ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ እና ምዕራብ ጎንደር ቋራ የመሸገው ጥምር የአገዛዙ ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ ደለጎ፣አፀደማርያም እና ሻሁራ ከተማ በአሁኑ ስዓት ከፍተኛ ሽንፈትን እያስተናገደ ይገኛል።መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ እና ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሰራዊት ጋር በመጣመር ደለጎ ከተማ የመሸገውን ፀረ አማራ ሀይል ክፉኛ እየተመታ ሲሆን አድዋ ክ/ጦ አፀደማርያምና ሻሁራ ቀጠናን እየተፋለሙት ይገኛል።

ዝርዝር ዜናውን አውደ ውጊያው እንደተጠናቀቀ የምናቀርብ ይሆናል።

ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥቅምት 18/02/2018
🙏1
ብልፅግና በአዲስአበባ ከተማ አፈሳ ማካሄዱ ተገለፀ።

አገዛዙ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ።

ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በርካታ ወጣቶች ታፍሰዉ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉ ታዉቋል።

በ11 ክፍለከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታፍሰዉ በሶስት መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉን ከአዲስአበባ  ከተማ ኗሪዎች ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግረዋል።

በተለይ እድሚያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለዉ ስለመወሰዳቸዉ ጭምር ኗሪዎች ተናግረዋል።አፈሳዉ በናዝሬት፣በደብረዘይት፣በሞጆ፣በሀዋሳ፣በይርጋለም፣በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች እንዲሁም በጋሞ እና ወላይታ ብዛት ያላቸዉ ወጣቶች ታፍስዉ በእየ አዳራሹ ታጉረዉ ይገኛሉ።

በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚታፈሱ ወጣቶች ቁጥር ከወትሮው በተለየ መልኩ መጨመሩ የተገለፀ ሲሆን የብልግና ኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ የኦሮሞን ስልጣን እንጠብቅ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነትን ሊያጠፉ ነዉ በሚል ስብከት ወጣቱ እየታፈሰ ነዉ ተብሏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
የፋኖ ድምፅ!!!
🙏21
የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች እየተካሄዱ ባሉ ጦርነቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሰላማዊ ሰዎች እና መሠረተ ልማቶች ጉዳት ይፋ እንዲደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠየቁ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም (# አሻራ ሚዲያ)

ደሳለኝ(ዶ/ር) የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ያቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ብሩህ ተስፋን የተሞላ ቢሆንም በኢትዮጵያውያን ከዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ካለው የሠላምና የጸጥታ መናጋት፣ የኑሮ ውድነትና የዴሞክራሲ ምህዳር መጥበብ አኳያ ከንግግራቸው ይዘት ጋር የሚጣረስ ነው የሚል እምነት አለኝ በማለት ወደ ጥያቄያቸው ተሻግረዋል።

ጥያቄያቸውን ከማቅረባቸው በፊት ግን አንድ ማሳሰቢያን ሰጥተዋል። እሱም ዛሬም የማነሳቸው ጥያቄያዎችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨለምተኛነት እንዳይወስዷቸው ያሳሰቡበት ነው።

“ጥያቄዎቹም የሕዝብ በመሆናቸው እንጂ ጨለምተኛ በመሆኔ አይደለም” ብለዋል።

በአማራ፣ ኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ጦርነትና ግጭቶች ተባብሰው በመቀጠላቸው ብዙዎች እየተጎዱ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደ ጸጥታ መሪነትዎ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በእነዚህ ጦርነቶች ምክንያት የተጎዱ ሰላማዊ ሰዎችና የሰለማዊ ሰዎች መሠረተ ልማቶች ቁጥር በግልጽ ይፋ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

“የጸጥታ ችግሮቹን ለመፍታት “ጽንፈኛ” እና “አሸባሪ” የሚላቸውን ቡድኖች ከመውጋት ባለፈ ለሁለቱ ክልሎች ከወታደራዊ አማራጮች ውጪ የተለየ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመስጠት መንግስት ለምን አይሰራም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርስ በእርስ ጦርነት አንገፍግፎታል፤ በሀገር ውስጥ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ መብላት ከብዶታል፤ ሀገራችንም እንደ ኮሎምቢያ ከውስጥ ታጣቂዎች ጋር ሀምሳ ዓመታትን እየተዋጋች ልትቀጥል አትችልም” ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተው አሳስበዋል።

“የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች የተፋጠነ ፍትሕ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም የፖለቲካ አቅጣጫ የተሰጠበት በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያለ ፍርድ እየተንገላቱ ነው፤ ቤተሰቦቻቸውም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀወዋል” ብለዋል።

በሕግ የማስከበር ስም የሚፈጸሙ የዘፈቀደ የፖለቲካ እስሮች፣ ለሚመጣው 7ኛ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ነፃና ተዓማኒነት ያለው እንዳይሆን ላለማድረጉ መንግስት የሚሰጠውን ዋስትናም ጠይቀዋል።
3🙏1
ከመቄት ወረዳና አካባቢው ህዝብና የፋኖ ሰራዊት ጋር በየ ፈርጁ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የህልውና ትግሉን ለማሳለጥ የሚያግዝ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት አመርቂ ስራ እየተሰራ ይገኛል::

የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ኢንጅነር አራጋው ያለው እና ሌሎች በየደረጅው ያሉ አመራሮች በተገኙበት የመቄት ወረዳና የአካባቢውን ማህበረሰብ እንዲሁም የአካባቢውን የፋኖ ሰራዊት በማወያየት የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የህዝብ አስተዳደሩን እና የፋኖውን ሚና ለይቶ በማሳወቅና በመስጠት የህልውና ትግሉን ማሳለጥ የሚቻልበት መንገድ ላይ አመርቂ ስራ እየተሰራ ይገኛል::

በዚህም ጥቅምት 15 እና 16/2018 ዓ.ም ከአካባቢው የፋኖ ሰራዊትና አመራር እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ በየደረጃው ያሉ የሰራዊቱ አመራሮች ከሰራዊቱ የመጣውን ገንቢ ሃሳብና አስተያየት በመቀበል ተበታትኖ እየታገለ ያለውን ሰራዊት ማሰባሰብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተመክሮ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ይገኛል::

የህዝብ አስተዳዳሪ ሆነው በህዝብ የተመረጡ አመራሮችም በተመሳሳይ ማህበረሰቡ ያነሳቸውን ሃሳብና አስተያየቶች እንዲሁም ጥያቄዎች በመቀበል በቀጣይ የህዝብ አስተዳደር መዋቅሩ ፋኖ ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ታጋዩ ይሰራቸው የነበሩ ስራዎች በመጋራትና በማቅለል በርካታ የህዝብ ስራዎችን በመሸከምና በማገልገል ለትግሉ ውጤታማነት የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በመምከር ወደ ተግባር የማስገባት ስራ ተሰርቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም
🙏1
በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

EOTCMK TV ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ  ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፈት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።

የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።

በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ  ከተማ  ሪፈር  መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። 

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።

በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቅሷል።
©ማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ
1💔1
በአፋብኃ ቲውድሮስ ዕዝ የተማረኩ ምርኮኞች!!
👍3🙏1
በአርበኛ መከታው ማሞ ከሚመራው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እና በአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ከሚመራው አሳምነው ዕዝ የተወጣጡ የፋኖ ኃይሎች በጋራ በመሆን በወሰዱት እርምጃ ታላቅ ድል መቀዳጀታቸው ታውቋል!

በመርሀቤቴ ቀጠና በተደረገ ውጊያ ጠላት "በክፉ ቀን የሚታደጉኝ" በሚል የሚመካባቸው ከ40 በላይ ጀበና ሰባሪ አየር ወለድ ኮማንዶዎች ሲገደሉ ከ25 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

ከተገደሉት መካከል የኮማንዶ ሻምበል አዛዦችና መስመራዊ አዋጊዎች ይገኙበታል የተባለ ሲሆን፡ በተጨማሪም በተለምዶ ጥርጥሩ ክላሽ በመባል የሚታወቀው በርካታ ጥቁር ክላሽንኮቭ መሣሪያ ማርከው መታጠቃቸው ታውቋል።

@መረብ
2👍2👎1🙏1