ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ኦሮምያ ምሥራቅ አርሲ መርቲ ወረዳ ዛሬም ተጨማሪ አንድ ሰው ተገድሏል ሲሉ ምንጮች ከቦታው ገለጹ።

ትናንት ከአጨዳ መልስ ምሳ ሊበሉ እንደተቀመጡ 5 ያክል ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውንና ታፍነው የተወሰዱ እንዳሉ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፤ ዛሬ አንድ የኦርቶዶክስ አማኝ የሆነ ሰው መገደሉን ምንጮች ገለጸዋል።

የተገደለው እንዳለ ሲሳይ የሚባል ሲሆን፤ ፈረቀሳ ቀበሌ ተገድሎ ዛሬ ሥርዓተ ቀብሩ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟልም ተብሏል።

በአንጻሩ የኦርቶዶክሳውያንን ግድያ ትኩረት ያልሰጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሌላ አጀንዳዎች ላይ ተጠምዶ ታይቷል ብለዋል ታዛቢዎች።

በብልጽግና የሚመራው "የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ" የሚባለው ስብስብም ተጠናክሮ የቀጠለውን የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አጣጥሎት ተመልክተነዋል። በገሐድ የታየውን ግድያ "አጣሪ ልዑክ ልኪያለሁ" ሲልም በፌስቡክ ገጹ ጽፎ ታይቷል።
💔2
በአማራነታቸው የተነሳ በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ከእየቤታቸውና ስራ ቦታቸው ከተወሰዱ በኋላ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ፍትህ ፈላጊ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን የጥቅምት 26/2018
የችሎት ውሎ በስፍራው ተገኝተው በመከታተል አጋርነትዎን ይግለጹ!

(1) በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የክስ መዝገብ (23) ሰዎች፣
(2) በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ (16) ሰዎች እና
(3) በእነ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም የክስ መዝገብ (5) ሰዎች ጥቅምት 26/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ።

በችሎት ተገኝተው በመከታተል በአማራነታቸው ያለ ፍትህ በግፍ ታስረው ለሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች አጋርነትዎን ይግለጹ!

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 25/2018)
👍31💔1
#ሌላ_የእልቂት_መርዶ_ከአርሲ፣ ኦሮሚያ

በቅርቡ ከ 25 በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ባለቁበት ጉናና መርቲ ወረዳዎች ዛሬም ማለትም
ጥቅምት 24 በመርቲ ወረዳ ልዩ ቦታው ጋዶ በሚባል አካባቢ ለደቦ የእርሻ ሥራ የወጡ ንጹሓን በሙሉ ታፍነው 5ቱ ወዲያው ሲገደሉ ቀሪዎቹ የደረሱበት አልታወቀም።

ራሳቸውን እንዳይከላከሉ በዓላማና በጥንቃቄ በመፈጸሙ  እጣ ፈንታቸው እልቂታቸውን ቆሞ መጠበቅ ኾኗል።

እናት ፓርቲ እልቂቱን በጽኑ ያወግዛል፤ ልባዊ ሐዘኑንም ይገልጻል።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
1
#አፋብኃ_እንደ_ንስር_ከፍብሎ_በመብረርላይ_ይገኛል
የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ እዝ የ201ኛ ኮር ምስረታ ተጠናቋል። በስሩ ያሉት ክፍለ ጦሮች
         54ኛ ክ/ጦር
         64ኛ ክ/ጦር
         74ኛክ/ጦርን በማቀፍ ምስረታው ተጠናቆ የኮሩ አመራሮችም በጋራ ትውውቅ በማድረግ ለቀጣይ ስራወች እራሳቸውን ዝግጅ በማድርግ ተልዕኮወችን በመስጠት በአዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ወደተግባር ተገብቷል።

      ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
               የኮሩ አመራሮች በከፊል
🙏2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

በምእራብ ጎንደር መተማ ወረዳ የአገዛዙ ደም መጣጭ ቡድን ክፉኛ እየተቀጣ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል።

ቀጠናው ላይ በተደረገው ተደጋጋሚ ሽንፈት የተነሳ ጭማሪ ሀይል ለማስገባት ፣ በትናንትናው እለት ጥቅምት 25/2018 የአገዛዙ ግብስብስ ፀረ አማራ የአውሬው ስርአት አስፈፃሚ ሀይል መነሻውን ምዕራብ አርማጭሆ ማሰሮ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለመግባት ሲንቀሳቀስ ፣ በአናብስቶቹ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድ በአርበኛ ገ/ህይወት እየተመራ እና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ በአርበኛ ተስፋየ እየተመራ ፣ ይህንኑ ግብስብስ ሀይል ሁለቱ ብርጌዶች ወሳኝ የሞት ወረዳ ታጉር ከምትባል ቦታ ደፈጣ በማድረግ ከቀኑ 9:00  ስአት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል። በዚህ ፈጣን የማጥቃት የደፈጣ ውጊያ የደነገጠው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አራጅ ቡድንና ሆዳም የብልፅግና ተስፋ ቆራጭ በራሳቸው መተማመን የሌላቸው ትንንሽ ጭንቅላቶች በአሁኑ ስአት በቀጠናው ከፍተኛ ሽንፈትንና ድንጋጤን ፈጥሮባቸዋል። ይህንኑ በደፈጣ የጀመረው ውጊያ በአሁኑ ስአት ወደ መደበኛ አውደ ውጊያ ተቀይሮ ፣ የአገዛዙ ጥምር ሀይል ቀለበት ውስጥ ገብቶ ክፋኛ እየተቀጠቀጠ መውጫ መግቢያ አጦ ይገኛል።የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህዝብ ግንኙነት አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳደረሰን አውደ ውጊያው በአስፈሪነቱና በድል እንደቀጠለ እንዳልተቋጨ አድርሶናል።

ከ9:00__11:00 ስአት በተደረገው ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት = 27
ቁስለኛ = 35
የሞርተር ቅምቡላ = 4
የዲሽቃ ተተኳሽ = 1 ሳጥን
ወታደራዊ ሻንጣ = ከ30 በላይ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ
ጥቅምት 26/2018
🙏1
አዲስ ቅዳም‼️                                                              

ጠላት ወደ አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧልል‼️

እረመጧ የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም ብርጌድ ዛሬ ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት ጠላትን ቁም ስቅሉን ስታበላዉ አርፍዳለች።

ጠላት በከተማዋ መዉጫ እና  መግቢያ ጨምሮ ምድሯ ላይ ሁሉ የቆፈረዉን የቁም ምሽግ በመተማመን ከአለዉ አራዊት  ዉስጥ ግማሹን ከፍሎ ኬላ ዘርግቶ ለመዝረፍ ወደ አሽዋ ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን በእረመጦቹ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ትንፋሾች  ሎሊስታ  ላይ ተይዞ  በመቀጥቀጡ አንድ ጓዱን ገብሮ የዝርፊያ እቅዱን ሳያሳካ ወደ አድጓሚ ተራራ እንዲፈረጥጥ ተደርጓል ።

በተመሳሳይ ዘራፊ ጓዱን ለመጠበቅ ከተማዋን በቁም ምሽግ ቁፋሮ የገበጣ ሜዳ ያስመሰላት የብልፅግና እንጉዳይ ጦር የእረመጦችን  ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ መንቀሳቀስ ገና እንደሰማ ጥቅምት 6ን እያስታወሰ የመሪዎቹን "ቁም¡" የሚል ትዕዛዝ  ወደ ጎን በመተዉ ለጊዜዉ ነፍሱን ወደሚያተርፍባት አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧል።

አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ  አዲስ ተስፋ!!!


ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም

ይበልጣል የዉነቱ (እሳቱ)
🙏1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

በምእራብ ጎንደር መተማ ወረዳ የአገዛዙ ደም መጣጭ ቡድን ክፉኛ እየተቀጣ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል።

ቀጠናው ላይ በተደረገው ተደጋጋሚ ሽንፈት የተነሳ ጭማሪ ሀይል ለማስገባት ፣ በትናንትናው እለት ጥቅምት 25/2018 የአገዛዙ ግብስብስ ፀረ አማራ የአውሬው ስርአት አስፈፃሚ ሀይል መነሻውን ምዕራብ አርማጭሆ ማሰሮ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለመግባት ሲንቀሳቀስ ፣ በአናብስቶቹ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድ በአርበኛ ገ/ህይወት እየተመራ እና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ በአርበኛ ተስፋየ እየተመራ ፣ ይህንኑ ግብስብስ ሀይል ሁለቱ ብርጌዶች ወሳኝ የሞት ወረዳ ታጉር ከምትባል ቦታ ደፈጣ በማድረግ ከቀኑ 9:00 ስአት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል። በዚህ ፈጣን የማጥቃት የደፈጣ ውጊያ የደነገጠው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አራጅ ቡድንና ሆዳም የብልፅግና ተስፋ ቆራጭ በራሳቸው መተማመን የሌላቸው ትንንሽ ጭንቅላቶች በአሁኑ ስአት በቀጠናው ከፍተኛ ሽንፈትንና ድንጋጤን ፈጥሮባቸዋል። ይህንኑ በደፈጣ የጀመረው ውጊያ በአሁኑ ስአት ወደ መደበኛ አውደ ውጊያ ተቀይሮ ፣ የአገዛዙ ጥምር ሀይል ቀለበት ውስጥ ገብቶ ክፋኛ እየተቀጠቀጠ መውጫ መግቢያ አጦ ይገኛል።የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህዝብ ግንኙነት አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳደረሰን አውደ ውጊያው በአስፈሪነቱና በድል እንደቀጠለ እንዳልተቋጨ አድርሶናል።

ከ9:00__11:00 ስአት በተደረገው ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት = 27
ቁስለኛ = 35
የሞርተር ቅምቡላ = 4
የዲሽቃ ተተኳሽ = 1 ሳጥን
ወታደራዊ ሻንጣ = ከ30 በላይ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ጥቅምት 26/2018
1🙏1
ምኒልክ ዕዝ ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እንደሆነ ይታወቃል::

በዚህም በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ህዝብ ጋር ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ህዝቡ የመረጣቸውን አመራሮች በመሾም አራት ንዑስ ወረዳዎችን በማሰባሰብ የአምባሰል ወረዳ አስተዳደርን መስርቷል:: በቀጣይም ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
🙏1
ጋሸና ዙሪያ ላይ የደጋው መብረቅ ኮር ከየ ክፍለ ጦሮቹ በተውጣጡ ሻለቆች ጥላትን ስቦ በማስገጥና ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም በተደረገው አውደ ውጊያ በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊትን ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ የሚኒሻና የፖሊስ አባላቶች በየግለሰብ ቤት እየተበተኑ የገቡና የተደበቁ ሲሆን ከተደበቁበት ጓዳ እየተመዘዙ በንስሮቹ ገቢ ተደርገዋል።

አውደ ውጊያው ከወትሮው በይዘቱ የተለየና በጋሸና ዙሪያ በጥላት ላይ ጠንካራ እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን ከዚህ ቀደም ነፃ የወጡ ቀጠናዎችን ከማፅናት ባለፈ ተጨማሪ ቦታዎችን መቆጣጠር ተችሏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር የሚድያ ክፍል
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
3🙏1
ፋኖ የአቅመ ደካሞችን ሰብል ሰበሰበ!!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር አመራሮች የአቅመ ደካሞችን ሰብል ሰብስበዋል!!

ከአዉደዉጊያ ጎን ለጎን የማህበረሰቡን ሰብል በመሰብሰብ አጋርነታቸዉን አሳይተዋል!!

የክፍለጦሩ የስታፋ አመራሮች እና የሰራዊቱ አባላት በሸዋ በረኀት ወረዳ፣ሀገረማሪያም እና ምንጃር ወረዳዎች የአቅመ ደካሞችን ሰብል በመሰብሰብ የህዝብ ልጅ መሆናቸዉን አስመስክረዋል።

ከአዉደዉጊያ ጎን ለጎን የአቅመ ደካሞችን ሰብል በመሰብሰባችን  ታላቅ ደስታ ተሰምቷናል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ የከሰም ክፍለጦር ማህበራዊ ዘርፋ ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ አሰፋ ተናግረዋል።

ወቅቱ ሰብል የሚሰበሰብበት ጊዜ በመሆኑ የማህበረሰቡን ሰብል በየተዋረዱ እየሰበሰብን እንገኛለን ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ህግ አገልግልት ክፍል ኮማንደር ነጋሽ አሰፋ ገልፀዋል።
3🙏1