ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ ከሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ መታገታቸው ተሰማ፡፡

በወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ115 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ16 በላይ ዐብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸው ታውቋል።

MK TV ጥቅምት 19 2018 ዓ.ም

ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በደረሰው መረጃ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ አርሴማ አጥቢያ የሚኖሩ ምእመናን በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ ደግሞ መታገታቸው ተገልጿል።

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ የአንዱ ሟች አባትና ወንድም መታገታቸው በመረጃው የተገለጸ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ምእመናን ስለሚገኙበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል፡፡

በመረጃው እንደተነገረው የሞቱት ሦስቱ ኦርቶዶክሳውያን በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ ሲሆን 27 ኦርቶዶክሳዉያን ደግሞ አሁንም ድረስ ታግተው ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎቹ ለጣቢያችን ገልጸዋል።

በግድያ ያላበቃው መከራና ስቃይ በሽርካ ወረዳ ብቻ በዘጠኝ ቀበሌዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳዉያን መፈናቀላቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳው ካሉ 37 አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከ16 በላይ የሆኑት አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውንና ከእነዚህም መካከል 3ቱ መሉ በሙሉ መዘረፋቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኦርቶዶክሳዉያን መገደል እንዲቆም ለሀገረ ስብከቱና ለመንግሥት አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግም ምላሽ እያገኙ አለመሆናቸውን ያነሱት ነዋሪዎቹ በዚህም አካባቢው በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛል ሲሉ ተናግርዋል፡፡

በተለይም በሀገረ ስብከት ደረጃ ለተፈናቀሉት ወገኖች ድጋፍም ሆነ ማጽናኛ ለማደረግ ጥረት ባለመደረጉ ማዘናቸውን የአካባቢው ምእመናን ገልጸዋል፡፡

እየደረሰ ያለው የሰው ሕይወት እልፈት ፣ መታገትና የንብረት ውድመት ችግር እልባት አንዲያገኝ የቅድስት ቤተ ክርሰስቲያን እና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት አሁንም ትኩረት ሰጥተው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
1💔1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!

ሻለቃ መሪውንና ብሬን ተኳሹን ጨምሮ 11 የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖን ተቀላቀሉ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ዋግሹም ብርጌድን የተቀላቀሉት:-

1. ሻለቃ ምስጋናው እንየው:- የፖሊስና የሚሊሻ አዛዥ
2. ወርቁ አድሴ:- ብሬን ተኳሽ
3. ኮንስታብል የኋላው ግርማይ:- የአገዛዙ ፖሊስና ሌሎች ስምንት ሚሊሻዎች የብልፅግናን ስርዓት በመጥላት ከድሃና አምደወርቅ ዱራ ግንባር ተነስተው ዋግሹም ብርጌድን ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።

ሲቀላቀሉ ይዘውት የመጡት ትጥቅ አንድ ስኪ፣አንድ ምንሽር፣አንድ M-40፣ስምንት ክላሽ፣330 የክላሽ ተተኳሽ፣ስድስት የእጅ ቦምብ፣40 የስኪና የምንሽር ተተኳሽ፣ 11 የወገብ ትጥቅ ይዘው ተቀላቅለዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 19 / 2018 ዓ.ም
👍1🙏1
አሁን በደረሰን መረጃ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሌ ዋቤ ወረዳ በቀቅሳ ቀበሌ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ 5 ምእመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በስልክ አድርሰዋል።

መረጃ ሰጭዎቻችን አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
@ሞአ ሚዲያ
💔1
ተቃውሞ ሰልፍ እና ሻማ ማብራት በስቶኮልም
💚💛❤️🇸🇪

በአማራ ህብዝ ላይ እየተፈጸሙ ያሉትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች የጦር ወንጀሎች እና ንጹሀን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የድሮን ጥቃት እናውግዝ ‼️

ቀን : November 1,2025

ሰአት : Klockan 15 till 17

Plats : Medborgarplatsen Torg

አዘጋጅ: ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
💔2