ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ቀጥታ ከስፍራው - ያገዛዙ ገመና ሲገለጥ | በበላይ እዝ የካራማራ ክፍለጦርን ከተቀላቀሉ ያድማ ብተና አባላት ጋር የተደረገ ቆይታ Global Fano Media
🙏31
➾ብልፅግና የሟች እናትና አባቷን አፍኖ በመውሰድ የውሸት ዶክመንተሪ እየሰራ መሆኑ ተሰማ

ነውረኛው የብልፅግና ቡድን "የሟች አ*ስ*ከ*ሬንን ጡት በመቁረጤ ለምን ተቆጣችሁኝ" በሚል የክብርት ሰማዕቷ ፋኖ ባለምን ቤተሰቦች አፍኖ በመውሰድ ፋኖ ገደላት የሚል ዶክመንተሪ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ክፍለጦር አረንዛው ዳሞት ብርጌድ አባልና የኮማንዶ ተመራቂ የሆነችው ፋኖ በአለም ዋሴ፡ ጥቅምት 02/2018 ዕለተ እሁድ በተካሄደ ውጊያ ቆስላ በጠላት እጅ የወደቀች ሲሆን፡ የጠላት ኃይልም በእጁ የወደቀችውን ፋኖ በአለምን በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ የሰውነት አካሏን ደጋግሞ በመውጋት እና ጡቶቿን በመቁረጥ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው የሚታወስ ነው።

የክብርት ሰማዕቷ ስርዓተ ቀብር ከሁለት ቀናት በፊት የተካሄደ ሲሆን፡ ነውረኛው የብልፅግና ቡድን ዛሬ ጥቅምት 11/2018 ዓ/ም አጥቢያ ሌሊቱን የሰማዕቷን ቤተሰቦች አፍኖ የወሰደ ሲሆን በቡሬ አቅራቢያ ብርሸለቆ (መኮድ) የስርዓቱ አፍ የሆኑ ሚዲያዎችን በመጥራት እናትና አባቷን አፈሙዝ ደቅኖ በማስፈራራት 'መከላከያ' አልገደላትም:: የሚል ንግግር እንዲያደርጉ ከውስጥ የደረሱን የአሻራ ምንጮች ገልጸዋል ።

የአረንዛው ዳሞት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ፍስሀ አደራው ለአሻራ ሚዲያ እንደገለፀው በትናንትናው ዕለት የምዕራብ ጎጃም ብልፅግና ካድሬዎች ለወላጅ አባቷ በስልክ ደውለው የገደሏትን ወታደሮች እርምጃ ወስደንባቸዋል።
ልጅህ ከሞተች በኋላ ማልቀስ አያስፈልግም ። በቂ ገንዘብ እንሰጥሀለን በማለት ዛቻ ሁሉ ደርሶታል ብሏል።

አባቷ ከዚህ በኋላ እኔም ታጥቄ ፋኖን እቀላቀላለሁ ማለታቸውን ተከትሎ አገዛዙ የክብርት ሰማዕቷ ቤተሰቦች ከሚኖሩበት በምዕራብ ጎጃም ዞን አርቢሲ መንፈሣዊት ተብላ ከምትጠራው ቀበሌ ዛሬ አጥቢያ ለሊቱን በአገዛዙ ወታደሮች ታፍነው ወደ ብርሸለቆ (መኮድ) መወሰዳቸው ተነግሯል።
3
አ.ፋ.ብ.ኃ ቴዎድርስ ዕዝ ጃዊ መተከል የልዩ ኮማንዶ ኃይል ምረቃ !

ሰልጥኖ ያልታገለ ነፃ አይወጣም !

መተከል|ጎጃም|አማራ
🙏2
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል /አፋብኃ/ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ለተከታታይ ስድስት (6) ወራት ያሰለጠናቸዉን ሶስተኛ ዙር የኮማንዶ እና የእግረኛ ሰራዊት የፋኖ አባላትን አስመረቀ።

እንደሚታወቀዉ ክ/ጦሩ ፣የክ/ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ #ሰንጥቅ ሻለቃ ሁለት ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን አሁን ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ "የበረሃው ዳኛ" የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የአሳምነዉ ኮርስ ልዩ የኮማንዶ እና የእግረኛ ሰራዊት ፋኖዎችን ማስመረቅ ተችሏል።

በህዝባዊ አቢዮት የተቀጣጠለው የአማራ የህልዉና ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመምጣት ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ከጠላት ማርኮ በመታጠቅ፣ ወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብን የተላበሱ የእሳት ነበልባል ወጣቶችን እያፈራ ይገኛል።

ስለሆነም ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር በስነልቦና እና በአካል ብቃት የተገነቡ አማራዊ እሴትን የተላበሱ የምንጊዜም የቁርጥ ቀን የሆኑ አይበገሬ የፋኖ ሃይሎችን ከክ/ጦር እስከ ብርጌዶች ድረስ በበቂ ሁኔታ አሰልጥኖ አስመርቋል።

ይህ ነበልባል የሆነ የበረሃ መብረቅ የፋኖ ሰራዊት በርካታ ጀብዶችን እየፈፀመ ይገኛል።
አማራ ሀገራዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎዉ እንዲረገጥ እና በህይዎት የመኖር መብቱ አንዲጠበቅለት ከተፈለገ #ፋኖነት መተኪያ የሌለዉ ዘላለማዊ የማንነት እና የነፃነት ተምሳሌት ነዉ።

የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል ክ/ጦር ህዝብ ክፍል!
🙏1
የአፋኖብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የሚኒሊክ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ በወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፈው
የአገዛዙ ሚሊሺያ ተንዶ ፋኖን መቀላቀሉን ተሰማ።

ከሰሞኑ በእስቴ መካነየሱስ ከተማ በተደረገዉ አዉደዉጊያ በርካታ የአገዛዙ ጥምር ጦር በብዛት ድል መደረጉን ተከትሎ ዛሬ ከ40 በላይ የሚሊሺያ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ከ180 በላይ ሰራዊት ያጠዉ አገዛዙ ብልፅግና ከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ የገባ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ሚሊሺያ በብዛት መዉጣቱን ተከትሎ የዞን እና የወረዳ ካድሬዎች የዕርስ በዕርስ ግጭት ገብተዋል።

የዕርስ በዕርስ ግጭቱ በክልሉ ባለስልጣናት ጭምር ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የባለስልጣናቱ ዋና ግጭት ደግሞ የእስቴ ሚሊሺያ ስምሪት ተደርጎ በተሾመዉ ቆራጡ ወይም በለጠ አንዳርጌ ጉዳይ መሆኑ ታዉቋል።

ሚሊሺያ እንዲመራ እስቴ የገበዉ በለጠ አንዳርጌ በሚሊሺያ በኩልም አመፅ ተነስቶበታል።ይህ በእንዲህ እነሰዳለ ዛሬ አገዛዙ ብልፅግና ለሞቱት የሚሊሺያ እና የአድማ ብተና አባላት ለቅሶ ሲያስለቅስ ዉሏል።በለቅሶዉ ላይ ሚሊሺያ በተኮሰዉ ጥይት በርካቶች ሲቆስሉ ህይወታቸዉ ያለፈ እንዳለም ታዉቋል።

በተያያዘ በስቦ ማስከዳት እና ስቦ መምታት ጥበቡ የጠላትን ካምፕ እያፈራረሰ የሚገኘዉ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ዛሬም በስቦ ማስከዳት ዉጤታማ ስራ ሰርቷል።

አዲስ ቅዳም ከተማ አድጓሚ ተራራ መሽጎ ከነበረዉ የጠላት ጦር ዉስጥ በትላንትና እና በዛሬዉ ለሊት 9(ዘጠኝ)የሚሊሺያ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ  በምዕራብ ጎንደር መተማ ድል ተቀዳጅቷል።

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አራተኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለጦር እና የሁለተኛ መይሳው ካሳ ኮር አጣናዉ ዋሴ ክፍለጦር በአገዛዙ ጥምር ጦር ኃይል ላይ እርምጃ ወስደዋል።

ዛሬ ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም ከመተማ ቅርብ ርቀት ሸመለ ጋራ የመሸገዉ የጠላት ሀይል የፋኖ ሀይሎች ወደ አሉበት ቀጠና ቢንቀሳቀስም ፋኖ በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ የጠላት ጥምር ጦር ኃይል ወደ መጣበት ተመልሷል።

ከሽመለጋራ የወጠዉ የጠላት ሀይል ባላሰበዉ እና ባልጠበቀዉ ሁኔታ በፋኖ ከፍተኛ ምት አስተናግዷል።በተደረገዉ አዉደዉጊያም የአገዛዙ ጦር ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ ወደ መሸገበት ምሽግ ተመልሶ ገብቷል።

የአራተኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ባንዲራው ግርማይ!!!
🙏1