ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
✍️ ሚዲያ ከማያውቃቸው ዝምተኛ የጎንደር አርበኞች መካከል ዛሬ አንድ የአርማጭሆ ጠገዴ ጀግና ላስተዋውቃቹህ~~👇👇

✍️የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የፋይናንስ መምሪያ አላፊ የሆነው በርካታ ስራዎችን እየሰራ የዋዋ ጎቤ ክፍለጦር መስራችና ምክትል አዛዥ በመሆን ከአርበኛ ሲሳይ አሸብር ከአርበኛ ሱጦታው መልኬ ጋር በመጣመር ከዘመነ ወያኔ የከፋኝ የአርበኝነት ትግል እስከ ሰሜኑ ጦርነት ቀጥሎም የአሁኑ የኦሮሙማ አገዛዝ ድረስ በመፅናት ለጎንደር ትግል መጠናከር አይነተኛ ሚና ያለው ቀናው መልከ መልካሙ ባለግርማ ሞገሱ ቀደምት ስመጥር አርበኛ በለጠ አዱኛ ይባላል::

አርበኛ በለጠ አዱኛ ከልጅነቱ ጀምሮ ለወያኔ ያለተገዛ ያላጎበደደ እምቢተኛው ጀግናችን ሲሆን ጀግና ማብቀል ከለመደው አርማጭሆ ወልቃይት ጠገዴ ካፈራቻቸዉ ጀግኖች መካከል አንዱ እና ዋነኛ ግንባር ቀደሙ ቆራጡ አርበኛ ነዉ ።

✍️አርበኛ በለጠ ተረኛዋ በዘመነ ወያኔ ትግል በዋናነት ከ2008ዓ.ም ጀምሮ የታገለ እና በአሳምነውነት የትግል እንቅስቃሴ ከእነ አርበኛ ሲሳይ አሸብር ፤ ከእነ ሱጦታው መልኬ ከሌሎችም የአርማጭሆ ጠገዴ ጀግኖች የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን ፋኖን በማደራጀት አይነተኛ ሚና ያለውና ለወያኔ መገርስስ እና መቀሌ መመሸግ ጉልህ የአርበኝነት ታሪክ በማስመዝገብ ቀጥሎም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጀምሮ የፋኖ መሪ በመሆን የተበታተነውን የፋኖ መዋቅር በማደራጀት ከአብራጅራ በመነሳት ጦሩን አዝምቶ ድል በመቀዳጀት ማርኮ አስታጥቆ የወያኔን ወራሪ በመመከት ወልቃይትን በማስመለስ ጀብድ በመስራት በድል የተመለሰ ሲሆን ለዚህም በወልቃይ ሰቲት ሁመራ ዞን ከሌሎች በርካታ የጎንደር አርበኞች ጋር የእርሻ መሬት ጭምር ተቀብሎ የነበር ቢሆንም በካህዲዎች ፋኖነትን በመካድ ለምን የኦሮሙማ ነጻ አውጭ ስርአታችን ተዋጋቹህ በሚል ጀግንነታቸውን በመካድ ለኦሮሙማ ስርአት የተወሸሙ ብአዲኖች አማካኝነት መሬት ከተወረሱት መካከል እሱ አንዱ ነው እሂን ካነሳነው አይቀር ሆቴሉን ሀብት ንብረቱን ትራክተሩን የቤተሰቡን ሀብት በወልቃይት ብአዲኖች የተወረሰውን ቤተሰቡ የተሳደደበትን የታሰረበትን ምረሽ ካልገባህ የቤተሰቦትህ ሀብት ንብረትም ይወረሳል እየተባለ እንደ እነ አርበኛ አስፋው ሰርጸ እና ሌሎችም የጎንደር የአርማጭሆ ጠገዴ አርበኛ ቤቱ ይቁጠረው.. ።

✍️ከሰሜኑ ጦርነት መልስም አማራን አንድ ለማድረግ ከሽዋ ከወሎ ከጎጃም ያሉ የፋኖ አርበኞቻችን ለአብነትም እነ አርበኛ በለጠ ሸጋው፤እነ አርበኛ አበበ ሙላቱ፤እነ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ፤ እነ አርበኛ ዶክተር ወንድወሰን ፤እነ አርበኛ መንበር አለሙ፤ እነ አርበኛ 50አለቃ ኮማንዶ ጌታቸው ሲሳይ ፤እነ አርበኛ ጥላሁን አበጀ ሌሎችም ጀግኖች የአማራን ፋኖ አንድ ለማድረግ ከእርቀት ተነስተው ጎንደር አብራጅራ ኮረደም ጓንጓ ቀጠና #የአማራ_ፋኖ_አንድነት_ምክርቤት በ2015ዓ.ም በጥቅምት ወራት እንዲመሰረት ከእነ ሱጦታው መልኬ ከእነ አርበኛ ሲሳይ አሸብር ከእነ አርበኛ የሐንስ ንጉሱ ከእነ አርበኛ ሰፈር መለስ ሌሎችም የጎንደር ቀደምት አርበኞች ጋር በመሆን ቦታ በማመቻቸት ቀጠናውን ከጠላት በማጽዳት ጉልህ አብርክቶ አድርጓል የተመሰረተው ምክርቤትም(የአማራ ድርጅት በማፍረስ የተካኑት የአማራ ታጋዮች ለምን እንዴት ፈረሰ እነማን አፈረሱት የሚለውን ባልገባበትም) ምክር ቤቱ ለበርካታ ወራቶች የአማራ መታገያ ድርጅት ሁኖ በዋናነት እነ አርበኛ መከታው ማሞ እነ አርበኛ ምሬ ወዳጆን እነ አርበኛ ሰፈር መለስ ጨምሮ ሌሎችም የአማራ የቁርጥ ቀን አርበኞችበጋራ በርካታ ስራዎች ተሰርቶበታል ታግለውበታል አታግለውበታል::

ከዛ ቀጥሎም ከእነ አርበኛ ዶክተር አታለለ ከእነ አርበኛ አንተህ ጎቤ መልኬ ከሌሎትም ጀግኖች ጋር በመሆን ግዙፉን የዋዋ ጎቤ ክፍለጦር በማደራጀት ምክትል አዛዥ በመሆን በርካታ አውደ ውጊያዎችን በማዋጋት ብቻ ሳይሆን ስናይፐሩን ወድሮ በመዋጋት በርካታ የቡድን መሳሪያዎችን በመማረክ ክፍለጦሩን
አስታጥቋል ።

✍️በመቀጠልም ዕዝ እንዲቋቋም ጉልህ አበርክቶ በማድረግ የቀድሞው የጎንደር ዕዝ ከፍተኛ አመራር በመሆን ያገለገለ ሲሆን አሁንም ደግሞ የቀጠናውን ፋኖ በኮር በዋቀር የተናበበ ወታደራዊ ጀብድ እንዲሰራ በጎ ሚና በመወጣት አልፎም የጎንደር ትግል ቅርጽ እንዲኖረው ያደረገ እና በአሁኑ ሰአት ዘመድ አዝማዱን እንዲሁም የአብራኩን ክፍይ ልጁን ፋኖ ሄኖክ በለጠን ጭምር አፈንኖ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የፋይናስ መምሪያ ሀላፊ በመሆን የአማራ ህዝብን የህልዉና ትግል ለማሻገር በጎንደር በተለያዩ ግንባሮች በመዘዋወር እያታገለ እየተጋለ እና ትግሉን በብቃት በጀግንነት እየመራ ይገኛል።

በዝምታ አርበኝነትይ ውርስ ያደረጉ ጀግኖችን ያብዛልን እያልኩ ጀግናው መሪያችን አርበኛ በለጠ አዱኛም በርታልን ጀግናው 🙏
ምስል :አርበኛ በለጠ አዱኛ እና የአብራኩ ክፋይ ልጁ ፋኖ ሄኖክ በለጠ አዱኛ !
ድል ለአማራ ፋኖ
አሸናፊው አማራ ✍️
ፍኖተ ዳሞት ሻለቃ የአርበኛ አብርሃም ጋሹ መታሰቢያ በፍ/ሰላም ከተማ የደፈጣ ውጊያ በማድረግ ዘክራዋለች::

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ፭ኛ ክፍለጦር
አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ዛሬ ማለትም መስከረም 30/012018 ዓ.ም ፍ/ዳሞት ሻለቃ በምዕ/ጎጃም ዞን  በፍ/ሰላም ከተማ ፍርን ላይ በዞኑ ግብርና ቢሮ ውስጥ ያለውን ጠላት ምሽግ ውስጥ በመግባት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት የቀጡት ሲሆን በዚህም 8 ሙት 5 ከባድ ቁስለኛ አድርገዋል። ይህንንም ኦፕሬሽን የመሩት የፍ/ዳሞት ሻለቃ ም/አዛዥ መልካሙ አረፍዓይኔ እና ም/ዘመቻ ከፋለ ይትባረክ ናቸው። በዚህም ያሰቡትን የወንድማቸውን የአርበኛውን ዓላማ ለማሳካት በስሙ በተመራ ኦፕሬሽን በተሳካ ተጠናቋል ።

@አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ፍሥሓ አደራው

ድል ለአማራ ፋኖ !!!
ድል ለአማራ ሕዝብ !!!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና  በላይ ዕዝ ሁለተኛ መይሳው ካሳ ኮር የካራ ማራ ክፍለጦር ዕጩ የፋኖ አባላትን እና የጤና ባለሙያዎችን በድምቀት አስመርቋል።

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሁለተኛ መይሳዉ ካሳ ኮር የካራማራ ክፍለጦር ለወራት ያሰለጠናቸዉን የፋኖ አባላት እና የጤና ባለሙያዎችን ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ስነስርዓቱ የአካባቢው ማህበረሰብ፣የኮር፣የክፍለጦር እና የብርጌድ እንዲሁም የሻለቃ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል ።

የሰዉ ኃይል አደረጃጀቱን እና አቅሙን በማሳደግ ሰፊ ቀጠናን መቆጣጠር የቻለዉ ካራማራ ክፍለጦር አዲስ የፋኖ አባላትን አሰልጥኖ ማስመረቁ ለቀጣይ የትግል ጉዞ ጉልህ ሚና እንዳለዉ ተገልጿል።

አዲስ ተመራቂ የፋኖ አባላት የቀጣይ የትግል ሂደት ለማፋጠን እና ትግሉን ለመቋጨት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

የተከበራቹህ አድማጭ ተመልካቾቻችን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሁለተኛ መይሳዉ ካሳ ኮር የካራ አማራ ክፍለጦር አዲስ የፋኖ አባላት የምረቃ ስነስርዓት ፕሮግራም በክፍለጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አንተነህ መክበብ ተዘጋጅቷል እንደሚከተለዉ ይቀርባል እስከ ፍፃሜው ድረስ አብራቹህን ቁዩ።

ማታ 1:00 ሙሉ ፕሮግራሙ በመረጃ ቲቪ ይቀርባል።
1
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

በሰሞኑ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በርካታ ሰራዊቱ የተደመሰሰበትና የተማረከበት ብልፅግና ከወለጋ ያመጣው የማዕከላዊ ዕዝ ሰራዊት ከወልድያ እየጠፋ ምኒልክ ዕዝን እየተቀላቀለ ነው::

ሰሞኑን በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከባድ ሽንፈት የገጠመው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና
የተደመሰሰበትንና የተማረከበትን አምስት ክፍለጦር ሰራዊት ለመተካት ከተለያየ ክልል ያመጣው ምልምል ሰራዊት ወልድያ ከደረሰ በኋላ እየጠፋና እየኮበለለ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን መስከረም 29/2018 ዓ.ም ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ሰባት አሳምነው ክፍለጦር ሁለት አጠቃላይ ዘጠኝ የሰራዊቱ አባላት ተቀላቅለዋል:: ኮሎኔል ሞገስ ዘገየን ጨምሮ የምኒልክ ዕዝ የክፍለጦር የኮርና የድርጅት ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል::

ኮብልለው ፋኖን የተቀላቀሉ የማዕከላዊ ዕዝ አባላት የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋትና ወረራ እየፈፀመ ያለው ብልፅግና ሁሉንም ነገሩን አሟጦ አማራ ላይ ወረራ እየፈፀመ ስለሆነ አማራ ሆነን አማራ ላይ ወረራ አንፈፅምም እንዲያውም እድሉን በማግኘታችን ደስተኛ ነን እንታገለዋለን ብለዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
መስከረም 30/2018 አ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

አሳዛኝ ዜና!!!
የአገዛዙ ሰራዊት ከጫካ ጭንብል ለባሽ ሚኒሻዎች ጋር በመሆን በህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋን ፈፀመ።

መስከረም 23/2018 ከጎንደር ገንዳውሀ ብዛት ያለው የህዝብ ተሽከርካሪ በአገዛዙ ሰራዊት እየታጀበ በጉዞ ላይ እያለ ከመቃ በትንሽ ኪ.ሜ ርቀት ግራር ከምትባል ቦታ የጉዞው ታሪክ ተቀይሮ ሌላ መልክ ሊይዝ ችሏል። በማይታሰብ መልኩ የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት የአማራን ህዝብ እንደ ሂሳብ ማወራረጃ ቀብድ መያዣ አድርጎ የጥፋት መንገዶችን እየፈበረከ በሰበባሰበቡ ንፁሀን የአማራውን ህዝብ ለእልቂት እየዳረገ የቆየ መሆኑ ይታዎቃል። በዚሁ ቀን የተፈፀመው ደግሞ በጣም ከባድ የጭካኔ ልክ ድራማቲክ በሆነ መልኩ እዚህ ቦታ ላይ ሲደርስ ከእጀባ የተመለሰ በመምሰል ከፊት ለፊት አካባቢው ላይ ያሰማራቸውን ጭንብል ለባሾችን በማድረግ እና ከኋላ ጨፍጫፊው የአብይ ሰራዊት በመሆን በሁሉም የህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ ተኩስ በመክፈት
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ንፁሀንን ለእልቂትና ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ዳርጓል።

አካባቢው ላይ ኔት ወርክ በማጥፋት ቁስለኞችን ህክምና ለማድረስም ሆነ መረጃዎችን ለማጠናከር ተግዳሮት የሆነ ሲሆን፣ ለጊዜው ቁጥራቸው የደረሰን ሴቶችንና ህፃናትን ጨምሮ ከ18 በላይ የተሰው ሲሆኑ ከ35 በላይ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።

ማሳሰቢያ: በምዕራብ ጎንደር በመተማ እና አጎራባች ወረዳዎች አማራና ቅማንት ለዘመናት በአብሮነት ተከባብሮና ተጋምዶ በፍቅር የሚኖርን ማህበረሰብ፣አሁን ላይ በተለየ መልኩ የብልፅግናው አገዛዝ በመካከል ጠባጫሪ አጀንዳዎችን ፍፁም ተለዋዋጭ የሆነ ሴራ፣ በስውር ከፍተኛ በጀት በመመደብ የውስጥ ጉዳይ አስፈፃሚዎችን ወክሎ እየሰራ ይገኛል። ስለሆነም የእርስ በርስ የማህበረሰብ ፍጅትን ለማስፈፀም የሚደረግን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ማህበረሰቡ ነቅቶና አውቆ አካባቢውን እንዲጠብቅና የዚሁ ተግባር አካል የሆኑትን የታጠቁም ሆነ ያልታጠቁ ቅጥረኞችን በአካባቢው ለሚገኝ የፋኖ ሰራዊት መረጃ በመስጠት እንድትተባበሩ ስንል ልባዊ ጥሪያችን ማስተላለፍ እንወዳለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
መስከረም 25/2018