ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
Notice
አፋብኃ ለተባበሩት መንግስታት የሰባዊ መብት ኮሚሽን አብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን የጦር ወንጀል ትኩረት እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።
ከአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ሴቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ የተላለፈ መልዕክት!

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና የሚፈፅመው አሰቃቂ ግፍ የጀመርነውን የህልውና ትግል ለድል እንድናበቃ የበለጠ ቁርጠኛ እንድንሆን ያደርገናል እንጂ ላፍታም ቢሆን አያዘናጋንም!

እያደረግነው ባለው ሁሉን አቀፍ የህልውና ተጋድሎ በርካታ አመርቂ ድሎችን እያስመዘገብን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በአውደ ውጊያ የሚገጥምን የነበረ ያለና ወደፊትም የሚኖርን መቁሰልና መሰዋት ከሰብዓዊነት በወጣ መንገድ ለበቀልና ለአሰቃቂ ግፍ መስሪያ መጠቀሙ አለምን ያነጋገረ ህዝባችንና ሰራዊታችንን ያስቆጣ አሳፋሪ ተግባር ነው::

የህልውና አደጋ የተጋረጠበትን ህዝባችንን ለመታደግ በጀመርነው የትጥቅ ትግል እኛ ሴት የአማራ ልጆች የበኩላችንን ጉልህ ሚና እየተወጣን ያለን ሲሆን በትግላችን እየተንኮታኮተ ያለው ፋሽስቱና አገር አፍራሹ የብልፅግና አገዛዝ በአውደ ውጊያ የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ሲያቅተው የተሰው እህቶቻችን ላይ የፈፀመው ተግባር ብልፅግና የአውሬዎች ስብስብ መሆኑን በአለም አደባባይ ያሳየና ያስመሰከረ ነው::

በመሆኑም ሰሞኑን በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር አባል የሆነችው ፋኒት ትግስት ወዳጁ እንዲሁም ሌሎች አባሎቻችን ላይ የተፈፀመው ኢሰብአዊ ድርጊት የጀመርነውን የህልውና ትግል ዳር ከማድረስና ነፃነታችንን ከመጎናፀፍ የሚያግደንና ላፍታም ቢሆን ከአላማችን መሳካት ግስጋሴ የሚገታን እንዳልሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምኒልክ ዕዝ ሴቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ፋኒት ዚነት አደም የተላለፈ መልዕክት!
ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ አመራሮች ምርከኞችን ጉብኝት አደረጉ፦

በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ በውርጌሳ ከተማ በቀን 08/02/2018 ዓም በተደረገ ኦፕሬሽን የተማረኩ አዲስ የተቋቋመችው 11ኛ ዕዝ 35ኛ ዋሊያ ክፍለ ጦር አባላት እና በተንታ የተማረኩ ሚሊሾች ዛሬ በቀን 12/02/2018 ዓም በልጅ እያሱ ኮር ከፍተኛ አመራሮች እና በድርጅቱ አመራሮች ጉብኝት ተደረገላቸው።

በጉብኝቱም በዕለቱ ስለነበረው የውጊያ ውሎ እና በምርከኛ አያያዝ እንዲሁም በወቅታዊ የሃገሪቷ የፖለቲካ ጉዳይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን መከላከያ ውስጥ እያሉ ይነገራቸው የነበረው እና በፋኖ ተማርከው ከመጡ በኋላ በህዝቡም በሠራዊቱም በኮሩ አመራሮችም የተደረገላቸው እንክብከቤ እጅግ አስደሳች እና ያልጠበቅነው ነው በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ለጓዶቻቸው ያሉበቱ ሁኔታ እጅግ ሰላም እንደሆነ እና በአገኙት አጋጣሚ በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የፋኖ አደረጃጀት እጅ እየሰጡ ህይወታቸውን ቢያተርፉ መልካም ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ጥቅምት 12/2018 አ.ም
3🙏1
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ግንባር ልዩ ስሙ አካምባ የተባለ ቦታ ላይ በፈፀሙት የደፈጣ ትቃት ከ50 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆነ::

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ለወረራ የመጣውን የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ሰሞኑን በበርካታ ግንባሮች በሚደረጉ ተጋድሎዎች ከባድ ምት በማሳረፍ እያፈረሱት ይገኛሉ::

ከዚህ ጋር ተያይዞም ዛሬ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ረፋድ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ግንባር በተሽከርካሪ ይንቀሳቀስ የነበረ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ልዩ ስሙ አካምባ የተባለ ቦታ ላይ የደፍጣ ጥቃት በመፈፀም አንድ ኦራል ሰራዊት ሲሸሽ በመገልበጥ እና በጥቃቱ አጠቃላይ ከ50 በላይ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::

ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም በነበረ ተጋድሎ አካምባ ላይ በተመሳሳይ አንድ በዲሽቃ የሚታጀብ ከፍተኛ አመራር ከሰባት አጃቢዎቹ ጋር ከነ ተሽከርካሪው በአሳምነው ክፍለጦር መካናይዝድ ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱ የሚታወቅ ነው::

በሌላኛው ተጋድሎ በተመሳሳይ ዕለት ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ጮቢ ግንባር ከፍተኛ የመከላከያ አመራርና የሬድዮ ኦፕሬተሮች በሐውጃኖ ክፍለጦር መካናይዝድ በሞርተር ጥቃት ሙሉለሙሉ ተደምስሰዋል::

ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ተኩለሽ ግንባር የዞብል አምባ ክፍለጦር መካናይዝድ ምሽግ የያዘ በርካታ የጠላት ሰራዊት ላይ ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ጥቅምት 12/2018 አ.ም
🙏5
ቀጥታ ስርጭት | የአብይ አህመድ የጦርነት ጉሰማና የአማራ ፋኖ የህልውና ትግል ግስጋሴ
ሰበር ዜና - ሰራዊቱ እየተናደ አለቀ | ከ 100 ሚንሻና አድማብተና ፋኖን ተቀላቀለ | ኮማንዶ ኃይሉ ኮበለለ - ጎጃም - ጎንደር - ድል ተበሰረ
🙏1
ከዓለም አቀፍ የአማራ ግብረኃይል የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

የአረመኔው የአብይ አህመድ ፋሽስት ሰራዊት በወጣት አርበኛ ሴቶቻችን ላይ የፈጸመውን የጭካኔ ጥግ መላው ዓለም ሊያውቀውና ሊያወግዘው ይገባል!!! ፋኒት በዓለም ዋሴ ፋኒት ትግስት ወዳጅ ይመር ፋኒት መቅደስ ተስፋዬ
የፋኖ አርበኞች የብልፅግና ሥልጣን አስጠባቂ ሰራዊትን ቁስለኛና ምርኮኛን በቅድሚያ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ አድርገው በምህረት ወደ የቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ አድርገዋል፡ እያደረጉም ነው። ምርኮኞች ቁጥራቸው በርከት ሲሉም ለዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ያስረክባሉ። የታወቀውን የዓለም አቀፍ ምርኮኛ አያያዝን ህግ ያከብራሉ። ይህ በፋኖ ዘንድ የተለመደ አሰራር ነው።

የ19 ዓመትዋ ወጣት በዓለም ዋሴ እንደማንኛውም ወጣት የራሷን ኑሮ አመቻችታ ተመሳስላ አስመስላ መኖር ትችል ነበር፤ ሆኖም ግን በአማራው ሕዝብ ላይ የሚደርሰው ሰቃይና መከራ፣ ሰደትና መፈናቀል፣ መገደልና መጨፍጨፍ አንገብግቧት ይህን አረመኔ የአብይ አህመድ ፋሽስት አገዛዝን ለመፋለምና ነጻነቷን ለማስከበር ቆርጣ ወስና የህልውና
ትግል ከሚያደርገው ፋኖ ጋር በአርበኝነት ተቀላቀለች። በፋኖም ውስጥ የመደበኛና የኮማንዶ ስልጠናዎችን ጨርሳ የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 5ኛ ክፍለ ጦር አባል ሆና ከሌሎች ጓዶቿ ጋር ለቅኝት ሰራ ተሰማርታ እያለ ድንገት በአረመኔው የአብይ አገዛዝ ወታደሮች ቀለበት ውስጥ ወደቀች። ጥቂት አርበኞች ሆነው የሚችሉትን ያህል ቢዋጉም የአብይ አህመድ ወታደሮች በርካታ ነበሩና ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም በጥይት ቆስላ ተማረከች።
የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ ወታደሮች ግን በጥላቻና በሰለጠኑበት የሃሰት ትርክት ስለሚመሩ ይህችን የ19 ዓመት ወጣት ፋኒት በዓለም ዋሴ ቆስላ ስትማረክ የፈጸሙባት ተግባር ግን ተሰምቶና ታይቶ የማያውቅ አስቃቂ የጭካኔ ጥግ ነው። ቁስለኛዋን ምርኮኛ ልብሷን አወላልቀው “አማራ” የሚለውን እጇ ላይ የተነቀሰችውን ንቅሳት በጩቤ ገፈው፤ ሁለቱንም ጡቶቿን በሳንጃ ቆራርጠው፣ መላ ሰውነቷን በሳንጃ ስለት ወጋግተው በኢሰብዓዊነትና እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ አስከሬኗን ማንኩሳ ከተማ መሀል አስፋልት ላይ ጥለው የአረመኔነታቸውን ጥግ ለሕዝብ አሳይተዋል። ይህ ነው የአብይ አህመድ ሰራዊት መለያ!

ከዚያ በፊት መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም በወገራ የበላይ ዘለቀ እዝ 3ኛ ኮር አምባራስ ክፍለ ጦር አባል የሆነችው አርበኛ ፋኒት መቅደስ ተስፋዬን በመግደል ሬሳዋን በመኪና በመጎተት አስፋልት ላይ ጥለው እንዳትቀበርም አስከሬኗን በጸሀይና በዝናብ እንዲበላሽ በማድረግ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም የአብይ ሰራዊት የተካነበትን የኢሰብዓዊ ባሕሪውን ለሕዝብ አሳይቷል።

ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ደግሞ በራያ በጮቢ በር ግንባር ተጋድሎ እያደረገች የተሰዋችው የምሥራቅ አማራ ኮር አንድ
ሀውጃኖ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው አርበኛ ፋኒት ትግሥት ወዳጅ ይመር ከአስከሬኗ ላይ አንደኛውን ጡቷን ቆርጦ እርቃኗን ሜዳ ላይ ጥሎ ሰቅጣጭና አረመኔያው ድርጊት የፈጸመው በጥላቻ የተሞላው የአብይ አህመድ ሰራዊት ነው።

አማራ ሆኖ በአማራው ላይ ይህንን የመሰለ የጭካኔ ተግባር ተፈጽሞ እያየንና እየሰማን ልባችንን አደንድነን መቀመጥ አለብን ወይ? ብለን መጠየቅና የህልውና ትግሉን በውስጥም በውጭም ያለን ሁሉ መርዳት ካልቻልን በእያንዳንዳችን ቤተሰብ ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል መገንዘብና ሁላችንም በጭንቀትና በተሰፋ መቁረጥ ከምንቀመጥ በምንችለው አቅምና መንገድ በተግባር የህልውና ትግሉን መደገፍና መርዳት ይኖርብናል። ይህን አስከፊ የጭካኔ ወንጀልንም መላው ዓለም እንዲያወቀውና እንዲያወግዘው ለተለያዩ የዜና አውታሮች ማድረስ፣ ለዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለመንግስታት፣ ለኮንግረስና ለፓርላማ አባላት በዘመቻ መልክ ማሳወቅ ይኖርብናል።

በወጣት የሴት አርበኞቻችን ፋኒት በዓለም ዋሴ፣ ፋኒት መቅደስ ተስፋዬና ፋኒት ትእግሥት ወዳጅ ይመር ላይ የደረሰው አስቃቂ አረመኔያዊ ተግባር የፈጸሙት ወንጀለኞችም በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ሰራ መሰራት ይኖርበታል።

በጀግንነት የተሰዉትን የነፋኒት በዓለም ዋሴንና ጓዶቿ ምስልና ታሪክ በሁላችንም ልብ ተቀርጾ እንዲቀመጥ በየአገሩ ያለን ሁሉ የተለያዩ የፈጠራ ሰራዎች በመስራት ለምሳሌ ምስሎቻቸው ያለበትን ቲሸርት በመልበስ፣ የሻማ ምሽቶች በማዘጋጀት በስማቸው ዝግጅት በማዘጋጀትና የመሳሰሉትን ቢያንስ ማከናወን ይኖርብናል።

የዚህ ፋሽስት ሰራዊት መሪ የሆነው የአብይ አህመድ አገዛዝን ዘመን እንዲያበቃ የማያቆም ዘመቻ መካሄድ ይኖርበታል።

በአገርም ሆነ በውጭው ዓለም የሕዝብን ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ በማስቀየር የዘረኛውና አረመኔው አብይ አህመድ
አገዛዝን እድሜ ለማስቀጠል ፕሮፓጋንዳ በመስራት የሚዳክሩ የሚዲያ ክፍሎች፣ የኢንቨስትመንት ደላላዎች፣ አገር ለአረብ እየተሸጠች “አዲስ አበባ አሽበረቀች አማረች” እያሉ ከንቱ ስብከታቸውን የሚያሰሙና በውስጥም በውጭም ሕዝብን ማዘናጊያ በርካታ የመዝናኛ እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ሀገር ሰላም የሆነች ይመስል ሕዝብን ዳንኪራ የሚያስረግጡና ገንዘቡን በአልባሌና ጭፈራ እንዲያባክን ሰራ የሚሰሩ ግለሰቦችም ሆኑ ተላላኪዎች እንዲሁም ማንኛውም ሰው ከዚህ የሆዳምና የባንዳ ሰራቸው እንዲታቀቡ እንመክራለን። ሀብት ለመሰብሰብ በመሯሯጥና የጨለማና የሀዘን
ዘመንን በጭፈራና በደስታ ለማሳለፍ የሚዳክሩትን ሁሉ እግዚአበሔር ልቦና ይስጣችሁ፣ ነገ ይህች አገር ሰትጠፋ
ተመልሳችሁ አገር አልባና ጨለማ ውስጥ የምትወድቁ መሆናችሁን እንድታወቁት፤ በታሪክም በሕዝብም ተወቃሽና ተጠያቂ መሆናችሁንም አትዘንጉ እንላለን!

የነፋኒት በዓለም ዋሴ ጀግንነት አርዓያ ሊሆነን፣ የተፈጸመባቸው አስቃቂ ድርጊትና እንዲዘገንነን እንዲቆጠቁጠን ነግ ተነግወዲያ በሌሎችም ጀግና እህቶችና ወንድሞቻችን ላይም እንዳይደገም ማድረግ የሁላችንም የህሊና ግዴታ ነውና በየከተማው በተለያዩ ምክንያቶች ተዳክመን፣ ፈዘንና ደንዝዘን በተለያዩ ምክንያቶች ተስፋ ቆርጠን የቆየን ሁሉ፤ የባሰ
እየመጣ ነውና ወጣት አርበኞቻችንን ወገኖቻችንን ተጋድሎ ስቃይና ግፍን በማስታወስ እንደገና እንነሳ! እንበረታታ!

እግዚአብሄር ለተሰዉት አርበኞቻችን ቤተሰቦችና ጓዶች መጽናናቱን ይስጥልን። ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን።
እግዚአብሔር የአማራውን የህልውና ትግል ይባርክ!

ድል ለአማራ የህልውና ትግል!
የአማራው ህልውና የኢትዮጵያም ህልውና ነው!!!

የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ ያብቃ! ወንጀለኞችም ለፍርድ ይቅረቡ!!!

@ዓለም አቀፍ የአምራ ግብረኃይል (ዓ/አ/አ/ግ/ኃ)
2🙏1