ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
🔥#የድል_ዜና‼️

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ጀብደኛዋ የሰሜን ብርቅየ ክፍለጦር በቀን 17/1/2018 ዓ.ም በሰሜናዊ ጎንደር ዞን በጠለምት ወረዳ በተል በተባለ ቀበሌ ከአገዛዙን ሰላም አስከባሪ እና ሚኒሻ ጋር በተደረገ ውጊያ ውጊያውን በድል በማጠናቀቅ  ከ50በላይ ሙት እና ከ35በላይ ቁስለኛ በማድረግ ከ50 በላይ የነብስ ወከፍ መሳሪያ መማረካቸው ታውቋል !!

የክፍለጦሩ ቀጠና የኔትወርክ ችግር በመኖሩ መረጃውን ያደረሰን ጓዳቸው የ4ኛ ደጃዝማች ኮር የረመጡ ደጀን ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው አርበኛ መምህር አስፋው አደራጀው ነው።
ድል ለአማራ ፋኖ
3🙏2
የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች አስቸኳይ የሆነ የቤት ስራ ተሰጥቷቸው እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

1. ፋኖ በድሮን እንዳለቀና እንደተሸነፈ ሁሉንም ካድሬና ደጋፊ ሰብስበው እንዲያሳምኑ

2. በተቻለ አቅም ሕዝቡን ሰብስቦ የኤርትራና የሕወሓት ሠራዊት በፋኖ እየተመራ አማራ ክልልን የጦርነት ቀጠና እያደረገ እንደሚገኝ የፈጠራ ወሬ እንዲያወሩ

3. በቴክኖሎጂ የተሻ እውቀት ያላቸው ካድሬዎች ማንኛውንም ምስልና ቪዲዮ በመጠቀም ሶሻል ሚዲያው ላይ ፕሮፓጋንዳ በመስራት ንቁ ሆኖ እንዲሳተፉ

4. ወቅታዊውን የፋኖ አቋምና እቅድ ማወቅ ስላልተቻለ አዲስ የመረጃ አባላትን በማሠባጠር መረጃ እንዲሠበስቡ ማድረግ

5. ዋና ዋና የብልፅግና አመራሮች ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል በየከተማው እንዲዞሩ...የሚል መመሪያ መጥቶ ወደ ስራ ተገብቷል። (ለምሳሌ ትላንት ከሰዓት በሗላ በግምት ከ 1:00/1:15 ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ የቆቦ አመራሮች ሲዞሩ ነበር።)

@መረብ ሚዲያ
👍41
ሰበር ዜና!

5ተኛ ቀኑን የያዘው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በታላቅ ድል ታጅቦ እንደቀጠለ ነው።

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና መብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አሃድ ጋር በመቀናጀት ትናንት ለዛሬ ሌሊት በመካነሰላም ግንባር የጠላትን ኃይል በመደምሰስ፣ በማቁሰል፣ በመበተን እና በመማረክ ከጥቅም ውጭ አድርገው መካነሰላም ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውለዋል::

በኦፕሬሽኑ የአድማ ብተና 23ተኛ ክፍለ ጦር በርካታ ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅ/ቤት አመራር የሆነው አቶ ሰይድ አብዬን ጨምሮ ሌሎች ባንዳዎች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል:: በድምሩ ከ45 ያላነሰ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል::

ውጊያው ሲጀመር ራሱን ለመከላከል አስቦ በአየር ማረፊያ፣ በለገአማራ ወንዝ እና በከተማይቱ መሀል በቡድን መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው ጠላት የጀግኖችን ክንድ ቀምሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል::

መካነሰላም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቦረና ማረሚያ ቤትን በመክበብ ፋኖ ባደረገው ትንቅንቅ በርካታ እስረኞችን ማስለቀቅም ተችሏል::

በዚሁ በመካነሰላም ግንባር ከትናንትት በስቲያ የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ ኮሎኔል ሀብታሙ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች 3 ባንዳዎችን መማረኩም ይታወሳል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 18/2018 ዓ.ም
2🙏2
የጎንደሬ በጋሻው ከፍለ ጦር ምክትል ሻለቃውን ጨምሮ ጠላትን ደመሰሰ ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆችው ቃኘው ብርጌድ ዛሬ መስከረም 18 /2018 ዓ/ም ከጠዳ ከተማ በመውጣት በዙሪያው ያሉ አርሶአደሮችን ቤት ለቤት በመቀስቀስ ሁላችሁም ፋኖ ናችሁ ፋኖ ልጅም አላችሁ ምረሽ መግባትና ማስገባት አለባችሁ እያለ ሲደሰኩር ቆንጆዎቹ ምክትል ሻለቃውን ጨምሮ አምስቱን ወደ ላይኛው ላይመለሱ በመቀንደሽ ሸኝቷቸዋል።

ህብረተሰቡን ለማወናበድ የመጣው የብርሃኑ ጁላ ወንበዴ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ በወጣበት እግሩ እየፈረጠጠ ወደ መገጭ ግድብ ተመልሶ ገብቷል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 18/2018 ዓ.ም
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ነፃ ባጣቸው የሰሜን እና የደቡብ ወሎ ዞን እና ወረዳ ከተሞች ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡

ዛሬ በቀን 18/01/2016 ዓም በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች

1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?
* ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ
* ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ
* የትግሉ ተግዳሮቶች
* የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ

2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ
* በወታደራዊ ቁመና
* በፖለቲካ ተቀባይነት
* የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም

3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ
* የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ማና
* የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት
* ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ

4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?

በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተመኩሯል፡፡

በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና እስከዛሬም ዘግይታችሃል በማለት ቁጭቱን በአደባባይ ገልፆል፡፡

በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡


የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ
መስከረም 18/2018 ዓ.ም
3👍2
በጉራጊ ህዝባዊ አመፅ ተቀስቅሷል!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ዛሬ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ባደረጉት ግጭት ሰዎች ሳይቆስሉና ሳይሞቱ እንዳልቀረ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ ፡፡
ወጣቶቹ ዛሬ ከፖሊስ ጋር የተጋጩት “ የሲናኖ ሴራ “ የተባለው ባህላዊ የሽምግልና ሥረዓት የባለቤትነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተከሠተ አለመግባባት ነው ተብሏል ፡፡
ወጣቶቹ የከተማዋን ጎዳናዎች በድንጋይ እና በጎማ ዘግተው መዋላቸውን የአይን እማኖች ተናግረዋል ፡፡ በከተማው እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ የተኩስ እሩምታ ይሰማ እንደነበር የጠቀሱት ነዋሪዎቹ የአምቡላንሶች ምልልስም በርቀት ተሰምቷል ብለዋል ፡፡
በከተማው መረጋጋት ባለመስፈኑ ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱ ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል ፡፡
“ ሲናኖ ሴራ “ የተባለው ባህላዊ የሽምግልና ሥረዓት በመስቃን እና በዶቢ የቤተ ጉራጌ ማህበረሰቦች መካከል የባለቤትነት ይገባኛል ጥያቄ ሲነሳ መቆየቱ ይታወቃል ፡፡
4
ለሶስተኛ ጊዜ በስርዓቱ የወደሙ ማህበራዊ ተቋማት!!

የእስቴ ወረዳ እና የመካነየሱስ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ሁሉንም ማህበራዊ ተቋማት አወለደመዋል።

ከዚህ በፊት የእስቴ ወረዳ አስተዳደር ሁሉም ቢሮዎች፣የመካነየሱስ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ቢሮዎች እና የእስቴ ወረዳ ግብርና ቢሮ ሁሉም ሁሉም ቢሮዎች፣ዛሬ አዳሩን ደግሞ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሹ በአገዛዙ ካድሬዎች እንዲወድም ተደርጓል።

ጉድ በል ጎንደር!!
1
ሰሞኑን ሕዝቡ "ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከነሙሉ ሰራዊቱና የጦር መሣሪያው ምኒልክ ዕዝን ተቀላቅሎ ነው?..ወይስ?" ብሎ ግራ እስኪጋባ ድረስ፡ የወገንን ኃይል በድል ቁንጣን ያጨናነቀ በምትኩ ደግሞ የጠላት ኃይልን ወሽመጥ ብጥስ ያደረገው ዘመቻ...በክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ሳጅን አደም አሊ/አባ ናደው/ ስም የተሰየመ ነው።

እጅግ በጣም ሀቀኛና ጀግና፣ ታማኝና አማኝ፣ ፅኑና ከአላማው ዝንፍ የማይል፣ሩህሩህና ቸር፣ ፍትህ አዋቂና አስተዋይ መሪ እንዲሁም አልሞ ተኳሽ ነው ይሉታል አብረውት ከምሽግ ውሎው የሚያድሩ ጓዶቹ።

ሳጅን አደም "አባ ናደው" የሚለውን ስያም ያገኘው የጎላሌውን ምሽግ በሰበሩበት ወቅት ነበር።

መረብ ሚዲያ ከዓመት በፊት ስለ ጎላሌው ምሽግ መሰበር ዘግቦት የነበረውን መለስ ብለን እናስታውሳችሁ....

ወቅቱ ወርሃ መጋቢት 2016 ዓ/ም ነበር። በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ጎረንጅ ቀጠና ልዩ ስሙ ጎላሌ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ።

ከወግዲ ወረዳ ወደ ጎረንጅ ያቀናው የአገዛዙ ጥምር ጦር፣ በጎረንጅ ቀጠና እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያካሂድ አርፍዶ ከሰዓት ከባድ ዶፍ ያዘለ ዝናብ መዝነብ በመጀመሩ ውጊያው ጋብ አለ።

ዝናቡ አላቆመም ዶፍና ውሽንፍር የቀላቀለ ዝናብ እየዘነበ ነው።

ጊዜው እየመሸ ነበር። ጀንበር ልግባ ልግባ እያለች በምትጣደፍበት በዚህ ቅጽበት አባ ናደው እስኪ በጎቼን ላሙቅ ብሎ ቦምብ በሽርጡ ቋጥሮ ከተቀመጠበት ብድግ አለ።

ጓዶቹ ዝናቡ በረድ እስከሚል መታገስ እንዳለባቸው ደጋግመው ቢነግሩትም አሻፈፈኝ አለ። "ሰዓቷ የወንድ ልጅ ሰዓት ናት" ነበር አጅሬ ምላሹ።

"አትከተሉኝ።ታሪክ ሰርቼ አስደምማችኋለሁ" ብሎ እግሮቹ በቅርብ ርቀት ወደ ሚገኘው የጠላት ምሽግ መራመድ ጀመሩ።ማምረሩን ያወቁ የተወሰኑ ጓዷቹ በቅርብ ርቀት ተከተሉት።

ሳጅን አደም ያን ከባድ ዶፍና ውሽንፍር ዝናብ መሀል ለመሀል ሰንጥቆ የጠላት ምሽግ ላይ ሲደርስ በሽርጡ ታቅፎ ይዞት የነበረውን ቦምብ በግራ እጁ እያነሳ፡ ቀለበቱን በጥርሱ እየነቀለ አከታትሎ ይወረውር ጀመር።

ቀን ላይ ሲዘንብ የዋለው ዝናብ ለብርድ የሰጣቸው የጥምር ጦር አባላት ሙቀት በሙቀት ሆኑ። ምሽጉ በዋይታ ተዋጠ። የድረሱልኝ ተማፅኖ የሚያቀርቡና የጣር ድምፅ  የሚያሰሙ የመከላከያና የአድማ ብተና እንዲሁም ሚሊሻ አባላት ስፍር ቁጥር አልነበራቸውም። ገሚሱ ጥሩ ባለሙያ እንደሰራችው ፍርፍር አካሉ ተቆራርሷል።ገሚሱ ደግሞ "ወይኔ እግሬ፡ ወይኔ እግሬ" ይላል። ገሚሱ ደግሞ "ማሎ፡ ማሎ፡ ሀደኮ፡ ሀደኮ" ይላል። ገሚሱ በዛ ዝናብ መሀል "ውሃ ስጡኝ? ውሃ ስጡኝ?" ይላል።

አባ ናደው በሽርጡ ታቅፎ የያዘውን ቦምብ መወርወሩን አላቆመም። እየመረጠ ቦምቡ ወዳልነካው የምሽጉ ስፍራ ይወረውራል።

ከሰማዩ ጉርምርምታ ጋር ተዳምሮ በቦምቡ ፍንዳታ ምድር ቃጤ ሆነች። ያሁሉ የወታደሩ ዋይታና የጣር ድምፅ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ፀጥ እረጭ አለ።ሰማዩም ከነ ሳጅን አደም አሊ ጋር ምክር እንዳለው ሁሉ መስኮቱን ጥርቅም አድርጎ ዘጋ። ያ አስፈሪው የጎለሌ ምሽግ፣ መከላከያ ሰራዊቱ ለወራት ያህል በግሬደር ታግዞ የሰራው የጎላሌው የኮንክሪት ምሽግ በነሳጅን አደም አሊና በጓዶቹ ክንድ ተደረመሰ።

በእለቱ በስፍራው የነበሩ ሰዎች በምሽጉ ውስጥ የሬሳ ክምር የሬሳ ነዶ ነው ያየነው ሲሉ የአይን ምስክርነታቸውን ሰተዋል።

ከዚህን ዕለት ጀምሮ ሳጅን አደም አሊ አባ ናደው ተባለ።የለጋምቦው አንበሳ እና የገነቴ ጌጥ የሆነው አባ ናደው እጅግ በጣም ደፋር በዛው ልክ ደግሞ እሩህሩህ ነው ይሉታል የትግል አጋሮቹ። የጎላሌን ምሽግ ደርምሶ ታሪክ የሰራው አባ ናደው በጀግንነት እና በወታደራዊ ጥበቡ የተመሰከረለት ነው።

ይህ ጀግና ከወራት በፊት ስለ አማራ ሕዝብ ሲል የክብር መስዋዕትነትን ተቀብሏል።
(የአርበኛውን ሙሉ የትግልታሪክ መረብ ሚዲያ ከወራት በፊት ለአድማጭ ተመልካቾቹ ማድረሱ ይታወሳል።)

ምኒልካውያኑ ዛሬ በዚህ ለምድር ለሰማይ በከበደ አርበኛ ስም ዘመቻ አውጀው የአማራ ሕዝብ ለምዕተዓመታት የሚፎክርበትንና የሚመካበትን ድል አስመዝግበዋል።

በቁሙ ትግል የሚሰምርለት፣ ሞቶሞ በስሙ ድል የሚታፈስበት እንቁ አርበኛ..ሳጅን አደም አሊ( አባ ናደው )

ክብርና ዘላለማዊ ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!
@መረብ ሚዲያ
1🙏1
🔸የአማራ ፊኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)

ሰሜን ብርቅዬ ክ/ጦር ጠላትን ደመሰሰች!!
መስከረም 17 የሚከበረውን የመስቀል በዓል እንደ ማዘናጊያ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተንቀሳቀሰው የጠላት ሰራዊት 55 ሙት፣25 ቁስለኛ ሲሆን 35 የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ምርኮ በማንሳት አኩሪ ተጋድሎ ውጤት አስመዝግበዋል።

በሰ/ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በስቂያ በተል ልዩ ስሙ "ዋሊያ አንገት " የተባለ ቦታ በተደረገ ብርቱ ወታደራዊ ፍልሚያ የአረመኔው ዓብይ ወራሪ ሰራዊት በቆፈረው የቀበሮ ጉድጓድ ተቀብሮበታል።

ድሉን ያስመዘገበው አፋብኃ የራስ አሞራው ፫ኛ ኮር ሰሜን ብርቅዬ ክፍለ ጦር ነው።ክፍለ ጦሩ በቀጠናው በመንቀሳቀስ ተደጋጋሚ ድል እያስመዘገበም ይገኛል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
2👍1