ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘይሴ ማሕበረሰብ እና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል ከባድ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል!

የዘይሴ ማሕበረሰብ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆነው አቶ ጥላሁን ከበደ በፌደሬሽን ምክር ቤት ያለውን ተሰሚነት ተጠቅሞ የዘመናት የልዩ ወረዳ ጥያቄያችንን አፍኖብናል" በሚል የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ ሲሆን፡ የወረዳና የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች የስራ ማቆም አድማውን ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ ከባድ የሆነ ጥቃት ተከፍቶባቸዋል።

ለክልሉና ለወረዳው ፀጥታ አካላት እገዛ ለማድረግ ወደ አከባቢው የገባው እራሱን "መከላከያ ሰራዊት" እያለ የሚጠራው የመንደር ዱርየ ስብስብ፡ ማሕበረሰቡ ላይ የዘፈቀደ ተኩስ በመክፈት በርካቶችን ለሞትና ለአካል ጉዳት እንደዳረጋቸው የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።

ማሕበረሰቡ በተደራጀ መልኩ በአገዛዙ ወታደሮች የተከፈተበትን ጥቃት እየመከተ ሲሆን፡ ትናንት በስቲያ ጥቅምት 13/2018 ዓ/ም ምሽት ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት በአንድ ፓትሮል ላይ ተሳፍረው የነበሩ እራሳቸውን "መከላከያ ሰራዊት" ብለው የሚጠሩ ከ10 በላይ ወታደሮች ሲገደሉ፡ ተሳፍረውበት የነበረው ወታደራዊ ተሽከርካሪ ፓትሮልም ሙሉ በሙሉ መውደሙ ታውቋል።

ሕዝባዊ አመፁ ተቀጣጥሎ የቀጠለ ሲሆን፡ ፀረ ሰላሙ የብልፅግና ቡድንም አመፁን ለማስቆም ያግዙኛል ያላቸውን የጦር መሣሪያዎችን እየተጠቅመ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።
🙏21
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው::

ከዘመቻ አባ ናደው መጠናቀቅ በኋላ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችና ዕዞች ወደ ቤተ-አማራ የገባው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰና እየኮበለለ ምኒልክ ዕዝን በስፋት እየተቀላቀለ ነው::

የኦሮሞ ብልፅግና ልዩ ሃይል ኦሮሚያ ላይ በአማራ ተወላጆች ላይ ሲፈፅመው የነበረውንና ዛሬም እየፈፀመው ያለውን ግፍ በተመሳሳይ የመከላከያ መለዮ ለብሶ ወደ አማራ ክልል በመግባት የሚፈፅመውን ግፍ እያየን እኩል የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተብለን ልንጠራ አንችልም ያሉ አባላቶቹ ባለፉት አስር ቀናቶች ብቻ 4 ስናይፐርና 28 ክላሽ 7000 የክላሽ ተተኳሽ 600 የስናይፐር ተተኳሽ እንዲሁም 60 የእጅ ቦምብ በመያዝ ከ32 በላይ ሰራዊት ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል::

ፋኖን ከተቀላቀሉት የ104ኛ ኮር የሰራዊቱ አባላቶች መካከልም 4 ሻምበል መሪና 3 የመቶ መሪ አመራሮች ይገኙበታል:: በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝን ሰራዊት የማፍረስና የማስኮብለሉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::

•ማስታወሻ፦ ስም ዝርዝርና ምስል ያላካተትነው በቀጣይ ለምንሰራው ስራ ደህንነት ስንል ነው!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም
🙏21
ጡት ቆራጩ የብልፅግና ቡድን በጎንደር ቋራ ቴዎድሮስ ከተማ በፈፀመው የድሮን ጥቃት፡ ቅዳሜ ገበያ ለመገብየት የተሰባሰቡ ገበያተኞች መገደላቸው ተሰምቷል።

ዛሬ ጥቅምት 15/2018 ዓ/ም ረፋድ 4:00 አከባቢ በቋራ ቴዎድሮስ ከተማ የቅዳሜ ገበያ ለመገብየት በተሰባሰቡ ገበያተኞች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት፡ በርካታ ንፁኋኖች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል።

በተመሳሳይ ይሄው ፀረ አማራ ኃይል ከቀናት በፊት በላይ ጋይንት ወረዳ ዛጎች ቀበሌ ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት አንዲት እናት ከነ ልጇ ተገድላለች።

ይህ ጡት ቆራጭና ፀረ አማራ የብልፅግና ኃይል ዛሬም በቋራ ቴዎድሮስ ከተማ የቅዳሜ ገበያን ለመገብየት በተሰባሰቡ ንፁኋኖች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈፅሟል።
1💔1
በዘመቻ አደም አሊ(አባናደዉ) ዘመቻ የተማረኩ የሚሊሻ እና የፖሊስ አባላት በፍቃዳቸዉ ፋኖን እንደሚቀላቀሉ ተናገሩ።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ከ መስከረም 14/2018 እስከ መስከረም 30/2018
ዓ.ም በፈጀዉ ዘመቻ አድም አሊ(አባ ናደዉ) አመርቂ ድል ማስመዝገቡ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ዘመቻ ላይ የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት ቡዙ አካላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት ይታወቃል።

በዚህም ዘመቻ ላይ ከ679 ምርኮኞች መካከል 100ዎቹ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሲሆኑ እነዚህ ምርኮኞችም እስካሁን በማወቅም ባለማወቅም የአማራን ህዝብ በድለናል ከአሁን ስዓት ጀምሮ ህዝባችንን በበደልነዉ ልክ ከፋኖ ወንድሞቻችን ጋር ተቀላቅለን እንክሰዋለን ሲሉ ተናግረዋል።

ምርኮኞቹ አክለዉም ይህ ፋሽዝም ስርዓት ምላሱ ብቻ እንደቀረ ገልፅዉ አሁንም በዚህ አገዛዝ ስር ያላቹህ ፋሽስቱ የብልፅግና አገዝ ጥምር ጦር የሚላቹህ የሰራዊት አባላት እና አመራሮች አሁንም ሳይረፍድባቹህ ያላቹህበት ስርዓት አገር አፍራሽ መሆኑን አዉቃቹህ ወደ እዉነተኛ ትግል ወደሆነዉ የአማራ ፋኖ እንድትቀላቀሉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዉ እኛ ተማርከን ህይወታችን ሰለተረፈ እድለኞች ነን ብለዋል።

በዚህም ለይ የ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ፅ/ቤት ኃላፊ አርበኛ ደስታዉ መለሰን ጨምሮ ሌሎች የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የዚሁ ዕዝ ክንፍ የሆነዉ ግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዉ ምርኮኞችን በሚፈልጉት ቀጠና ባሉት ኮሮች እና ክ/ጦሮች ሂደዉ እንዲታገሉ የድልድል ስራ ሰርተዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

አፋብሃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ክፍል ኋላፊ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን!
ጥቅምት 15 /2018 ዓ.ም
1🙏1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የአገዛዙ ጥምር ሀይል እና አሸርጋጁ የብልፅግና አጀንዳ በቀላሉ ከማቋረጥ ባሻገር ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ስብሰባውን መበተን ተችሏል።

በዛሬው እለት በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ሽመለጋራ የዞንና የወረዳ ሆድ አደር የብልፅግና አሽከሮች ከአገዛዙ ጥምር ሀይል ጋር እንደተለመደው ስለ አማራ ሁሉን አቀፍ የጀኖሳይድ ፀያፍ ተግባራቸውን ለመፈፀምና የጥፋት አጀንዳ ይዘው ለመዶለት ስብሰባ ለማድረግ እየተዘጋጁና እየተሰባሰቡ ባለበት ስአት ነበልባሎቹ የበረሀ ፈርጦች መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድ በአርበኛ ገ/ህይወት አዳነ እየተመራ እንዲሁም በአናብስቶች ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ በአርበኛ ተስፋየ ማስረሻ መሪነትና መረጃን ቀድሞ በማፈንፈን ሁለቱ ብርጌዶች ጠላት ባላሰበበት ሁኔታ ከቀኑ 6:00 ስዓት ወደ ቀጠናው ተስፈንጥሮ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት መፈፀም ተችሏል።ውጊያውን እስከ 9:00ስዓት በማስቀጠል በጥምር ሀይሉ ላይ ከፍተኛ ድል ማስመዝገብም ተችሏል።

በዚህ ልዩ መብረቃዊ ጥቃት ስብሰባውን ከመበተን ባሻገር የአገዛዙ ጥምር ሀይል ሙት 10፣ ቁስለኛ ከ13በላይ ሲሆን  የብልፅግናው አሸርጋጅ ምስለኔዎች በየ ጓዳው ጎድጓዳው እግሬ አውጭኝ በማለት በየቤቱም ቀሚስ በመልበስ እና በመመሳሰል በየ ስርቻው በመግባት እራሳቸውን አትርፈዋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ

      ጥቅምት 15/2018
1🙏1
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ መምሪያ ከድሮን ጥቃት ራስን የመከላከል አስገዳጅ ፕሮቶኮልና ቅድመ ጥንቃቄን በተመለከተ አስቸኳይ መግለጫ ሰጠ!

የጠላት እግረኛ ሃይል ወይም ምንም ዓይነት ግዳጅ መወጣት ያልቻለዉ የዐቢይ አገዛዝ የጭካኔ በትሩን ከፍተኛ በሆነ ድሮን ጥቃት ጀምሯል፡፡ የድሮን አሰሳና ጥቃት ተጠናክሮ ከመቀጠሉ ጋር በተያያዘ በርካታ ንጹሃንና ሰራዊታችን ለኢላማ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እነዚህ ቅድመ ጥንቃቄዎች ቀድመዉ ሊወሰዱ ስለሚገባ በአስገዳጅ ሁኔታ ይተግበሩ ሲል የዕዙ ወታደራዊ መምሪያ ማሳሰቡን ብላክ ላዬን ሚዲያ ተመልክቷል።

የፋኖ ሰራዊታችን በብዛት ሆኖ ክፍት መኪኖች ላይ ማለትም እንደ ሲኖትራክ፣ ኦራል፣ አይሱዙ ወዘተ ተጭኖ መንቀሳቀስ የለበትም፡፡ አስገዳጅ በሆነ የቡድን እንቀስቃሴ ወቅት የተቆራረጠና ዝግዛግ ዓይነት ቅርፅ ያለው የጉዞ መስመር ማድረግ የድሮኑን ዒላማ ማነፍነፍና መፈለግ እንዲሁም የመመልከት አቅጣጫ ያስተዋል።

የድሮን ድምዕ ከተሰማ ወይም ምልክት ከታየ ራስን ጥላ ወዳለው በርከት ያለ ዛፍ ወይም ዋሻ መጠለል አለብን፡፡ ጥላ ከተጠለለ ካሜራው በደንብ ለመመልከትና ዒላማ ለመለየት ይቸገራል። ለመጠለል የገባንበት ዛፍ ወይም ጫካ ካለ ዉስጥ ለዉስጥ ርቀትን መጓዝ አለብን፡፡ የወገንና የተማረኩ ተሽከርካሪዎችን ቅጠል፣ ሃረግ ወይም ጨርቅ መሸፈን በቅኝት ወቅት ዒላማ እንዳይሆኑ ያደርጋል፡፡ የቤትና የመኪና የሚያንፀባርቁ መስታዉቶችን ጭቃ በመቀባት ጨረር የሚያርፍባቸውን ነገሮች ሁሉ ማደብዘዝ ይገባል ነው ያለው ዕዙ፡፡

ዕዙ በተጨማሪም ስለ ሞባይል አጠቃቀም አቅጣጫ የሰጠ ሲሆን፤  ሞባይል ስልክ የሚጠቀሙ የተፈቀደላቸው የፋኖ አባላትና አመራሮች ሎኬሽን ዝግ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ የያዙት ስልክ ስማርት ከሆነ በድሮን እንቅስቃሴ ወቅት በመጀመሪያ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባትና የበረራ ምልክቱን በመጫን Airplane Mode ካደረጉ በኋላ የድሮኑ እንቅስቃሴ ዝም እስኪል ድረስ የስልኩን ባትሪን በማጥፋት፤ ስልኩ ራቅ ብሎ መቀመጥ አለበት፡፡ የትኛዉም የፋኖ አባል ስልኩ ላይ ቴሌግራምና ቴሌብር የተባሉ የመተግበሪያ አፕልኬሽኖች መኖር የለባቸዉም ብሏል፡፡

አንድ የፋኖ ሠራዊት አሃድ በትዕዛዝ ከሆነ ቦታ ሲንቀሳቀስ እስከ ሚደርስበት ቦታ ድረስ የሞባይል ስልክ ዝግ አድርጎ መንቀሳቀስ ግዴታ አለበት፡፡ በጉዞ ወቅት ለሚኖር የመረጃ ትስስር አጭር ሞገድ ራድዮኖችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ የጉዞ የእንቅስቃሴና የስብሰባ ቦታ ተለዋዋጭና እጅግ ምስጢራዊ መሆን አለባቸው:: ስብሰባ ሊያደርጉበት የፈለጉት ቦታ አስቀድሞ የታወቀ ከሆነ እቅድ እንዲቀየር እናሳስባለን፡፡

የስብሰባና ሥልጠና ቦታዎችን በግልፅ ሜዳ ላይ አለማድረግ ግድ ሲሆን ከጧቱ 5:00 - 9:00 ሰዓት የጠላት ሃይል ከሳተላይት ላይ ምስል ለመዉሰድ ምቹ የሚሆንበት ጊዜ ስለሆነ የኃይል ስብስብና ክምችቶችን ሙሉ ለሙሉ በእነዚህ ሰዓት ዉስጥ አስወግዱ፡፡

የዕዙ ወታደራዊ መምሪያ አክሎም፤ ድሮን የፀሃይ ጨረር አቅጣጫ ባለበት መነፅሩ በትክክል መመልከት ስለማይችል የፋኖ ሰራዊት ቦታ ለመያዝ ሲንቀሳቀስ የፀሃይ ጨረረ መስመርን ከፊት ለፊት ማድረግ ይገባል፡፡ የቅኝት ድሮን በአካባቢው ከታየ ፈጥኖ ቦታ መቀየር፤ መሳሪያ ይዞ በቡድን አለመንቀሳቀስ፤ ቤት ዉስጥ ለምግብ ወይንም በአዳራሽ ዉስጥ ለስበሰባ አለመገኘትን በአስገዳጅ ይተግብሩ ብሏል፡፡

ብዛት ያለዉ የፋኖ ሃይል እንቅስቃሴ ማድረግ ከተፈለገ ከቀን ይልቅ በሌሊት ማንቀሳቀስ ተግባራዊ መደረግ አለበት::

በሌሊት የጉዞ ወቅትም ሆነ የካምፕ ቆይታ ጠላት የሳተላይት ምስል እንዳይወስድ የመስመር ሰልፍ ባትሪዎችን ወይንም ብዛት ያለዉ የካምፕ መብራት አለመጠቀም፡፡

የጠላት አብዛኞቹ ድሮኖች በሌሊት የማይሰሩ ሲሆን እጅግ በጣም ጥቂቶቹ በሌሊት የሚሰሩት ደግሞ የመሳሪያና ሰራዊት ክምችት አለ ተብሎ የተጨበጠ መረጃና አቅጣጫ ካገኙ ብቻ ለተጠና ኢላማ ይጠቀሙታል፡፡

በመሆኑም የወገን ሀይል በክምችት ዉስጥ ሁኖ የትኛዉም ካምፕ ዉስጥ እንዳያድር፣ ከዚህ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ሁሉም ሰራዊት በምሽግ ዉስጥ ሌሊቱንም ሆነ ቀን ራሱን በቻለ የተጠናከረ የድሮን ዋርድያ ጥበቃ እንዲያሳልፍ እናሳስባለን፡፡ ከጥንቃቄ ጉድለት የሚያጋጥሙ ጉዳቶችን እንቀንስ ብሏል ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ደለለ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ም/ሰብሳቢና ጦር አዛዥ።
1🙏1
በፋሽስቱ ኦህዴድ ብልፅግና ወረራ ምክንያት በአማራ ምድር ሰብዐዊ እርዳታን ማድረስ አልተቻለም

በፀጥታ ችግር እና ውስን ተደራሽነት ምክንያት በአማራ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎች እየተስተጓጎሉ ነው_ የዓለም ምግብ ፕሮግራም

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በአማራ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎች በቀጠለው አካባቢያዊ የመንግስት ዘመቻ ምክንያት ፀጥታ ችግርና የተደራሽነት ውስንነት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የሎጂስቲክስ ፈተናዎች እየገጠሙት መሆኑን አስታወቀ።

ድርጅቱ አማራ ክልልን በተመለከተ ባወጣው የሥራ ሁኔታ ግምገማ ሪፖርት፣ በተለይም በ #መተማ እና በ #ምሥራቅ_አማራ አካባቢዎች ያለው በመንግስት ወታደሮች የሚመራው የጸጥታ ችግር የዕርዳታ አቅርቦቶችን ትራንስፖርት በእጅጉ እያዘገየ መሆኑን ጠቁሟል።

ሪፖርቱ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የንግድ ትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት መኖሩን በመጥቀስ፣ ለተቸገሩ ማኅበረሰቦች ዕርዳታ በወቅቱ እንዳይደርስ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን አስረድቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ምንም እንኳ እነዚህ ገደቦች ቢኖሩም፣ የሎጂስቲክስ ክላስተር በግጭት ባለበት ክልል ውስጥ የሰብዓዊ አጋሮች ሥራቸውን መቀጠል እንዲችሉ ትራንስፖርትን፣ ማከማቻን እና ቅንጅትን ጨምሮ የጋራ አገልግሎቶችን ማቅረቡን መቀጠሉን ገልጿል።

@ሞዐ ሚዲያ
3💔1
የአረመኔዉ አገዛዝ ሰራዊት እየፈራሰ ይገኛል!!!

የብልጽግና መራሹ መንግስት አማራን የማጥፋት የሴራ ዘመቻ የተረዱ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እየከዱ ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

በቀን 13/02/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴዎድሮስ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር አባይ መተከል ብርጌድን የተቀላቀሉ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ዝርዝር:-
1.ይልቃል ጓዱ= አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
2.ተመስገን ጓዱ=አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
3.አገር ሰላም=አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
4.አዝመራዉ ገኔ=አድማ በትን=ከዱርቤቴ የወጣ
5.እንደሻው አቤ=ሚሊሻ ከወርቅ ሜዳ የወጣ
6.ቢሻዉ አይኔለም= ሚሊሻ ከወርቅ ሜዳ የወጣ
7.ንጉሴ መልኩ= ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
8.ተሾመ ታመነ=ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
9.አከለ ሞገስ= ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
10.እንግዳዉ ዘሪሁን=አድማ በትን ወርቅ ሀገር ላይ የተማረከ
11.እምቢአለ አከለ=ሚሊሻ ከፓዊ መንንደር 24
12.ትርፌ ተባረክ= ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24
13.ሙሉ ታዴ  = ሚሊሻ ከፓዊ መንደር 24 
14.አስር አለቃ ትዕዛዙ= መከላከያ የ4ኛ ክ/ጦር ሰንጥቅ ልዩ ተወርዋሪ ሻለቃን የተቀላቀለ
15.አስር አለቃ ታደሰ -መከላከያ =የ4ኛ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ሰንጥቅ ሻለቃን የተቀላቀለ
16.አስር አለቃ አስማማዉእጅጉ= ከጃዊ በመዉጣት በላይ ዘለቀ ብርጌድን የተቀላቀለ

በሌላ ዜና በዛሬዉ እለት በ15/02/2018 ዓ.ም የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ ያጣዉ የአረመኔዉ የአገዛዙ መንግስት ጀኔራሎችን እና ኮለኔሎችን  በመያዝ የክልል እና የዞን አመራርን ጨምሮ ከ14 በላይ ፓትሮል እና 3 ኦራል  መኪና የጠላት ኃይል በመያዝ ከፓዊ ወደ ወርቅ ሜዳ ከተማ በመግባት ስብሰባ ለማካሄድ የሞከረ ቢሆንም ይህ መረጃ ቀድሞ የደረሳቸዉ የ4ኛ ክ/ጦር ነበልባሎቹ የአባይ መተከል ብርጌድ የፋኖ አባላት ወደ ወርቅ ሜዳ ሰርገዉ በመግባት በአራቱም አቅጣጫ  ጎሌ ካሜፕ፣ ሀይስኩል ት/ቤት ካምፕ፣ ጁኒየር ት/ቤት ካምፕ በከፈቱት መብረቃዊ ጥቃት ቦቅቧቃዉ የብልፅግና አመራር ስብሰባዉን ሳይጀምር መከረኛዉን እግረኛ ሰራዊት አጋፍጦት ፈጣሪ ሆይ አዉጣኝ በማለት ወደ መጣበት ፓዊ ከተማ ፈርጥጧል።

"አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ"

ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ኃላፊ
4🙏1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

ሰበር የድል ዜና!!!

በዛሬው እለት በምዕራብ ጎንደር ሽንፋ የመሸገው የአገዛዙ ጥምር ሀይል ክፉኛ እየተቀጠቀጠ ይገኛል።

በአርበኛ ባበይ የሚመራው መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ካራማራ ክ/ጦ በዚሁ እለት በሽንፋ ከተማ ከንጋቱ 11:00 ጀምሮ ወደ ጠላት ምሽግ በመጠጋት በአይበገሬዎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች ብርቱ ክንድ እያረፈባቸው እስካሁኑ 2:00 ስዓት ድረስ 2ምሽግ በማስለቀቅ እያበራዩት ይገኛሉ።

ዝርዝር የውጊያውን ድል ቀጣይ የምናሳውቅ ሲሆን አውደ ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥቅምት 16/2018
4🙏3
ሰበር....
"አቸፈር ወንድየ ያ ግድም ያ ግድም፡
ተኳሹ ብዙ ነው አያረማምድም"

ፋኖ በዱር ቤቴ ከተማ ዘልቆ በመግባት 18 የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ወታደሮችን ሲገድል 25 የጦር መሣሪያም ማርኮ መታጠቁን አስታወቀ!

በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ስር የሚገኘው አቤ ጉበኛ ብርጌድ አቸፈር ዱርቤቴ ከተማ ውስጥ በመግባት በወሰደው እርምጃ 18 የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን መረብ ሚዲያ ከክ/ጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።

በጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ስር የሚገኙት የአቤ ጉበኛ ብርጌድ አባላት ዛሬ ጥቅምት 16/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ ወደ አቸፈር ዱርቤቴ ከተማ ዘልቀው በመግባት የጡት ቆራጩ ብልፅግና ቡድን ኃይል ላይ ከባድ ጥቃት በመሰንዘር ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል።

በዚህ ኦፕሬሽን እራሳቸውን "የመከላከያ ሰራዊት" ብለው የሚጠሩ 10 ወታደሮችንና ስምንት የበአዴን እግር አጣቢ የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ በድምሩ 18 የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪዎች ሲገደሉ፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸውን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በኦፕሬሽኑ ሙትና ቁስለኛ ከተደረጉት የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ወታደሮች በተጨማሪ፡ 20 ክላሽንኮቭ፣ አምስት ኤስኪ መሣሪያ እና 350 የክላሽ ተተኳሽ በፋኖ መማረኩ ነው የተነገረው።
 
በተጨማሪም በውጊያው፡ ሁለት የጠላት ወታደራዊ ፒካፕ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
🙏1
1/ የደጅአዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ በ2ቦታዋች ላይ ጥቃት ፈፀመ።
፨አፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር ደጅአዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ ሻለቃ ሁለት ጥቅምት 15ለ16 ከምሽቱ 2:00 በደብረ ማርቆስ ከተማ በተለምዶ የጁቤ መገንጠያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መኮረኒ ፋብሪካው ላይ መሽጎ በሚገኘው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ላይ በቦንብና በብሬን የታገዘ ውጊያ አድርገዋል።
፨በዚህ ውጊያ ዋርድያውን እና ተጨማሪ 5 የአረመኔው አሽከር ወዲያውኑ ሲደመሰሱ 7 ቁስለኛ ሆኗል።
፨በዚሁ ምሽት መኮረኒ ፋብሪካው ላይ ጥቃት ፈፅማ የተመለሰችው ሻለቃ 2 ዳግም ከሌሊቱ 7ሰዓት አምበር ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በነበረው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ላይ በተፈፀመ ማጥቃት ዋርድያው ወዲያውኑ ሲሸኝ 3 የአረመኔው አሽከሮች ቁስለኛ ሆኗል።
ውጊያውን ፋኖ ምትኩ ሽፈራው በብቃት መርቶታል።
💪💪💪
2/ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር አቤ ጉበኛ ብርጌድ አቸፈር #ዱርቤቴ ከተማን በመቆጣጠር ታላቅ ጀብድ ፈፅሟል ።

ጀብደኛዉ ክ/ጦር አቸፈር ወንድዬ ዱርቤቴ ላይ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ፣አድማ ብተና፣ጡት ቆራጩን የአረመኔዉ አገዛዝ እንደ ጉድ ተወቅቷል።

የዛሬዉ ይለያል
አቸፈር ወንድዬ ያ ግድም ያ ግድም
ተኳሹ ብዙ ነዉ አያረማምድም

በዛሬዉ አዉደ ዉጊያ

በዛሬው ዕለት በነበልባሎቹ የአቤ ጉበኛ ልጆች ዱርቤቴ ከተማን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት

_ 8 ተላላኪ ሚሊሻ ወደ ላይ የተሸኜ ሲሆን
_ 10 የአብይ ዙፋን አስጠባቂ የኦሮሞ ልዬ ሀይል በተመሳሳይ ወደ ላይ ተሸኝቷል ።
_የቁስለኛ ቁጥር በዉል አይታወቅም በዚህ ሰዓት የዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቁስለኛ ተጨናንቋል ።

ምርኮን በተመለከተ በዛሬው ዕለት 16/02/2018
_ 20_ ክላሽ መሳሪያ
_ 5_ sks መሳሪያ
_ 350_ የክላሽ ጥይት
_ 2_ ፓትሮል ፒካፕ መኪና የተቃጠሉ ሲሆን በአጠቃላይ በአገዛዙ የአብይ ተላላኪ ቡድን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ና ቁሳዊ ኪሳራ ጭምር አድርሷል።
3🙏1
ሰበር ዜና!

አንሻ ክፍለ ጦር በዛሬው እለት መቄት አርቢት ራስ ደጀን በሚባል ቦታ ላይ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል ሰሩ።

ጥላት ከኮን እስከ ጋሸና ያለ የለለውን ሰራዊት በመካናይዝድ ደረጃ ሰብስቦ ወደ መቄት ሰብሮ ለመግባት ከአንሻ ክፍለ ጦር ጋር ከባድ ውጊያ ያደረገው የፋሽስቱ ሰራዊት በአናብስቶቹ አንሻ ክፍለ ጦር ባግባቡ ተመክቶ በመልሶ ማጥቃት ተመትቶ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ጋሸና ፈርጥጧል።

አይደፌሬዎቹ አንሻ ክፍለጦር በአርበኛ ጨለፍ ተስፋው እየተመሩ የጥላትን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ የፋሽስቱን ሰራዊት ታሪክ አድርገዋቸዋል። ከጨጭሆ እስከ ጋሸና አፍንጫ ጥግ ድረስ አደረጃጀታቸውን ዘርግተው የጥላትን ሰራዊት እያጓለሉት የሚገኙት እነዚህ የአናብስት ስብስቦች አኩሪ ታሪክን በመስራት የአብይን መካናይዝድ ሰራዊት ሰባብረውታል ገሚሱ ሙት ሌላው ቁስለኛ ከነዚህ የተረፈው ፈርጥጧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
🙏1
የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ጭፍጨፋ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ቀጥሏል::

በዚህ ሶስት ቀን ውስጥ በተደረገ ጦርነት ቤተ አምሓራ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር የአገዛዙን የሻለቃ ምክትል አዛዥ ወደማይቀረው ቤቱ ሸኝታዋልች። ከዚህ ቀደም ሀሙሲት በተባለ ቦታ መራር ብትርን የተመታው የአብይ አህመድ ተከፋይ ሰራዊት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ፤ ምክትል አዛዡ ቁስለኛ ሆኖ ወደ ህክምና በፓትሮል የተወሰደ ቢሆንም በትናንትናው እለት የተከፋይነት ተግባሩን ተሰናብቶ ወዴ ሲዖል ገስግሷል።

ይህ የመረረ የፋኖ በትር ያበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን ኢላማ አድርጎ ከረፋዱ ጀምሮ ይህ ዜና አየር ላይ እስከዋለበት ጊዜ ድረስ የሞርተር ድብደባ በንፁሀን ላይ ሲፈፅም ውሏል።

በዚህም ፀያፍ ተግባሩ ደላንታ ወረዳ ተበኮ ቆላ በተባለ ቦታ ላይ በሞርተር የሁለት ንፁሀን ግለሰቦች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሶባቸው ሆስፒታል ህክምና ገብተዋል።

በሌላ ተመሳሳይ ድርጊት ከቆቦ ከተማ ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተጠመደ መድፍ ወደ ራያ ቆቦ ድንጋይ ቀበሌ ድብደባ በመፈፀም ሁለት ባልና ሚስት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ቤትና ንብረት አውድሟል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
🙏1
የበረሀዋ አናብስት ዛምብራ ብርጌድ ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ስር የሚገኜው የበረሀው አናብስት ዛምብራ ብርጌድ በደጀን ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በዛሬው እለት በደጀን ወረዳ ሙዣን ተዝካረማሪያም ቀበሌ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ጥልቅ ውይይት አካሂዶል። በውይይቱ መድረኩ የአማራ ህዝብ ከአረመኔው አገዛዝ ጋር እያካሄደ ያለው የህልውና ትግል በተመለከተ እንዲሁም የአብይ አህመድ አረመኔዊ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን አረመኔዊ ድርጊት በውይይት መድርኩ ለተገኙ የማህበረሰብ ክፍል የዛምበረሃ ብርጌድ አመራሮች ሰፋ ያለ ግንዛቤ ሰተዋል።

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!

ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
2🙏1