ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ  ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዋና አስተዳዳሪ አርበኛ ደመላሽ ደመቀ የዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር አመራሮች በተገኘበት የማህበረሰቡ ሰብል ተሰበሰበ!!

የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዋና መሪ አርበኛ ደመላሽ ደመቀ በተገኘበት ፋኖዎች ሁለቱን ማለትም የኦሮሞ ማህበረሰብ እና የማጀቴ ማህበረሰብ በሚያስተዳዱረበት አካባቢ የሸመልስ አብዲሳ  ኃይለ ኦነግ ሸኔ በአማራው ማህበረሰብ ላይ ሰብል እንዳይሰበሰብ በማድረግ ህዝባችን እንዲሰቃይ ተደርጎ የነበር ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን አርበኛ ደመላሽ ደመቀ በሁለቱ ማለትም ኦሮሞኛና አማራኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ ሚኖሩበት ማህበረሰብ ክፍል የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ደመላሽ ሻለቃ ቃኞዎችን ይዞ በመግባት የህዝባችን ሰላም በማስጠበቅ አሸባሪወን ኦነግ ሸኔ በመከላከል በአስደማሚ ሁኔታ የህዝባችንን እንባ እያበሱና ወደ ማይቀረው ድል እየተራመዱ ይገኛሉ።

እንደ ኢትዮጵያ ተወልደን እንደ አማራ በምንታረድባት ሀገር  የክረምት (የልምላሜ) ወራት አልቆ የበጋ (የምርት መሰብሰቢያ ) ወራት እየገባ ባለበት ሰዓት አማራውን በተለያዩ የጦርነት ግንባሮች አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ በተለይም ሁለት ቋንቋ ተናጋሪዎች ከሚኖሩበት የአማራው ማህበሰብ ክፍል በሆነው በኤፍራታና ግድም ወረዳ በእየግዜው ትንኮሳዎች ሲያደርግ የቆዩ መሆኑ አያሌ አገራት የሚያቁት ሃቅ ነው።

የብልፅግና አገዛዝ ቀንበር ተሸካሜ አብይ አህመድና ብአዴን በአማራ ህዝብ ላይ ያላደረሱት ግፍና እንግልት የለም እኛ ፋኖዎች በምንኖርባት ሀገራችን ማነኛውንም ቋንቋ ተናጋሪዎች አከብርን የምንኖር ብንሆንም የአማራ ህዝብን በሰላም ሰርቶ ወጦ ወርዶ እናት ሃገሩኑ ኢትዮጵያን ከአረመናዊ ስርአት ለመቀበል አንድዬ ነፍሳቸው እየሰጡ ከውጊያ ጎን ለጎን የህዝባችን ሰብል በመሰብሰብ የበጋ ጊዜ  በሰፊው የድሮን መጋለጥ ፣ በአፃፋ እርምጃ ሰብል መውደምና መሰል በርካታ ውድመቶች  ስለሚኖሩ ለመከላከል  እንጂ  ለማጥቃት_እድሉ ጠበብ ይላል ስለሆነም ባሉን ጊዜያት የአፋብኃ አንድነትን በተግባር የሚያስመሰክር በመላው አማራ  በተመሳሳይ_ሰዓትና  በተመሳሳይ_ቀን የሚጀምር ቅስም ሰባሪ የሆነ  ዘመቻዎችን በማካሄድ የህዝባችን ነፃነት የምናወጣበት  ግዜ እየመጣ ነው ሲል የክፍል ጦሩ መሪ ገልጿል።

መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ

  ጥቅምት 04/02/2018 ዓ.ም
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አራተኛ ደጃዝማች ኮር ተከዜ ክፍለጦር በዘራፊ ኃይሎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን አስታወቀ።

በማዕከላዊ ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ወረዳ አዲሲቱ ወልቃይት ቀበሌ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 5 ዘራፊ ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወስዷል።በአካባቢው በርካታ ሌቦች በአገዛዙ ብልፅግና ተደራጅተዉ ዝርፊያ እንዲፈፅሙ ተልዕኮ ተሰቷቸዉ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ወረዳ በመሰማራት በማህበረሰቡ ላይ ዘረፋ በመፈፀም ላይ እንዳሉ ክፍለጦሩ በሰራው ኦፕሬሽን ሙሉ ሌቦችን በቁጥጥ ስር ማዋሉ ይታወሳል።

በወልቃይት ጠገዴ ወረዳ አዲሲቱ ወልቃይት ቀበሌ አንድ የቀይ መስቀል ሰራተኛ፣አንድ ሹፌር እና ነጋዴ በአምስት ዘራፊ ሀይሎች ታግተዉ በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አራተኛ ደጃዝማች ኮር ተከዜ ክፍለጦር ነፃነት ብርጌድ እንዲለቀቁ መደረጋቸዉን የተከዜ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ አበበዉ ወርቁ ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግሯል።

ዘራፊ ኃይሎችን የማፅዳት ዘመቻዉ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ዘራፊ ኃይሎችን ከቀጠናው ሙሉ ለሙሉ ለማፅዳት ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ዉይይት መደረጉንም ጭምር ኃላፊው ተናግሯል።

ፋኖን እና ማህበረሰቡን ለመነጠል በአገዛዙ ብልፅግና በኩል ተልዕኮ የተሰጣቸዉ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች የቀይ መስቀል ሰራተኞች በማገት የፈፀሙት ህገወጥ ድርጊት በፋኖ እና በማህበረሰቡ ትብብር እንዲከሽፍ ተደርጓል ያለዉ አርበኛ አበበዉ ወርቁ ይህ ሆን ተብሎ የሚደረገዉ ደግሞ በገንዘብ ተገዝተው ፋኖን ከማህበረሰቡ ለመነጠል ነዉ ሲል ገልጿል።ማህበረሰቡ የአገዛዙን ብልፅግና ሴራ በመረዳቱ በዚህ ተግባር የተሰማሩ ሌቦችን አጋልጦ እየሰጠን ይገኛል ብሏል።

አርበኛ አበበዉ ወርቁ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ተከዜ ክፍለጦ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ !!!!!!!!
🙏2
አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ
ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
  ጦርነትን መቋጫ ከሆኑት ስልቶች መካከል በዋናነት የጠላትን ሀይል ማናጋት ፣እረፍት መንሳት ፣መበተን  እና መደምሰስ  ዋናዎቹ ናቸው። 
   የአብይ አሕመድ መዋቅር  የሚተማመንበት የፖለቲካ ተሰላፊ ማህበረሰብ እንዳይኖረው ካደረግን አመታት አልፎናል። የሚደገፍበት ማህበራዊ መሠረቱ በሁሉም  የኢትዮጵያ ክፍል አጧል። አሁን ያለኝ የሚለው አማራጭ በሀይል ደፍጥጦ መግዛት ነው ።ለ7 አመታት ያክል ሞከረው ሀይልሉንም ፣ተተኳሹንም ፣መሳሪያውንም ተቀብለነዋል። የቀረው አማራጭ በድንገት  አንድ ቀን ፈርጥጦ  ጥገኝነት  መጠየቅ ነው።
ይህን የተረዳው ሕዝባችን በነቂስ በመውጣት ከፍኖ ጎን በመሰለፍ  እየተፋለመ ይገኛል። እንደ ሕዝብ የመጣውን እንደ ሕዝብ መመከት ላይ እንገኛለን።
የአፋብኃ  ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለጦር  ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ከየዘለቃ እነወንድ የግል ባለመሳሪያዎች ጋር በጥልቀት በመወያየት ጠላት ፈርጥጦ ጥገኝነት እንዲጠይቅ  በማድረግ ረገድ ሀላፊነት ወስደው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህን የፋኖ ጥንካሬ ያዩ እና የደረሰባቸውን ምት መቋቋም ያቃታቸው የአረመኔው ሰራዊት አባላት ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። በጋራ በመሆን ከ16 በላይ የሚሆኑ  የጠላት ሃይል አብራጅት ብርጌድን እና ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!

አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

        ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
1
ሰበር መረጃ!

ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የጠላት ወታደራዊ የማዘዣ ቦታ የሆነችውን ደጎማ ከተማን ከበባ ውስጥ በማስገባት በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ።

ዛሬ ጥቅምት 04 / 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር መብረቅ ክ/ጦር ፣ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ፣ ፋናየ ውቤ ክ/ጦርና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ነብዩ አሳምነው ብርጌድ በ4 አቅጣጫ ከጠላት ምሽግ ድረስ በመግባት የጨበጣ ውጊያና ቦንቦ ውርወራ የደረሰ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አድርገዋል።

በሴጋ ፣ በአንባጨራ ፣ በአንባ ዙሪያና በደንጎርሳ ምሽጎች የጠላት ኃይል የተቀጠቀጠ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ጥምር ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።

ከማክሰኝት ደጎማና ከአርባያ ደጎማ የሚወስዱ ሁለቱን መንገዶች ዝግ በማድረግ ውጊያው የተካሄደ ሲሆን የጠላት ኃይል ድጋፍ ለመስጠት በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ መግባቱም ታውቋል።

በዚህም ሰበብ ክፋኛ የቆሰሉትን የጠላት ኃይላት ወደ ከፍተኛ ህክምና ማድረስ አለመቻላቸውም ተገልጿል።

በውጊያው የተገኙ ድሎች መካከል
** 15 እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።
** 23 ቁስለኛ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በደጎማ ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ ታውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በትላንትናው እለት ጥቅምት 03/ 2018 ዓ.ም በ6 አቅጣጫ ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦርንና ታድሎ ብርሃን ክ/ጦሮችን ለመበተን ከፍ ሲልም ደግሞ ለመደምሰስ በሚል አቅዶ የመጣውን የጠላት ኃይል አሳፍረው መመለሳቸው ታውቋል።

ውጊያው ከምንዝሮ አርሴማ እስከ አይባ ደንቀዝ ከፍተኛ ቦታዎችን ያካለለ ሲሆን የጠላት ኃይል ከፍተኛ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ኪሳራዎችን አስተናግዶ ሊመለስ ችሏል።

ከአዘዞ ፣ ከአምባ ጊዮርጊስ ፣ ከደጎማና ከአርባያ ተውጣጥቶ የመጣው የብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል የዘወትር ግብሩ የሆነውን ሞትና ቁስለትን በክንደ ፈርጣማዎቹ ፋኖዎች ተከናንቦ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ወደመጣበት እየተመለሰ መሆኑ ታውቋል። በውጊያው 9 የሞተ ሲሆን 6 ቁስለኛ ተደርጓል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ጥቅምት 04 / 2018 ዓ.ም
1
ከእንግዲህ ክተት ብለህ የምታስፈጀው የአማራ ገበሬ የለም : አማራ የሚዋጋው ለህልውናው ነው።

ያለ ፋኖ ጥሪ የሚዘምት አማራ ፤ ያለ ፋኖ ቡራኬ የሚንቀሳቀስ ታጣቂ አይኖርም።

ብሔራዊ አጀንዳ እያመጣችሁ የአማራን ገበሬ በጦርነት እሳት እየማገዳችሁ ሲያሻችሁ ዳር ቆማችሁ የምትሞቁበት አለፍ ሲል የአማራን ሞት በጀት ማወራረጃ የምታደርጉበት ዘመን በፋኖ ክንድ ተጠናቋል።

አዲሱ ትውልድ እንኳን ፊት ለፊት ያለውን የኢትዮጵያ እና ምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ዓለም የያዘችውን ድብቅ ምስጢር ጠንቅቆ የሚያውቅ ሐይል ነው።

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያለውን አማራ በማንቃት ፣ በማደራጀት ፣ በማስታጠቅ ወደ ጠላቱ እንዲተኩስ እያለማመድነው እንገኛለን ።

ይህ ልምምድ መጨረሻው ምን እንደሚሆን በመጭዎቹ ጥቂት ጊዜያት እናንተም ዓለምም የሚያየው ጉዳይ ይሆናል።

ከእንግዲህ በአሻጥር የሚታለል ፣ በጥቅም የሚደለል የአማራ መሪ ወደፊት የሚመጣ ይመስልሃል !?

@ማርሸት ፀሐይ ደምሴ
👍1
በርካታ የብልፅግናው ሚሊሻ አባላት ፋኖን ተቀላቀሉ።

በሸዋ መርሀቤቴ አውራጃ በሚዳና ሬማ ከተማ ዙሪያ በብልፅግናው ፕሮፖጋንዳ ተታለው ከፋሽስቱ አገዛዝ ጋር ተሰልፈው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ህዝባቸውን ሲበድሉ ቢቆዩም በቀጠናው ከተሰማራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር ያቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

ሁለተኛ ሳምንቱን ባስቆጠረው በቀጠናው እየተካሔደ ባለው ተከታታይ አውደ ውጊያ የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ከመቸውም ጊዜ በላይ ያለ የሌለ ሀይሉን በሬማ ቀጠና ዙሪያ እያሰለፈ ይገኛል።

ከለሚ፣ ከመርሀቤቴ አለም ከተማ፣ ከመንዝ ግሼራቤል እና ከሚዳ መራኛ ከተማ በርካታ ሜካናይዝድ ሀይሉን ወደ ሬማ ከተማ በማንቀሳቀስ ሙሉ አቅሙን የተጠቀመ ሲሆን ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር እልሕ አስጨራሽ ተጋድሎ እያደረገች መሆኑን ክፍለጦሩ አስታውቋል።

ይሕ በእንዲሕ እንዳለ ሰራዊቱ በገፍ እየፈረሰበት ፣በአይበገሬው ሰራዊታችን ጠንካራ ክንድ እረፍት ያጣው የአማራ ጠሉ የብልፅግናው ወራሪ ሰራዊት በዝሕ ሰዓት በሬማ አጎራባች ወረዳ በሆነችው በደራ አማራዎች ላይ ከሚዳና ደራ ከሁለት አቅጣጫ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ የደረሰውን የገበሬዎችን አዝመራ እና ቤቶችን እየተቃጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
4🙏1
ሰበር አዲስ ቅዳም‼️

19 ተመክሮ አይድን በጥዋቱ ተሸኝቷል!

ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ/ም ከለሊቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ አዲስ ቅዳም ከተማ ዉስጥ በመግባት ባደረገችዉ የእጅ በእጅ ዉጊያ የታገዘ ድንገተኛ ኦፕሬሽን በጠላት ላይ ከፍ ያለ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

በዚህ ከለሊቱ 12:00 ስዓት እስከ እረፋድ 5:00 ስዓት ድረስ ለተከታታይ 5 ስዓታት በቆየ ልዩ ኦፕሬሽን
አዲስ ቅዳም ስላሴ ፣ አባ አይናለም ፣ከብት ገበያ እና ባታ ቤተክርስቲያን መሽጎ የነበረዉ ከሞት የተረፈ ጠላት በፋኖዎች አረር የተሸኙ 19 እድለቢስ ጓዶቹን ሳያነሳ ቁስለኛ እና ቁሳቁሱን በእየ ሜዳዉ እያንጠባጠበ ሙሉ በሙሉ ምሽጉን በመልቀቅ ወደ አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧል።

አጠቃላይ በዛሬዉ የአዲስ ቅዳም ከተማ ልዩ ኦፕሬሽን
_19 የብልፅግና ታጣቂ ሲወገድ
_27 ቁስለኛ ሁኖ
_16 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ብዛት ካለዉ ተተኳሽ ጋር በምርኮ ገቢ ተደርጓል።

ፋኖነት አሸናፊነት‼️
Estibel A Zerihun
🙏62
[ ከአርበኛ ሸጋ ጌታቸው/ ቋረኛው የተላለፈ መልዕክት ]

ጠላቶቻችን አጠፋናቸው ሲሉ በዝተን የምናድር  ባልዋልንበት ሲያውሉን በእውነት የቆምን።

እንደ ወርቅ የነጠርን እደ ብረት የተነከርን የግዜው የነጻነት ምጽአት ነን በእውነት የቆምነን የነጻነት ምሳሌ ነን።

ብቻ እንጠንክር የዘመኑ ነጻነት እኛው ነን።
ለመከራ የተፈጠርን ሳይሆን
ለነጻነት የታደልን ልጆች ነን።

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በለይ ዘለቀ እዝ
ም /ክ/ ወታደራዊ አዛዠ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው !

ህልውናችን በተባበረ ክዳችን !
🙏3
ሁለት የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት አባላት በደፈጣ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በ602ኛ ኮር 7ኛክ/ጦ 5ኛ ሬጅመንት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት በአባ ኮስትር ብርጌድ የውስጥ የመረጃ ደህንነት ክትትል በተሰጠው የደፈጣ ኦፕሬሽን ሁለት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

1ኛ.ኦብሳ አብዴላ ብሬን ተኳሽ እና ድሽቃ ምድብተኛ እና
2ኛ.አብድል ኑር ረዲ አህመድ ሞርተር ተኳሽ ድሽቃ ምድብተኛ የነበረ የካባቢውን ማህበረሰብ አለባበስ በመመሳሰል በጉዞ ላይ እንዳሉ በአባ ኮስትር ብርጌድ የውስጥ መረጃ ደህንነት ክትትል አማካኝነት በኮስትር ልጆች በደፈጣ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት አባላት አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ግፍ፣እና በደል በመረዳ አገዛዙን በመክዳት ወደ ቤተሰቦቻችን ለመሄድ በጉዞ ላይ እያለን ነው በአባ ኮስትር ብርጌድ የፋኖ አባላት በቁጥጥር ስር የዋልነው ብለዋል።

አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!
        ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
🙏1
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ከሰፈረው በኮሎኔል መብሬ አስማማው ዋሴ ከሚመራው አድማ ብተና መካከል የ22ተኛ ሻለቃ አዛዥ የሆነው ኢ/ር አዝመራውን መደምሰሱ ተረጋገጠ::

ከደቡብ ወሎ ዞን መቀመጫ ደሴ ከተማ በስተምዕራብ ከሚገኙት 11 ወረዳዎች አንዷ የሆነችው መሀል ሳይንት ወረዳ መቀመጫ ደንሳ ከተማ ውስጥ ሰሞኑን በተከታታይ ለ3 ቀናት የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት የማጥቃት እርምጃ ወስዶ የጠላትን ኃይል መደምሰሱ፣ ማቁሰሉ እና መበታተኑ የተገለፀ ሲሆን ኮሩ ካቀፋቸው ክፍለ ጦሮች መካከል የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር፣ መብረቅ ክፍለ ጦር እና ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የተወሰኑ አሃዶች በውጭጩ ወደ መሀል ሳይንት የላኩት ኃይል ከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፅሞ ከአድማ ብተና ሻለቃ አዛዥ በተጨማሪ የኮሎኔል መብሬ አስማማው ዋሴ አጃቢ የሆነ ስናይፕር ተኳሽ እንዲሁም ሔኖክ የተባለ የ22ተኛ ሻለቃ ዘመቻ መሪን እና 3 የብልጽግና አመራሮችን ከበርካታ የጠላት ሰራዊት አባላት ጋር መደምሰሱ ተረጋግጧል::

የመሀል ሳይንት ወረዳ ኮማንድ ፓስት ከዚህ ቀደም የያዛቸው የግፍ እስረኞችን ሰብስቦ ወደ ካምፕ ወስዶ ለጦርነት ከለላነት እንደተጠቀማቸውም ታውቋል:: ደንሳ ከተማ ዳር እየተገነባ ያለው ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የመሸገው ጠላት የሆስፒታሉን ህንፃዎች እና እስረኞችን እንደ ጋሻ ተጠቅሞ ራሱን ለመከላከል ቢሞክርም እነ ሞት አይፈሬ ካምፑን ተጠግተው በቦንብ ስላጋዩት ብትንትኑ ሊወጣ ችሏል::

የደንሳውን ድንገተኛ ኦፕሬሽን ተከትሎ አንድ ጋንታ አድማ ብተና ሙሉ በሙሉ ተበትኗል:: የጋንታው አባላት ከነበሩት ሶስቱ ወደ ኮሩ ሰራዊት በገዛ ፍቃዳቸው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ሲከዱ 15 ሰላም አስከባሪዎችም ጠላትን ከድተዋል::

የኮሩ ሰራዊት ደንሳ ከተማን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር የጠላት ኃይል ከጎረቤት ወረዳዎች የሰው ኃይል ጭማሬ ጠይቆ ከመካነሰላም በኩል አጋዥ ቢላክለትም አስከሬን አጅበው ቀብር ከመፈፀም ውጭ የሰጡት የተለየ ድጋፍ የለም:: በዛሬው እለት ማለትም መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጭምር የለቅሶ ስነ-ስርዓት ላይ ጥይት ሲተኩሱ ማርፈዳቸውን ነው ለማወቅ የቻልነው:: ከትናንት በስቲያ አመራሮች ሲቀበሩም የቡድን መሳሪያ ተኩስ ጭምር እንደነበር ተረጋግጧል::

የደንሳውን ኦፕሬሽን የመሩት የምኒልክ ዕዝ ም/ዘመቻ መሪ ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ፣ የዕዙ ም/ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ፣ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አዛዥ ሻለቃ አብነው ታደሰ፣ የባለሽርጡ ክፍለ ጦር ወታደራቂ አማካሪ ሻለቃ ክንዱ ሰውነት፣ የባለሽርጡ ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ መቶ አለቃ ታደሰ አስፋው እንዲሁም የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ወታደራዊ አዛዥ ፋኖ አበበ መኩሪያ እና የኮሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ጌትነት ሲሆኑ በኮሩ ስር ካሉት ክፍለ ጦሮች መካከል ከ3ቱ የተውጣጣ ኃይል በመያዝ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ መፈፀም ተችሏል:: በተለይ የ22ኛ ሻለቃ አዛዥ ኢ/ር አዝመራው እና ሔኖክ የተባለው የሻለቃው ዘመቻ መሪ መደምሰሳቸው የጠላት ኃይልን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶት የተበተኑትም ተመልሰው ወደ ካምፕ አለመግባታቸውና አድራሻቸው መጥፋቱ ታውቋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም
4🙏1
ሰበር ሰበር ዜና!!!

ወንድሞቻችን አንድ ሁነዋል!!!
ፍቅር አሸንፏቸዋል!!!
የአማራ ህዝብን አስቀድመዋል!!!

መልካም ዜና🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🥰4🙏1