ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
🔸የአማራ ፊኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)

ሰሜን ብርቅዬ ክ/ጦር ጠላትን ደመሰሰች!!
መስከረም 17 የሚከበረውን የመስቀል በዓል እንደ ማዘናጊያ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተንቀሳቀሰው የጠላት ሰራዊት 55 ሙት፣25 ቁስለኛ ሲሆን 35 የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ምርኮ በማንሳት አኩሪ ተጋድሎ ውጤት አስመዝግበዋል።

በሰ/ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በስቂያ በተል ልዩ ስሙ "ዋሊያ አንገት " የተባለ ቦታ በተደረገ ብርቱ ወታደራዊ ፍልሚያ የአረመኔው ዓብይ ወራሪ ሰራዊት በቆፈረው የቀበሮ ጉድጓድ ተቀብሮበታል።

ድሉን ያስመዘገበው አፋብኃ የራስ አሞራው ፫ኛ ኮር ሰሜን ብርቅዬ ክፍለ ጦር ነው።ክፍለ ጦሩ በቀጠናው በመንቀሳቀስ ተደጋጋሚ ድል እያስመዘገበም ይገኛል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
2👍1
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

ንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ከማሻ እስከ ደብረዘይት ድረሳ ባለው ቀጠና ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

6ኛ ቀኑን በያዘው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ተጋድሎዎችን እያደረገ ያለው አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ በንዑስ ወረዳው ካደራጀው ከ500 በላይ አባት አርበኛ ጋር በመጣመር መስከረም 18/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ ከማሻ እስከ ደብረዘይት ባለ ቀጠና ያገኘውን ፀረ አማራ ሰራዊት ሲጠርጉት ውለዋል::

በተጋድሎው የወረዳው ምክትል የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሰይድ አሊን ጨምሮ ከ15 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ከ25 በላይ ቁስለኛ ሆኗል:: በዚህ ውጊያ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከጊንባ ከአጅባርና ከማሻ ተሰባስቦ የመጣ አድማ ብተናና ሚሊሻ ነው ጉዳቱን ያስተናገደው:: በግል ትጥቁና ተተኳሹ ተጋድሎ እያደረገ ያለው አባት አርበኛ ጦር ታላቅ ጀብዱ እየፈፀመ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
🙏1
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

ንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ እዋ ቀጠና ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::

አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ መስከረም 18/2018 ዓ.ም እዋ ቀጠና ላይ እዋ ትምህርት ቤት መሽጎ የነበረን ጠላት በከበባ አስገብቶ በማፈን በርካታውን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

በተጋድሎው ታቦሮች በርካታ ጠላት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ጠላት ላይ ሰብዓዊ ኪሳራ ከማድረስ ባሻገር ስድስት ክላሽ ማርከዋል:: በተጨማሪም ከጠላት ጋር በማበርና በመወገን ህዝባቸው ላይ የሚፈፀመውን ዘር ማጥፋት መረጃ በመስጠትና በዘረፋ እንዲሁም በሌሎች እኩይ ተግባሮች እየተሳተፉ ያሉ ግለሰቦች መታቀብ ባለመቻላቸው የማያዳግም አስተማሪ እርምጃ የሚወስዱ መሆኑን ብርጌዱ አሳውቋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
🙏21
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

ለአማራ ወጣቶችና የአማራን የህልውና ትግል የምትደግፉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ:-

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች አዲስ ምልምል የፋኖ ሰራዊት ማሰልጠን ይፈልጋል:-

በዚህ መሠረት ነፃ በወጡ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም ነፃ ባልወጡና በተለያየ አካባቢ የምትገኙ ወጣቶች የአማራ ህዝብ የህልውና ትግልን ለአንዴና ለመጨረሻ በድል ለማጠናቀቅ በሚደረገው ርብርብ አማራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን በሚከተሉት መመልመያ መስፈርቶች መሰረት ከመስከረም 19/2018 ዓ.ም ጀምሮ ነፃ በወጡ ቀጠናዎች በሚገኙ ቢሮዎቻችን በአካል እየመጣችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን:-

👉 የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች አዲስ ምልምል የፋኖ ሰራዊት መመልመያ መስፈርቶች:-

1. እድሜው ከ18 እስከ 40ዓመት ለወንድ፣ ከ18 እስከ 35 ዓመት ለሴት
2. መፃፍና ማንበብ የሚችል/ትችል
3. አማራዊ ስሜት ያለው/ያላት
4. በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ህጎች፣መመሪያዎችና ደንቦች ተገዥ የሚሆን/የምትሆን
5. ለማንኛውም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ፋኖ ግዳጅ ዝግጁ የሆነ/ች
6. ከደባል ሱሶች ነፃ የሆነ/ች( ጫት፣ሲጋራ፣ሀሺሽ እና መሰል አደንዛዥ እፆችና አልኮል)
7. ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ /የሆነች
8. በማንኛውም ቦታ ቢመደብ/ ብትመደብ መስራት የሚችል/ የምትችል
9. የአማራ ብሔርተኝነት የገባው/የገባት
10. ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
11. የሚኖርበትን አካባቢ የሚገልፅ መታወቂያ ያለው /ያላት
12. በአካባቢው ማህበረሰብ የተመሠገነስነ-ምግባር ያለው/ያላት

ማሳሰቢያ:-ከዚህ በፊት በሰሜኑ ጦርነት በፋኖነት የሰለጠነ/የሰለጠነች በክተት ወደ ማሰልጠኛ ተቋሞች እንድትገቡና አማራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፤ ይህንን ሳትወጡ ብትቀሩ ለአማራ ህዝብ ጥቁር ታሪክ ጥላችሁ እንዳታልፉ ታሪካዊ ጥሪ ተደርጎላችኋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
🙏3
መንግሥታዊ ሽብር በአዲሱ ዓመት ሊገታ ይገባል!
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በተለያዩ ሥርዓቶች እንደተለመደው ሕዝብ በአዲስ ዓመት ተስፋ እንዲሰንቅ መጠናቸው ቢለያይም ግጭቶችን በማቆም፣ የፖለቲካ እሥረኞችን በይቅርታ በመፍታት፣ የሰውን ኑሮ ያከበዱ ጫናዎችን በማቅለል ጥረቶችን ሲያደርጉ ታዝበናል፤ በታሪክ ድርሳናትም ተጽፎ ይገኛል።

በዚኽ አዲስ ዓመትም ከሂደታዊ አስገዳጅነቱ በመለስ ሥርዓቱ ወደቀልቡ ተመልሶ እንዲኽ ያሉ በጎ መነሳሳቶችን ይወስድ ይኾን ወይ? የሚል ጥቂት የማይባሉ ዜጎች ሀሳብ ነበር። ያ ሳይኾን በተቃራኒው እገታ፣ ግድያ፣ ዛቻ፣ ድሮን ጥቃት፣ ፖለቲካዊ ውጥረቶች፣ የኑሮ ጫና እና መሰል ሥርዓት ወለድ ምስቅልቅሎች ልካቸውን፣ አኃዛቸውንና ቦታቸውን ቀይረው የሕዝቡን ስቃይ እያናሩት ይገኛሉ፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን ከወልዲያ 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ሣንቃ ከተማ በመስቀል በዓል ዕለት ከቀኑ 6፡00 ጤና ጣቢያ ላይ ከቀኑ 6:00 ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቤተሰብ ሲያስታምሙ የነበሩ 3 ሰዎች ተገድለዋል፤ አንዲት የጤና ጣቢያው የጽዳት ሠራተኛ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባታል፤ 3 የጤና ጣቢያው የሕክምና ባለሙያዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ የ 6 ዓመት ሕጻን ልጅ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዳለች። ከዚኹ ጋር ተያይዞ ላሊበላ ከተማ ከሚገኙ ቅርሶች መሐል የኾነውና ከአንድ ቋጥኝ ፍልፍል የተሠራው ገነተማርያም ቤተክርስቲያን አቅራቢያ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ እስከአኹን ባለን መረጃ የተጎዳ ሰው ባይኖርም "የቅርሱን መሠረት ነክቶት ይኾን ወይ?! ብለን ሥጋት ገብቶናል" ብለውናል የአካባቢው ነዋሪዎች። ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት እንዲኽ ያለውን ዘፈቀዳዊና ሥርዓት ወለድ መንግሥታዊ ሽብር በጽኑ ያወግዛል፤ ለሞቱትም ልባዊ ኃዘኑን ይገልጻል። በቅንጅታችን ደጋግመን እንዳልነው ጦርነቶች በተኩስ አቁምና በድርድር እንዲቋጩ፣ ሕዝቡም የሰላም አየር እንዲተነፍስ፣ ወንድም ወንድሙን የሚገድልበት የደም ቁማር በአስቸኳይ እንዲቆም ኹሉም ተፋላሚ ወገኖች ሕዝብን በማስቀደም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን፡፡  

በሌላ በኩል እሑድ መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ በመስቃን ወረዳ በሚኖሩ ኹለት ወንድማማች ሕዝቦች ስናኖ ሴራ በተሰኜ የአካባቢው ባሕላዊ እሴት አከባበርና ባለቤትነት ዙሪያ በተነሳ ብጥብጥ ጉዳቶች እንደተከሰቱ ከአካባቢው ምንጮች ለማወቅ ችለናል፡፡ የፀጥታ ኃይሉ ችግሩ ሲፈጠር በቅርበት በመገኘት ለማረጋጋት ያደረገው ጥረት በበጎ የሚታይ ኾኖ በዘፈቀዳዊ ተኩስ ሳቢያ እስከሞት የደረሰ ጉዳት መድረሱን መስማት ልብ ሰባሪ ክስተት ኾኖ አግኝተነዋል፡፡ ከኹሉም ነገር በፊት የማኅበረሰብ ደኅንነት ቅድሚያ ተሰጥቶት በአካባቢውም ያለው አስተዳደራዊ ችግር በስክነትና በወንድምአማችነት መንፈስ እንዲፈታ በአደራ ጭምር ማሳሰብ እንወዳለን፡፡  

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት
መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
👍2
ፍ/ሰላም ገራይ ላይ የጠላት ሃይል እርምጃ ተወሰደበት።

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ፭ኛ ክፍለጦር
አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ብርጌድ ዛሬ ማለትም መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ/ም ጠላት ፍኖተ ሰላም ከነበረ ጎሬው በመውጣት ወደ ጀግኖቹ ሀገር ገራይ ለመግባት ያለ የሌለ ኃይሉን ሰብስቦ ቢሄድም በእነ አይቀመሴ ሻለቃ አበረ ምናሉ ልጆች ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 5:30 በተደረገ ውጊያ የጠላት ኃይል ረግፏል።

በዚህም
ከ  20 በላይ ሙት
ከ18 በላይ ቁስለኛ ሲሆን 2 ክላሽ መማረክ ተችሏል።

@አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፍሥሓ አደራው
🙏2
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

ከዘመቻ አባ ናደው ጎን ለጎን ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር ከ100 በላይ አዳዲስ ፋኖዎችን አስመረቀ::

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ከ100 በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረገው የውባንተ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ጎበዜ በአውደ ውጊያ ጠላትን በማንበርከክ እና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው እየሰራ ያለው የውባንተ አባተ ክፍለጦር መደበኛ ሰራዊት በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ታሪካዊ ጀብድ ለመፈፀም ተዘጋጁ ብሏል።

የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ አርበኛ ሸጋው ወርቄ በበኩሉ የትግሉን መሠረታዊ አላማ በንድፍ ሀሳብ በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ስልጠና በተግባር እንደምታረጋግጡ አልጠራጠርም ብሏል።

አማራ እንደ ህዝብ የገጠመውን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ ጥቃት ድባቅ በመምታት የአባቶቻችን ታሪክ እንድትደግሙ ታሪካዊ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ፋኖ በሪሁን ደምሌ አደራዊ መልዕክቱን አስተላልፏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
👍3
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር የደጅአዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ  ጉዳልማ ላይ ከ12:00 - 7:00 ሰዓት ከፍተኛ ትንቅንቅ የታየበት ውጊያ ሲያደርግ ውሏል።

በውጊያው የአረመኔው አሽከር ምሊሻና አድማ ብተና እንደ ክፉኛ ሲመታ ውሏል።

ነበልባሎቹ የተድላ ጓሉ ልጆች ለአረመኔው ሰራዊት የእግር እሳት የሆኑበት ሲሆን በውጊያው 19 የጠላት ሀይል ሲደመሰስ  21 ቁስለኛ ሆኗል።

7 ክላሽ 1 አብራረው በድምር 8 መሳሪያ ተማርኳል።
1.ጌቴ ሙሉዓዳም
2.እንዳላመው ያለው
3.ልጥገበው ጌቴ
4.ሙሉቀን ደምስ
5.ጌቱ ማሞ
6.አዝመራው መኩ የሚባሉ ምሊሻዎች ወደ ላይኛው ተሸኝተዋል።

የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት:-
1.ተግባር ማናዬ የተባለ አርሷደር እረሽኗል
2.አበዋ ምህረቴ የተባለውን ሲያቆስል የግለሰብ ባጃጅ አቃጥሏል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!

አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏1
4 ንፁሀን በድሮን ጥቃት ተገደሉ።

አገዛዙ ባለፉት ቀናት ወልዲያ ከተማ ዙሪያ 11 የድሮን ጥቃት እንዳደረገ የተገለፀ ሲሆን፤ ዛሬ በራያ ቆቦ ወረዳ ቃሊም ከተማ 12ኛ የድሮን ጥቃት በመፈፀም ከረፋዱ 4:00 ላይ ራያ ቆቦ ቃሊም ከተማ ቃሊም ትምህርት ቤት አካባቢ አገዛዙ ባደረገው የድሮን ጥቃት 4 ንፁሀን እንደተገደሉ ምንጮች ገልፀዋል ።

4 የአካባቢው ወጣቶች በአንድ ላይ ሲንቀሳቀሱ በነበረበት ወቅት ላይ የድሮን ጥቃቱ እንደተፈፀመ ተገልጹአል።

በትላንትናው እለት ከላሊበላ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ከአንድ ቋጥኝ ተፈልፍላ በተሰራችው ገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተመሳሳይ የድሮን ጥቃት እንደተፈፀመ ይታወቃል። ከትላንት ወዲያ እንዲሁ ሳንቃ ጤና ጣቢያ በፈፀመው የድሮን ጥቃት በሕክምና ላይ የነበሩ ንፁሀንን ጨምሮ የሕክምና ባለሙያዎች እንደተገደሉ መዘገባችን ይታወሳል።
💔2
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

ዛሬም ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይት እየተደረገ አዲስ የአስተዳድር መዋቅር እየተዘረጋ ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ነፃ ባጣቸው የሰሜን እና የደቡብ ወሎ ዞን እና ወረዳ ከተሞች ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡

ዛሬ በዕለተ ሰኞ በቀን 19/01/2016 ዓም በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡

በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች

1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?
* ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ
* ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ
* የትግሉ ተግዳሮቶች
* የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ

2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ
* በወታደራዊ ቁመና
* በፖለቲካ ተቀባይነት
* የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም

3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ
* የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት
* የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት
* ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ

4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?

በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተመኩሯል፡፡

በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና በተለይ ሙስሊም ጠል ናቸው በሚል አገዛዙ ትግሉን እንድንጠላው መንግሥት በፋኖ ላይ ትልቅ ጥላቻ እንዲኖረን ብዙ የሰራ ቢሆንም ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል እና ዛሬ ጥርጣሬያችንን ለማጥራት ችላቹሃል በማለት ሃሰተኛውን የብልፅግና ስርዓት በጋራ ለመታገል ቃል ገብቷል፡፡

በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ስትባሉ የነበረውን የሃሰት ስም ማጥፋት በተግባር የህዝብ ልጅ መሆናችሁን አሳይታቹሃል እኛም ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
3🙏1
ሰበር ዜና!

የጎንደር ከተማ አካል በሆነችው ጠዳ ክ/ከተማ እና በጎንደር ዙሪያ ወረዳ  ማክሰኝት ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ተጋድሎ እየተደረገ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ከተለያዩ  ክፍለ ጦር የተወጣጡ    ጀግኖቻችን በጥምረት  ዛሬ መስከረም 19  /2018 ዓ/ም  ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በተመሳሳይ  ማክሰኝት ከተማ ዙሪያ እና  ጠዳ  ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአገዛዙ ወታደራዊ ቤዞች ላይ ያነጣጠረ  እርምጃ ተወስዷል።

በአውደ ውጊያው በጠላት በኩል ከፍተኛ  የሆነ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን ወደ ገጠር ለኦፕሬሽን የላከውን ጥምር ሀይል በመኪና በማመላለስ ለመከላከል የሞከረ ቢሆንም ከሞትና ከቁስለት ሳይታደጋቸው ቀርቷል።
  
      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ነው!!

    አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
       መስከረም 19/2018 ዓ.ም
🙏1