ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የጎንደር ፋኖ አዛዦች ለጋራ የአማራ ዓላማ መሰባሰብን አስመልክቶ በዓለም አቀፍ ፋኖ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት ፳፻፲፰ ዓም

በቅርቡ የጎንደር ፋኖ አዛዦች ልዩነታቸውን ወደ ጎን ትተው በአንድ የጋራ አማራ ዓላማ ለመሰለፍ የወሰኑት ውሳኔ ለህዝባችን እና ለንቅናቄያችን ታሪካዊና ተስፋ ሰጪ ጊዜን የሚያበስር ኣስደሳች ዜና ነው። ከመከፋፈልና ከግጭት
ይልቅ ራዕይን እና የጋራ ግቦችን ለመረጡት አዛዦች፣ ተዋጊዎች እና ደጋፊዎች ሁሉ ሞቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።

ይህ አጋጣሚ ትልቁ ኃይላችን ከአንድነት እንደሚመጣ ጠንካራ ማሳሰቢያ ሆኖ ያገለግላል፤ በህብረት ስንጓዝ የሚያቆመን
ሃይል የለም፤ እንደ አንድ ስንናገር ዓለም ያስተውላል። የተዋሃደ አመራር የአማራ ትግልን መሰረት ከማጠናከር ባለፈ ሰፊ አለም አቀፍ እውቅና እና ድጋፍ የማግኘት እድሎችን ያሳድጋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የትግላችን መቀናጀት፣ የጋራ ግባችን እና የዲሲፕሊን ጥረትን ሲገነዘብ የህልውና ትግላችንን እንቅስቃሴ የመደገፍ ዕድሉ ሰፊ ነው።
የጎንደር ፋኖ አዛዦች በአንድነት አመራር መሰባሰባቸው የፖለቲካ ጥበብ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ እና በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ላይ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነትን ያሳያል። አዛዦቹ የጋራ ራዕይን በመከተል የአማራ ንቅናቄ የተደራጀ፣ የተቀናጀ እና ለፍትህ የቆመ፣ ደህንነት እና ዘላቂ መረጋጋት ለማምጣት ቆርጦ የተነሳ ሰራዊት መሪ
መሆናቸውን አሁን በተግባር አሰመስክረዋል። ይህ አንድነት የንቅናቄውን ስልታዊ አሰላለፍ እና የአሠራር አቅምን ያጠናክራል፣ ይህም በእቅድ፣ በሰብአዊ ጥረቶች እና በአለም አቀፍ ተሟጋችነት የተሻለ ቅንጅት እንዲኖር ያስችላል።
ለሰላም እና ለሰብአዊ መብቶች ቁርጠኛ ከሆኑ አጋሮች ጋር ለውይይት እና ለትብብር ጠንካራ መሰረት ይፈጥራል።

የአንድነቱ ውሳኔ ቢዘገይም የፖለቲካ ስኬትን ብቻ ሳይሆን የሞራል ስኬትንም ተገንዝበናል፤ በግለሰብ ልዩነቶች ላይ የጋራ ግቦች ድል ነስተዋል። ተመስገን።

የአማራ ፋኖ የወሰደዉ የአንድነት ዉሳኔ ለመላዉ አማራ የህልዉና ዋስትና ወይም ደጀን ከመሆኑም በላይ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ ዉስጥ እጅግ በጣም ወሳኝ ጠንካራ የጋራ ታሪካዊ ህብረት እንደነበረዉ ምስክርነት የሚሰጥ ነዉ። ጀግኖች በፍቅር እየተላቀሱ ሲተቃቀፉ ማየት እንዴት ደስ ይላል - ከጎናቸዉ በአንድነት በነቂስ አብሮ መሰለፍ ሰዓቱ አሁን
ነዉ። ስለዚህ አንድነት ምንድን ነዉ? አንድነት ይቅርታ ነዉ። አንድነት መቻቻል ነዉ። አንድነት መተማመን ነዉ። አንድነት መሠረት ነዉ። አንድነት አንድ አማራጭ ነዉ። አንድነት ሐገር ነዉ። አንድነት አሸናፊነት ነዉ አንድነት
ድምቀት ነዉ። አንድነት ፍቅር ነዉ። አንድነት መከባበር ነዉ። አንድነት ለሌላዉ መሆን ነዉ። አንድነት ተሽሎ መገኘት ነዉ። አንድነት ሕይወት ነዉ። አንድነት ተግባር ነዉ። አንድነት ፍሬ ነዉ። አንድነት ምስክርነት ነዉ። አንድነት ሐቀኝነት ነዉ። አንድነት በልጦ መገኘት ነዉ። አንድነት ህልዉና ነዉ። አንድነት ሚስጥር ነዉ። አንድነት ጥበብ ነዉ። አንድነት ከለላ ነዉ ። አንድነት ህብረት ነዉ። አንድነት ማወቅ ነዉ። አንድነት መሰላል ነዉ። አንድነት ዉበት ነዉ። አንድነት እዉቀት ነዉ። አንድነት ዋስትና ነዉ። አንድነት ደጀን ነዉ። አንድነት አለኝታ ነዉ። አንድነት ወግ ባህል ነዉ። አንድነት ታሪክ ነዉ። አንድነት ሻማ ነዉ። አንድነት በር ነዉ። አንድነት ዉቅያኖስ ነዉ። አንድነት መኖር ነዉ። አንድነት መቻል ነዉ። አንድነት ሁሉንም ነዉ።

ይህ የአማራ ፋኖ አመራሮች አንድነት በመላው አማራ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ፤ ወደዚህ አንድነት እንዲመጡ ብዙዎች የህይወት፣ የገንዘብ፣ የጉልበትና የጊዜ መስዋእትነት የተከፈለበት፤ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ማገዝ ያልቻለው አብዛኛው ህዝብ በፀሎት እግዚአብሔርን የለመነበት አሳሳቢ ጉዳይ ነበር።

አሁን የሰማነው ዜና ተመስገን አስብሎናል። ምክንያቱም ፩ኛ የፋኖ አመራሮች አንድነት የአማራን ህዝብ ሰቆቃ እና ችግር በአጭር ጊዜ ያቃልላል፤ ፪ኛ ግንባር ላይ ያሉ አመራሮች አንድ ሲሆኑ ተበታትነው የሚሰሩ የተለያዩ የአማራ
ሲቪል አደረጃጀቶች ወደ አንድ እንዲመጡ ያደርጋል፤ ፫ኛ የአማራ ፋኖ ሰራዊት፣ የአማራ ሲቪል ድርጅቶችና በውጭ የሚኖሩ የአማራ ልጆች በጋራ ሲሰሩ የዐማራ ግፍና ሰቆቃ ያበቃል፣ የኢትዮጵያንም ትንሳዔ ያበስራል።

ሰማዕታቶቻችን ህይወታቸውን የገበሩት የፋኖ አመራር ተከፋፍሎ ለማየት አይደለም፤ ለህዝባቸው ክብር፣ ነፃነት እና ህልውና ሁሉንም ነገር ሰጥተዋል። መሪዎቹ አንድ ላይ በመሰባሰብ ይህንን የተቀደሰ ግዴታ አክብረዋል እናም በሁሉም የአማራ ልብ፣ ከጎንደር እስከ ጎጃም፣ ከወሎ እስከ ሸዋ፤ የእኛንም የዲያስፖራ ዐማራ ልጆችና ተወላጆች የነጻነት ተስፋ አድሰዋል። በተጨማሪም፣ ይህ አንድነት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰላማዊና ፍትሃዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመረጋጋት
እና ለፍትህ ከሚጥር ኃላፊነት የተሞላበት እና ያተኮረ እንቅስቃሴ ጋር ለመሳተፍ አዲስ እድል ይሰጣል። በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ይህን የተባበረ አመራር አስፈላጊውን ድጋፍ እንድንሰጠው የሚገፋፋም ጥሪ ነው። ዕውቀታችን፣ ሀብታችን ጉልበታችን እና ጽኑ እምነታችን ለትግሉ እንድናበረከትም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ቀስቃሽ ክስተት ነው።
ወደፊት ያለው ጉዞ ፈታኝ ይሆናል፣ ነገር ግን በአንድነት፣ በዲሲፕሊን እና በራዕይ፣ ስኬታማ እንደሚሆን የበኩላችን አስተዋጽዖ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል። በጋራ የአማራ ህዝብ በብቸኛ ትውልድ አገሩ በሰላም፣ በእኩልነት እና በደህንነት የሚኖርበትን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መፍጠር እንችላለን።

አማራዊ አንድነት ጋሻችን፣ መሳሪያችንና ብቸኛ
እጣ ፈንታችን ነው። ለህዝባችን፣ ለነፃነታችንና ለወደፊታችን አንድነት ይህ የጎንደር ፋኖ አመራር ስምምነት ትልቅ ሚና ይኖረዋል።

በመጨረሻም፣ የአማራ ህዝብ በጠላቶቹ ከተፈፀመበት ግፍና ስቃይ በተጨማሪ ሃሳዊ ፋኖና ህገወጥ ህግ አልባ ታጣቂ ቡድኖች ከፍተኛ ግፍ እየፈጸሙበት መሆኑን ስንሰማ ሀዘናችንን ልብ ሰባሪና ጥልቅ መሆኑን እየገለፅን፤ የፋኖ አመራር እንደ ደቡብ ጎንደር በለሳና እና አዲስ ዘመን ባሉ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነትና ህግ አልበኝነት ለመግታት፤ ብሎም ለማስወገድ ከህዝቡ ጋር በመተባበር ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ እና ተከላካይ የሌላቸውን እና ተጋላጭ የሆኑ
ወገኖቻችን ከውስጣዊ ብዝበዛ እና ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲጠብቁ አጥብቀን እናሳስባለን።

አንድነት ትግላችንን በድል ለመወጣት!
አንድነት ለፋኖ ድል አድራጊነት!
ድል ለአማራ ህዝብ!

ዶክተር አምባቸው ወረታ /ሊቀመንበር ማርእሸት መሸሻ / ጠቅላይ ጸሃፊ
1👍1🙏1
ለተከታታይ 6 ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ የሽፈራው ገርባው ብርጌድ ልዮ ኮማንዶ ተመርቀዋል።

ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎዶሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ለተከታታይ ስድስት ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ ልዮ ኮማንዶች በዛሬው ዕለት ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል።

በቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው የበረሃው አናብስት ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ከዚህ ቀደም በእግረኛ የሰለጠነ ወታደራዊ ሰራዊት ለ2ኛ ዙር እና በልዮ ኮማንዶ 1ኛ ዙር ያስመርቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት በተከታታይ ስድስት ወራት በተላያዩ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ የሁለተኛ ዙር ልዮ ኮማንዶዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

በዚህ የምርቃ ስነ ስርዓት በክብር የተገኙ እንግዶች፣ የክፍለ ጦር አመራሮች፣ የብርጌድ አመራር እና የሻለቃ አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበርሰብ በተገኙበት በሸበል በረንታ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል።

እንደራጃለን፣እንሰለጥናለን፣እንታጠቃለን የአማራን ህዝብ ከአረመኔው አገዛዙ ስረዓት ነፃ እናወጣለን።

በስምንተኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ስር ባሉ ብርጌዶች ተመሳሳይ የልዮ ኮማንዶዎች ስልጠናዎች ወደፊት ይቀጥላሉ!

   አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
           ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
🙏2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

ሰበር የድል ዜና!!!

በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ያልበለፀገው የብልፅግና የቡግንጅ ስርዓት አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት ፀረ አማራ ጀኖሳይድ ቡድን በቀጠናው ተለዋዋጭ የሴራ ካርዱን በመምዘዝ በየስአቱ ሁሉን አቀፍ ጀኖሳይድ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ የክህደት ስርዓቱን ለማስቀጠል አሁንም አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኗል።በትናንትናው እለት በሽመለጋራ የመሸገው ይህኑ ሀይል በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ካራማራ ክ/ጦ ከፍተኛ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ከንጋቱ11:00__ቀኑ 7:30 በተደረገው አውደ ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት: 35
ቁስለኛ:39 በለይ
የፀረ ሽምቁ አመራር መሳፍንትና የፖሊስ ኮሚሽነሩም አፈር ከድሜ በልተዋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥቅምት 17/2018
2🙏2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

ሰበር የድል ዜና!!!

በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ያልበለፀገው የብልፅግና የቡግንጅ ስርዓት አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት ፀረ አማራ ጀኖሳይድ ቡድን በቀጠናው ተለዋዋጭ የሴራ ካርዱን በመምዘዝ በየስአቱ ሁሉን አቀፍ ጀኖሳይድ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ የክህደት ስርዓቱን ለማስቀጠል አሁንም አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኗል።በትናንትናው እለት በሽመለጋራ የመሸገው ይህኑ ሀይል በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ካራማራ ክ/ጦ ከፍተኛ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ከንጋቱ11:00__ቀኑ 7:30 በተደረገው አውደ ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት: 35
ቁስለኛ:39 በለይ
የፀረ ሽምቁ አመራር መሳፍንትና የፖሊስ ኮሚሽነሩም አፈር ከድሜ በልተዋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥቅምት 17/2018
🙏2
ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶችን በማድረግና የመዋቅር ዝርጋታዎችን በማካሄድ በአገዛዙ ላይ ፖለቲካዊ ኪሳራ ማድረሱን ቀጥሏል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነው ኮር ስር የሚገኘው በአርበኛ ብርሀን አሰፋ/ዘንዶው/ የሚመራው ጥራሪ ክፍለ ጦር ከሚያደርጋቸው ውጊያዎች ጎን ለጎን በተቆጣጠራቸው አከባቢዎች ከማሕበረሰቡ ጋር ጥልቅ ውይይት ማካሄዱን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በስብሰባው የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳትና የትግሉን የወደፊት መንገዶች በመገምገም የሚታዩ ክፍተቶችን ነቅሶ በማውጣት መወያየት የተቻለ ሲሆን ትግሉን በመቀላቀልና በመደገፍ ባጠረ ጊዜ የህልውና ትግሉ የሚቋጭበትን በዝርዝር በማስቀመጥ ማህበረሰቡ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበት በመተማመን ውይይቱን መቋጨት ተችሏል ተብሏል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ማሕበረሰቡን ለፍትሕ እጦት ዳርጎት የነበረውን የብልፅግናን መዋቅር በማፈራረስ ሕዝብ ተኮር የሆኑ መዋቅሮችን መዘርጋት ተችሏል ነው ያለው የጥራሪ ክ/ጦር ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ።
1🙏1
አማራ ጠል ኃይሎች የአማራ የሆነን ሁሉ ያወድማሉ።

ከላይ የምትመለከቱት የአብይ ወንበር አስጠባቂዎች የግለሰቦችን  ሞተር ሲያቃጥሉ ነው።

በአማራ ጥላቻ ያበደው በሀገር መከላከያ ስም የተሰበሰበው የአንድ ብሔር የበላይ ጠባቂ ሰራዊት ባገኘው አጋጣሚ የአማራ የሆነን ሀብት ንብረት በዝህ መልኩ ነው የሚያነደው

አማራ የሆነ በሙሉ የመታገል ግዴታ አለበት።
አባት ለልጁ በሬውን ላሙን ያለ ንብረቱን ሽጦ ለልጁ ሞተር ይገዛል የኦሮሙማው ሰራዊት በዝህ መልኩ በጭፈራና በዕልልታ የሀገሩን ዳር ድንበር እያስከበረ ጀብድ የሰራ ይመስል ቀብረር ብሎ እዬቀረጸ ያቃጥላል አማራ ሁኖ ይህ የማይቆጨው ካለ ምንም ልንል አንችልም።

@አሻራ
1🔥1
ዛሬም ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይት እየተደረገ አዲስ የአስተዳድር መዋቅር እየተዘረጋ ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ነፃ ባወጣቸው የሰሜን ወሎ ዞን መካከል በሀብሩ ወረዳ ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል በሩጋ መነዮ ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡

ዛሬ በዕለተ እሁድ በቀን 16/02/2016 ዓም በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ ሩጋ መነዮ ቀበሌ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡

በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች

1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?
* ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ
* ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ
* የትግሉ ተግዳሮቶች
* የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ
*የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት አካባቢያቸውን ከፋሽቱና ወራሪው የአብይ አህመድ ሰራዊት እንድጠብቁ ግንዛቤ ተስጥቷል።

2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ
* በወታደራዊ ቁመና
* በፖለቲካ ተቀባይነት
* የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም

3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ
* የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት
* የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት
* ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ

4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?

በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተሞክሯል፡፡

በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና በተለይ ሙስሊም ጠል ናቸው በሚል አገዛዙ ትግሉን እንድንጠላው መንግሥት በፋኖ ላይ ትልቅ ጥላቻ እንዲኖረን ብዙ የሰራ ቢሆንም ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል እና ዛሬ ጥርጣሬያችንን ለማጥራት ችላቹሃል በማለት ሃሰተኛውን የብልፅግና ስርዓት በጋራ ለመታገል ቃል ገብቷል፡፡

በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ስትባሉ የነበረውን የሃሰት ስም ማጥፋት በተግባር የህዝብ ልጅ መሆናችሁን አሳይታቹሃል እኛም ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት
ፋኖ መሀመድ ሞገስ

ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
🙏2