ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ለአባ ኮስትር የብርጌድ አመራሮች እና አባላት የፖለቲካ ትምህርት የሰጡበት መድረክ በፎቶ።

የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ማርሸት ፀሀዩ፣ አርበኛ ጥላሁን አበጄ፣ የፖለቲካ መኮንኖች፣ የክፍለ ጦር እና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት የአባ ኮስትር ብርጌድ አመራር እና አባላት ጥልቅ የሆነ የፓለቲካ ትምህርት ተሰጥቷል።

መስከረም 24/2018 ዓ.ም
የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች እና ከመምህራን ጋር የሚደረኩ ውይይቶች እንደቀጠሉ ናቸው።

የአ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮሰ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ብርጌዶች ደባይ ጮቄ ብርጌድ በደባይ ጥላትግን የዳማ፣ ወደብ እየሱስ፣ ቅድሰቴ ቀበሌ፣ ዛምበረሃ ብርጌድ በደጀን ጥርጭ እና ጀባ ቀበሌ፣ ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በሸበል በረንታ ሱሃ ተፋሰስ ቀበሌ እንዲሁም አባ ኮስትር ብርጌድ በእነማይ ቀሸምሽ ቀበሌዎች ላይ ሰፋ ያለ ህዝባዊ ውይይት አካሂደዋል።

       መስከረም 30/2018 ዓ.ም
@ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
ከአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🙏1
የድል ዜና

ትናትና በቀን 29/01/2018 ዓ/ም የ አ ፋ ብ ኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ  አፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ቃኚ ቡድን በአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ መከላከያ ሰራዊት ላይ በመርሀ-ቤቴ ገርን ቀርጫ በተባለ ቦታ አስደማሜ ጀብድ መስራታችን ይታወቃል።

የአብይ አህመድ ሚኒሻ በጀግኖች የአሳምነው አናብስቶች አይቀጡ ቅጣት ከመቀጣትም አልፎ ሙትና ቁስለኛ የሆነበትም ነበር።
ይበንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሚኒሻ
የሞተ =8
ከባድ ቁስለኛ =3
ቀላል ቁስለኛ= 4
እንዲሁም በተረጋገጠ ዜና የብርሃኑ ጁላመከላከያ
የሞተ = 7
ቁስለኛ =10 ሆኖ ከሞቱት ሚሉሾች ውስጥ የተወሰኑት በስም ዝርዝር አካተናል!!

የተማረከ ክላሽ = 2 ከእነ ሙሉ ትጥቅ ከ120 የክላሽ ፍሬ ጋር ሲሆን አንድ የመንግስት ፓትሮል ከጥቅም ወጭ የሆነ : ሽንፈቱን መቋቋም ያቃተው አረመኔ አገዛዝ የሞተበትን አስክሬን እና ቁስለኛ ሲያስጭን ከቆየ በኋላ በደረሰበት የሰውና የንብረትም የተበሳጨው አገዛዙ የበደል ብትሩን ዘግናኝ በሆነ መንገድ በንፁኃን ላይ ፈፅሟል።

በመሆኑን አያሌው በሽዬ የተባለ የ45 አመት አዛውንት በገረን ቀበሌ ኗሪ የነበረና እና በአፈዘዝ ቀበሌ ይኖር የነበረ ጎለምሳ ወጣት ትርሻ ገብሬ የተበለ የ40 አመት ጎረምሳ እረሽኗል።

በሌላ ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ-ያዕቆብ 1ኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ደመላሽ ሻለቃ ዛሬ በቀን 30/1/2018 አ.ም ከከሌቱ 9:00 በዲሽቃና ሞርተር የጦር መሳሪያ በታገዘ አውደ ውጊያ በከርካሜ፤ ፈርድውሃና ሌመን አካባቤ መሽጎ የነበርውን የብርሃኑ ጁላ ወንበር አስጠባቂ ሚሻና መከላከያ በአጣዬ ሆስፒታል የሚገኝ 8 ከባድ ቁስለኛ በማድረግና የቀሩት እና የሞቱን የአሳምነው አናብስቶች ከንጋቱ ጀምሮ ደፈጣ በመያዝ እሬሳ አላስነሳ ስላሉት አሁን ከተለያዩ ቦታዎች ኃይሉን በማሰባሰብ ላይ የሚገኝ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን በነገው እለት የምናሳውቅ ይሆናል።

መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ተዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ 1ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው።
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳች"
አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
2🙏1
ሞት አይፈሬው አባይ ሸለቆ ብርጌድ ታላቅ ተጋድሎ ፈፅሟል

የ9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ ከመርጡለ ማርያም ከተማ እስከ ጉናጉና አቡነ ሀቢብ በተዘረጋው ውጊያ በአራት አቅጣጫ ባደረገው ተጋድሎ ድል ተቀናጅቷል ።
በመርጡለ ማርያም ከተማ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል የመሸገውን የአገዛዙን ሰራዊት ድባቅ በመምታት የጀመረው የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ትንቅንቅ በርካታ የአረመኔውን ሰራዊት በመደምሰስ ምርኮኛ ማድረግ ችሏል።በሆስፒታሉ የመሸጉ የአረመኔው ሰራዊት እና የፖሊስ አባላት ገሚሶቹ ሲማረኩ ፻ አለቃ ደሳለኝን ጨምሮ በርካቶች ተገድለዋል።

በአቡነ ሀቢብ ቤ/ክርስቲያን ላይ በነበረው ሌላኛው ትንቅንቅ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የተደረገ ሲሆን ከ50 በላይ የአረመኔው ሰራዊት በምሽጋቸው ተቀብረዋል ።ከጉናጉና እስከ አሉሻ ከሰዓት በተደረገው ፍልሚያም የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ከፍተኛ የጠላት የጦር አዋጊዎችን ጨምሮ ብዙዎችን የአድማ ብተና አባላት ደምስሷል።

ከመካነ ሰላም መርጡለ ማርያም እየተወረወረ አስደናቂ ጀብድ እየፈፀመ የሚገኘው አባይ ሸለቆ ጠላት የተቆጣጠራቸውን ወሳኝ ቦታዎችን መቆጣጠር ችሏል ።በዛሬው ታላቅ ገድልም መርጡለ ማርያም ከተማ በመግባት የጠላትን ኃይል በመማረክ የድል ግስጋሴውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
🙏1
ፋኖ የጦርነት ህግ አክባሪ መሆኑን በተግባር አስመስክረናል።

አለማቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር (ICRC) ወደ ቀጠናችን በመግባት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የአለማቀፍ ህግን በማክበርና ጥበቃ በማድረግ ተቀብለን አነጋግረናቸዋል።

በዚህም፦
1. በዘመቻ አደም አሊ የቆሰሉና ከፍተኛ ጉዳት ያለባቸውን 16 የአገዛዙ ሰራዊት አባላትን በዕዙ ኮማንድ አባላት ዉሳኔ ተሰጥቶበት በዕዛችን ጤና መምሪያ በኩል ፈርመዉ ወስደዋል። ይህም የፋኖ ትግል የአለማቀፍ የጦርነት ህጉን አክባሪ መሆኑን በተግባር አሳይተናል።

2. አገዛዙ ምርኮኛ እንደሌለው አድርጎ የከዳቸዉ ምርኮኞችን እንዲጎበኙ አድርገናል። በምርኮኞች አያያዝ እጅጉን መደሰታቸውን አረጋግጠዉልናል።
3. ተቋሙ(ICRC) ፍፁም ገለልተኛ ሆኖ ዕዛችን በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በሚሰራቸው ጉዳዮች ላይ ተግባብተናል።

ምንጭ፦ በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና የምኒልክ ዕዝ ፖለቲካዊ ጉዳዮች መምሪያ ክፍል!
3