ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

EOTCMK TV ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ  ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፈት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።

የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።

በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ  ከተማ  ሪፈር  መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። 

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።

በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቅሷል።
©ማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ
1💔1
በአፋብኃ ቲውድሮስ ዕዝ የተማረኩ ምርኮኞች!!
👍3🙏1
በአርበኛ መከታው ማሞ ከሚመራው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እና በአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ከሚመራው አሳምነው ዕዝ የተወጣጡ የፋኖ ኃይሎች በጋራ በመሆን በወሰዱት እርምጃ ታላቅ ድል መቀዳጀታቸው ታውቋል!

በመርሀቤቴ ቀጠና በተደረገ ውጊያ ጠላት "በክፉ ቀን የሚታደጉኝ" በሚል የሚመካባቸው ከ40 በላይ ጀበና ሰባሪ አየር ወለድ ኮማንዶዎች ሲገደሉ ከ25 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

ከተገደሉት መካከል የኮማንዶ ሻምበል አዛዦችና መስመራዊ አዋጊዎች ይገኙበታል የተባለ ሲሆን፡ በተጨማሪም በተለምዶ ጥርጥሩ ክላሽ በመባል የሚታወቀው በርካታ ጥቁር ክላሽንኮቭ መሣሪያ ማርከው መታጠቃቸው ታውቋል።

@መረብ
2👍2👎1🙏1
አባ ኮስትር ብርጌድ ለተከታታይ 3(ስስት) ወር ያሰለጠናቸውን የእግረኛ ሰራዊት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ ለተከታታይ 3(ሶስት) ወራት ያሰለጠናቸውን የእግረኛ ሰራዊት ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም ለ3ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

በግዙፍ የአባ ኮስትር ብርጌድ የ3ኛ ዙር የእግረኛ ሰራዊት የምረቃ ፕሮግራሙ በክብር የተገኙት አርበኛ ጥላሁን አበጄ፣የኮር አመራሮች ፋኖ ምስጋናው ይታየው እና ፋኖ ባየ ደስታ፣የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮች፣የአባ ኮስትር ብርጌድ አመራሮች፣የሻለቃ አመራሮች፣ለአማራ ህዝብ የነፃነት ታጋይ አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በዚህ ፕሮግራም የተገኙ የክብር እንግዶች በተገኙበት ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአባ ኮስትር ቅየ ለእነማይ ለምጨን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀዋል።

በምርቃ ፕሮግራሙ የተገኙት አመራሮች እንደተናገሩት አባ ኮስትር ብርጌድ ከአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዙ ጋር እያደርገ ያለው ተጋሃድሎ ሳይበግረው በተለያዩ ቦታዎች ውጊያዎችን በማድርግ በረካታ ገድል ሲፈፅም የቆየ ቢሆንም በድርጅቱ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የሚሰጣቸውን የትኛውም አይነት ወታደራዊ ግዳጅ/ሚሽን በብቃት ከመፈፀም ጎን ለጎን በዚህ ፈታኝ ወቅት ወታደሩን በመልሶ ማሰልጠን አንድ አይነት ወጥ የሆነ ወታደራዊ ቁመና የወሰዱ ተመራቂ የፋኖ አባላትን ማስመርቁ ለጠላት ቅስም መስበሪያ ለወዳጅ ደስታን ይዞ መጥቷል ብለዋል። ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በኮስትር ቅየ ለምጨን ለመሰባሰባችን ምክንያት የሆናቹህ የአባ ኮስትር ብርጌድ 3ኛ ዙር የእግረኛ ሰራዊት ተመራቂ አባላት አደረሳቹህ አደርሰን ብለዋል።

ውድ ተመራቂዎች በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኛቹህ የክብር እንግዶች ወደዚህ የህልውና ትግል ከመግባታችን በፊት እንደሚታወቀው ሰርቶ መብላትን ያስተማረው፣ኢትዮጵያ ከውጭ ወራሪ እና ከውስጥ ሰላቶ እና ባንዳን ያፀደው፣ሀገር የገነባው፣ሀገር ያቆመው የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በራሱ ሀገር፣በእራሱ እርስት ሲያሻቸው በሀይማኖቱ፣በዕርስቱ፣በማንነነቱ፣በአማራነቱ ምክንያት ከ37 በላይ የመኖር መብቱ ተገፎ ቆይቷል ብለዋል።

በመሆኑም በዚህ የትጥቅ ትግል የምንገኝ የህልውና ታጋዩች በሙሉ በአባ ኮስትር ቅየ እነማይ ጀግኖች እነ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወረቅ፣ፋኖ ጠቅል አለህኝ፣ ኢንጅነር ተሾመ፣ፋኖ የፀደው በየነ፣ቅዱሱ እና በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው የትግል ጓዶቻችን እና ንፁሀን አማራዎች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ቅዱስ ትግል ወደ ፊት ለማራመድ እና የአሸናፊነትን ድል ለማምጣጥ በተለያዩ ወታደራዊ ግዳጆች ጎን ለጎን ደከመኝ፣ ሰለቸኝ፣ ብርዱ እና ሙቀቱ እየተፈራረቅን አሸናፊዎች እንሆናለን በብለዋል።

እኛ ለእናተ የምንሰጣቹህ በድርጅታችን መሪዎች በብዙ ስቃይ እና መከራ፣ በብዙ ውጣ ውርድ እዚህ የደረሰው የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል አደራ ሲሆን እናተ ደግሞ ይህንን አደራ ተቀብላቹህ የድል ባለቤት ታደርጉን ዘንድ የሁላችንም ተስፋ ነው ብለዋል።

በእንደዚህ አይነት የህልውና ትግል ቀደም ሲል ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ሀገራችንን ከቀኝ ግዛትና ከባርነት ነፃ አድረገው አስርክበውናል።እንደምሳሌ ብንጠቅስ ዛሬ  ያለንበት ቦታ እነማይ ለምጨን እና አካባቢው አንዱ ነው። አርበኝነትን ስናነሳ ይህ ቀጠና መረሳት በፍፁም አይቻልም።የአርበኞች መነሀሪያ የአርበኞች መፍለቂያ የጀግኖች መሰባሰቢያ ከሆኑት ውስጥ ይህ ለምጨን እና አካባቢው ቀጠና አንዱ ነው።

በዛሬው እለት ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም የ3ኛ ዙር እግረኛ ተመራቂ የፋኖ አባላት እናተ የጀግናው አርበኞች በላይ ዘለቀ ልጅ ናቹህ በመሆኑም በእርስታችን፣ በቅያችን በእነማይም ይሁን በመላው አማራ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአማራን ህዝብ የአረመኔዊ ድርጊት በመስራት በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኘን በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልን መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለን።

እንሰለጥናለን፣እንደራጃለን፣እንታጠቃለን፣የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን።

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
  ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
2🙏1
"የአማራ ሕዝብ ሕልውናው እና በክብር የመኖር መብቱ በማያወላውል ሁኔታ እስኪረጋገጥ ድረስ፣ ፋኖ የጀመረውን ትግል አያቆምም።"

ለንደን ፋኖ

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፓርላማ ምላሽ ላይ
ከለንደን ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

ቀን: ጥቅምት 18፣ 2018 ዓ.ም

ለንደን ፋኖ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው፣ በለንደን ስለተካሄደው የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ተቃውሞ የሰጡትን ምላሽ በጽኑ እንደሚቃወም ይገልጻል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የተቃውሞ ዓላማዎቻችንን በቅጡ ያልተረዳ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ግፍ ለመደበቅ ያለመ እና እውነቱን የካደ አሳፋሪ ተግባር ነው።

በአማራው ሕዝብ ላይ በጦርነትና በጭፍጨፋ የተነሳ የመኖር እና ያለመኖር የሕልውና ስጋት እያለ፣ የሕዝብ ወኪል አስሮ መደራደር እንደማይቻል እና ''የምክክር ኮሚሽን" የሚባለው ስብስብ የገዢው ቡድን ሥልጣን ማራዘሚያ እንጂ የችግሩን ሥር መፍታት ዓላማው እንዳልሆነ ለንደን ፋኖ በእርግጠኝነት ይረዳል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የራሱን ዜጎች ''አላውቃችሁም'' የሌላ ሃገር ዜጎች ናችሁ በማለት እጅግ አሳፋሪ ክህደት የፈጸመ መሆኑን በአንክሮት እናሳውቃልን።

በመሆኑም የጠቅላይ ሚኒስትር ''ነይ ባዩ" አነጋገር የችግሩን ምንጭ ከመፍታት ይልቅ፣ ሕዝብን የማዘናጊያ መንገድ ብቻ እንደሆነ እናምናለን።

የአማራ ሕዝብ ሕልውናው እና በክብር የመኖር መብቱ በማያወላውል ሁኔታ እስኪረጋገጥ ድረስ፣ ለንደን ፋኖ የጀመረውን ትግል አያቆምም።

በአማራ ሕዝብ ላይእየተካሄደ ያለው ጦርነት እስኪቆም፣ የጅምላ ጭፍጨፋው ፍጻሜ እስኪረጋገጥ እንዲሁም በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት ለፍትህ እንኪቀርቡ ድረስ፣ የለንደን ፋኖ ድምፁን አጠናክሮ ለዓለም ማኅበረሰብ ማሰማቱንና ለሕዝቡ ድምፅ መሆኑን ይቀጥላል።

ድል የሕልውና አደጋ ለገጠመው የአማራ ሕዝብ!

ለንደን ፋኖ - ለንደን፣ እንግሊዝ
4🙏2