ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

በሰሞኑ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በርካታ ሰራዊቱ የተደመሰሰበትና የተማረከበት ብልፅግና ከወለጋ ያመጣው የማዕከላዊ ዕዝ ሰራዊት ከወልድያ እየጠፋ ምኒልክ ዕዝን እየተቀላቀለ ነው::

ሰሞኑን በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከባድ ሽንፈት የገጠመው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና
የተደመሰሰበትንና የተማረከበትን አምስት ክፍለጦር ሰራዊት ለመተካት ከተለያየ ክልል ያመጣው ምልምል ሰራዊት ወልድያ ከደረሰ በኋላ እየጠፋና እየኮበለለ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን መስከረም 29/2018 ዓ.ም ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ሰባት አሳምነው ክፍለጦር ሁለት አጠቃላይ ዘጠኝ የሰራዊቱ አባላት ተቀላቅለዋል:: ኮሎኔል ሞገስ ዘገየን ጨምሮ የምኒልክ ዕዝ የክፍለጦር የኮርና የድርጅት ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል::

ኮብልለው ፋኖን የተቀላቀሉ የማዕከላዊ ዕዝ አባላት የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋትና ወረራ እየፈፀመ ያለው ብልፅግና ሁሉንም ነገሩን አሟጦ አማራ ላይ ወረራ እየፈፀመ ስለሆነ አማራ ሆነን አማራ ላይ ወረራ አንፈፅምም እንዲያውም እድሉን በማግኘታችን ደስተኛ ነን እንታገለዋለን ብለዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
መስከረም 30/2018 አ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

አሳዛኝ ዜና!!!
የአገዛዙ ሰራዊት ከጫካ ጭንብል ለባሽ ሚኒሻዎች ጋር በመሆን በህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋን ፈፀመ።

መስከረም 23/2018 ከጎንደር ገንዳውሀ ብዛት ያለው የህዝብ ተሽከርካሪ በአገዛዙ ሰራዊት እየታጀበ በጉዞ ላይ እያለ ከመቃ በትንሽ ኪ.ሜ ርቀት ግራር ከምትባል ቦታ የጉዞው ታሪክ ተቀይሮ ሌላ መልክ ሊይዝ ችሏል። በማይታሰብ መልኩ የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት የአማራን ህዝብ እንደ ሂሳብ ማወራረጃ ቀብድ መያዣ አድርጎ የጥፋት መንገዶችን እየፈበረከ በሰበባሰበቡ ንፁሀን የአማራውን ህዝብ ለእልቂት እየዳረገ የቆየ መሆኑ ይታዎቃል። በዚሁ ቀን የተፈፀመው ደግሞ በጣም ከባድ የጭካኔ ልክ ድራማቲክ በሆነ መልኩ እዚህ ቦታ ላይ ሲደርስ ከእጀባ የተመለሰ በመምሰል ከፊት ለፊት አካባቢው ላይ ያሰማራቸውን ጭንብል ለባሾችን በማድረግ እና ከኋላ ጨፍጫፊው የአብይ ሰራዊት በመሆን በሁሉም የህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ ተኩስ በመክፈት
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ንፁሀንን ለእልቂትና ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ዳርጓል።

አካባቢው ላይ ኔት ወርክ በማጥፋት ቁስለኞችን ህክምና ለማድረስም ሆነ መረጃዎችን ለማጠናከር ተግዳሮት የሆነ ሲሆን፣ ለጊዜው ቁጥራቸው የደረሰን ሴቶችንና ህፃናትን ጨምሮ ከ18 በላይ የተሰው ሲሆኑ ከ35 በላይ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።

ማሳሰቢያ: በምዕራብ ጎንደር በመተማ እና አጎራባች ወረዳዎች አማራና ቅማንት ለዘመናት በአብሮነት ተከባብሮና ተጋምዶ በፍቅር የሚኖርን ማህበረሰብ፣አሁን ላይ በተለየ መልኩ የብልፅግናው አገዛዝ በመካከል ጠባጫሪ አጀንዳዎችን ፍፁም ተለዋዋጭ የሆነ ሴራ፣ በስውር ከፍተኛ በጀት በመመደብ የውስጥ ጉዳይ አስፈፃሚዎችን ወክሎ እየሰራ ይገኛል። ስለሆነም የእርስ በርስ የማህበረሰብ ፍጅትን ለማስፈፀም የሚደረግን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ማህበረሰቡ ነቅቶና አውቆ አካባቢውን እንዲጠብቅና የዚሁ ተግባር አካል የሆኑትን የታጠቁም ሆነ ያልታጠቁ ቅጥረኞችን በአካባቢው ለሚገኝ የፋኖ ሰራዊት መረጃ በመስጠት እንድትተባበሩ ስንል ልባዊ ጥሪያችን ማስተላለፍ እንወዳለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
መስከረም 25/2018
አገዛዙ ብልፅግና በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉሀ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰላማዊ ዜጎች ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ።

በመንግስት አካላት የተደራጁ የቅማንት ፅንፈኛ ኃይሎች በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ተደጋጋሚ ወንጀሎችን መፈፀማቸዉን ተከትሎ የገንዳ ዉሀ ከተማ እና አካባቢው ኗሪዎች ይህንን ድርጊት ለማዉገዝ ወደ አደባባይ ቢወጡም በአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር እንዲበተኑ ተደርገዋል።

ፀረ አማራው የብልፅግና ጥምር ጦር ድምፃቸዉን ለማሰማት ወደ አደባባይ በዉጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ተማሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች መታሰራቸዉ ታዉቋል።

ዝርዝሩን በማታ የዜና እወጃችን ይጠብቁን
1
ሰበር ዜና!

ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር በደፈጣ የጠላት ድሽቃ ተኳሽን ጨምሮ ሌሎችንም የጠላት አሽከሮች ደመሰሰ።
       
ዛሬ መስከረም 30/2018 ዓ.ም  ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ  ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦርና ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር አሃዶች በጥምረት ምንዝሮ ላይ የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረጋቸው ታውቋል።
   
ሰሞኑን ጠላት ግብስብስ ኃይሉን የቦታ ቅይይር እያከናወነ መሆኑን ተከትሎ ከጎንደር ወደ ማክሰኝት ከ30 በላይ ተሽከርካሪዎችን አጅበው በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩ የአድማ ብተና አባላት ላይ የማያዳግም እርምጃ  ተወስዷል።
  
በእጀባ ላይ የነበረው የአድማ ብተና አባላት ሲያጅቡት የነበረውን ተሽከርካሪዎች በመተው ወደ ማክሰኝት አቅጣጫ መፈርጠጣቸውም ታውቋል።
    
በደፈጣ ጥቃቱም የድሽቃ ተኳሹን ጨምሮ 11 የአድማ ብተና አባላትን እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል። ከ8 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
          
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
           
@አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ ፋኖ አብነት ሞላ
                      መስከረም 30/ 2018 ዓ.ም
🙏3
አገዛዙ ብልፅግና በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉሀ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰላማዊ ዜጎች ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ።

በመንግስት አካላት የተደራጁ የቅማንት ፅንፈኛ ኃይሎች በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ተደጋጋሚ ወንጀሎችን መፈፀማቸዉን ተከትሎ የገንዳ ዉሀ ከተማ እና አካባቢው ኗሪዎች ይህንን ድርጊት ለማዉገዝ ወደ አደባባይ ቢወጡም በአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር እንዲበተኑ ተደርገዋል።

ፀረ አማራው የብልፅግና ጥምር ጦር ድምፃቸዉን ለማሰማት ወደ አደባባይ በዉጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ተማሪዎች፣የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች መታሰራቸዉ ታዉቋል።
4
በባህርዳር ዙሪያ አገዛዙ ያወደማቸው የጤና ተቁአማትና ት /ት ቤቶች
1
ሸር ሸር ይደረግ!

የአገዛዙ ሰራዊት እየፈፀመ ያለውን ነውረኛ ተግባር ልናጋልጥ ይገባል።

የአገዛዙ አረመኔው ሰራዊት መምህራን እና የት/ቤት ጥበቃዎችን እንዲሁም አርሶ አደሮችን አፍኖ ወስዶል።
1ኛ.መ/ር ባዩሽ ተሹ
2ኛ.አቶ ታምሩ እስከዚያ እና ሁለት አርሶ አደሮችን በሁለት አምባ ዲቢሳ ቀበሌ ኖሪ የነበሩ አርሶ አደረሮችን አፍኖ አፍኖ መውሰዱን ማረጋገጥ ችለናል።

በእነማይ ወረዳ ሁለት አንባ ዲቢሳ ቀበሌ መምህራን፣ የት/ቤት ጥበቃ እንዲሁም አርሶ አደሮችን አፍኖ መውሰዱን ማረጋገጥ ችለናል። የአገዛዙ አረመኔው ሰራዊት #የሀሰት_ደረሰኝ በማዘጋጀት ፋኖን ማርከናል : ፋኖ እጅ ሰጥቷል : የፋኖን አመራር ይዘናል : እያለ የውሸት ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጨው ውሸት መሆኑን ልናረጋግጥላቹህ እንወዳለን።

በዛሬው እለት መስከረም 30/2018 ዓ.ም በሁለት አምባ ዲቢሳ ቀበሌ በአርሶ አደሮች በተኙበት በቤታቸው ላይ ከበባ በመፈጸም "4" ፋኖዎችን ማርከናል የሚለው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ያሰራጨው መረጃ #የሀሰተኛ_ፕሮፖጋንዳ እና #መሰረት_ቢስ መሆኑን እና በአገዛዙ አረመኔው ሰራዊት የተያዙት ግለሰቦች ንፁሀን አርሶ አደር፣ መምህር፣ የት/ቤት ጥበቃ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችለናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተስፋ የቆረጠው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ወደፊትም አርሶ አደሮችን በመያዝ ፋኖ ማርከናል የሚል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሊሰራ እንዳሰበ ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠናል።  
                                                                           መስከረም 30/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ፣
🙏1