ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!

ሻለቃ መሪውንና ብሬን ተኳሹን ጨምሮ 11 የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖን ተቀላቀሉ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ዋግሹም ብርጌድን የተቀላቀሉት:-

1. ሻለቃ ምስጋናው እንየው:- የፖሊስና የሚሊሻ አዛዥ
2. ወርቁ አድሴ:- ብሬን ተኳሽ
3. ኮንስታብል የኋላው ግርማይ:- የአገዛዙ ፖሊስና ሌሎች ስምንት ሚሊሻዎች የብልፅግናን ስርዓት በመጥላት ከድሃና አምደወርቅ ዱራ ግንባር ተነስተው ዋግሹም ብርጌድን ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።

ሲቀላቀሉ ይዘውት የመጡት ትጥቅ አንድ ስኪ፣አንድ ምንሽር፣አንድ M-40፣ስምንት ክላሽ፣330 የክላሽ ተተኳሽ፣ስድስት የእጅ ቦምብ፣40 የስኪና የምንሽር ተተኳሽ፣ 11 የወገብ ትጥቅ ይዘው ተቀላቅለዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 19 / 2018 ዓ.ም
👍1🙏1
አሁን በደረሰን መረጃ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሌ ዋቤ ወረዳ በቀቅሳ ቀበሌ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ 5 ምእመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በስልክ አድርሰዋል።

መረጃ ሰጭዎቻችን አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
@ሞአ ሚዲያ
💔1
ተቃውሞ ሰልፍ እና ሻማ ማብራት በስቶኮልም
💚💛❤️🇸🇪

በአማራ ህብዝ ላይ እየተፈጸሙ ያሉትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች የጦር ወንጀሎች እና ንጹሀን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የድሮን ጥቃት እናውግዝ ‼️

ቀን : November 1,2025

ሰአት : Klockan 15 till 17

Plats : Medborgarplatsen Torg

አዘጋጅ: ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
💔2
የአደረጃጀት ዜና !!

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ201ኛ ኮር የ74ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።

የክፍሐጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ማርሸት ፅሐው ፣ በአርበኛ ይትባረክ አንዳርጌ እና በመቶ አለቃ አበበ አስተባባሪነት እንዲሁም በ201ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ላይችሉህ ገበየሁ እና በኮሩ አደረጃጀት ሀላፊ አርበኛ አንለይ እንየው ተባባሪ አስተባባሪነት ተጠናቋል ።

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
2