ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ክፍል፡ ከመስከረም 14/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት በተካሄደው "በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ(አባ ናደው)" የተገኙ ድሎችን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ!
🙏1
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በጦር ሜዳ በፋኖ የሚደርስበትን ከባድ ኪሳራ መቋቋም ሲያቅተው ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ የጄትና የድሮን ጥቃት እየፈፀመ የህይወት የአካልና የንብረት ብሎም የስነ ልቦና ጉዳት እያደረሰ ይገኛል::

በበርካታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ታጅቦ ከተጠናቀቀው ዘመቻ አባ ናደው ማግስት የኦሮሚያ ብልፅግና ልዩ ሃይልን ጨምሮ ተጨማሪ ሁለት ዕዝ በማስገባት በከፍተኛ መካናይዝድ ሃይል እንዲሁም በጄትና በድሮን ታግዞ ማጥቃት ቢያደርግም የፈለገውን ውጤት ማምጣት ባለመቻሉና ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማስተናገዱ በሞርታር በታንክ በመድፍና ቢኤም እንዲሁም በጄትና ድሮን ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ ድብደባ እየፈፀመ የንፁሃኖችን ህይወት በጅምላ እየቀጠፈ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እያደረሰ እንስሳትን ጨምሮ ቤትና ንብረት እያወደመ የስነ ልቦና ስብራት ጭምር እያደረሰ ይገኛል::

ዘመቻ አባ ናደውን ጨምሮ ከጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ተከታታይ አምስት ቀናቶች በመቶዎች የሚቆጠር የተለያየ የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ ተዋጊውን ሳይሆን ከተማ ላይ እና የገጠር መንደሮችን ጨምሮ ታስቦበት ንፁሃኑን ህዝብ ኢላማ ያደረገ ድብደባ ፈፅሟል:: በተጠቀሰው ቀን ከ33 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት በመፈፀም ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 10/2018 አ.ም
1
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ገነቴ ከተማ አቅራቢያ በጉባላፍቶ እና መቄት ቀጠና ውስጥ ከፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ባደረገው ትንቅንቅ በርካታ የጠላት ኃይል ላይ እርምጃ መውሰዱ ተገለፀ::

ጠላት ወደ ውጊያው ቀጠና ተጨማሪ ኃይል አስልኮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ በመክፈት አስከሬን ለማንሳት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ በነበረበት ቅጽበትም ክፉኛ የተመታ ሲሆን አስከሬኑን አዝረክርኮ በ4 አምቡላንስ ቁስለኞችን ብቻ ይዞ መውጣቱ ታውቋል::

በአርበኛ ሼህ ይማም ሙሀመድ የሚመራው የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር የተወሰኑ አባላትን ያቀፈ ቡድንን በመጠርነፍ አርበኛ ከረም ማህሙድ በቀጠናው በመንቀሳቀስ ላይ ሳለ በድንገት ለማፈን ወደ ቀጠናው የገባው ጠላት ከበባ ቢፈፅምም እራሱ ተከቦ መብረቃዊ ጥቃት ተሰንዝሮበት ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን ሊያስተናግድ ችሏል::

በተያያዘ ዜና በዚሁ በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ውስጥ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት ሜካናይዝድ ምድብተኞች በሞርተር የታገዘ ውጊያ በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት ላይ ቢከፍቱም የኮሩ ሰራዊት ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሮ በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን የአድማ ብተና ሻለቃ አዛዥን ጨምሮ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ኃይልን መደምሰሱ ታውቋል:: ውጊያው በዛሬው እለትም ቀጥሎ የኮሩ ሰራዊት ጠላትን የመበተን እና የመደምሰስ ስራ መስራቱን ለማረጋገጥ ችለናል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏1
የድል ዜና ቀጥታ ከግንባር | የደፈጣው ድል በወሎ ግንባር | በሸዋ ህዝቡና ፋኖ መግባባት ላይ ደረሱ | ፋኖ ለሀጅ ሙፍቲ ሕልፈት መግለጫ
🙏1
የድል ዜና ቀጥታ ከግንባር | የደፈጣው ድል በወሎ ግንባር | በሸዋ ህዝቡና ፋኖ መግባባት ላይ ደረሱ | ፋኖ ለሀጅ ሙፍቲ ሕልፈት መግለጫ
🙏1
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ መስከረም 14/2018 ዓ.ም የተጀመረው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በበርካታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ታጅቦ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም መጠናቀቁን በማስመልከት የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ ፊታውራሪ ድርሳን ብርሃኔ እና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ በለጠ ሸጋው የተሰጠ መግለጫ!

ዘመቻው፣ መስከረም 14/2018 ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት በአምስቱም ኮሮች በተመሳሳይ ሰዓት ውጊያ በመክፈት ከጀመርንበት ቅጽበት አንስቶ የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ፡-

ምስራቅ አማራ ኮር 1፣ ምስራቅ አማራ ኮር 2፣ ላስታ አሳምነው ኮር፣ ልጅ ዕያሱ ኮር፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ የዕዙ ልዩ ዘመቻ እንዲሁም በአንዳንድ ቀጠናዎች በቅንጅት የድርጅታችን አካል የሆኑት ቴዎድሮስ ዕዝ፣ አሳምነው ዕዝ፣ በላይ ዘለቀ ዕዝ እና መላው የሰራዊታችን አባል፣ በየደረጃው የሚገኙ የኃይል አመራሮች እና የዕዛችን ሥራ አስፈጻሚ አመራሮች 24/7 እረፍት አልባ የውጊያ ተሳትፎና አመራር በመስጠት የኀልውና ትግሉን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ማስገባት ተችሏል፡፡

ዘመቻው ታቅዶ ወደተግባር ከተገባበት ጊዜ ጀምሮ የድርጅታችን አፋብኃ ቀጠናዊ አመራሮች የሞራል ድጋፍ ከመስጠት ጀምሮ፤ የዘመቻው አካል በመሆን የጠላትን እንቅስቃሴ በመገደብ አልፎም ባደረግናቸው የጋራ ውጊያዎች፣ የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል መሪ ድርጅት እንደተፈጠረ በተግባር አሳይተናል፡፡

ለ18 ቀናት ያለ እረፍት በዘለቀው ዘመቻ አባ ናደው በርካታ የነፍስ ወከፍ የቡድንና መካናይዝድ ጦር መሳሪያዎችን ከበርካታ ተተኳሽ ጋር እንዲሁም ከ24 በላይ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በምርኮ የተገኘበት ሲሆን፤ ጠላት አምስት ክፍለጦሮቹ የተበተኑበት፤ ውጊያን አቅደው የሚመሩ የውጊያ መሃንዲሶቹን ጨምሮ በርካታ መስመራዊ መኮንኖቹን ያጣበት፤ በመቶዎች የተማረኩበትና በሽዎች ሙትና ቁስለኛ የሆነበት ስኬታማ ዘመቻ እንደነበር በግምገማችን አረጋግጠናል፡፡

ከወታደራዊ ድል አኳያ!
👉 6 ሞርተር፣ 3 የሞርተር ምጣድ እና 103 የሞርተር ቅንቡላ
👉 8 ዲሽቃ
👉 33 ብሬን
👉 13 ስናይፐር
👉 1343 ክላሽ
👉 8 ሽጉጥ
👉 487 የእጅ ቦምብ
👉 25 ሬድዮ መገናኛ
👉 448 የክላሽ ካዝና
👉 613 የደረትና የወገብ ትጥቅ
👉 62479 የክላሽ ተተኳሽ
👉 34570 የብሬን ተተኳሽ
👉 15614 የዲሽቃ ተተኳሽ
👉 679 ምርኮኛ
👉 3003 የተደመሰሰ
👉 567 ወታደራዊ ሻንጣ
👉 24 መኪና፣ የወታደራዊና የፖለቲካ አመራሮች መኪና ኦራል፣ አምቡላንስ፣ ፓትሮልን ጨምሮ (አገዛዙ ወታደራዊ መጠቀሚያ አድርጎቸው የነበሩትና የተማረኩት አምቡላንሶች ለሕዝብ አገልግሎት እንዲዉሉ ተደርጓል።)

የአማራ የኀልውና ትግል ከጀመረበት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ጠላት ካስተናገዳቸው ኪሳራዎቹ እጅግ የከበደውን ኪሳራ በዘመቻ አደም አሊ አስተናግዷል፡፡

ፓለቲካዊ:-
ፋኖ በርካታ ወረዳዎችን፣ ከ40 በላይ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይት አካሂደናል፣ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በሰፊው የዘረጋበት፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀጣይ እንደ አማራ፣ አፋብኃ በሚያውጀው ዘመቻ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ትልቅ ፍንጭ የሰጠንበት አቅማችንን ለወዳጅ ጠላት ያሳየንበት ልዩ ዘመቻ ነበር፡፡

በጥቅል ግምገማችን በዘመቻው የፋኖ የኀልውና ትግል አዲስ የትግል ምዕራፍ የደረሰበት በመሆኑ በተመዘገበው ድል ሰራዊታችንና ድርጅታችን ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነው መላው የአማራ ሕዝብና የአማራ ትግል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

አማራን ሰበርነው እያሉ ጠላቶቻችን ቢያወሩም ታላቁ አማራ እንደማይሰበር እንደውም ጠላቶቹን በሰዓታት እድሜ መደምሰስና ማጥፋት እንደሚችል በዚህም የአማራ ሕዝብ ተወስዶበት የነበረው የፖለቲካ ብልጫና እንዲሁም ድብት መነቃቃት የፈጠረ ነው ብለን እናምናለን። የወታደራዊ ድል በፓለቲካው ግንባር እንዲደግም እንደ ድርጅት እየተሰራበት ይገኛል። ከሕዝብ አስተዳደርና ሕዝባዊ ውይይት አኳያ የዕዛችን አንዱ ተቋም የሆነው ጸሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የፖለቲካ መኮንኖች ማሰልጠኛ ማዕከል የሰለጠኑ የፖለቲካ መኮንኖች በተለያዩ ቀጠና ያደረጉት ስራ የሚደንቅ ነው። ወደ ፋኖ ያልገባችሁ የአማራ ሙህራን በዚህ አጋጣሚ ኑ ትግሉን ተቀላቀሉ ፖለቲካውንም አግዙ ለማለት እወዳለሁ።

በተጨማሪም ነፃ በወጡ ከተሞችና የወረዳ ማዕከላት ደማቅ አቀባበል ያደረገልን ሕዝባችን፣ በተሳትፎው የትግሉ ባለቤትነቱን ዳግም አስመስክሯል!!

ከዲፕሎማሲ አኳያ:-
ከምንም በላይ የአማራ ፋኖ ትግል ዓለማቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንደሚያከብር፣ በምርኮኛ አያያዙ ለዓለማቀፉ ማኀበረሰብ በማሳየት ትግላችን ራስን የመከላከል፣ እንዲጠፋ የተፈረደበትን ሕዝብ ኀልውና የማዳን ተልዕኮ እንደሆነ በተግባር ማስመስከር ችለናል፡፡

የአለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ (International humanitarian law) በሚደነግገው መሠረት ሰብዓዊ ክብራቸውን በጠበቀ ሁኔታ የያዝናቸው የቀድሞ የብልጽግና ሰራዊት አባላት ይህን ምስክራቸውን በዓለማቀፉ ማኀበረሰብ አባላት ፊት መስክረዋል፡፡ ይህ አዲሱ የአማራ ኀልውና ትግል የታሪክ ምዕራፍ ነው፡፡

ሌላው መሪያችን ዋርካው ምሬ ወዳጆ በይፋ ባቀረበው ጥሪና ድርጅታችን አፋብኃ ከአለማቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በውስጥ በተፃፃፈው መሰረት በውጊያ የቆሰሉ የብልፅግና ሰራዊቶችን ለቀይ መስቀል አስረክበናል:: በተጨማሪም ምርኮኞችን ጎብኝተዋል::

ይህ ተግባራችን የፋኖን የህልውና ታጋይነት በሰፊው ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ያስመሰከረ ነው::

በቀጣይም እንደ ድርጅት በምናደርጋቸው ዘመቻዎች ለአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ ተገዢ ሆነን እስከ አራት ኪሎ ድረስ እንደምንዘልቅ ዳግም ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም
🔥2🙏1
እነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው 15 የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ፍ/ቤት ቀርበዋል ፤ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ ይመስከር በሚል በስር ፍ/ቤቱ በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የተጠየቀው ይግባኝም ውድቅ ተደረገ።

በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው የሽብር መዝገብ ተከሳሽ የሆኑ 15 የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ጥቅምት 10/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበዋል።

በመዝገቡ ከተካተቱትና ጉዳያቸውን በቂሊንጦ ማ/ቤት ሆነው ከሚከታተሉት 16 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች መካከል 16ኛው አማረ መለሰ የተባለ ተከሳሽ ግን በእስር እና በምርመራ ወቅት በደረሰበት እንግልት ታሞ በሕክምና ላይ በመሆኑ በችሎት እየተገኘ አይደለም።

ባለፈው ዓመት መጨረሻ መዝገቡ የተቀጠረው ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ እንዲመሰክር በሚል በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ልደታ ምድብ ችሎት በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት በተከሳሽ ጠበቆች በኩል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተጠየቀውን የይግባኝ ክርክርን ውጤት ለመጠባበቅ ነበር።

ጥቅምት 10/2018 በነበረው ችሎት ለመረዳት እንደተቻለው በጠበቆች በኩል የቀረበው የይግባኝ ክርክር ውድቅ ተደርጎ ፣ አለ የተባለው ምስክር ከመጋረጃ በስተጀርባ እንዲመሰክር ተብሏል።

በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ 16 ተከሳሾች ላይ ክሱ ከተመሰረተ እና ሂደቱም ከቀጠለ 1 ዓመት ከ8 ወር በኋላ ነው በዐቃቤ ሕግ በኩል ወሳኝ ምስክር አለኝ በሚል ተጠይቆ በፍ/ቤቱ ተቀባይነት ያገኘው።

ዐቃቤ ሕግ 15 የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ አመራሮችና አባላትን ካስመሰከረ በኋላ ሁኔታውን በመገምገም አሰልጥኖ ያመጣው አዲስ ምስክር ነው በሚል ተከሳሾች የተቃወሙት መሆኑ አይዘነጋም።

በመቀጠል ደግሞ ከመጋረጃ በስተጀርባ ይመስክር የሚለውንም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከምስክሩ ደህንነት አንጻር በሚል የተቀበለው መሆኑ ቅር ያሰኛቸው ተከሳሾች ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ፍ/ቤቱ የአገዛዙ የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑን በማቆም እንዲሰራ ካልሆነ ግን በችሎቱ ለመዳኘት እንደሚቸገሩ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።

በተከሳሽ ጠበቆች በኩልም ጉዳዩን እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት መውሰዳቸው እና ይግባኙ ተቀባይነት ማጣቱ ከላይ የተላለፈ የፖለቲካ ውሳኔ እያስፈፀሙ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ተከሳሾች ተቃውመውታል።

በመጨረሻም ፍ/ቤቱ የጠ/ፍ/ቤቱ የይግባኝ ውሳኔ ደብዳቤ እንዲደርሰው እንዲሁም ጠበቆችና ተከሳሾች በቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊ በም/ኮምሽነር ጣሰው እና በዋናነት በግቢ ጥበቃና ደህንነት ኃላፊ ዋና ኢ/ር ድሪባ ሰንበቶ ላይ ከሕክምና ፣ ከፍተሻ እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ጨምሮ ላነሷቸው በርካታ ቅሬታዎች ሁለቱ ኃላፊዎች ቀርበው የሚሰጡትን ምላሽ ለመስማት በሚል ለጥቅምት 18/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

@ሞዐ ሚዲያ
አውሎግሶን አንድነት- Awulogson Andinet
3
ከ2000 በላይ ህዝብ የተሳተፈበት የህዝብ ንቅናቄ መድርክ በሸበል በረንታ ወረዳ ተካሄደ።

ጥቅምት11/2018 ዓ.ም

አፍብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በሸበል በረንታ ወረዳ ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም ህዝባዊ ውይይት አካሒዷል።

በስብሰባው ለወቅታዊ ሁኔታወችና አረመኔው አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ አያደረሰው ሰላለው አሰቃቄ ጭፍጨፍ ከፍተኛ ውይይት ተከሂዶል።በውይይት መድርኩ:-
➤ፋኖ ከማህበረሰቡ ጋር ስለ አለው ግንኙነት
➤የሎጀስቲክ አሰባሰብን በተመለከተ
➤የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ
➤የቀበሌ ማህበራዊ ፍትህ አሰራርን በተመለከተ
➤የአረመኔው አገዛዙ እየፈፀመ ስላለው አረመኔዊ ድርጊት በተመለከተ በአጠቃላይ የቀበሌ የጎበዝ አለቃዎችን በመገምገም በወቅታዊ ጉዳዮች ጉዳይ ላይ የአብይ አህመድ ስረዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ስላለው አረመኔዊ ተግባር ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶል።በመጨረሻም የህዝባዊ ውይይት መድርኩን የመሩት የክፍለ ጦር አመራሮች በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል እንዲሁም ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በሸበል በረንታ በሚያደረጋቸው ተጋድሎዎ ህዝባችን እንደ ትላንቱ እያካደ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራሮች በሸበል በረንታ ወረዳ የሚገኜው ሽፈራው ገርባው ብርጌድ እና የሻለቃ አመራር በድርጅቱ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የሰጣውን የስራ ኃላፊነት በተሰጣቸው የስራ ዘርፍ ለተከታታይ አራት ቀን በመገምገም ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ከፋኖ አባላቱ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይት መድርኩ ለሽፈራው ብርጌድ ቃልኪዳን ውባለ እና ውባለ ተገኑ ሻለቃ አመራር እና አባላት በክፍለ ጦሩ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የፖለቲካ ግንባታ ተሰጥቷል። የውይይት መድርኩን የመረው የክፍለ ጦር አመራሮች በአጠቃላይ ስለ ትግላችን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለብርጌድ አመራሮች፣ ለሻለቃ አመራሮች እና አባላት ሰፋ ያለ ትምህርት ተሰጥቷል።

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
    ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት
2🙏2
ቀጥታ ከስፍራው - ያገዛዙ ገመና ሲገለጥ | በበላይ እዝ የካራማራ ክፍለጦርን ከተቀላቀሉ ያድማ ብተና አባላት ጋር የተደረገ ቆይታ Global Fano Media
🙏31