ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአደረጃጀት ዜና !!

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ201ኛ ኮር የ74ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።

የክፍሐጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ማርሸት ፅሐው ፣ በአርበኛ ይትባረክ አንዳርጌ እና በመቶ አለቃ አበበ አስተባባሪነት እንዲሁም በ201ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ላይችሉህ ገበየሁ እና በኮሩ አደረጃጀት ሀላፊ አርበኛ አንለይ እንየው ተባባሪ አስተባባሪነት ተጠናቋል ።

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
2
ሰበር ዜና!

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝና አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ኃይሎች በጥምረት በጠላት ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ ድል ተቀዳጁ!
      
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ክ/ጦሮችና አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ክ/ጦሮች የጋራ ጠላትን በጋራ መደምሰስ የሚል እቅድን አንግበው የጠላት ኃይል ሰፍሮ በሚገኝባቸው በተለያዩ ከተማዎች ሰርጎ በመግባት አስደናቂ ጀብዶችን ሰርተዋል።
       
በትላንትናው እለት የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካል የሆኑት ጎ/በጋሻው ክ/ጦርና ጥቁር አንበሳ ክጦር አሃዶች እንዲሁም አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ እዝ በአርበኛ ታርቆ ከበደ የሚመራው አሃድ በጋራ በመሆን በምዕራብ በለሳ አበየና ድርቃ ልደታ በተባሉት አካባቢዎች የብልጽግናን ወንበር አስጠባቂ ኃይል ሲያበራዩት ውለዋል።
   
በውጊያው የሞቱበትን 3 መከላከያዎችና
3 ሚሊሻዎችን ድርቃ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ላይ ቀብሮ የሄደ ሲሆን  ሌሎች ቁጥራቸው በርከት ያሉ የመከላከያና የሚሊሻ ቁስለኞችን ወደ አርባያ ከተማ ይዞ ፈርጥቶ አምልጧል። የአርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞችም ቁስለኞችን ለማትረፍ ሽር ጉድ ሲሉ ተስተውለዋል።
   
ከዚሁ የአንድነት ዜና ሳንወጣ ዛሬ ጥቅምት 19ለ 20 2018 ዓ.ም አጥቢያ ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር አሃዶችና አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ አፄዎቹ ክ/ጦር ማክሰኝት ከተማ በ3 አቅጣጫ ዘልቆ በመግባት የጠላትን ኃይል መውጫ መግቢያ አሳጥተውት አርፍደዋል።
   
ለሰዓታት ያህል ከተማዋን  በቁጥጥር ስር አድርገዋት የቆዩ ሲሆን የከተማዋ ሚሊሻና የስርዓቱ አገልጋይ ካብኒዎች እግራቸው ወደአመራቸው መፈርጠጣቸውን የመረጃ ምንጫችን ገልጿል።
     
ቁጥራቸው በእውን ማወቅ የማይቻል የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
  
ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል ሰፍሮ በሚገኝባቸው ከተሞች  አምባ ጊዮርጊስና አዲስ ዘመን ላይ ከትላንት ማታ ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እልህ አስጨራሽ ውጊያ እያደረጉ ነው።
      
ማታ አመሻሽ ላይ ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር  አምባ ጊዮርጊስ ከተማ ላይ በ3 አቅጣጫ በመግባት በአብይ ጡት ቆራጭ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል። 

በጥቃቱ
5 የመከላከያ አባላት ወዲያውኑ ሲሞቱ
8ቱ ደግሞ ክፋኛ በመቁሰላቸው የተነሳ በሪፈር ለከፍተኛ ህክምና ደባርቅ ከተማ ተልከዋል።
     
የጠላት ኃይል ቁሳዊ ፣ ሰባዊና ፖለቲካዊ ኪሳራን ያስተናገደበት ጥቃት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
       
የጠላት ኃይል ማዘዣ ጣቢያ በሆነችው አዲስ ዘመን ከተማ ላይ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር  በ3 የውጊያ ግንባሮች እየተፋለሙ ይገኛል።
  
በስተ ምስራቅ  አቅጣጫ አፄ እያሱ ክ/ጦር በስተ ስሜን አቅጣጫ መብረቅ ክ/ጦር በ2 ግንባሮች በስተ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ፋናየ ውቤ ክ/ጦር፣ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ብርጌዶችና የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አካል የሆነው ነብዩ አሳምነው ብርጌድ  የአዲስ ዘመን ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን መሬቶች በመጠቀም  በጠላት ኃይል ላይ የበላይነትን ወስደዋል።
       
ከእብናት ድጋፍ ለመስጠት የሚመጣን የጠላት ኃይል አፄ እያሱ ክ/ጦር አግዶ ይዞ እንዳያልፍ ያደረገ ሲሆን አዲስ ዘመን ከተማ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን ግብስብስ ኃይል ያለምንም ስጋት ምሽጉ ድረስ ዘልቆ በመግባት እልህ አስጨራሽ የፊት ለፊት ውጊያ ማካሄድ  ተችሏል።
   
በውጊያው
ከ15 በላይ ሲሞት
   12 የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በከተማው ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸው ታውቋል
  
በአጠቃላይ ከሰሞኑ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተደረጉ ያሉ ወታደራዊ ዘመቻዎች የጠላት ኃይል ከፍተኛ ቁሳዊ ፣ ሰባዊና ፖለቲካዊ ኪሳራዎችን ያስተናገደበት ግዳጅ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

        ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
   አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
             ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
1
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ላይ በተፈፀመ ጥቃት የተገደሉ 20 የሚደርሱ ንፁኋኖች አስከሬናቸው ከየወደቀበት እየተለቀመ ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙ ተነገረ!
💔1
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ201ኛ ኮር የ74ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።

የክፍሐጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ማርሸት ፅሐው ፣ በአርበኛ ይትባረክ አንዳርጌ እና በመቶ አለቃ አበበ አስተባባሪነት እንዲሁም በ201ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ላይችሉህ ገበየሁ እና በኮሩ አደረጃጀት ሀላፊ አርበኛ አንለይ እንየው ተባባሪ አስተባባሪነት ተጠናቋል ።
🙏1
"መሪጌታ በላይ አዳሙ ተደብድበዋል ፤
ቄስ በላይ መኮንን ከተከበሩ መሪጌታ በላይ አዳሙ የማይከበሩበት ምክንያቱ ምንድን ነው?"

(የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው)

የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጥቅምት 18/2018 በነበረው ችሎት በቂሊንጦ ማ/ቤት እና በተለይም በተቋሙ ጥበቃ እና ደህንነት ኃላፊ በኢ/ር ድሪባ ሰንበታ ላይ ካቀረቡት ክስ መካከል በከፊል ፦
 
የወገብ እና የእግር በሽተኛ ነኝ ፤ ፍ/ቤቱ ፈቅዶልኝ በዋና በር እየገቡ ቤተሰቦቼን አገኝ ነበር ፤ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ ከመጡ በኋላ ነው የተከለከልኩት።

እኔ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቤ ጭምር ተሰድቦ እንኳ ችግሩን በሰላም ተነጋግረን እንድንፈታ ነበር ጥረትና ፍላጎቴ ይሁን እንጅ ሊታረሙ ስላልቻሉ ነው ክሱን ወደ ፍ/ቤት ለማምጣት የተገደድኩት።

በእስር ቆይታዬ በበደረሰብኝ እንግልት ቆሜ ማናገር አልችልም ፤ አሁንም ቁጭ ብዬ ቤተሰቦቼን እንዳነጋግር ይፈቀድልኝ።

"ቅዘናም አማራ " ብለው ተሳድበዋል ፤ ዳኝነት ካለ ይማሩ ብለን ነው ያመጣናቸው ፤ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በምርመራ እንዲያጣራው ትዕዛዝ ይሰጥልን።

ከላይ እስከ ታች እኛው ነን ምንም አታመጡም ብለውናል።

መሪጌታ በላይ አዳሙ ተደብድበዋል ፤
ቄስ በላይ መኮንን ከተከበሩ መሪጌታ በላይ አዳሙ የማይከበሩበት ምክንያቱ ምንድን ነው?

በብሔራችን ተሰድበናል ፤ ተዋርደናል ፤ በእኛ ምክንያት ሕዝባችን ሊሰደብና ሊዋረድ አይገባም።

በፍተሻ ወቅት ባልታጠበ እጃቸው ነው እንጀራውን የሚነኩት ፤ ዞን 4 እና ዞን 5 ላይ የተለዬ ጫና እያደረጉብን ነው።

በእኛ ስም የተያዘ ሕገ ወጥ ነገር የለም ፤ አለ ካሉ ተጨማሪ ክስ አድርገው ያምጡ በማለት ተናግረዋል።

በመሀል ችሎቱ እንዳይናገሩ ሲከለክላቸው ፦

ተዉ ይህ ጊዜ ያልፋል ፤ እኔ ብሞት መልሱ ለትውልድ ነው፤ እኛ ያልነውን ብቻ ሰምታችሁ ፍረዱ አላልኩም ፤ ግን ከዚህ በላይ ምን እንሆናለን? ቅዘናም አማራ እየተባልን ነው።

በእርግጥ ይህ ችሎት ስዩም ተሾመን በጓዳ አነጋግሮ የመለሰ ነው ፤ በደል እየተፈፀመብን ነው ፤ አድሎ አለ።

ካጠፋሁ ይቅርታ የሚያናግረኝ ግን ግፉ ነው ፤ በእኔ ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና በደል ፣ ስቃዩ ነው የሚያናግረኝ።

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 19/2018)
💔1
የተቃውሞ ትችት ኃላፊነትን መወጣት እንጂ ባንዳነት አይሆንም!

ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በፓርላማ ያቀረብኳቸው ጥያቄዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት የሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው። እኔ እንደ ሕዝብ ተወካይና ተቃዋሚ ፖለቲከኛነቴ፣ የመንግሥትን ሥራ መተቸትና ለሕዝብ ጥቅም መቆም ስራየም፣ ግዴታዬም ጭምር ነው።

የምመራባቸው ብቸኛ መርሆዎች የአማራ ሕዝብ ህልውናና የኢትዮጵያ ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሞች ናቸው። ከዚህ በመነሳት ማክሰኞ ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረብኳቸው ጥያቄዎች ላይ የገዢው ፓርቲ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት እና ወዶ ገብ መሸጦ "ተቃዋሚዎች" ላቀረቡት ሦስት ክሶች ግልጽ ምላሽ እሰጣለሁ። ይሄን የማደርገው የተነሱት ክሶች ክብደት ምላሽ የሚገባቸው በመሆናቸው ሳይሆን አጋጣሚውን በመጠቀም ባቀረብኋቸው በርካታ የፖሊሲና የትግበራ ጉዳዮች ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዲፈጠር ውይይት እንዲካሄድባቸው ምልከታዎቼን በተብራራ ሁኔታ ለማጋራት ነው።

ክስ አንድ፦ የአስመራ መንግሥት ወኪል፣ አገልጋይና ባንዳ ነህ

ይህ ክስ መሰረተ-ቢስ፣ ተራ ስም ማጥፋት ነው። የፖለቲካ ትችትን በባንዳነትና በክህደት ስም ለመምታት የሚደረግ አሳፋሪ ሙከራም ነው። የቤተሰቤ ታሪክ የጀግንነት ታሪክ፣ በላብና በጥረት ሰርቶ የማደር እንጂ በመሸጦነት እና በባንዳነት የማደር አንዳችም ነገር የለበትም። አባቴ ወታደር ጫኔ ዳኜው በዘውዳዊ ስርዓቱ፣ ወንድሜ መቶ አለቃ አያሌው ጫኔ (የሀረር ጦር ት/ቤት ምሩቅ እና የነብሮ ክፍለ ጦር መኮንን) በወታደራዊ ደርግ ዘመን፣ እንዲሁም ሌላው ወንድሜ ተስፋሚካኤል ጫኔ (የሁርሶ ወታደራዊ ት/ቤት አሠልጣኝ) በኢሕአዴግ ዘመን፣ ሶስቱም ኢትዮጵያን በከፍተኛ ጀግንነት እና ብቃት ያገለገሉ ወታደሮች ናቸው። ቅድመ አያቶቼም በሁለቱም በኩል እነ ቀኛዝማች ደስታ ብሩ እና ብላታ ጥሩነህ ኪዳኑ እንደአብዛኛው የጎጃም፣ አማራ ገበሬ አርበኞችም ነበሩ። ቤተሰቤ ለሀገር ሉዓላዊነትና አንድነት በደም ዋጋ የከፈለ ነው። ባንዳነት ከእኔም ሆነ ከቤተሰቤ ታሪክና እሴት ጋር ባዳ ነው። ስለዚህ ባንዳ ያላችሁኝ ተቺዎቼ ባንዳነት ይኖርባችሁ ከሆነ በዙሪያችሁ ፈልጉ፣ ከኛ ቤት ባንዳ የለም ነው መልሴ።

ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረብሁት ጥያቄ ዓላማው አጣዳፊ የውስጥ ችግሮችን ከማስቀደም ይልቅ የባሕር በር አጀንዳን በማስቀደም በውጭ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረጉ ስልታዊ ስህተት መሆኑን ለማሳየት ነው። ስለዚህም የሀገሪቱ የፖለቲካ ጉልበት በመጀመሪያ የውስጥ ሰላም ግንባታ ላይ እንዲውል አሳስቤያለሁ።

ከዚህ በተረፈ እግዚአብሔር ይመስገንና በሙያዬ የትም ዓለም ሂጄ ሰርቼ ኑሮዬን ማሸነፍ የምችልበት የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ አለኝ። በፖሊሲ አውጪነት እና ከፍተኛ አመራርም በቂ ልምድ አለኝ። ስለዚህ ኑሮዬን ለመደጎም የየትኛውም አካል ቅጥረኛ የመሆን ግዴታ የለብኝም። ለጊዜው ግን እኔ የባሕር ዳር ሕዝብና የአማራ/የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካይ እንደራሴ ነኝ፤ የምወክለውም የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ብቻ ነው!

ክስ ሁለት፦ ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷን ትቃወማለህ

በፓርላማው ንግግሬ "ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን የምቀበለው ነኝ" ብዬ በግልጽ አመላክቻለሁ። የባሕር በር ማግኘት ብሔራዊ ጥቅም መሆኑን እንኳን እኔ 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ የአንድ መስሪያ ቤት ፖስተኛ እንኳን ይገነዘበዋል።

ተቃውሞዬ ያለው የባሕር በርን በተመለከተ በጉዳዩ አያያዝ ዘዴ ላይ ነው። መንግስት የባሕር በርን እንደ "ህልውና ጥያቄ" በማቅረብ ሀገሪቱን ወደ ጦርነት አፋፍ እየመራ መሆኑን ተችቻለሁ። የእኔ አቋም የባሕር በር ጥያቄው በሰላማዊ፣ በሕጋዊና ሰጥቶ መቀበልን መሠረት ባደረገ አካሄድ ብቻ መፈታት አለበት የሚል ነው። ሀገራችን አሁን በውስጥ ጦርነት ተወጥራ ባለችበት ሁኔታ፤ የውስጥ ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ ሲገባት በባሕር በር ስም ተጨማሪ የውጪ ጦርነት ውስጥ በመግባት በዚህ ጉዳይ ሌላ የዜጎች ደም እና ሕይዎት መክፈል የለባትም ነው። ጦርነትን የሚጋብዝ አካሄድ መቃወም የሀገር ፍቅር እንጂ ባንዳነት አይደለም። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ሕወኃት/የትግራይ ኃይሎች በወገኖቼ ላይ ማይካድራን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የፈጸሙትን የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት እና ሁለንተናዊ የጦር ወንጀል በመቃወም አማራ ክልል ውስጥ የተደረገውን ራስን የመከላከል ጦርነት ደግፌያለሁ፣ ግን አልኩራራበትም (በአማራ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል የፈጸሙ የትግራይ ኃይሎች በፍትህ አደባባይ መቅረብ እንዳለባቸው በተደጋጋሚ እንደገለጽሁት ሁሉ፣ በትግራይ በንጹኃን ተጋሩዎች ላይ በተፈጸመው የጦር ወንጀል ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውም አካልም በተመሳሳይ በፍርድ አደባባይ እንዲዳኝ እፈልጋለሁ)። ስለዚህ ራስን የመከላከል የግዴታ ጦርነት ካልሆነ፣ አባቱ የጦርነት ሰለባ የሆነ ወታደር ልጅ እንደመሆኔ ጦርነትን በየትኛውም ምክንያት አልደግፍም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ስላረበበው የጦርነት ስጋት ላቀረብሁት ጥያቄ በምላሻቸው የባህር በር ለማግኜት የግድ ጦርነት ውስጥ መግባት የለብንም የሚለውን ነገር አስረግጠው ተናግረዋል (ዛቻውን እንደ ባርጌይኒንግ ችፕና የዲፕሎማሲ ቀዳዳ መፍጠሪያ ጫና ማድረጊያ ታክቲክ አድርጌ ነው የተረዳሁት)።

ክስ ሦስት፦ ሁልጊዜ ትችት ብቻ እንጂ አማራጭ ሀሳብ የለህም

ይህ ሀሳብ አብዛኛውን ጊዜ የፖለቲካ ሀሁ ከማይረዱ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በተደጋጋሚ የሚነሳ ነው። አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ የሕዝብን ችግሮች እና እሮሮዎች እንዲሁም የመንግሥትን ክፍተት ማሳየት ዋናው ሥራው ቢሆንም፣ በጥያቄዎቼ እና በንግግሬ ግን ከመተቸት ያለፈ ግልጽ አማራጭ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን አቅርቤያለሁ።

ሀ) የጸጥታ ጉዳይን የተመለከተው አማራጭ፦ ለአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከወታደራዊ አማራጭ ውጪ የተለየ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጠይቄያለሁ። ከትግራይ ኃይሎች፣ ከፋኖ እና ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር መንግስት የገባበትን ሁኔታ በአርቆ አስተዋይነት በድርድር እንዲፈታ ግልጽ ጥሪ አቅርቤያለሁ።

ለ) የኢኮኖሚ ጉዳይን የተመለከተው አማራጭ፦ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር መንግሥት አዲስና አስቸኳይ ዕቅድ እንዲያቀርብ እንዲሁም ወሳኝ ማኅበራዊ ወጪዎችን ሳይቀንስ የውጭ ዕዳውን ለመክፈል ሚዛናዊ የፊስካል ፖሊሲ እንዲከተል ግፊት አድርጌያለሁ።

ሐ) የውጭ ግንኙነት ጉዳይን የተመለከተው አማራጭ፦ የመንግሥት ከፍተኛ የፖለቲካ አቅም የውስጥ የፖለቲካ ግጭቶችን ለመፍታትና ከዜጎች ጋር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር እንዲውል በግልጽ ጠቁሜያለሁ። የኢህአዴግ የውጪ ፖሊሲ ጠንካራ ጎን የነበረው መርሆ "የውስጥ ሰላም የውጭ ስኬት መሰረት ነው!" የሚለውን እኔም የምገዛው የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ መርህ ነው።

እንደ ማጠቃለያ፦ በገዢው ፓርቲ ላይ በማንኛውም ጊዜ የማቀርበው ትችቴ ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ቆሜ የምጠይቀው ሕጋዊ የፖለቲካ ትችት እንጂ በቅጥረኝነት የመጣ አይደለም። የገዢው ፓርቲ ኃላፊነት የፖለቲካ ትችትን በአላዋቂዎች የብሔራዊ ክህደት ክስ ለማኮላሸት ከመሞከር ይልቅ ለቀረቡት ወሳኝ ጥያቄዎች አሳማኝና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ነው።
የእኔ የፖለቲካ ሥራ ትኩረት ደግሞ በተረዳሁት ልክ የሕዝቤን ህልውና እና የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ማስከበር ነው!

(ፎቶ፦ የተቃዋሚ የፓርላማ አባላት የሆኑ ወዳጆቼ አቶ ባርጠማ እና አቶ ብርሐኑ ጋር ፤ በምክር ቤቱ ጥያቄ ባቀረብሁበት ወቅት የተወሰደ።)
1🙏1
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ስራ አስፈፃሚዎች የስራ ግምገማ አካሄዱ!
    
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ከተመሰረተ አምስት ወራታትን እያስቆጠረ ነው። በእነዚህ ወራት በርካታ ወታደራዊ  ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትርፎችን ማግኘት ተችሏል።
   
ከትርፎችም ባሻገር ትግሉ ወደ ፊት እንዳይስፈነጠር ተግዳሮት የሆኑትን ችግሮች በመለየት ከስር ከስር የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በመንደፍ በተግባር የተደገፈ ስራዎችን ማከናወን የእለት ተእለት ልምድ ሆኖ ቀጥሏል።
     
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ኮሩ ከተመሰረተ አንስቶ በወታደራዊ ፣ በማህበራዊ  ፍትህ አሰጣጥና በፖለቲካዊ  ሁኔታ የገጠሙንን ችግሮች ፣ ኮሩ በሚያስተዳድራቸው ሰፊ ቀጠናዎች የሰላምና የጸጥታ ሁኔታን ከማስፈን አኳያ ፤ አሁናዊ የጠላትን አቋምና ፍላጎት እንዲሁም እንደ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ  አሁናዊ ሁናቴ እንዲሁም እንደ ኮራችን ያለንበትን ቁመና አስመልክተን ከላይ የተዘረዘሩትን እያንዳንዱን ዝርዝር ጉዳዮችን በማንሳት ውይይት ተደርጓል።
 
በተለይ ደግሞ ውስጠ ዲሞክራሲን በውስጣችን ከማስፈንና ከመለማመድ አኳያ ሰፋ ያለ ጊዜን ተወስዶ ውይይቶች ተደርገዋል። እንደ ተቋም መርህንና አሰራርን ተከትሎ መመሪያን ከማስተገበርና ከመተግበር አንፃር ጠለቅ ያለ ግምገማንና ሂስን እንደ ማውረድ ድረስ የደረገ ግምገማ ተደርጓል።
     
በውይይቱ ወቅት በድክመት የተነሱ አንዳንድ የተቋምን መመሪያ ያልተከተሉ አሰራሮች በቀጣይ መስተካከል እንዳለባቸው መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በጥንካሬ ውይይቱ ላይ እንደ አርአያ የተጠቀሱ የተግባር ክንውኖች ከዚህ በበለጠ ጎምርተው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።
 
በመጨረሻም የቀጣይ ስራዎቻችን ላይ ትኩረት በመስጠት የንድፈ ሃሳብ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱና ግምገማው ተቋጭቷል።

          ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
     የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ፭ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ አብነት ሞላ
                       ጥቅምት 20/2018ዓ.ም
2🙏1
ለሀገር ለወገን ክብርና ሕልውና ዘብ የቆሙ ዋርካዎቹ... የዘመናችን እንቁ ጌጦች!

አርበኛ ሻምበል ገብሩ ልይህ፣ አርበኛ ሻምበል መሰረት አለሙ፣ አርበኛ አለምነህ ኪዴ፣ አርበኛ በላይ ዘለቀ!

አባት አርበኞቹ፣ ዋርካዎቹ!
🙏2
ከ50 በላይ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን መከላከያ ሰራዊት አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ!

"በአማራ ሕዝብ ላይ ጡት እስከ መቁረጥ የሚያደርስ ጥላቻ ያለበት የአገዛዝ ቡድን ጋር አንቀጥልም" በሚል ፋኖን ከተቀላቀሉት ከ50 በላይ ወታደሮች መካከል አንድ የሻለቃ አዛዥን ጨምሮ 11 የሻምበል አመራሮች እንደሚገኙበት መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ 46 ጥቁር ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 11ሺ 350 የክላሽ ተተኳሽ እንዲሁም 90 የእጅ ቦምብ በመያዝ በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና አፄ ምኒልክ ዕዝን ስለመቀላቀላቸው የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

ወታደሮቹ ፋኖን የተቀላቀሉት ባለፉት ተከታታይ ቀናት መሆኑንም የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለጣቢያችን በላከው መረጃ ጨምሮ ገልጿል።
🙏2
‎የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን የትምህርት ተቋማትን መሰረት ያደረገ የሞርተር ጥቃት ፈፀመ።
‎===============
‎የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን የፋኖ ኃይች በሌሉበት በአሳግርት ወረዳ የትምህርት ተቋማትን መሰረት ያደረገ የሞርተር ጥቃት በመፈፀም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጎሉ አድርጓል::

‎ይህ የጥፋት ቡድን ጥቅምት 19/2018 ዓ ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በአሳግርት ወረዳ ታሞ ቀበሌ ከፈፀማቸው ስድስት የሞርተር ጥቃቶች መካከል ሁለቱ በታሞ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ÷ አራቱ በመሀል ታሞ ከተማ ላይ ወድቋል::

‎ በዚህም የሞርተር ጥቃት የተደናገጡ ተማሪዎችና መምህራት የትምህርት ገበታቸውን በማቋረጥ ተበትነዋል::

‎የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን በዘፈቀደ በጣለው በዚህ የሞርተር ጥቃት አንድ አርሶ አደር ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ሲደርስ አንድ የቤት እንሰሳት ደግሞ ተገድሏል::

መረጃውን ያደረሰን አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የቡልጋ ክ/ጦር ሪፖርተር ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"

‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል
💔1
ዞብል አምባ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ከፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ደላንታና ጋሼና መካከል ላይ ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::


ዞብል አምባ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ዛሬ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም ከደላንታ ወደ ጋሼና ሃይል ለመጨመርና ለማጠናከር ሲጓዝ የነበረውን የአገዛዙን ዙፍን ጠባቂ ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድባቅ የመታችው ሲሆን ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በመካናይዝድ ጭምር በመታገዝ ከስድስት ሰዓት ያላነሰ ፊት ለፊት ከባድ ውጊያ ቢከፍትም ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ አንገቱን በማስድፋት ድል ተቀዳጅተዋል::

ስለሆነም አገዛዙ በእግረኛ ሰራዊቱ ድሮውንም እምነት ስለሌለው የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ኢላማውን ህዝብ ወደሚበዛባቸው አካባቢዎች ያደረገ የመካናይዝድ መሳሪያ መድፍ ዙ23 እንዲሁም በ107 የታገዘ ድብደባ በማድረግ ሲዋጋ ቢውልም ዞብል አምባ 5ተኛ ሻለቃ በርካታ ሃይሉን በመምታት ወደ ነበረበት መልሳዋለች::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
4🙏1