ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅሟል።

በአፋብኃ ምዕ.አ.ቀ.ቴ.ዕዝ የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅሞ ድል ተቀናጅቷል።

ጥቃቱ የተፈመው በትላንትናው እለት መንግስት ተብዮው የህዝብ ጠላት ከአዴትና ከሌላም ቦታ በመሰባሰብ የተለመደ ፕሮፖጋንዳውን ለመርጨት በሚዶልቱበት ወቅት ለዙሪያ ጥበቃ ባስቀመጧቸው ሆድ አደሮች ላይ ነው።
ጥቃቱ የተፈፀመው ጠላትን ከሁለት አቅጣጫ በመክበብ ሲሆን በዚህ ጥቃትም 5 የመከላከያ አባላት ሲሞቱ 3ቱ ቁስለኛ ሆነዋል።

በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት  በዙ-23 ደብረ -ፅላሎ ወደተባለ ቀበሌ አርሶ አደሮች ለስራ እንደተሰማሩ ፣ህፃናቱና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች በተበተኑበት ህዝቡን ለመምታት በታሰበ መልኩ ከርቀት ሲደበድብ ውሏል።

         አዲስ ትውልድ
         አዲስ አስተሳሰብ
         አዲስ ተስፋ
የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት

          ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
🙏3
ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶዎች በድምቀት አስመረቀ::

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶዎች ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::

የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ሁለንተናዊ ተጋድሎ እያደረገ ያለው ፋኖ አዳዲስ ምልምል ፋኖዎችን በእግረኛ እና በልዩ ኮማንዶ ብሎም በመካናይዝድ ደረጃ እያሰለጠነና እያስመረቀ ነባሩን የፋኖ ሰራዊት በሰው ሃይል እያጠናከረ ይገኛል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም የዕዙ ስልጠና መምሪያ በበርካታ ቀጠናዎች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠነ እያስመረቀ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል::

ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም
🙏4
መንግስት ለአርሲው ግድያ “ ይቅርታ እንዲጠይቅና ካሣ እንዲከፍል ” ኢሕአፓ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ይህንን ያለው ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣውና ለአዲስ ማለዳ በላከላት መግለጫ ላይ ነው፡፡

ፓርቲው በመግለጫው “ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር እና ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በጉና እና በመርቲ ወረዳዎች 17፣ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሽርካ ወረዳ 3፣ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳ 5 በድምሩ 25 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ” ብሏል፡፡

ኢሕአፓ በምዕመኑ ላይ የተፈጸመው ግድያና አካላዊ ጉዳትን አውግዞ መንግስት ተጠያቂነቱን እንዲያምን እና ወንጀሉን የፈጸሙት አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳስቧል፡፡

ለደረሰው ግድያና አካላዊ ጉዳት የተሰማውን ሐዘን የገለጸው ፓርቲው መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅና አስፈላጊ ያለውን ካሳ ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲከፍል ጠይቋል፡፡ የፓርቲው መግለጫ ሲቀጥል ጉዳት ከደረሰባቸው ባለፈም የዕምነቱን ተከታዮች፣ የእስልምና ተከታዮች ላይ ለደረሱት ጉዳቶች በተመሳሳይ ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል፡፡

ከጥቂት አመታት ወዲህ የተባባሱት መጠነ-ሰፊ በዕምነትና በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረቱ ግድያዎች፤ አፈናዎች፣ እገታዎች፣ ማፈናቀሎች፣ የንብረት ንጥቂያዎችና ውድመቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ መንግስት የዜጎችን የመኖር መብት እንዲያረጋግጥ ጠይቋል፡፡
2👍1
ብልጽግና በሊቦ ከምከም ወረዳ ንጹሃን አርሶ አደሮችን ጨፈጨፈ።
በትላንትናው እለት ጥቅምት 20 /2018 ዓ.ም በሊቦ ከምከም ወረዳ ቡራ እግዚአራብ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጭሮየ ከተባለው አካባቢ በመከላከያና የአማራ ህዝብ ጡት ነካሽ በሆነው ሚሊሻ አባት እስከነ ልጁን እና ከብቶችን ግጦሽ ላይ በማገት ላይ የነበረን የ8 ዓመት ህፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ 7 በላይ ንጹሃን አርሶ አደር አማሮችን በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽነዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እዚሁ ቀበሌ ላይ ዘመድ ለመጠየቅ ከሌላ ቦታ የመጡ የቡራ እግዚአራብ ቀበሌ ነዋሪ ያልሆኑ ተጨማሪ አባትና ልጅም በግፍ ተረሽነዋል። ከተረሸኑት ንጹሃን አማሮች መካከል:-
1- ሞላ ታከለ
2-አስቻለው ሞላ
3- ሃብቴ አዲሴ
እንዲሁም ሌሎች ለጊዜው ስማቸው ያልደረሰን ወገኖቻችንም ተወልደው ባደጉበት ፣ ድረው ኩለውና አርሰው አንደፋርሰው በኖሩበት ቀያቸው በብልጽግና አረመኔ አሽከሮች የጭካኔ ጥግ በተሞላበት አኳኋን ተረሽነዋል።
ሌሎች
2 ንጹሃን አማሮችም ክፋኛ ቆስለው አምልጠው በህክምና ላይ ይገኛሉ።
ይህ ዘር የማጥፋት ዘመቻ አሁን ላይ የተጀመረ ባይሆንም ይበልጥ ተባብሶ አድማሱን እያሰፋ በመቀጠል ላይ ነው።
#Stop Amhara Gennocide !!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ጥቅምት 21/2018 ዓም
2🙏1💔1
ጀግኖቹ እስቴ ዴንሳ ብርጌድ የእስቴ ወረዳ ፖሊስ ፅ.ቤት አዛዥን ከባድ ቁስለኛ አድርገዉታል!!!

እስቴ መካነየሱስ ከተማ ቀበሌ 1 ታረቀኝ መታሰቢያ ሆቴል በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት ባህሩ አዳነ የተባለ የወረደዉ ፖሊስ ፅ.ቤት አዛዥ ከባድ ጉዳት ሲያስተናግድ አንድ ሚሊሻ ደግሞ እስከ ወዲያኛዉ ተሸኝቷል።ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ደግሞ ቁስለኛ ተደርጓል።

ዝርዝር መረጃዉን እንመለስበታለን!!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
🙏3
በሚዳና ሬማ ቀጠና 264 የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለፋኖ መስጠታቸው ታወቀ!

በቀጠናው ከነበረው የሚኒሻ ኃይል መካከል ከ80% በላይ የሚሆነውን ማፈራረሱን ፋኖ አስውቋል።

ለፀረ አማራው ብልፅግና ኃይል ተላላኪ እና የአማራን ሕዝብ የከዳ የባንዳ ስብስብ የሆነው የበአዴን ቡድን በሸዋ ቀጠና በሚዳና ሬማ ወረዳ ያሰፈረው "የጭንቅ ቀን አሻጋሪየ" በሚል የሚጠራው የሚሊሻ ኃይል እየፈራረሰ እጁን ለፋኖ እየሰጠ መሆኑን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የተላላኪ ተላላኪ በመሆን በራሱ ሕዝብ ላይ ህልቆ መሳፍርት ግፍና መከራ እየፈፀመና እያስፈፅመ ካለው እራሱን "የሚኒሻ ኃይል" እያለ የሚጠራው የሆድ አደር ስብስብ፡ በመስተመጨረሻም የነሽመልስ አብዲሳ ቡድን <<አማራን ከአማራ ጋር የማጫረስ ሴራ>> ገብቶት ከነ ሙሉ ትጥቁ ከስምሪት ቀጠናው በመጥፋት ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል።

ፀረ አማራውና የሆድ አደሮች እንዲሁም የባንዳዎች ስብስብ የሆነው የበአዴን ቡድን በሸዋ ቀጠና በሚዳና ሬማ ወረዳ አስፍሮት ከነበረው የሚኒሻ ኃይል መካከል በቁጥር 264 አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ስር የሚገኘው አፄ ዳዊት ክ/ጦርን ስለመቀላቀላቸው የኮሩ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

በሚዳና ሬማ ወረዳዎች ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች ማለትም፡ ከቄጠማ እና ሙህሬ ቀበሌ 32 የሚኒሻ አባላት፣ ከይጎቢያ ቀበሌ 79፣ ከአዝማ ቀበሌ 28፣ ከጠባቢት ቀበሌ ዘጠኝ(09)፣ ከመጅት ቀበሌ 35፣ ከአላቦ ቢራባ ቀበሌ 81፡ በድምሩ 264 የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው አፄ ዳዊት ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል ነው ያለው የኮሩ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ።

እነዚህ የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለፋኖ መስጠት የጀመሩት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መሆኑን ለጣቢያችን የገለፀው የኮሩ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል፡ በሁለቱም ወረዳዎች ከ80% በላይ የሚሆነውን የሚኒሻ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ማፍረስ ችለናል ብሏል።
🙏2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር 4ኛ ቀን የያዘው እልህ አስጨራሹ ውጊያ የስርአቱ አስፈፃሚ ግብስብስ ጥምር አራጅ ቡድን በደለጎና በሻሁራ ቀጠና 4ኛ ቀኑን በያዘው አውደ ውጊያ ከፍተኛ ሽንፈትን እያስተናገደ ይገኛል።

በዛሬው እለት ጥቅምት 21/2018 የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ ከሁለቱ ከተሞች ሻሁራና አፀደማርያም ተስቦ ወደ ሞት ቀጠና በከበባ ውስጥ የገባው ፀረ አማራ ቡድን ከጧቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ በተደረገው አውደ ውጊያ ከፍተኛ ድል ማስመዝገብ ተችሏል።

በዛሬው አውደ ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት= 36;
ቁስለኛ= 44
ሲሆን አሁንም አውደ ውጊያው እንደቀጠለ ይገኛል።

2ኛው አውደ ውጊያ በቋራ ደለጎ የቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ጋር በመጣመር የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሀይል 4ኛ ቀኑን በተጠናከረ መልኩ በሚደረገው አውደ ውጊያ ከፍተኛ ድልን ማግኘት ተችሏል። የጠላት ሀይልም ለጊዜው በውል ያልታወቀ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ውሏል አሁንም በአናብስቶቹ ከበባ ውስጥ በመግባቱ እግር አውጭኝ ብሎ ተራራ ላይ ተሰቅሎ ቀና ሲል ሰማይ ዝቅ ሲል መሬት ሁኖበታል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ጥቅምት 21/2018 ዓም
👍6🙏4
ሰበር መረጃ!

ከደጋው መብረቅ ኮር የተሰጠ የአንድነት ብሥራት መግለጫ

የአማራ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ሞት ከጥላው የቀረበ መሆኑንና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የአገዛዙ ኃይልና አማራ ጠል ኃይሎች በአማራው አንገት ላይ ያለማቋረጥ ሠይፍ እያሳረፉ ያሉበት ጊዜ መሆኑን ለአፍታም እንኳን የማንዘነጋው ጉዳይ ነው። አማራን በሌሎች ወገን ሕዝቦች ለማስጠላት የተኬደበት ርቀትም ረጅም ነው፤ በቢሮክራቲክ ተቋማት፣ በፖለቲካዊ ሹመት፣ በዲፕሎማሲው ረገድ ሳይቀር አማራው ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ይገኛል፡፡ የአማራ ፋኖን ትግል በድል ለመቋጨት የአማራ የህልውና ታጋዮች አንድነት ወሳኝ ነው፡፡

እኛ የአማራ ፋኖዎች ወደ በረሃ የወረድነው፣ ቤታችንን ዘግተን ዱር ቤቴ ያልነው፣ የአማራ ሕዝብ ላለፉት ዘመናት በጎበጠ የፖለቲካ ትርክት ምክንያት ተገዳይና ተሳዳጅ መሆኑ እንዲያበቃ፣ ነጻነቱን እንዲያገኝ ነው። እኛን ከክፋት ሠሪዎች ጋር ፊት ለፊት በጠመንጃ አፈሙዝ እንድንጋፈጥ ያደረገን ወገናችንን በሀገሩ ላይ ከእኩልነት ደረጃ አውርደው በሕልውና ጥያቄ ቅርቃር ውስጥ ስላስገቡት ነው። የአማራ ሕዝብ የህልውናና የፍትሕ ትግል በሞራል፣ በሰብአዊነት፣ በሃይማኖት፣ በማኅበራዊና ዓለም አቀፋዊ የሕግ ሚዛኖች ሁሉ ፍትሓዊ ብቻ ሳይሆን ሰው ሆኖ መፈጠር የሚያስከትለውን ራስን በክብር የመጠበቅ ተፈጥሮአዊ እዳን የመክፈል የማይቀር ትግል ነው።

ታላቁ ሰማዕት ፕ/ር አሥራት ወልደየስ “አማራ የለም” ለሚሉ ጠላቶች ምላሽ ሲሰጡ “አማራ የለም ትላላችሁ፤ ለመግደል ስትፈልጉት ግን ታገኙታላችሁ” እንዳሉት ጠላቶቻችን በጅምላ ሊጨፈጭፉን የሚፈልጉን ሕዝቦች ነን፡፡ ይኸውም ከወለጋ እስከ ባሌ፣ ከሞያሌ እስከ ማይካድራ ድረስ የተደረገ የትላንት ታሪክና እስከ ዛሬ የቀጠለ በአለም ፊት በገሃድ እየተፈጸመ ያለ ሐቅ ነው፡፡

ጠላቶቻችን መርጠው የማይገድሉን፣ በጋራ የዘመቱብን፣ በአማራነታችን ብቻ በጅምላ የሚፈጁን ከሆነ እኛ በአንድነት በመሠለፍ ትግላችንን ከድል ምዕራፍ ለማድረስ የሚያግደን ምናለ? ሥልጣን ነውን? ገዳይ በበዛበት፣ ሕዝባችን ዕለት ዕለት እየሞተ ባለበት ሁኔታ የትኛው ሥልጣን አጓጉቶን ነው? ዝና እና ሕዝበኝነት ነውን? ሕዝባችን በሞትና በስደት መከራ በሚያይበት ሀገር ላይ ሆነን እኛ ታጋዮች ስለ ምን ዝና መናገር እንችላለን? ፍትሕ በተጓደለበት ሕዝባችን ፊት ስለምን ዝና ልናወራ እንችላለን? ኃብትና ገንዘብ ነውን? ለመሞት ወስነን ዱር ቤቴ ያልን መቼና እንዴት በምን ሁኔታ ልንሞት እንደምንችል እያወቅን ኃብትና ገንዘብ ምናችን ነው? ለአንድነታችን እንቅፋት የሚሆንብን ምክንያት ሁሉ ከሕዝባችን ክብርና ሕልውና በታች ነው፡፡ ሆኖም ግን ሰበብ በማብዛት አንድ ላይ ለመቆም የሚቆዝም ቢኖር ከጠላቶቻችን ጋር የተሰለፈ አልያም ለግል ፍላጎቱ ያደረ ነውና ባንዳ መሆኑን በዚህ እናውቀዋለን።

ስለሆነም እኛ ቀደም ሲል የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አመራሮች ከአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አመራሮች ጋር በአማራ ሕዝብ የትግል መስመር፣ መዳረሻ ዓላማና ግብ፣ መዋቅራዊ የግንኙነት መስመር፣ የትብብርና የአጋርነት ማዕቀፍ ላይ ባደረግነው ተከታታይ ጥብቅ ውይይት በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅሬታዎችን በወንድማዊ ይቅርታ በመዝጋት ፍጹም መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ በመሆኑም ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ከዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የደጋው መብረቅ ኮር በሚል አምስት ክፍለ ጦሮችን የያዘ አደረጃጀት ያለው ግዙፍ ኃይል አደራጅተን በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጋር በመዋሐድ በአንድ መዋቅር ለመታገል መስማማታችንን አንድነታችንን ለምትናፍቁ ወገኖቻችን ስናበሥር በታላቅ ደስታ ነው።

በደጋው መብረቅ ኮር የተካተቱ ክፍለጦሮች:-
1. ፅናት ክፍለጦር
2. ደጀን ክፍለጦር (የቀድሞው የደጋው መብረቅ ክ/ጦር)
3. አንሻ ሰይድ ክፍለጦር
4. ሰንጥቅ ክፍለጦር
5. ቀኝ-አዝማች ተበጀ ክፍለጦር እንዲሁም በሻለቃ አደረጃጀት ያሉ ሀይሎችን ያካተተ ኮር መሆኑን ለመላው የትግሉ ደጋፊ እና ታጋዩ መግለፅ እንፈልጋለን።

የደጋው መብረቅ ኮር አመራሮች እና ኃላፊነታቸው ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

1) ሰብሳቢ …………… አርበኛ ኃብቴ አባቡ
2) ወታደራዊ አዛዥ …. አርበኛ ተመስገን አለባቸው
3) ም/ወታደራዊ አዛዥ …... አርበኛ ማረጉ አስፋው
4) ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ … አርበኛ መ/ር ብርሃን አረጋ
5) ዘመቻ ኃላፊ ……. አርበኛ አስፌ አበጋዝ
6) ም/ል ዘመቻ………. አርበኛ ጨለፍ ተስፋው
7) ሎጂስቲክስ …….. አርበኛ መሳፍንት ደሴ
8) ቃል አቀባይ ….. አርበኛ መ/ር መኩሪያ አጋዥ
9) ፋይናንስ …… አርበኛ 10 አለቃ ሙላቱ ሰጠ
10) ም/ፋይናንስ ...........አርበኛ ፍቅር አራጌ
11) የሰው ኃብት አስተዳደር …….. አርበኛ መካሽ የኋላው
12) መረጃና ደህንነት ……………. ***
13) ስልጠና መምሪያ ……. አርበኛ 100 አለቃ ሲሳይ
14) ም/ስልጠና መምሪያ ...... አርበኛ ጋሻው ቢያርጎ
15) ሕግ ክፍል ....... አርበኛ 100 አለቃ ፈለቀ ጌትነት
16) ህክምና መምሪያ ……… አርበኛ ዶ/ር መላኩ የሻነው
17) ወታደራዊ አስተዳደር …… አርበኛ ናቲ ውዱ
18) ም/ል ወታደራዊ አስተዳደር ....... አርበኛ ውበት ደምሴ
19) ሚዲያ ክፍል ………. አርበኛ እሸቱ አባተ
20) ኦርዲናንስ ....... አርበኛ ሙሉጌታ አሻግር
21) ሴቶች ጉዳይ …… ፋኒት መቅደስ ብርሃን
22) የሕዝብ አስተዳደር …… አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ
23) ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ … አርበኛ አወቀ ብዙአየሁ
24) የኮር ልዩ ዘመቻ ………. አርበኛ አበበ ቢራራ
25) የኮር ም/ል ልዩ ዘመቻ ........ አርበኛ ኪዳን ወዳጄ
26) ኦዲትና ኢንስፔክሽን ….. አርበኛ አንደበት ወረታ
27) የኮር አማካሪ …….. አርበኛ አለሙ ገላው
28) የኮር ም/ አማካሪ ........ አርበኛ እንዳለማው ፈጠነ
29) ግዥ ……… አርበኛ አለበል ተካልኝ
30) ወታደራዊ አደረጃጀት ….. አርበኛ ሻለቃ ወንድሙ፡
31) ም/ወታደራዊ አደረጃጀት ........ አርበኛ ሻምበል ደመቀ እንየው

በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ የአማራ ቀጠናዎች የምንገኝ ፋኖዎች ለድል የምንበቃውና የወገናችንን ግፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በፍጥነት እንዲያከትም የምናደርገው በአንድነትና በመተባበር መታገል ስንችል ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የታወጀው አንድነት በወሎ ቀጠና ይሁን እንጂ አገዛዙ የሀገር በጀት ይዞ ያለ እረፍት በገፍ እያሰለጠነ የሚልከውን የጠላት ኃይል የክተት ጦርነት መክቶ ድል ለማድረግ በሌሎችም የአማራ ቀጠናዎች በልዩነት የምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት እንድትመጡ ያስፈልጋልና ወንድማዊ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን፡፡

በመጨረሻም፣ በተፈጠረው አንድነት የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እየገለጽን በቀጣይ የሚጠብቀን ትግል ውጣ ውረድ ያለበትና ከፍተኛ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ መላው የአማራ ልጆች ሁለንተናዊ ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የደጋው መብረቅ ኮር
ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም.
7🙏3