ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በደብረማርቆስ  ከተማ ውስጥ የአድማ ብተና አዛዡን  ኢላማ ያደረገ  ጥቃት ሲፈፀም ፖዊ ፖሊስ ጣቢያው ላይም ጥቃት ተፈፅሟል።

በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ደብረ ማርቆስ ወንቃ አካባቢ በሁለት ፖትሮል ላይ ሆነው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም የአድማ ብተና  አዛዥ ኢንስፔክተር እንዳለው አላምርን  ጨምሮ በርካታ ፖሊሶችን ማቁሰልና መደምሰስ ተችሏል። ሁለቱን ፖትሮሎችም  በተካሄደው ማጥቃት ከጥቅም ውጪ ማድረግ ተችሏል።

እኒህ ፖሊሶች ማታ ማታ  ጨለማን ተገን አድርገው የደብረማርቆስ እና አካባቢውን ማህበረሰብ ስልክና ገንዘብ የሚዘርፉ፣ የሚደበደቡና የሕዝብን ጥቅም አሳልፈው የሰጡ  እና ሆዳቸው በሕዝብ ገንዘብ የሞሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችለናል።

በትናንትናው ዕለት  ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር አባይ መተከል ብርጌድ የፋኖ አባላት መተከል አዉራጃ ወደ ፓዊ ከተማ ሰርገዉ በመግባት በጠላት ላይ ኪሳራ አድርሰዋል።

ተወርዋሪ ኮከቦቹ ፓዊ ከተማ በመግባት ፖሊስ ጣቢያው ላይ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት በርካታ የአብይ ተላላኪ ፖሊሶችን መግደል እና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።

በተመሳሳይ በትናንተናው ዕለት  አስር ዓለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ችጓሊ ከተማን ተቆጣጥረዋል።

ችጓሊ ከተማ የሚገኘዉን የአረመኔዉን ጡት ቆራጭ ካንፕ ሙሉ በሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር  የጠላትን ሎጅስቲክ ሙሉ በሙሉ መማረክ የተቻለ ሲሆን ቀንደኛ የስርዓቱ የጭን ገረድ ባንዳ በቁጥጥር ስር ዉሏል።ብዛት ያለዉ  አድማ ብተና እና ሚሊሻ መደምሰስና ማቁሰል ተችሏል።
ፎቶ  :- ኢንስፔክተር እንዳለው አላምር የ4ኛ ፖሊስ ጣቢያ አድማ መከላከል አዛዥ  ቆስሎ ደብርማርቆስ ሆስፒታል የሚገኝ።
1👍1
ሰበር ዜና!

ከበረኸት ወረዳ መተህ ብላ ከተማ ደብረብርሃን ሄዳ ሽልማት መቀበል ላልቻለችው  ቀፀላ ተገኑ የተላከ የሽልማት ቁሳቁስ በፋኖ የመረጃና ደህንነት ሰዎች ቁጥጥር ስር ዋለ።

በወ/ሮ ሰዓዳ ኢብራሒም (ጀማነሽ) የሰ/ሸዋ ዞን ብልግና ፖርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና በወ/ሮ  የሮምነሽ ጋሻውጠና የሰ/ሸዋ ዞን የሴ/ህ/ጉ መምሪያ ኃላፊ ተፈርሞ የወጣ የምስክር ወረቀትና ጋቢ መነሻዉን ከደብረ ብርሃን መድረሻውን በረኸት  ወረኸት ወረዳ መተህ ብላ ከተማ ባደረገ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ መኪና  ተጭኖ  በመንቀሳቀስ ላይ እያለ አክርሚት በተባለ ቦታ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክ/ጦር ተስፋ ብርጌድ የመረጃና ደህንነት ሰዎችና የብርጌዱ ከፍተኛ አመራሮች  ቁጥጥር ስር ዉሏል።

እንደ አይጥ ከጎሬያቸዉ መዉጣት ያልቻሉት እና ደብረ ብርሃን ሄደዉ ስብሰባም ሆነ ሌሎች ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ያልቻሉት የወረዳዉ ካድሬዎች ወደ ወረዳዉ በቀላሉ መግባትም ሆነ መዉጣት እንደማይቻል የተረዱት መካሻ አለማየሁ፣ሰአዳ ኢብራሂም እና መሰሎቻቸዉ የሰ/ሸዋ  ዞን አመራሮች ምንም አይነት ስራ ባልሰሩበት በሀሰት ሪፖርት እራሳቸዉን እያረኩ በርቀት መመሰጋገኑን ቀጥለውበታል።

በወቅቱ እቃዉ ከቦታዉ ሲንቀሳቀስ ቀድሞ መረጃ የነበራቸዉ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ እዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ብርጌድ የመረጃና ደህንነት ባለሙያዎችና  አመራሮች  ጥብቅ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዉ ያለምንም በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል።
       
መረጃዎን ያደረሰን አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም  ሪፖርተር ነው።

       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
‎የአፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
‎   
   ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም
1👍1
አገዛዙ ብልፅግና በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የድሮን ቅኝት አሰሳ ሲያደርግ ዉሏል።

ዛሬ ጥቅምት 14/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በደብረ ማርቆስ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አከባቢዎችን ጨምሮ በጅጋ ከተማና በአከባቢው፣ በሆዳንሽ፣ በፍኖተሰላም ዙሪ፣በቡሬ ባህርዳር ዙሪያ በሚገኙ ገጠራማ መንደሮች፣ በቲሊሊ ከተማና በአከባቢው፣ በደበምጫ ወረዳ ዋድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢና በሌሎች የምዕራብ አማራ ቀጠናዎች ላይ ተከታታይ የሆነ የድሮን ቅኝት ሲያደርግ ዉሏል።

በጎንደር ጉና ተራራ እና አካባቢ፣በእብናት እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማክሰኝት እና አካባቢው የድሮን አሰሳ ሲደረግ ዉሏል።

ጡት ቆራጩና ኦህዴድ መሩ የብልፅግና አገዛዝ ሰሞኑን በባህርዳር ዙሪያ አንድ የገጠር ቀበሌ ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት ተሰባስበው የመጠጥ ውሃ ሲቀዱ የነበሩ እናቶች ላይ በፈፀመዉ የድሮን ጥቃት ህይወታቸዉ ማለፉ መዘገባችን ይታወሳል።ትናንት ደግሞ በደቡብ ጎንደር ጋይንት ዛጎች በፈፀመዉ የድሮን ጥቃት አንድ የ70 አመት አዛዉንት እና እናት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጡት ቆራጩና ነውረኛው የዐብይ አህመድ ቡድን፡ ለገበያም ሆነ ውሃ ለመቅዳት፣ ወፍጮ ቤትም ሆነ ቤተ ክርስቲያን ወይም መስጂድ ላይ ሰዎች ተሰብስበው ካየ የድሮን ጥቃት ሊፈፅም ስለሚችል፡ ማሕበረሰቡ ለጥቃት ከሚያጋልጡ ድርጊቶች በመቆጠብ እራሱን መጠበቅ እንደሚገባው ተጠቁሟል።
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማ ላይ ድል ተቀዳጅቷል።

አንጋፋው ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ሰሃት ቲሊሊ ከተማን በመቆጣጠር ጡት ቆራጭ የሆነዉን ወንበዴ ቡድን ላይ በወረደዉ እርምጃ በርካታ የአገዛዙ ጥምር ጦር ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዷል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቲዎድሮስ ዕዝ ሶስተኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለጦር
#ቲሊሊ_ዘንገና_ብርጌድ
#ግዮን_ብርጌድ
#ቀኝ_አዝማች_ስሜነህ_ደስታ_እንጅባራ_ብርጌድ እና
#ቢትወደድ መንገሻ_ጀምበሬ ብርጌድ
#፲_አለቃ_ኤፍሬም_አጥናፉ_ብርጌድእና
#ቡያ_ሻለቃ በተሳተፉበት ዉጊያ የጠላትን ሀይል ብትንትኑን በማዉጣት ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ችለዋል።

በመሸጉበት የቲሊሊ 1ኛ ደረጃ ህብረት የትምህርት ቤት ካምፕ ላይ በሞርተር ሲደበደብ ካምፑን ለቀዉ በመሮጥ እንደ ቀበሮ በማሱት ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረዉ ህይታቸው ሲያተርፉ፤ ከመሃል ከተማ እስከ ጅባይታ በተዘረጋው የእጅ በእጅ ውጊያ ጠላት ላይ ከፍተኛ ምት በማሳረፍ ቅስሙን መስበር ተችሏል።

ይህንንም ተከትሎ ከእንጅባራ እየተግተለተለ የመጣው ሀይል ሽፋን ሆኖ ሊያተርፍ ቢሞክርም ቺማ ስላሴ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ ሲገረፍ አርፍዷል።

ለሶስት ሰሃታት በዘለቀው አውደ ውጊያ ከ20 በላይ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ተወግዶ ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሃይል ቁስለኛ ሁኗል።
1👍1🙏1
ሰበር ‼️
የ ሸዋሮቢት ፀጥታ እና ደህንነት በመሆን የምድርን ሲዖል ለህዝባችን ሲያሳይ የነበረዉ ወደል ባንዳ ለማ ወንዳፈራዉ ተሸኝትዋል ‼️
7🙏2
የአብይ አህመድ ሰራዊት በአርሶአደሮች ላይ ጥቃት ፈፀመ!!

ጥቅምት 13 / 2 / 2018 አሸባሪው የአብይ ሰራዊት ከደብረታቦር ከተማ አቅራቢያ መገንዲ ቀበሌ ገበሬውን መሳሪያ አምጡ በማለት አስገድዶ ለመቀማት ሙከራ አድርጓል።

አርሶአደሩ በብስጭት ተኩስ በመክፈት ደፈርሻ ወርቅነህ የተባለ ገበሬ 1መከላከያ በመግደል 1አንድ ደግሞ በማቁሰል እራሱን ሰዉቷል። አብራ የነበረችው የጀግናው አርሶአደር ልጅ ዝናሽ ደፈርሻ የአባቷን መሳሪያ አንስታ የአገዛዙን ጥምር ጦር በመፋለም የአባቷን መሳሪያ ይዛ አምልጣለች።

መረጃው የጉና ክ\ፍ ጦር ሚዲያ ክፍል ነው።

በዝርዝር እንመለስበታለን!!!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
3
ሰበር ዜና!

ፅናት ክፍለ ጦር የፋሽስቱን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::


በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣው የሽመልስ አብደሳ ጭራቅ ሰራዊት በደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ ልዩ ስሙ ሀሙሲት በሚባል ቦታ ላይ እምሽክ ተደርጎ ተበልቷል። ስልታዊ ስበት በማድረግ የጥላትን ሰራዊት ወደ ሞት ምድብ ስቦ በማስገባት ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ተሸኝተዋል።
ከ9:30 እስከ 12:30 ድረስ ጦርነቱ የዘለቀ ነበር።

በዚህ ሁኔታ የጥላት ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ መሬት በግስላዎቹ ነፍጥ እየተፈለፈለ የረገፈ ሲሆን፤ ከፊቱ የሚነጠፈውን ጓዱን የተመለከተ ጥላት ለተዎሰነ ሰዓት ባለበት ቁሞ ሞደስ ናፈቀኝ እሮሮውን ቢያላዝንም ግስላው ፋኖ ወደ ፊት በማጥቃት ከሞደስ ናፍቆት ወደ ማይቀረው ሲዖል ተሸኝቷል። "አንድ ጥይት ለአንድ ጥላት" በሚል የአማራ ብሂል ለአንድ ጥላት በአንድ ጥይት ግንባር ግባሩን ተበርጭሷል።

በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ያስተናገደው የሽመልስ አብደሳ ሰራዊት የሞራል ውድቀት፤የቁስ ክስረትን አስተናግዷል።
አገዛዙ ክፉኛ የቆሰለውን ሰራዊቱን በፓትሮል ወደ ወገልጤና ጤና ጣቢያ እያጋዘ አምሽቷል።
ድሉ እደቀጠለ ነው! ዝርዝሩን እንመለስበታለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የፅናት ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ጥቅምት 14/2081 ዓ/ም
🙏3
አገዛዙ ዛሬም ትምህርት ቤቶችን በድሮን እያወደማቸው ነው!

በአፋብኅ ምዕ.አ.ቀ.ቴ.ዕዝ 2ተኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ያሉ የቀበሌ ትምህርት ቤቶችን መንግስት በድሮን እያወደማቸው ይገኛል።

ፋኖ ለተተኪው ትውልድ በማሰብ ትምህርት ቤቶችን ለቆ ለካምፕነት የማይጠቀም ቢሆንም ምንም አይነት ፋኖ በሌለበት የሸበሌ ትምህርት ቤትን ፋኖን አገኛለሁ በሚል ቅዥት በድሮን አፈራርሶ አማራን በህይወትም በንብረትም ሊያጠፋ መምጣቱን በይፋ አረጋግጧል።

መንግስት ተብዮው በአንድ በኩል ትምህርት ይጀመር እያለ ፋኖን በየወረዳወች እየጠየቀ በሌላ በኩል ደግሞ የትምህርት ተቋማትን በድሮን የማፍረሱ ድራማው ፋኖ ህፃናትን መንግስት በቀላልና በከባድ መሳሪያ አውድሟቸዋል፤ እያወደማቸው ይገኛል።

በዚህ የድሮን ጥቃት  ምንም ፋኖ በአካባቢው ባይኖርም የትምህርት ቤቱን ሳር ለከብት የሚያጭዱና ጤፍ አጨዳ ለቀን ስራ የሄዱ ሶስት ንፁሀን ተሰውተዋል።

ከዚህ በፊት በጎንጅ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ላይ ድሮን ተጥሎ ንፁሀን መቁሰላቸውና ላብራቶሪ ክፍሉ ሙሉ በሙሉ የህዝቡ ንብረት መውደሙ ይታወሳል ሲል የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ገልጿል።
💔21🔥1
............. የአደረጃጀት ዜና !! .............

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የ54ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

በዚህም አዲስ ተዋቅሮ የተጠናቀቀው 54ኛ ክፍለጦር በቀደመው አደረጃጀት የመብረቁ ተፈራ ብርጌድ ፣ የመዝገበ ጮቄ ብርጌድ እና መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድን ያካተተ ሆኖ ተመስርቷል ።

ክፍለጦሩ በአምስት ሬጅመንቶች የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሬጅመንቶች አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።

የክፍሐጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በዕዙ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ማርሸት ፀሐው ደምሴ ፣ በዕዙ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ይትባረክ አንዳርጌ እና በዕዙ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን አስተባባሪነት ተጠናቋል ።

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
👍41🙏1