ ብርጌዶችን ይዞ የነበረው የ9ኛ ሳሙዔል አወቀ ክፍለጦር ወደ ግዙፋ 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለጦር በማሳደግ በቀጠናው ከፍ ብሎ አየበረረ ይገኛል።

ክፍለጦሩም በ5 አንጋፋ ሬጅመንቶች ተዋቅሮ የመጀመሪያው ምዕራፍ የፕወዛና አባላቱን በተመደቡበት ቦታ የማስገባት ስራቸውን በድል በማጠናቀቅ፣ ሁሉም ሬጅመንቶች እና አባላቱ በተመደበት ቦታ ተገኝተው ቀጠናቸውን በንቃት መከታተልና ትዕዛዝ በመጠባበበቅ ላይ መሆናቸውን የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ ፋኖ በላይነህ እናውገው አሳወቀዋል።

ለዚህ ድል መገኘትም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የ74ኛ ክ/ጦር አመራርሮች፣ ለሬጅመንት አመራሮች፣ ለሬጅመንት አባላት፣ ለወረዳዎቹ ጊዜያዊ መስተዳድር አባላት እና በጦሩ እንቅስቃሴ ወቅት ልዩ አሸኛኘት እና አቀባበል ላደረገልን እነብሴ ሳር ምድር ፣ጎንቻ ሲሶ እነሴ እና እናርጅ እናውጋ ወረዳ ማህበረሰብ፣የጎበዝ አለቃ መዋቅር እና የገበሬው ጦር በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናየን በክ/ጦሩ ስም አቀርባዋል።

   ይሄንን የአደረጃጀት ስራ በጥራትና በፍጥነት በመሰራቱ እና ድርጅቱ፣ ባለፋት ሶስት ቀናት ማለትም ከጥቅምት 25 እስከ 27/02/2018 ዓ/ም ብቻ

➦ከመርጦለማርያም .....ከተማ 7 ምኒሻ
1. እምቢያለ አየለ= ኮርያ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
2. ይርጋ እባቡ =ኮርያ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
3. ሃብታሙ ዉዱ= በደዉ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
4. አወቀ ደርጀዉ= አብራራው ከነሙሉ ትጥቁ
5. አወቀ አስናቀዉ= በደዉ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ
6. እንዳለው ታደሰ = ጀሌ
7. አስናቀዉ አሻግሬ ኮፍ ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ ይዘው

   ➦""ከግንደወይን ከተማ 2 ምኒሻ
1. አረጋ እንየው = ኮፍ ክላሽ
2. ታዴ እንየው= ሰሜን

➦""ከፈለገ ብርሃን ከተማ 2 የመከላከያ አባላት ከ14ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት አባላት የሆኑት
1. ክቡር አታክልት= ኮርያ ክላሽ፣የወገብ ትጥቅ፣1ቦንብ፣150 ፍሬ የክላሽ ጥይት
2. ጋሻው ገብሩ= ኮርያ ክላሽ፣የወገብ ትጥቅ፣ 1ቦንብ፣ 150 ፍሬ የክላሽ ጥይትበመያዝ በአጠቃላይ 11 የጨፍጫፊውና ሰወበላው ስርዓት በቃን በማለት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ፋኖም ለመጡት የመከላከያ እና ምኒሻ አባላት ሞቅ ያለ አቀባበል በማድረግ በድርጅቱ ትዛዝ መሰረት በፍላጎታቸው እንዲተዳደሩ ማለትም ወደፋኖ መደበኛ መዋቅር ገብተው መታገል ወይም በገበሬው ጦር ጋር በመሆን ቤተሰባቸውን እየመሩ ትግሉን መደገፍ እነደሚችሉ እድል ተሰጥቷቸዋል።

አነዚህ የምኒሻና የመከላከያ አባላትም ሳያውቁ እና በተሳሳተ አላማ ተሸውደው እስካሁን በአማራ  ህዝብ ላይ መንግስት ለሚያደረገው ዘር ማጥፈት ተግባር ተሳታፊ በመሆናቸው መላውን የአማራ ህዝብ ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን ሌላው የምኒሻ፣ አድማ ብተናና ፖሊስ አባላትም የእነሱን ፈለግ ተከትሎ ፋኖን እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገዋል ሲል የ ቴዎድሮስ እዝ የ201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ሐብታሙ የሱፍ ገልጿል።
1👍1🙏1