ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ77ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

ክፍለጦሩ በአምስት  ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።

የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ስሜነህ ሙላቱ  ፣ በአርበኛ ግሩም ምሳሌ እና በሀምሳ አለቃ ታደሰ ልንገር አስተባባሪነት ተጠናቋል ።

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
🙏4
ወምበርማ ብርጌድ የሁለት ቀኑ የወምበርማ ብርጌድ ተጋድሎ

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክ/ጦር ወምበርማ ብርጌድ  ሽንዲ ከተማ የመሸገዉን የአገዛዙ  አገልጋዮች  ከፈራረሰዉ ሥርዓት ከአለቆቻቸዉ ተልዕኮ ተቀብለዉ ወደ ወገዳድ ሲንቀሳቀሱ ነበልባሎቹ የወምበርማ ብርጌድ ቆጥላን ላይ ረጅም ሰዓት በማድፈጥ ከሁለት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት ከጠላት ጋር ሀይለኛ ተጋድሉ አድርገዋል።

በአዉደ ዉጊያም ፦ ከ15 በላይ የአገዛዙ ሀይል ወደላይኛዉ  እንደተሸኙ እንዲሁም 4 ፓትሮል ቁስለኛ ከወገዳድ ጭኖ ወደ ማርቁማ እንደወሰዳቸዉ እና ወደ ሲኖ መኪና ገልብጦ ሽንፈቱን ለመደበቅ  ቡሬ ሆስፒታል እንደወሠዳቸዉ የዉስጥ ምንጮቻችን ገልፀዉልናል።

በደረሰባቸዉ ከባድ ምት ተደናግጠዉ ወገዳድ መሽጎ ጠላት ቢያድርም አይበገሬዎቹ የወምበርማ ብርጌድ ሽንዲ ከተማ ሰርገዉ በመግባት ሀይለኛ ተጋድሎ ፈፅመዋል ። በአዉደ ዉጊያዉም በቁጥር ያልታወቀ የአገዛዙ አገልጋዮች ወደላይኛዉ ሲሸኙ ፣ ቁስለኛዉን እንደተለመደዉ ወደ ጤና ጣቢያ አስገብቷል ።

@ወምበርማ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት መመሪያ : ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም
3🙏1
የአደረጃጀት ዜና

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚገኙ ክፍለ ጦሮችን ወታደራዊ መመሪያው በሚጠይቀው መስፈርት መሰረት በአዲስ መልኩ የማደራጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል::

በዚህም  መሰረት በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ እና ከላላ ወረዳ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ 2 ክፍለ ጦሮች ማለትም ሸዋንግዛው ካሳ ክፍለ ጦር እና ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ወደ አንድ እንድመጡ በማድረግ ሰራዊታቸው ተበውዞ በ3 ሻለቃዎች የተዋቀረ አዲስ ውህድ ክፍለ ጦር የተመሰረተ ሲሆን ስያሜውም የስመጥሩው ጀግና ማስታወሻ እንዲሆን በሚል ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ተብሎ እንዲጠራ ሰራዊቱ በሙሉ ድምፅ ወስኗል::

ክፍለ ጦሩ የተዋቀረባቸው ሻለቃዎች ስያሜም በትግሉ ሂደት የተለየ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፅመው በተሰው ጓዶች ስም እንዲሆን የተደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት 1ኛ ሻለቃ ሸዋንግዛው ሻለቃ ሲባል ለሻለቃ 2 ደግሞ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል:: በብስቁልሉ ኦፕሬሽን ጠላትን አንቀጥቅጦና በርካቶችን ደምስሶ በስተመጨረሻ ጥይት ሲያልቅበት ትጥቄ ጠላት እጅ አይገባም ብሎ  ብሬኑን ድንጋይ ላይ ከስክሶ በክብር እና በጀግንነት በተሰዋው በአርበኛ አህመድ አቀስታ ስም ደግሞ 3ተኛው ሻለቃ ተሰይሟል::

በሪፎርሙ መሰረት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው አርበኞች ክፍለ ጦሩን በእውቀት እና በእውነት እንዲመሩ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል::

1ኛ. አርበኛ አለልኝ ተሰማ - ዋና አዛዥ
2ኛ. አርበኛ ጀማል ብሬን - ምክትል አዛዥ
3ኛ. አርበኛ ዳዊት ፍሰሀ - የወታደራዊ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ
4ኛ. አርበኛ አህመድ ሁሴን - ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
   4.1 አርበኛ አቢ ሙሉ - ምክትል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ

5ኛ. አርበኛ እንድሪስ አቢ - ሎጅስቲክስ
6ኛ. አርበኛ ይመር ሁሴን - የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
7ኛ. አርበኛ ጀማል ክብረት - ፋይናንስ
  7.1. አርበኛ ኡመር አሊ - ምክትል ፋይናንስ
8ኛ. አርበኛ ክብረት አባው- የወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ
   8.1. አርበኛ አህመድ ሙስጠፋ - የወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
9ኛ. አርበኛ ሙሀመድ ደረሰ - ኦርዲናንስ
   9.1. አርበኛ አቡዬ በቀለ - ምክትል ኦርዲናንስ
10ኛ. አርበኛ አብዱ ሙሀመድ - የሰው ኃይል ዘርፍ ኃላፊ
11ኛ. አርበኛ ጌታዬ እረሽድ - የህክምና ዘርፍ ኃላፊ
   11.1. አርበኛ አሰን አቡዬ - የህክምና ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
12ኛ. አርበኛ አሊ ሙሀመድ - ሀብት አሰባሳቢ
   12.1. አርበኛ ክራር - የሀብት አሰባሳብ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ

እነዚህ አርበኞች የክፍለ ጦሩ አመራሮች ሆነው በአብላጫ ድምፅ ስለተመረጡ እነሱም በበኩላቸው ትግሉን በአግባቡ ለመምራት በአማራ ህዝብ እና በፈጣሪ ስም ቃል ገብተዋል::

ከአደረጃጀት ሪፎርሙ በተጨማሪ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ ለክፍለ ጦር እና ሻለቃ አመራሮች የወታደራዊ አመራር ስልጠና መስጠቱ ታውቋል::

ለክፍለ ጦሩ ሰራዊት አባላትም ወታደራዊ እና የፓለቲካ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በዋናነት በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እንድወስዱም ተደርጓል::

የክፍለ ጦሩን ሰራዊት የግዳጅ አፈፃፀም ብቃት ይበልጥ ለማሻሻል እና የማድረግ አቅሙን ለማዳበር ሲባል በቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባይ ክፍለ ጦር አመራር ሻለቃ ክንዱ ሰውነት አማካኝነት ለተከታታይ 15 ቀናት ወታደራዊ ስልትን የተመለከተ የተግባር እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለሰራዊት አባላት እንደተሰጠም ነው ለማረጋገጥ የቻልነው::

ሰራዊቱ በፓለቲካ እና በውትድርናው ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ ኖሮት ግዳጁን በብቃት እንድወጣ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ሰራዊቱ የሚተዳደርበትን ወታደራዊ መመሪያ ለሁሉም በማሳወቅ በመመሪያው መሰረት ለመታገል ፍቃደኛ የማይሆኑት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የማስተካከል ስራ ሊሰራ እንደሚገባ የዕዙ ዋና ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ለኮሩ አመራሮች አስታውሶ ከእንግዲህ ተጠያቂነት ያለው አሰራር ተግባራዊ እንደሚሆን መናገሩም ታውቋል::

ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ በበኩሉ ስለ መሪነት እና ሌሎች ወታደራዊ ጉዳዮች ለክፍለ ጦር እና ሻለቃ አመራሮች ስልጠና ሲሰጥ ባስተላለፈው መልዕክት እጃችሁ ላይ ያለው የሰው ህይወት ነውና በእውቀት እና ጥበብ ይህን ትግል ልትመሩ ይገባል ሲል አሳስቧል:: ኮሎኔሉ ወታደራዊ ስነ-ምግባርን በተመለከተም ለአመራሮቹ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ሰርቷል:: በመጨረሻም አመራሮቹ መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠና ቀጣይነት ባለው መልኩ ቢሰጠን ሲሉ ይበልጥ የመማር እና የማወቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🙏31
~ ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ  ግንባር ለፋኖ ኃይሎች የተሰጠ የአጋርነት መግለጫ!

የተከበራችሁ መላው የአፋር ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በሙሉ  እንደምታወቀው የአፋር "ኡጉጉሞ" ነፃነት ግንባር፣ የአፋር ህዝብ ክብርና ጥቅም እንዲሁም ልዑላዊነትና ድህንነት ከየትኛውም የውስጥና የውጭ ጠላት እንዲጠበቅና እንዲከበር ለበርካታ አመታት በደምና በአጥንት ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ግንባር መሆኑ ይታወቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ወደመደበኛ የትጥቅ ትግል በመሸጋገር ላይ እንዳለን ይታወቃል።

የአሁኑን ትግላችን ከዚህ ቀደሙ የተለየ ያደረገው፦

አንደኛ፡- የብልፅግና ቡድን የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለሌላ አሳልፎ ሊሰጥ በመሆኑ፤

ሁለተኛ፦ ቀይ ባህርን የኢትዮጵያ አካል እናደርጋለን በማለት የብልጽግና አገዛዝ የሚቀሰቅሰው ጦርነት፣ በይበልጥ አፋርና አፋርን ለማጋደል የተጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ፤

ሦስተኛ፡- ክልሉን በለውጥ ስም ስልጣን የተቆጣጠረውና ለ7 አመታት እየመራ የሚገኘው የብልፅግና ቡድን በማናለበኝነት የህዝብ ሀብት መበዝበዝና ጎሳን ከጎሳ በማጋጨት ወንጀል  እየፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ፤

አራተኛ፡- በአፋር መሬት ላይ ለአብይ አህመድና የአገዛዙ ፍላጎት ማስፈፀሚያ እየሰለጠኑ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች አፋርን የደም መሬት ሊያደርጉት እየሰሩ በመሆኑ፤

በእነዚህና ሌሎች የትግል መነሻ ምክንያቶች   የአፋር ህዝብ ያልተገባ የመስዋዕትነት እንዲከፍሉ ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑ የአሁኑን የትጥቅ ትግላችን የተለየ ያደርገዋል።

በአሁኑ ሰዓት በምናደርገው የተደራጀ ትግል የአብይ አህመድ ወኪል፣  አድርጎ ያስቀመጠውን የአወል አርባን አገዛዝ ከውጭም፣ ከውስጥም ሁነን እያፈረስነው እንገኛለን።

በዚህም አመርቂ ውጤቶችን አግኝተንበታል። በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው የአወል አርባን ወታደራዊ አመራሮችና ሲቭል አመራሮች እየተቀበልን እንገኛለን።

ከዚህ በፊት በመግለጫችን እንዳስታወቅነው፣ በሶማሌ ክልል እጅ አዙር መሪነትና በጂቡቲ ስፖንሰርነት፣ የተባበሩት የሶማሌ አሸባሪዎች የአፋር ህዝብ ላይ በኢሳ ሽፋን ያወጁት ወረራ ለ7 አመታት በንጹሃን ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። 

ከወትሮ በተለዬ የአፋር ህዝብ በገዛ ቤቱ እያሸበሩና እየገደሉ ቢሆንም የአፋር ህዝብ በብርቱ ክንድና በሙሉ ልብ እየመከታቸው ከራሱ አልፎ ኢትዮጲያን ከዚያድ ባሬ ህልምና ቅዠት እየታደጉ አብዛኛው አሸባሪዎችን ወደ መሬት እቀበሩ የተቀሩት ደሞ በመመከት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ማድረግ ላይ ነው።

ሕዝባችን በራሱ ትግል ክልሉን ከወራሪው ነፃ ያደረገ ቢሆንም በሚያሳዝን መልኩ ይሄንን የተባበሩት ሶማሌ ተስፋፊያን የከፈቱብን ግልፅ ወረራ የፌድራል መንግስት ወራራውን ከማስቆምና ከመከላከል በተቃራኒ የአብይ ቡድን በጂቡቲ ያለውን የሥልጣን ጥቅምና ቀጠናዊ የቡድን ፍላጎት በማስቀደም በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈፀም የተባበሩት ሶማሌ ወረራ በግልፅ እየደገፍ ይገኛል።

አፋርን በቴክኒካል ሴራና የእጅ አዙር ተፅዕኖ በማዳከም አሸባሪዎቹን ወደ አፋር ልዑላዊ ግዛት እምብርት ላይ እንዲመለስ ግፊት በማድረግ ላይ ነው። ይህ እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር ወንጀል ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወንድም የሆነውን የኤርትራ ህዝብን ለመውጋትና የሚሰለጥኑ ኃይሎች ለአፋር ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለአካባቢው የከፋ አደጋ እንደሚያመጣ ህዝባችን ያምናል።

በትላንትናው ዕለትም የአፋር ሕዝብ ይሄ ነገር መቆም እንዳለበት ተቃውሟውን በተለያዩ መንገድ ገልጿል፣ ይሄ ጉዳይም እስከ ነጻነት ድረስ የሚቀጥል መሆኑን የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ያስታውቃል።

የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ከሰሞኑ በአማራ ክልል ወሎ ግንባር በአገዛዙና በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በኩል እየተደረጉ ያሉ ውጊያዎችን በትኩረት እየተከታተለ ይገኛል።

የፋኖ ኃይሎች ከባዶ እጅ በመነሳት ዛሬ ላይ በመካናይዝድ የታገዘ መደበኛ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን ተገንዝበናል። የተሰየመው ዘመቻም ዘመቻ አደም አሊ የሚል መሆኑን፣ ዘመቻው የተሰየመለት ፋኖ፣ በትግል ላይ የተሰዋ ሙስሊም ፋኖ መሆኑንም አረጋግጠናል።

ይህ የፋኖ ኃይሎችን የአንድ ኃይማኖት ሰዎች ናቸው፣ የቀድሞውን ሥርዓት ለመመለስ ነው የሚታገሉ የሚለውን የብልጽግና አገዛዝ የሐሰት ፍረጃ፣ እንዲሁም በፍረጃው ለተሳሳቱ ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ሁኖ አግንተነዋል።

የፋኖ ኃይሎች እያደረጉ ላለው ከባድ ትግል እውቅና የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

የአማራ ሕዝብና የአፋር ሕዝብ ከትናንት እስከዛሬ በመከራም፣ በደስታም የጋራ እጣ ፈንታ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል።  አሁን ላይ በአብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት ተቀባይነት የሌለውና ለሀገር ወዳዱ የአማራ ሕዝብም ይሄ የማይገባው መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እያደረጉት ያለው ተጋድሎ ከነሱም መግለጫዎች በተደጋጋሚ እንደተረዳነው የመላው ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ነጻነት እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል።

እኛም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር በቀጣይ ከፋኖ ኃይሎች ጋር በጋራ በመታገል የአብይ አህመዱን የብልጽግና አገዛዝ ለአንዴና ከመጨረሻ ጊዜ በመጣል በእኩልነት የጋራ አገር ለመገንባት  በትብብር እንደምንሰራ ስንገልጽ በደስታ ነው።

በመጨረሻም አፋርን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ የአማራ ሕዝብን ለማውድም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መላው የአፋር ሕዝብ እንዲቃወምና እንዲያስቆም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ይጠይቃል፣ እንዲቆም እንደምንሰራ መግለጽ እንፈልጋለን።

መላው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የትግል መነሻዎቻችን ተረድቶ በሀገራችን ላይ የተደቀነው ብሄራዊ አደጋ በጋራ ትግል እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን።

ግመሎቻችን ጭምር የሚያውቋት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳትወድቅ፣ ነፃ ሀገር እንድትኖረን ለትግላችን አስፈላጊውች ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን !

ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ
🙏41
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

ሰበር የድል ዜና!!!
በመተማ ወረዳ 3ኛ ቀኑን ያስቆጠረው አውደ ውጊያ በድል እንደቀጠለ ይገኛል።

የአገዛዙ ሀይል ከምዕራብ አርማጭሆ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለጭማሪ ከቀጠናው ለመግባት ሙከራ ቢያደርግም ፣ በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ ባደረጉት ጣምራዊ ልዩ ኦፕሬሽን ከጥቅምት 25/2018 ከቀኑ 9:00 ላይ የጀመረው አውደ ውጊያ እስከ ጥቅምት 26/2018 ሙሉ ቀኑን እስከ ምሽት 12:00 ስአት ፣ መውጫ መግቢያ አጥቶ ከፍተኛ ሙትና ቁስለኛ ከማስተናገዱ ባሻገር የደረሰበትን ከፍተኛ በትር መቋቋም ሲያቅተው በማታ ስአት እግሬ አውጭኝን ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ድምጡን አጥፍቶ ከታፈነበት ቦታ ወጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሽንፈት ያላዳነውን የድረሱልኝ ታፍኛለሁ ጩኸት ለማገዝ ከመተማ የተነሳው የአገዛዙ ጥምር ሀይል አሁንም ላንተስ ማን ይዞልሀል አይነት ሌላ ያልተጠበቀ ከባድ መብረቃዊ ጥቃት በነበልባሎቹ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ተካ ብርጌድ በአርበኛ ደሴ ተገኘ ስምሪት ሰጭነት ከመተማ ወጣ ብሎ ጓንግ ከምትባል ቦታ ላይ ይህን አረመኔ አራጅ ቡድን በዛሬው እለት ጥቅምት 27/2018 ከጧት ጀምሮ አይቀጡ ቅጣት እየቀጡት ይገኛሉ።

በጥቅሉ ባለጊዜ ነኝ ባዮች የዘር ፓለቲካ አራማጆች የኦሮሙማ ስርአት አራጊ ፈጣሪዎች በየ ጊዜው በአማራ ላይ የሚዶሉቱትን ተለዋዋጭ የጥፋት ሴራ እና ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ በጭፍን ጥላቻ ህዝባችን ለመሰልቀጥ ያዘጋጁት በመከላከያ ስም የሚነግደው የስርአቱ አስፈፃሚ ከየትም መጣ ከየት ወደ ቀጠናው መግባትም ሆነ ከገባም መውጣት እንደማይችል ፣ በፋኖ ብርቱ ክንድ ከፍተኛ ሽንፈት እየደረሰበት ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ምድሩም የእግር እሳት እየሆነበት ይገኛል።

የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህ/ግ አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳሳወቀን በአሁኑ ስአት የአገዛዙ አረመኔ በየ አቅጣጫው የጭንቀት ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ለንፁሀን ህይወትና ንብረት ስጋት ሆኖ ይገኛል። አካባቢው ላይም የድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ማህበረሰቡም ሆነ የፋኖ ሀይል ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክት ማስተላለፍ እንወዳለን።

በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
ወደ መተማ ከተማ 1 አይሱዙ አስክሬንና 2 አምቡላንስ ቁስለኛ አንስቶ የወሰደ ሲሆን አውደ ውጊያው ይህን መረጃ እስካጠናቀርንበት 7:30 ድረስ እንደቀጠለ ይገኛል።
🙏2
ከደሴ አፍንጫ ስር ልዩ ኮማንዶዎች ተመረቁ!

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ስር ተወርዋሪዋ በላጎ ሻለቃ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ለወራት ያሰለጠነቻቸው ዕጩ ኮማንዶዎችን ማስመረቋን የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም ኮሮቹና በዕዙ ልዩ ዘመቻ በበርካታ ቀጠናዎች እያሰለጠነ ነባሩን ፋኖ በሰው ሃይል እያጠናከረ የህልውና ትግሉ በሚፈልገው ልክ ራሱን እየተደራጀ ይገኛል::

ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ስልጠናውን በቀላል ወጭ ነገር ግን የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እየተሰጠ የከፍተኛ እውቀትና ስነምግባር ባለቤት እያደረገ ለህልውና ትግሉ እያቀረበ ይገኛል ነው ያለው ሕዝብ ግንኙነት መምሪያው።