ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል /አፋብኃ/ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ለተከታታይ ስድስት (6) ወራት ያሰለጠናቸዉን ሶስተኛ ዙር የኮማንዶ እና የእግረኛ ሰራዊት የፋኖ አባላትን አስመረቀ።

እንደሚታወቀዉ ክ/ጦሩ ፣የክ/ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ #ሰንጥቅ ሻለቃ ሁለት ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን አሁን ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ "የበረሃው ዳኛ" የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የአሳምነዉ ኮርስ ልዩ የኮማንዶ እና የእግረኛ ሰራዊት ፋኖዎችን ማስመረቅ ተችሏል።

በህዝባዊ አቢዮት የተቀጣጠለው የአማራ የህልዉና ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመምጣት ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ከጠላት ማርኮ በመታጠቅ፣ ወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብን የተላበሱ የእሳት ነበልባል ወጣቶችን እያፈራ ይገኛል።

ስለሆነም ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር በስነልቦና እና በአካል ብቃት የተገነቡ አማራዊ እሴትን የተላበሱ የምንጊዜም የቁርጥ ቀን የሆኑ አይበገሬ የፋኖ ሃይሎችን ከክ/ጦር እስከ ብርጌዶች ድረስ በበቂ ሁኔታ አሰልጥኖ አስመርቋል።

ይህ ነበልባል የሆነ የበረሃ መብረቅ የፋኖ ሰራዊት በርካታ ጀብዶችን እየፈፀመ ይገኛል።
አማራ ሀገራዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎዉ እንዲረገጥ እና በህይዎት የመኖር መብቱ አንዲጠበቅለት ከተፈለገ #ፋኖነት መተኪያ የሌለዉ ዘላለማዊ የማንነት እና የነፃነት ተምሳሌት ነዉ።

የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል ክ/ጦር ህዝብ ክፍል!
🙏1
የአፋኖብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የሚኒሊክ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ በወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፈው
የአገዛዙ ሚሊሺያ ተንዶ ፋኖን መቀላቀሉን ተሰማ።

ከሰሞኑ በእስቴ መካነየሱስ ከተማ በተደረገዉ አዉደዉጊያ በርካታ የአገዛዙ ጥምር ጦር በብዛት ድል መደረጉን ተከትሎ ዛሬ ከ40 በላይ የሚሊሺያ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ከ180 በላይ ሰራዊት ያጠዉ አገዛዙ ብልፅግና ከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ የገባ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ሚሊሺያ በብዛት መዉጣቱን ተከትሎ የዞን እና የወረዳ ካድሬዎች የዕርስ በዕርስ ግጭት ገብተዋል።

የዕርስ በዕርስ ግጭቱ በክልሉ ባለስልጣናት ጭምር ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የባለስልጣናቱ ዋና ግጭት ደግሞ የእስቴ ሚሊሺያ ስምሪት ተደርጎ በተሾመዉ ቆራጡ ወይም በለጠ አንዳርጌ ጉዳይ መሆኑ ታዉቋል።

ሚሊሺያ እንዲመራ እስቴ የገበዉ በለጠ አንዳርጌ በሚሊሺያ በኩልም አመፅ ተነስቶበታል።ይህ በእንዲህ እነሰዳለ ዛሬ አገዛዙ ብልፅግና ለሞቱት የሚሊሺያ እና የአድማ ብተና አባላት ለቅሶ ሲያስለቅስ ዉሏል።በለቅሶዉ ላይ ሚሊሺያ በተኮሰዉ ጥይት በርካቶች ሲቆስሉ ህይወታቸዉ ያለፈ እንዳለም ታዉቋል።

በተያያዘ በስቦ ማስከዳት እና ስቦ መምታት ጥበቡ የጠላትን ካምፕ እያፈራረሰ የሚገኘዉ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ዛሬም በስቦ ማስከዳት ዉጤታማ ስራ ሰርቷል።

አዲስ ቅዳም ከተማ አድጓሚ ተራራ መሽጎ ከነበረዉ የጠላት ጦር ዉስጥ በትላንትና እና በዛሬዉ ለሊት 9(ዘጠኝ)የሚሊሺያ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ  በምዕራብ ጎንደር መተማ ድል ተቀዳጅቷል።

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አራተኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለጦር እና የሁለተኛ መይሳው ካሳ ኮር አጣናዉ ዋሴ ክፍለጦር በአገዛዙ ጥምር ጦር ኃይል ላይ እርምጃ ወስደዋል።

ዛሬ ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም ከመተማ ቅርብ ርቀት ሸመለ ጋራ የመሸገዉ የጠላት ሀይል የፋኖ ሀይሎች ወደ አሉበት ቀጠና ቢንቀሳቀስም ፋኖ በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ የጠላት ጥምር ጦር ኃይል ወደ መጣበት ተመልሷል።

ከሽመለጋራ የወጠዉ የጠላት ሀይል ባላሰበዉ እና ባልጠበቀዉ ሁኔታ በፋኖ ከፍተኛ ምት አስተናግዷል።በተደረገዉ አዉደዉጊያም የአገዛዙ ጦር ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ ወደ መሸገበት ምሽግ ተመልሶ ገብቷል።

የአራተኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ባንዲራው ግርማይ!!!
🙏1
የደጀን ከተማ ኖሪዎች በአረመኔው ጡት ቆራጭ አገዛዝ ካድሪዎች ታሰሩ!

የአረመኔው ጡት ቆራጭ አገዛዝ አስፈፃሚ ቅጥረኛ ሆዳም ካድሪዎች በደጀን ከተማ የከተመዋ ኖሪዎችን ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላቹህ በማለት እያሰሩ መሆኑንን አረጋግጠናል።

ከታሰሩት ሰዎች መካከል:-
1ኛ. ይልቃል   
2ኛ. አበባው ዳምን
3ኛ. ተመስገን  .. …. ማህበራት ሰራተኛ
4ኛ. ፍቃዱ   .. …..  ማህበራት ሰራተኛ
5ኛ. ማርቆሴው  .....  ድላላ ስራ
6ኛ. መኩሪያት .....  ንግድ ባንክ ሰራተኛ

በደጀን ወረዳ ጢቅ ቀበሌ ለንግስና በዓል ጨፈራቹሀል ተብለዉ የታሰሩ:-
1ኛ. ይበልጣል ወርቄ
2ኛ. ገርባቸው ወርቄ
3ኛ. አብርሀም ታደለ
4ኛ. አበበ ባንቴ
5ኛ. አለባቸው መኩሪያው በአገዛዙ ቅጥረኛ ካድሪዎች ታፍነው ታስረዋል።

የዚህም ድርጊት ፈፃሚ እና አስፈፃሚ አካላት ውስጥ:-
1ኛ. የአሻግሬ ቸርነት ...  ፖሊስ አዛዥ
2ኛ. አዲሱ አባብየ   .... ሚኒሻ ሀላፊ
3ኛ. ዳኘ ደንቀው  ......   ሰላምና ደህንነት ኃላፊ እና ሌሎችም በስም ያልጠቀስናቸው የአገዛዙ ጡት ቆራጭ ሰራዊት አገልጋዮች ይገኙበታል።

በመሆኑም በዚህ ድሪጊት የተሳተፍ የአገዛዙ ቅጥረኛ አመራሮች ላይ የቀኜ አባላት እርምጃ እትወስዱ ጥቆማ እንሰጣለን።

በደጀን ወረዳ ደጀን ከተማ በከተማዋ ማህበረሰብ፣ ሹፊሮች እና ነጋዴዎች ላይ አገዛዙ እየፈፀመ ያለውን በመረዳት እንዲሁም በደጀን ወረዳ የሚገኜው ዛምበረሃ ብርጌድ በደጀን ወረዳ ምንጅ ቀበሌ በፈፀመው ጀብድ ተስፋ በመቁረጥ አገዛዙን በመክዳት ወጥተዋል።

ከእነዚህም የሚሊሻ አባላት ውስጥ:-
1ኛ. መኳንንት ጠጁ
2ኛ. እንዳወቀ አስማረ በአጃቢነትና በተወርዋሪነት እያገለገሉ የነበሩ የሚሊሻ አባል ይገኙበታል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም
3
"ፍተሻውን ልታዘምኑ ይገባል እንጅ እስከ መቼ ነው በሴት ልጅ ማህፀን እጅ እየሰደዳችሁ የምትፈትሹት ፤ ይህኮ ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ወንጀል ነው።"

መሪጌታ በላይ አዳሙ

መሪጌታ በላይ አዳሙ በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ በሽብር የተከሰሱ ሲሆን የቂሊንጦ ማ/ቤትን እና ኃላፊዎችን በተመለከተ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጥቅምት 10/2018 በነበረው ችሎት ካቀረቡት አቤቱታ የተወሰደ ፦

መስከረም 29/2018 ለጥየቃ በመጣች ባለቤቴ ላይ በፍተሻ ስም ከመድፈር የማይተናነስ ወንጀል ፈጽመዋል።

ፍተሻውን ልታዘምኑ ይገባል እንጅ እስከ መቼ ነው በሴት ልጅ ማህፀን እጅ እየሰደዳችሁ የምትፈትሹት ፤ ይህኮ ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ወንጀል ነው።

ይህን ቅሬታየን ለቂሊንጦ ማ/ቤት አስተዳደር ለማቅረብ በምሄድበት ጊዜ በኢ/ር ድሪባ ሰንበቶ ቢሮ ውስጥ እና በር ላይ በብዙ ሰዎች ፊት ክብሬ ተገፎ በካቴና እጄን ታስሬ በከስክስ ጫማ ተደብድቤያለሁ ፤ በእጄ ላይም ጉዳት አድርሰውብኛል ፤ ተገቢ ሕክምናም አላገኘሁም።

እኔን ብቻ ሳይሆን የተፈጠርኩበትን ማንነቴን የሚነካ ስድብ ሰድበውኛል።

ከነበርኩበት ዞን 4 ወደ ዞን 2 አስገድደው እንድዛወር አድርገዋል ፤ ዐይነ ስውር ቤተሰቤ ለመጠየቅ በማይመቻት ቦታ ወስደውኛል።

አሁንም ፍ/ቤቱን የምጠይቀው ዳኝነት ፦

1) ተገቢ የሆነ ሕክምና እንዳገኝ ፣
2) ከዞን 2 ወደነበርኩበት ዞን 4 እንድመለስ፣
3) ቤተሰቦቼን በተለይ ደግሞ ዐይነ ስውር አክስቴ ለመጠየቅ በሚመቻት ቦታ እንዳገኛት ቢፈቀድልኝ ፣
4) ኢሰብአዊ የሆነ ፍተሻ እንዲቆም ለማ/ቤቱ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ።

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 11/2018)
3
"ፌደራል ፖሊስ የወሰደብንን ንብረት እየመለሰ ባለመሆኑ ፒያሳ ላይ ስልኮቻችንን ከእጃችን እየነጠቁ ከሚወስዱት ነጣቂዎች ለይተን ለማየት እየተቸገርን ነው።"

ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ

በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጥቅምት 10/2018 በነበረው ችሎት ዓባይ ዘውዱ በፌደራል የተነጠቀውን ንብረት በተመለከተ ካቀረበው አቤቱታ ፦

እስካሁን ድረስ ፌደራል ፖሊስ የወሰደብኝን 5 የሞባይል ስልኮች እና አንድ ቪዲዮ ካምራ አልመለሰልኝም።

በእርግጥ ይህ አካሄድ የፕሬስ ነጻነት እንዳይኖር የመስሪያ ንብረትን በመንጠቅ ባለሙያዎችን ለማዳከም ታስቦ የሚደረግ መሆኑ ግልጽ ነው።

ፌደራል ፖሊስ ስለምን የወሰደውን ንብረት እንዲመልስ አይደረግም ? ፤ ፍ/ቤቱም ተደጋጋሚ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ሊፈጸምልን አልቻለም።

ሁለት ዓመት ሙሉ ስለተነጠቅነው ንብረት እየጠየቅን ነው የከረምነው ፤ ካልተፈታ አሁንም ልንቀጥል ነው ማለት ነው።

በመጀመሪያውም ሆነ ተሻሻለ በተባለው ክስ ላይ ኤግዚቢት ያልተባለ ንብረት ስለሆነ ሊመለስልን ይገባል።

ፌደራል ፖሊስ የወሰደብንን ንብረት እየመለሰ ባለመሆኑ ፒያሳ ላይ ስልኮቻችንን ከእጃችን እየነጠቁ ከሚወስዱት ነጣቂዎች ለይተን ለማየት እየተቸገርን ነው።

ችግሩ ከግለሰብ አመራሮች አልፎ ተቋማዊ መልክ እየያዘ በመሆኑ ሁኔታው አሳሳቢ ነው ፤ ፍ/ቤቱ ንብረታችን እንዲመለስ ያድርግ።

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 11/2018)
2