ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአፍብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ

የደጋው መብረቅ ክ/ጦር ከፋሽስቱ አብይ አህመድ ወታደር ጋር በተደረገ ወጊያ የፍሽስቱን ወታደር ወደ መግደያ ወረዳ ስቦ በማስገባት በርካታ ሃይሉን በመምታት ታላቅ ጀብድ ፈፅሞ ድል ተጎናፀፈ::

ትናትና ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ ያላሰበው ድብደባ የደረሰብት የብርሀኑ ጁላ ሰራዊትም ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ ሲፈረጥጥ የነበረበትን ፓትሮልም በክንደ ብርቱዎቹ አነጣጥሮ ተኳሾች ተመቶ ወድሟል። ምንም እንኳን የሚሰራውና የሚያደርገው ቢያጣ ይህ ዘረ ጨፍጫፊ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲፈረጥጥ ከፊቱ ያገኘውን የጋማ ከብቶችን ሳይቀር እየገደለ ነበር።

ከዚህ ጋር ተያይዞም እንስሶችን በጥይት በመደብደብ አፀያፊ ተግባር የፈፀመ ሲሆን በርካታ እንስሶችን ገድሏል።ይህ አፀያፊ ተግባሩ አልበቃው ያለው ሽመልስ አብደሳ ከፍቶ የለቀቀው አማራ ጠል ሰራዊት በጋዞ ወረዳ ሸራገነት ጤና ጣቢያ በመግባት የህሙማን መገልገያ የሆኑ ቁሳቁሶችን፣
መድሃኒት፣ ስትሬቸር፣ ዊልቸር እና ሞተር ዘርፎ የአካባቢውን ማህበረሰብ የህክምና ተቋም አውድሟል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ጥቅምት 13/2018 አ.ም
1😁1
ሰሞኑን የውቤ ልጆች ከፍተኛ ድል በተቀዳጁበት በእስቴ ቀጠና ከተማረከው የጦር መሣሪያ መካከል ጥቂቱ።

በአፋብኃ አርበኛ በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ስር የሚገኙት የጉና ክፍለጦር አናብስቱ ጥቅምት 09/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በእስቴ መካነየሱስ ቀጠና በነበሩ የጡት ቆራጩ ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሳቸውን መረብ ሚዲያ መዘገቡ አይዘነጋም።

ይህ የምታዩት ምስል በጉና ክ/ጦር እስቴ ዴንሣ ብርጌድ ስር በምትገኝ በአንዲት ሻለቃ የተማረከ ሁለት ብሬንና አስራ አምስት ክላሽ ነው። ቀሪዎቹ በክ/ጦሩ ስር የሚገኙ ሻለቃዎች የማረኩትን የመሣሪያ አይነትና ብዛት ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
🙏32👎2
Operation Aba Nadew: A Triumph For Humanity!
Fano Abebe Fentaw,
Head Of Public Relations, AFNF Menelik Command
በውርጌሳ የተማረኩ የደቡብ ዕዝ 35ኛ ዋልያ ክፍለ ጦር አባላት በልጅ እያሱ ኮር በተደረገላቸው እንክብካቤ እና የፖለቲካ ግንባታ በመደሰት እና በቁጭት ለአማራነታችን እንታገላለን በማለት ትግሉን ተቀላቀሉ፦

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር በቀን 08/02/2018 ዓም በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ በውርጌሳ ከተማ በተካሄደ ውጊያ ለተማረኩ የ35ኛ ዋልያ ክፍለ ጦር አባላት ላይ ዛሬ ማለትም በቀን 13/02/2018 ዓም የአማራ ህዝብ የትግል መነሻ እና አሁን የደረሰበት አጠቃላይ ቁመና በኮምፒውተር በተደገፈ እና በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ መዋቀራዊ የዘር ማፅዳት ለማሳየት ሙከራ ተደርጎል፡፡

በመሆኑም የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የከረሙት በቄለም ወለጋ አካባቢ በመሆናቸው በአማራው ላይ ሲሰራ የነበረውን ደባ በአይን እናየው ስለነበር እኛም መውጫ አጥተን እንጂ የመከላከያው ተቋሙ ራሱ አማራ ጠል መሆኑን በተደጋጋሚ ጊዜ በትናንሽ ጥፋት በግፍ በተረሸኑ ጓዶቻችን የተማርንበት ቢሆንም ጥለን ለመውጣት መውጫ ቀዳዳ ስንናፍቅ እንደነበረ እና ፈጣሪ ፈቅዶ ዛሬ ከእናንተ ጋር አገናኝቶናል ሲሉ በደስታ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በመላው አማራ እየተደረገ ባለው ሰፊ አውደ ውጊያ ምክንያት ወደ ቤተሰብ የሚያስኬደን ምንም ምቹ ሁኔታ ስለሌለ የልጅ እያሱ ኮር አባል በመሆን ከወንድሞቻችን ጋር ለአማራነታችን እስከ መጨረሻው እንታገላለን በማለት ሠራዊቱን ተቀላቅለዋል፡፡

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የልጅ እያሱ ኮር ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ
ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም
🙏1
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የመቄት ወረዳ ጊዜያዊ የሲቭል አስተዳር መዋቅር ዘረጋ::

በወረዳው ያሉትን 36 ቀበሌዎች በሶስት ንዑስ ወረዳዎች በማዋቀር እና በቀጠናው የሚገኙ የፋኖ ሀይሎችን ስንቅና ትጥቅ በሟላተ እንዲሁም የወረዳውን ሕዝብ የፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮችን በበላይነት የሚመራ ሰባት (7) አብይ ኮሚቴዎችን ማዋቀር ተችሏል።

1ኛ ዋና አስተዳደር .... መ/ር በሪሁን ደምሌ
2ኛ ም/አስተዳደር .. 50 አለቃ መንግስቱ ካሳ
3ኛ ሰላምና ደህነት ... ወታደር መንግስቱ ያለው
4ኛ ፖለቲካ ዘርፍ ....ጌታሁን ባዬ
5ኛ ማህበራዊ ዘርፍ ... ወታደር አዳነ መንግስቴ
6ኛ ፋይናስ ኃላፊ ...... ቢራራ ፀጋነው
7ኛ ሎጅስቲክ ኃላፊ .... ሳሙኤል አያሌው

ማስታወሻ:-
ከላይ በአብይ ኮሜቴነት በተቀመጡት ስር የሚሟሉ ነገር ግን በዝርዝር ያልተቀመጡ ኮሚቴዎች በድርጅቱ የሲቭል መመሪያ መሰረት የሚሟሉ አሉ::

የንዑስ ወረዳ መዋቅሮችን በተመለከተ ከላይ የተቀመጠው አብይ ኮሚቴ የሚያደራጀው ሲሆን ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ የሚሰራ ይሆናል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ጥቅምት 13/2018 አ.ም
🙏1
ሰበር ዜና!

በሻለቃ ሀብቴ እባቡ (አባ መቻል) የምትመራው
የድል በር ከፋች የሆነችው የአፋብሀ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ክፍለ ጦር በተከታታይ አውደ ውጊያን እያደረገች ድል እያሰመዘገበች ትገኛለች።

በዛሬው እለት ማለትም ጥቅምት 13/2018 ዓ /ም በጋዞ ወረዳ እስታይሽ ከተማ ላይ ባደረገችው አውደ ውጊያ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት መደምሰስ ሲቻል
በዚሁ ፋኖዎች ከጥላት ነፃ ባዎጡት ቦታ ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ ሁለት(2) የመከላከያ ሰራዊቶች ልብሳቸውን ቀይረው ተገኝተዋል። ስምንት (8) ክላሽ በምርኮ ሲገኝ ከሶስት መቶ (300 )በላይ ተተኳሽ መማረክ ተችሏል።

ከፋኖዎቹ የደረሰበት መራር በትር ቁስለኞቹን ወዴ እስታይ ከተማ ጤና ጣቢያ ያስገባ ቢሆንም የእስታይሽ ጤና ጣቢያ ቁስለኞቹን ለማስተናገድ ከአቅም በላይ ስለሆነበት ወደ ወልድያ ሆስፒታል እያጓዘ ይገኛል። ከዚህ በታች በምስሉ ላይ የሚታዩት የገበሬ ልብስ ቀይረው ከግለሰብ ቤት ውስጥ ተደብቀው የተማረኩት የመከላከያ ሰራዊት ምስል ነው::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ
የደጋው መብረቅ ክፍለጦር ቃል አቀባይ የዶክተር መላኩ
ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም
🙏1