በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ማእከል ዘገባ አመልክቷል።
በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፊት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።
የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።
በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ ከተማ ሪፈር መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውም በዘገባው ተወስቷል።
ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በነገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።
በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሚል ከፍተኛ ስጋት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን የቤተ ክርስቲያን ፣ የምዕመናንና የንጹሃን ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሰዋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ተጠይቋል።
በሌላ ዜና
አሳዛኝ ዜና
በአማራ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እና መከራ መገደል መታረ*ድ አሁንም እደቀጠለ ሲሆን በኦሮሚያ ወስጥ ናኖ ጃዊ ቀበሌ ጉና ወረዳ አርሲ አርባ ጉጉ ክፍለ ሀገር በቀን 13 ለቀን 14 አጥቢያ ለሊት የታረዱ አማራዎች የስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል፦
1) ሻውል ይፍሩ ከነ ባለቤቱ
2) እታገኘው አስፍው ጋር
3) መስቲካ ማሞ
4) አበበ አስፋው
5) ሰርካለም ተስፋዬ
6) ፋኑሴ ዘውዴ ከ 3 ልጆቻቸው ጋር
7) የሺ መልስ ከልጇጋር
8) ሽብር ሸዋንግዛው
9) ሄለን ሙላቱ
10) ሚኪ ሙላቱ ሲሆኑ 2 የ4 አመት እና የ9 አመት ልጆችም ቆስለው ሕክምና ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
@አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ

💔2❤1
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው::
ከዘመቻ አባ ናደው መጠናቀቅ በኋላ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችና ዕዞች ወደ ቤተ-አማራ የገባው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰና እየኮበለለ ምኒልክ ዕዝን በስፋት እየተቀላቀለ ነው::
የኦሮሞ ብልፅግና ልዩ ሃይል ኦሮሚያ ላይ በአማራ ተወላጆች ላይ ሲፈፅመው የነበረውንና ዛሬም እየፈፀመው ያለውን ግፍ በተመሳሳይ የመከላከያ መለዮ ለብሶ ወደ አማራ ክልል በመግባት የሚፈፅመውን ግፍ እያየን እኩል የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተብለን ልንጠራ አንችልም ያሉ አባላቶቹ ባለፉት አስር ቀናቶች ብቻ 46 ክላሽ 4 ጀሌ 11350 የክላሽ ተተኳሽ እንዲሁም 90 F1 የእጅ ቦምብ በመያዝ ከ50 በላይ ሰራዊት ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል::
ፋኖን ከተቀላቀሉት የሰራዊቱ አባላቶች መካከልም 1 ሬጅመንት አመራር 6 ሻምበል መሪ እና 5 ምክትል ሻምበል መሪ አመራሮች ይገኙበታል:: በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝን ሰራዊት የማፍረስና የማስኮብለሉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም

🙏1
በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ ከሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ መታገታቸው ተሰማ፡፡
በወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ115 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ16 በላይ ዐብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸው ታውቋል።
MK TV ጥቅምት 19 2018 ዓ.ም
ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በደረሰው መረጃ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ አርሴማ አጥቢያ የሚኖሩ ምእመናን በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ ደግሞ መታገታቸው ተገልጿል።
ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ የአንዱ ሟች አባትና ወንድም መታገታቸው በመረጃው የተገለጸ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ምእመናን ስለሚገኙበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል፡፡
በመረጃው እንደተነገረው የሞቱት ሦስቱ ኦርቶዶክሳውያን በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ ሲሆን 27 ኦርቶዶክሳዉያን ደግሞ አሁንም ድረስ ታግተው ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎቹ ለጣቢያችን ገልጸዋል።
በግድያ ያላበቃው መከራና ስቃይ በሽርካ ወረዳ ብቻ በዘጠኝ ቀበሌዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳዉያን መፈናቀላቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳው ካሉ 37 አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከ16 በላይ የሆኑት አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውንና ከእነዚህም መካከል 3ቱ መሉ በሙሉ መዘረፋቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡
የኦርቶዶክሳዉያን መገደል እንዲቆም ለሀገረ ስብከቱና ለመንግሥት አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግም ምላሽ እያገኙ አለመሆናቸውን ያነሱት ነዋሪዎቹ በዚህም አካባቢው በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛል ሲሉ ተናግርዋል፡፡
በተለይም በሀገረ ስብከት ደረጃ ለተፈናቀሉት ወገኖች ድጋፍም ሆነ ማጽናኛ ለማደረግ ጥረት ባለመደረጉ ማዘናቸውን የአካባቢው ምእመናን ገልጸዋል፡፡
እየደረሰ ያለው የሰው ሕይወት እልፈት ፣ መታገትና የንብረት ውድመት ችግር እልባት አንዲያገኝ የቅድስት ቤተ ክርሰስቲያን እና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት አሁንም ትኩረት ሰጥተው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

❤1💔1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
ሻለቃ መሪውንና ብሬን ተኳሹን ጨምሮ 11 የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖን ተቀላቀሉ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ዋግሹም ብርጌድን የተቀላቀሉት:-
1. ሻለቃ ምስጋናው እንየው:- የፖሊስና የሚሊሻ አዛዥ
2. ወርቁ አድሴ:- ብሬን ተኳሽ
3. ኮንስታብል የኋላው ግርማይ:- የአገዛዙ ፖሊስና ሌሎች ስምንት ሚሊሻዎች የብልፅግናን ስርዓት በመጥላት ከድሃና አምደወርቅ ዱራ ግንባር ተነስተው ዋግሹም ብርጌድን ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።
ሲቀላቀሉ ይዘውት የመጡት ትጥቅ አንድ ስኪ፣አንድ ምንሽር፣አንድ M-40፣ስምንት ክላሽ፣330 የክላሽ ተተኳሽ፣ስድስት የእጅ ቦምብ፣40 የስኪና የምንሽር ተተኳሽ፣ 11 የወገብ ትጥቅ ይዘው ተቀላቅለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 19 / 2018 ዓ.ም

👍1🙏1
አሁን በደረሰን መረጃ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሌ ዋቤ ወረዳ በቀቅሳ ቀበሌ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ 5 ምእመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በስልክ አድርሰዋል።
መረጃ ሰጭዎቻችን አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
@ሞአ ሚዲያ

💔1