ቀን፦ ጥቅምት ፳ ፫/፳ ፻ ፲ ፰ ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
በላይ ዘለቀ ዕዝ በጉባኤ መቋጫ ላይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
“በድርጅታዊ ማዕከላዊነት የኅልውና ትግላችንን ዓላማ እናሳካለን!!!”
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በላይ ዘለቀ ዕዝ ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም ዓመታዊ የሥራ አሥፈጻሚ ጉባኤውን አድርጓል። የጀመርነው የኅልውና ትግል ከያዝነው ነባራዊ እውነት ባሻገር፣ ብርቱ መረዳትን፣ ክህሎትንና ልዩ ልዩ የትግል ስልተ መንገዶችን መንደፍንም ጭምር አጥብቆ ይሻል።
በውይይት ፖለቲካዊ አቅም ያድጋል፣ በውይይት የሃሳብ ልዩነቶች ይገራሉ/ይታረቃሉ፣ በውይይት ጓዳዊ መስተጋብሮች ይዳብራሉ፣ በውይይት አዳዲስ የአሠራር መንገዶች ይቀየሳሉ። ከምንም በላይ ደግሞ ልዩልዩ ሥልጠናዎችን በጋራ መውሰድ አንድም መስጠት የአረዳድ ልዩነቶችን ለማጠበብ ያግዛል። በዚህ መሠረት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በላይ ዘለቀ ዕዝ አመራሮች ለጋራ ትግል፣ ለጋራ ዓላማና ግብ በጋራ መምከርና መሰልጠን በማስፈለጉ ይህ ታሪካዊ ጓባኤ ተዘጋጅቶ በተሳካ መንገድ ተጠናቋል። ጉባኤው ቀጠናችን ላይ የሚገኙትን አስቸጋሪ ሰንሰለታማ ተራሮችንና ቁልቁለቱን በማቆራረጥ ከሃያ ቀናት በላይ ጉዞን በጠላት መካከል አቆራርጠን የመከርንበት፣ አቅጣጫዎችን ያስቀመጥንበት፣ የጋራ መገነዛዘቦችን የፈጠርንበት ትልልቅ ውሳኔዎችን ያሳለፍንበት ታሪካዊ ጉባኤ ነው።
የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ መሪ ቃል “በድርጅታዊ ማዕከላዊነት የኅልውና ትግላችንን ዓላማ እናሳካለን” የሚል ሲሆን ድርጅታዊ ማዕከላዊነት አሁን ላይ ያለውን የተበታተነ ኃይል፣ የተበታተነ ሃሳብ፣ የተበታተነ አደረጃጀትን በአማራነት እሴት አንድም በአማራነት አስተሳሰብና በመታገያ ጉዳያችን አይለወጤ ነገረ ጉዳይ አማካይነት የሚከናወን ቁልፍ እሳቤ ነው። የኅልውና ትግላችን እድገቱ፣ የአደረጃጀትና የኃይል ግንባታ ስፉህነቱ፣ የጠላት ደካማና ተለዋዋጭ የአጥፊነት መንገዱ፣ የቀጠናው መልክዓ ፖለቲካዊ ተለዋዋጭ እንቅስቃሴው፣ የዓለም
አቀፍ ግዙፍ ተቋማት ሥርዓቱ ላይ ያላቸው አተያይን በተሟላ መንገድ ማስተካከል የሚቻለው ወጥ የሆነ ማዕከላዊነቱን የጠበቀ ተቋማዊ አንድም ድርጅታዊ አሠራርን ማሳደግና ማከበር ሲቻል እንደሆነ በጽኑ
እናምናለን። ድርጅታዊ ማዕከላዊነት ተቋማዊ መርኅና አሠራር ከላይ ወደ ታች፣ በአንጻሩ በድርጅት ጥላ ሥር የሚገኙ አሓዶች፣ ግለሰቦች ከታች ወደ ላይ የሚያከናውኗቸው የሠመሩ ተግባቦቶች እንዲፈጠሩ ጉልህ ሚና
ይጫወታል። በዚህ ሂደት ውስጥ ድርጅታዊ አሠራሮች፣ ህግና ደንቦች፣ ነባራዊ እውነት፣ ዘመን ዘለል ልሂቅነት፣ ዓለምአቀፍ አሠራርን ያማከለ ምክንያታዊነት፣ ለህዝብ ጥቅምና ለወል ዓላማ መስዋዕት ከፋይነት ማጠንጠኛ
ቁልፍ ጉዳዮቹ ናቸው። ድርጅታዊ ማዕከላዊነት እኔነትን ይጠየፋል በአንጻሩ በእኛነት፣ በአብሮነት፣ በአንድነትና በአንድ ተቋማዊ አሠራር ተገዥነት የሚጓዙት የአሠራር መሠረት ነው። ለዚህ መሰሉ አሠራር በላይ ዘለቀ ዕዝ
የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላትና መላው የዕዛችን የሠራዊቱ አመራሮችና አባላት የሚያምኑበትን፣ የሚያሸንፉበትን፣ ጠላትን የሚነቅሉበትን፣ የሕዝባችንን ዘለቄታዊ ኅልውና የምናረጋግጥበትን በማዕከላዊ አንድ አሠራርነት፦ አንድ አመራርነት፣ አንድ ግን የጋራ ውሳኔ ሰጭነት፣ የጋራ ጠላት ላይ ማበር መተባበርነት፣ አንድ ተቋም መፍጠርነት፣ በአማራነት አንድ መሆንነት ላይ ትኩረታችን፣ ውይይትና ሥልጠናችንን ማድረግ
ችለናል።
በጥቅሉ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በላይ ዘለቀ ዕዝ በጉባኤው መቋጫ ላይ የሚከተሉትን ሦስት የአቋም መግለጫዎች በማውጣት ጉባኤውን ቋጭቷል።
1. የአብይ አሕመድ አረመኔያዊ አገዛዝ ባለፉት ሰባት ዓመታት በመላው አገሪቱ አማራዊ ማንነት ያላቸውን አካላት ያለ አንዳች ምክንያት እንደ አውሬ እያደነ በጅምላ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉ፣ ከቀያቸው ማፈናቀሉ፣ ሃብት ንብረታቸውን ማውደሙ ገሐደ የወጣ ሐቅ ነው። ከምንም በላይ ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት ክልላችን ውስጥ ጦር አዝምቶ ያልፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት የለም።
ሕዝባችንንም በጅምላ በአየር ኃይልና በሜካናይዝድ ጦር ጨፍጭፏል፣ ዓለምአቀፋዊ የጦር ወንጀልም ፈጽሟል። እንዲሁም ለማኅበራዊ፣ ምጣኔሃብታዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ሕዝባችንን ዳርጎታል። በዚህ ሥርዓታዊ አውዳሚነት ሂደት ውስጥ የፋኖ መካች ትግልና እንቅስቃሴ ባይኖር ኖሮ ግፍና መከራው
በመቶዎች እጥፍ ሊጨምር በቻለ ነበር። ስለሆነም በመንግሥትነት ጭምብል የሚነግደው ይህ ወንጀለኛ ሥርዓት በአጭር ጊዜ እንዲወገድ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ማእከላዊነትን ጠብቀን የትግል መንገዳችንን ሥልታዊነት (Strategize) አድርገን ለመታገል ያለንን ጽኑ አቋም
እንገልጻለን።
2. የኅልውና ትግላችንን የገጠመው የኃይል እጥረት ሳይሆን ያለንን ሰፊ ኃይል በአንድ አስተባብሮና አቀናጅቶ ጠላት ላይ አለመተባበር እንደሆነ የታመነ ጉዳይ ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ አጠገብ ካለ ወንድም ይልቅ ሩቅ ላለ አካል ከፍተን የሰጠነው ጆሯችን ብዙ ዋጋ አስከፈለን። የአንድ አማራዊ ማንነት ባለቤቶች ሆነን፣ አንድ ጠላት ኖሮን፣ አንድ ዓይነት ሞት ተደግሶልን እኛ ለምን አንድ
መሆን ተሳነን ካልን ቁጭ ብለን መነጋገር አለመቻላችን ካልሆነ ሌላ ምክንያት የለንም። “መለያየት ሞት ነው” እንዳለ ባለቅኔው መለያዬት ለተደገሰልን ሥርዓታዊ የሞት ድግስ ራስን ማዘጋጀት ነው፣ መለያየት የሕዝብን ሰቆቃ ማራዘሚያ መንገድና ጸረ ሕዝብነት ነው፣ መለያዬት ልሂቅነት ሳይሆን የዘመናችን የአላዋቂነት ጥግ ነው፣ መለያዬት በድርጅታዊ ማዕከላዊነት አለመጓዝና ትልቁን ዓላማና
ግብ መዘንጋት ነው። ስለሆነም ማሸነፊያ መንገዳችን የሕዝብን እንባ ማበሻ መሃረባችን፣ የተደበቀም የተገለጠም የጠላት አሠራርና እቅድን ማርከሻ ፍኖታችን፣ በኅልውና ትግላችን ስም በሕዝብ ላይ የሚቀልዱ ባለግል ፍላጎት አጋች፣ ሌባ ዘራፊና ተላላኪ ባንዳዎች ማጥሪያ ወንፊታችን አንድነት ብቻ ነው። ይህንን ቅዱስ ተግባር ለማከናወን ቁጭ ብሎ “እውነትን፣ እውቀትን፣ ፍጹም መተማመንን” ማእከል አድርጎ መነጋገር መቻል እንደሆነ በጽኑ እናምናለን። ለዚህ ተግባራዊ ሥራ ደግሞ የበላይ ዘለቀ እዝ እስከ መጨረሻው ድረስ ተጉዞ የማሸነፊያ ቁልፍ የሆነው አንድነት እንዲመጣ ያለንን ጽኑ አቋም እንገልጻለን።
3. በአፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ታፍራና ተከብራ የምትኖረውን ታላቋን ሃገር ኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ተደማጭነቷን፣ ታሪካዊ ልዕልናዋን በማኮሰስ፣ በውስጥ ዓለምአቀፍ የጦር ወንጀል እየፈጸመ፣ በቀጠናው ሃገሪቷን ወደ ጦርነት አዙሪት ውስጥ ለማስገባት እየተደረጉ ያሉ የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ አካሄድ የሥርዓቱን የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ድህነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ጉዳይ ነው። የምሥራቅ አፍሪካ መልክዓ ፖለቲካ በየቀኑ መልኩንና ገጽታውን እየለዋወጠ የሚገኘውም በግንባር ቀደምትነት በብልጽግና ተናካሽ የፖለቲካ አካሄድ እንደሆነ ለማንም የተሰወረ አይደለም። ይኸው የምሥራቅ አፍሪካ

❤3🙏1
ቀጠና በርካታ የተፈጥሮ ሃብቶች ያሉት፣ የበርካታ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ማኅበራዊና መሰል የባህል፣ የቋንቋ፣ የእምነት እንዲሁም የሥነ ልቡና ተጋሪነት ያለው በመሆኑ አብሮ የመልማት፣ ሥነ ምኅዳራዊ ተጋሪነትና ተጠቃሚነት ያለው መሆኑን እንኳን የሚያስብበት ፖለቲካዊ መርኅና ስሪት
የሌለው የቀጠናው ጸረ-ሰላም ኃይል መሆኑን በዓለም አደባባይ እያሳየ የሚገኝ በመሆኑ ይህንን እኩይ እብሪተኛ ቡድን እስካልተወገደ ድረስ በውስጥም በቀጠናውም ሠላም መስፈን እንደማይችል በጽኑ እናምናለን።
ስለሆነም በውስጥ የሃገሪቱ ሁሉንአቀፍ ቀውስ እንዲስተካከል በውጭ ቀጠናዊ ቀውሱ
እንዲስተካከል ቀውስ ጠማቂውን በተባበረ ክንድ ማስወገድ ቁልፉ ተግባራችን እንደሆነ ያለንን ጽኑ አቋም እንገልጻለን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በላይ ዘለቀ ዕዝ

❤2🙏1
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አባ ናደው የተገኙ ድሎችን አስጠብቆ አዳዲስ ድሎችንም እያስመዘገበ ቀጥሏል!
በሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎችና ታዳጊ ከተሞች:ኮን፣እስታይሽ፣ሃሙሲት፣አሁንተገኝ፣ ቀበሮ ሜዳ እና ሌሎች ታዳጊ ከተሞች በምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ገብተዋል:: እነዚህ ድሎች እየተመዘገቡ ያሉት አዲስ በተደራጀው በኮሩ ሰብሳቢ በሻለቃ ሃብቴ እባቡ እና በወታደራዊ አዛዡ አርበኛ ተመስገን አለባቸው የሚመራው የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ሲሆን የዞብል አምባ ክፍለጦር አሃድ የሆነችው 5ኛ ሻለቃም የበኩሏን ጉልህ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች::
ተጋድሎው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ዳውንት ወረዳ ሙሉ ለሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው:: ደላንታ ወረዳ ከወረዳ መቀመጫው ወገልጤና ከተማ ውጭ ሙሉ ለሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው:: መቄትና ጋሼና ከከተሞቹ ውጭ ያሉ ቀበሌዎች 100% በምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ናቸው:: ሌሎች ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎችም በቅርቡ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ይሆናል::
ከዘመቻ አባናደው በድል መጠናቀቅ በኋላ በርካታ ቁጥር ያለው እግረኛና ኮማንዶ ሰራዊት ወደ ቤተ-አማራ በማስገባት በመካናይዝድና በአየር ሃይል በጄትና በድሮን ታግዞ በሙሉ አቅም ወደ ማጥቃት የገባውን የፋሽስቱን ሰራዊት ምሽግ ለቆ ወደ ፋኖ ቀጠናዎች እንዲገባ በማድረግ በአውደ ውጊያ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም በመማረክ ከአውደ ውጊያ ውጭ በማስኮብለል ብትንትኑን እያወጣነው እንገኛለን::
ፋሽስቱ ብልፅግና በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ እና ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ምስራቃዊ ቀጠናዎች እስከ አፋር አጎራባች አካባቢዎች ባለፉት አምስት ቀናቶች ከባድ ማጥቃት ቢያደርግም በምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር በኮሩ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ደባሽ መምሬ እና በኮሩ ዘመቻ አርበኛ እንድሪስ ጉድሌ አጋፋሪነት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው አሳፍረው በዘረራ ቀጠናውን ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

🙏1
ከጋሸና ከተማ በቅርብ ርቀት በተደረገ ውጊያ ስምንት የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ 15 ወታደሮች መቁሰላቸው ተሰምቷል።
ውጊያው የተካሄደው ትልቅ ወታደራዊ ጠቀሜታ እንዳላት ከሚነገርላት ከጋሼና ከተማ ወደ ወልድያ መውጫ መጨረሻ ካሉ መንደሮች መካከል አንዱ በሆነው ጥምጥማት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ መሆኑን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በዚህ ስፍራ ዛሬ ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ከእኩለ ቀን በኋላ በተደረገ ውጊያ የጠላት ብልፅግና ኃይል ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን ሲከናነብ፡ በአንፃሩ ደግሞ የፋኖ ኃይል በውስን ኃይል ትልቅ ድል ያስመዘገበበት አውደ ውጊያ ሆኖ አልፏል።
በቅርቡ የደጋው መብረቅ ኮርን መስርተው በምኒልክ ዕዝ ስር ከተካተቱ ክ/ጦሮች መካከል አንዱ የሆነው ደጀን ክ/ጦር ጥምጥማት ላይ በወሰደው እርምጃ ስምንት የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ሲገደሉ፡ 15 ወታደሮች ደግሞ መቁሰላቸውን የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ያስታወቀው።
በውጊያው ሙትና ቁስለኛ ከተደረጉት ወታደሮች በተጨማሪ ሦስት የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተማርከዋል።
በቅርቡ ተመስርቶ በምኒልክ ዕዝ ስር የተካተተው ኮሩ፡ ምስረታውን ካበሰረበት እለት ጀምሮ እያደረጋቸው ባለው ተጋድሎዎች አራት ኪሎ ላለው የፀረ አማራው ኃይል ከባባድ መርዶዎችን፡ በአንፃሩ ደግሞ የወገን ኃይልን በድል ቁንጣን የሚያጨናንቁ ጀብዶችን በመፈፀም በድል ታጅቦ ቀጥሏል።

ኦሮምያ ምሥራቅ አርሲ መርቲ ወረዳ ዛሬም ተጨማሪ አንድ ሰው ተገድሏል ሲሉ ምንጮች ከቦታው ገለጹ።
ትናንት ከአጨዳ መልስ ምሳ ሊበሉ እንደተቀመጡ 5 ያክል ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውንና ታፍነው የተወሰዱ እንዳሉ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፤ ዛሬ አንድ የኦርቶዶክስ አማኝ የሆነ ሰው መገደሉን ምንጮች ገለጸዋል።
የተገደለው እንዳለ ሲሳይ የሚባል ሲሆን፤ ፈረቀሳ ቀበሌ ተገድሎ ዛሬ ሥርዓተ ቀብሩ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟልም ተብሏል።
በአንጻሩ የኦርቶዶክሳውያንን ግድያ ትኩረት ያልሰጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሌላ አጀንዳዎች ላይ ተጠምዶ ታይቷል ብለዋል ታዛቢዎች።
በብልጽግና የሚመራው "የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ" የሚባለው ስብስብም ተጠናክሮ የቀጠለውን የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አጣጥሎት ተመልክተነዋል። በገሐድ የታየውን ግድያ "አጣሪ ልዑክ ልኪያለሁ" ሲልም በፌስቡክ ገጹ ጽፎ ታይቷል።

💔2
በአማራነታቸው የተነሳ በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ከእየቤታቸውና ስራ ቦታቸው ከተወሰዱ በኋላ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ፍትህ ፈላጊ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን የጥቅምት 26/2018
የችሎት ውሎ በስፍራው ተገኝተው በመከታተል አጋርነትዎን ይግለጹ!
(1) በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የክስ መዝገብ (23) ሰዎች፣
(2) በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ (16) ሰዎች እና
(3) በእነ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም የክስ መዝገብ (5) ሰዎች ጥቅምት 26/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ።
በችሎት ተገኝተው በመከታተል በአማራነታቸው ያለ ፍትህ በግፍ ታስረው ለሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች አጋርነትዎን ይግለጹ!
(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 25/2018)

👍3❤1💔1
#ሌላ_የእልቂት_መርዶ_ከአርሲ፣ ኦሮሚያ
በቅርቡ ከ 25 በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ባለቁበት ጉናና መርቲ ወረዳዎች ዛሬም ማለትም
ጥቅምት 24 በመርቲ ወረዳ ልዩ ቦታው ጋዶ በሚባል አካባቢ ለደቦ የእርሻ ሥራ የወጡ ንጹሓን በሙሉ ታፍነው 5ቱ ወዲያው ሲገደሉ ቀሪዎቹ የደረሱበት አልታወቀም።
ራሳቸውን እንዳይከላከሉ በዓላማና በጥንቃቄ በመፈጸሙ እጣ ፈንታቸው እልቂታቸውን ቆሞ መጠበቅ ኾኗል።
እናት ፓርቲ እልቂቱን በጽኑ ያወግዛል፤ ልባዊ ሐዘኑንም ይገልጻል።
ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

❤1
#አፋብኃ_እንደ_ንስር_ከፍብሎ_በመብረርላይ_ይገኛል
የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ እዝ የ201ኛ ኮር ምስረታ ተጠናቋል። በስሩ ያሉት ክፍለ ጦሮች
54ኛ ክ/ጦር
64ኛ ክ/ጦር
74ኛክ/ጦርን በማቀፍ ምስረታው ተጠናቆ የኮሩ አመራሮችም በጋራ ትውውቅ በማድረግ ለቀጣይ ስራወች እራሳቸውን ዝግጅ በማድርግ ተልዕኮወችን በመስጠት በአዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ወደተግባር ተገብቷል።
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
የኮሩ አመራሮች በከፊል

🙏2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር
በምእራብ ጎንደር መተማ ወረዳ የአገዛዙ ደም መጣጭ ቡድን ክፉኛ እየተቀጣ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል።
ቀጠናው ላይ በተደረገው ተደጋጋሚ ሽንፈት የተነሳ ጭማሪ ሀይል ለማስገባት ፣ በትናንትናው እለት ጥቅምት 25/2018 የአገዛዙ ግብስብስ ፀረ አማራ የአውሬው ስርአት አስፈፃሚ ሀይል መነሻውን ምዕራብ አርማጭሆ ማሰሮ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለመግባት ሲንቀሳቀስ ፣ በአናብስቶቹ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድ በአርበኛ ገ/ህይወት እየተመራ እና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ በአርበኛ ተስፋየ እየተመራ ፣ ይህንኑ ግብስብስ ሀይል ሁለቱ ብርጌዶች ወሳኝ የሞት ወረዳ ታጉር ከምትባል ቦታ ደፈጣ በማድረግ ከቀኑ 9:00 ስአት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል። በዚህ ፈጣን የማጥቃት የደፈጣ ውጊያ የደነገጠው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አራጅ ቡድንና ሆዳም የብልፅግና ተስፋ ቆራጭ በራሳቸው መተማመን የሌላቸው ትንንሽ ጭንቅላቶች በአሁኑ ስአት በቀጠናው ከፍተኛ ሽንፈትንና ድንጋጤን ፈጥሮባቸዋል። ይህንኑ በደፈጣ የጀመረው ውጊያ በአሁኑ ስአት ወደ መደበኛ አውደ ውጊያ ተቀይሮ ፣ የአገዛዙ ጥምር ሀይል ቀለበት ውስጥ ገብቶ ክፋኛ እየተቀጠቀጠ መውጫ መግቢያ አጦ ይገኛል።የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህዝብ ግንኙነት አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳደረሰን አውደ ውጊያው በአስፈሪነቱና በድል እንደቀጠለ እንዳልተቋጨ አድርሶናል።
ከ9:00__11:00 ስአት በተደረገው ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት = 27
ቁስለኛ = 35
የሞርተር ቅምቡላ = 4
የዲሽቃ ተተኳሽ = 1 ሳጥን
ወታደራዊ ሻንጣ = ከ30 በላይ
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጥቅምት 26/2018

አዲስ ቅዳም‼️
ጠላት ወደ አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧልል‼️
እረመጧ የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም ብርጌድ ዛሬ ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት ጠላትን ቁም ስቅሉን ስታበላዉ አርፍዳለች።
ጠላት በከተማዋ መዉጫ እና መግቢያ ጨምሮ ምድሯ ላይ ሁሉ የቆፈረዉን የቁም ምሽግ በመተማመን ከአለዉ አራዊት ዉስጥ ግማሹን ከፍሎ ኬላ ዘርግቶ ለመዝረፍ ወደ አሽዋ ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን በእረመጦቹ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ትንፋሾች ሎሊስታ ላይ ተይዞ በመቀጥቀጡ አንድ ጓዱን ገብሮ የዝርፊያ እቅዱን ሳያሳካ ወደ አድጓሚ ተራራ እንዲፈረጥጥ ተደርጓል ።
በተመሳሳይ ዘራፊ ጓዱን ለመጠበቅ ከተማዋን በቁም ምሽግ ቁፋሮ የገበጣ ሜዳ ያስመሰላት የብልፅግና እንጉዳይ ጦር የእረመጦችን ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ መንቀሳቀስ ገና እንደሰማ ጥቅምት 6ን እያስታወሰ የመሪዎቹን "ቁም¡" የሚል ትዕዛዝ ወደ ጎን በመተዉ ለጊዜዉ ነፍሱን ወደሚያተርፍባት አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧል።
አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!!
ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም
ይበልጣል የዉነቱ (እሳቱ)