ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ምኒልክ ዕዝ ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እንደሆነ ይታወቃል::

በዚህም በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ህዝብ ጋር ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ህዝቡ የመረጣቸውን አመራሮች በመሾም አራት ንዑስ ወረዳዎችን በማሰባሰብ የአምባሰል ወረዳ አስተዳደርን መስርቷል:: በቀጣይም ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
🙏1
ጋሸና ዙሪያ ላይ የደጋው መብረቅ ኮር ከየ ክፍለ ጦሮቹ በተውጣጡ ሻለቆች ጥላትን ስቦ በማስገጥና ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም በተደረገው አውደ ውጊያ በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊትን ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ የሚኒሻና የፖሊስ አባላቶች በየግለሰብ ቤት እየተበተኑ የገቡና የተደበቁ ሲሆን ከተደበቁበት ጓዳ እየተመዘዙ በንስሮቹ ገቢ ተደርገዋል።

አውደ ውጊያው ከወትሮው በይዘቱ የተለየና በጋሸና ዙሪያ በጥላት ላይ ጠንካራ እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን ከዚህ ቀደም ነፃ የወጡ ቀጠናዎችን ከማፅናት ባለፈ ተጨማሪ ቦታዎችን መቆጣጠር ተችሏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር የሚድያ ክፍል
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
3🙏1
ፋኖ የአቅመ ደካሞችን ሰብል ሰበሰበ!!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር አመራሮች የአቅመ ደካሞችን ሰብል ሰብስበዋል!!

ከአዉደዉጊያ ጎን ለጎን የማህበረሰቡን ሰብል በመሰብሰብ አጋርነታቸዉን አሳይተዋል!!

የክፍለጦሩ የስታፋ አመራሮች እና የሰራዊቱ አባላት በሸዋ በረኀት ወረዳ፣ሀገረማሪያም እና ምንጃር ወረዳዎች የአቅመ ደካሞችን ሰብል በመሰብሰብ የህዝብ ልጅ መሆናቸዉን አስመስክረዋል።

ከአዉደዉጊያ ጎን ለጎን የአቅመ ደካሞችን ሰብል በመሰብሰባችን  ታላቅ ደስታ ተሰምቷናል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ የከሰም ክፍለጦር ማህበራዊ ዘርፋ ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ አሰፋ ተናግረዋል።

ወቅቱ ሰብል የሚሰበሰብበት ጊዜ በመሆኑ የማህበረሰቡን ሰብል በየተዋረዱ እየሰበሰብን እንገኛለን ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ህግ አገልግልት ክፍል ኮማንደር ነጋሽ አሰፋ ገልፀዋል።
3🙏1
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ99ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

ክፍለጦሩ በአምስት  ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።

የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ፣ በአርበኛ ስሜነህ ሙላቱ አስተባባሪነት ተጠናቋል ።

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
🙏3
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ77ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

ክፍለጦሩ በአምስት  ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።

የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ስሜነህ ሙላቱ  ፣ በአርበኛ ግሩም ምሳሌ እና በሀምሳ አለቃ ታደሰ ልንገር አስተባባሪነት ተጠናቋል ።

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
🙏4