ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ   ‎ሰባት ለሰባ ክ/ጦር ለተከታታይ አራት ቀን ባካሄደው ውይይት የክ/ጦሩን አመራሮች በድጋሚ በመሰየም በሰላም ተጠናቀቀ።
‎=============
‎መስከረም 5/2018 ዓ ም
‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሰባት ለሰባ ክ/ጦር ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው ውይይት ነባር እና አዳዲስ የክ/ጦሩን አመራሮች ገምግሞ ማሻሻያ በማድረግ መድቧል::

‎ክ/ጦሩ የአመራር ምደባ ያካሄደው ወደ እዙ ባደጉ እና የአጼ ዘርዓ ዓዕቆብ ኮር መመስረቱን ተከትሎ ወደ ኮር የሄዱ አመራሮች በመኖራቸው ነው::

‎ይህንን የአማራር ሽግሽግ ክ/ጦሩ ለማሟላት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አመራሮች ባሉበት ለተከታታይ አራት ቀን ግምገማ ካካሄደ በኋላ ነባር እና አዳዲስ አመራሮችን ክ/ጦሩን እንዲመሩ መድቧል::

‎ይህ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ የአፋብኃ ማእከላዊ ኮማንድ አባል እና የዕዙ ዋና መሪ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ፥ የዐሰዙ ም/ል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ እና የአሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ባዩ አለባቸው ባሉበት ተካሄዷል::

‎በዚሁ መሰረት ፥
👉የሰባት ለሰባ  ክፍለጦር ዋና መሪ ........ ፋኖ ደመላሽ ደመቀ
👉ወታደራዊ አዛዥ .......አረጋ ሙሉነህ
👉ምክትል አዛዥ  ኦፕሬሽን...... እሸቱ በቀለ
👉ምክትል አዛዥ አስተዳደር...... እንዳለ ሸዋዬ
👉ዋና ዘመቻ መምሪያ........ነጋ ንጉሴ
👉ምክትል ዘመቻ ............ጌታሁ ንጉሴ
👉ምክትል አዛዥ ሎጀስቲክ...... ታሪኩ አየለ
👉 ኦርዲናንስ.....ታምራት እምሻው
👉ቀልብ እና እደላ.....የምሩ ግዛው
👉 የህክምና ቡድን መሪ ........ይንገስ ከፈለኝ
👉ድርጅት ጉዳይ ....በለጠው ጋሻነህ
👉ፖለቲካ ዘርፍ .......ዳዊት ገ/መስቀል
👉ፋይናንሰ ...........ከበደ ሀብቴ
👉ሪፖርተር  ...........ዝናው በቀለ
👉አስተዳደራዊ ጉዳይ ........አባተ መስፍን
👉አደረጃጀት ............ንጉስ መሰለ
‎ ሆነው ተመርጠው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

‎መረጃውን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያዕቆብ ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል አድርሶናል።

           " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
‎       መስከረም 05/2018 ዓ.ም
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

የአፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክፍለጦር ከስበር ሻለቃ የተውጣጡ ተወርዋሪዎች ከወረኢሉ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ሰኞ ገበያ ከተማ መስከረም 4/2018 ዓ.ም አዳር በመግባት ከተማዋ መሽጎ የነበረው ባንዳ ሚሊሻና ፖሊስ ምንም ሳይተኩስ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ቀሪው ብትንትኑ የወጣ ሲሆን ሶስት የስርዓቱ ገረድ በመሆን ህዝብን የፋኖ ደጋፊ ናቸው እያሉ ሲያግቱ ሲረሽኑ ሲያሰቃዩ የነበሩ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሌላውም ከዚህ በመማር በህዝባችን ላይ ጥፋትና ወንጀል ፈፅሞ ማምለጥ እንደማይቻልና አብይ አህመድና ቡድኑ ሳይገባውም ገብቶትም ከእሱ ጎን የቆመ አካል ቢሞትም ቢቆስልም ደስታው ፋኖ የቆሰለ የተሰዋ ያክል እኩል መሆኑን በአደባባይ እያረጋገጠላችሁ እንደሁ ብዙ ማሳያዎች አሉ ምክናየቱም ሆዳሞች ሆናችሁ ወገናችሁን ለመውጋት ቢዘምቱም እናተም አማራ ስለሆናችሁ መቸም አያምናችሁምና በፍጥነት አስተውሉና ለወንድሞቻችሁ እጅ በመስጠት መታገሉ ቀርቶባችሁ ህይወታችሁን እንድታተርፉ አስቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሱልጣን የሱፍ አፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 5/2017 ዓ.ም
👍1
መንደር 29 ላይ የተሳካ ደፈጣ በመጣል አመራሩ ተገደለ።

የአ/ፋ/ብ/ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ነበልባሎቹ የአባይ መተከል ብርጌድ የፋኖ አባላት በአረመኔው የአገዛዙ ተላላኪ ሚሊሻ እና አድማ በትን አባላት ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ፈፅሟል። በቀን 05/01/2018 ዓ.ም የበረሃ ፈርጦቹ የአባይ መተከል አባላት
ከወርቅ ሀገር እና መንደር 29 ከተባለ ቦታ መካከል ደፈጣ በመያዝ:-
1.ፈረደ ቸኮል_ የደቅ ሊቀመንበር የነበረ የፋኖ ቤተሰብን የሚያሰቃይ እና የፋኖ ቤቶችን የሚያስፈርስ ባንዳ
2.ሙሉ ታገል_ አድማ በትን
3.ጌትነት አቤ _ አድማ በትን
4.እንዳወቅ አጥናፍ_ አድማ በትን
እንዲሁም 3 የሚሊሻ  አባላትን ጨምሮ በጠቅላላ 7 የጠላት ኃይል መደምሰስ ተችሏል። እንዲሁም 3 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ተማርኳል።

አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ !

አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

        መስከረም 05/2018 ዓ.ም
1
42 ሀገራት በኢትዮጵያ የሲቪክ ምህዳር መጥበብ እንዳሳሰባቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቁ

አርባ ሁለት ሀገራት በኢትዮጵያ በተያዘው አመት ከሚካሄደው ምርጫ ቀደም ብሎ በመሰረታዊ መብቶች ላይ ገደቦች መጣላቸውን በመጥቀስ በሀገሪቱ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቁ።

ሀገራቱ ባሳለፍነው ባወጡት የጋራ መግለጫ “በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ፣ በተለይም ሀሳብን በነፃነት የመናገር፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እና የመደራጀት መብቶች መገደባቸው አሳስቦናል” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፣ “በቅርቡ በሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተፈጸመውን ማስፈራራት እና እገዳን ጨምሮ የሲቪክ ምህዳር መጥበብ እና መዘጋት አሳሳቢ ነው” ብለዋል። ሀገራቱ በገለልተኛ መገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ማስፈራራትም ስጋት እንደፈጠረባቸው በመግለጽ፣ ለእነዚህ ክስተቶች ግልጽ የሆነ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

ፊርማቸውን ያኖሩት ሀገራቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት በ2024 ሪፖርቱ ላይ “በመንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች መፈጸማቸው መገለጹን” ጠቅሰው ይህም አሳሳቢ መሆኑን አመላክተዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ በ2025 በህጻናት እና በትጥቅ ግጭቶች ዙሪያ የቀረበን ሪፖርት በመጥቀስ፣ “የህጻናት መገደልና የአካል ጉዳት ማድረስ፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ እንዲሁም መታገትን ጨምሮ በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ” በእጅጉ እንደሚያሳስባቸውም ገልጸዋል።

በተጨማሪም፤ “የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች ሁሉም ተዋናዮች በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይን ጨምሮ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በደል ለማስቆም ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን” ብሏል መግለጫው።

በተለያዩ አካላት እየተፈጸመ ያለውን “ በንጹሃን ሰዎች ላይ ግድያና ጉዳት ማድረስ፣ ማሰቃየት፣ ኢ_ሰብዓዊ አያያዝ፣ በግዳጅ መሰወር፣ የዘፈቀደ እስር እና ማቆየት፣ በንጹሃን ሰዎች መሰረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን፣ እንዲሁም ከባድ ደረጃ ላይ የደረሰ ወሲባዊ እና ጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት” በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል።

ሀገራቱ ባለስልጣናት በአገር አቀፍ ደረጃ የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ፣ ፍትህና ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል።

የጋራ መግለጫው በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ሂደት ውስጥ መሻሻል ባለመኖሩም ስጋቱን ገልጿል። ተአማኒነት ያለው የሽግግር ፍትህ እና የተጠያቂነት ማዕቀፍ መተግበር “ለተጎጂዎች እና ከጉዳት ለተረፉት ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና እርቅ ለማረጋገጥም ወሳኝ ነው” ሲል አስታውሷል።

ሀገራቱ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት “ከተባበሩት መንግስታት እና ከሌሎች የጥበቃ አካላት ጋር እንዲተባበር እና ገልተኝነታቸውን እንዲያከብር” አሳስበዋል።

ሁሉም ወገኖች ተጨማሪ ጥሰቶች ከመፈጸም እንዲታቀቡ እና መረጋጋትን ለመመለስ በሰላማዊ ውይይት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቴዋል።

(አዲስ ስታንዳርድ- አስ እንደዘገበው)
3
በ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ብርጌዶች የህዝብ ውይይቶች እና የመሰረተ ልማት ስራዎች እንደቀጠሉ ናቸው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ እነማይ ወረዳ አዲስ ዓለም ቀበሌ እና ደብረ ገነት ጎተራ ቀበሌ መስከረም 05/2018 ዓ.ም ህዝባዊ ውይይት አካሂዶል።

አባ ኮስትር ብርጌድ የሰለጠነ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በመገንባት የህዝብ አስተዳደር ስራዎችን በመስራት ትግሉን እያጦጣፈ ይገኛል።አባ ኮስትር ብርጌድ በእነማይ ወረዳ ደብረ ገነት ጎተራ ቀበሌ ግዚያዊ አስተዳደር የቀበሌ የፍትህ አካላትን በመሰብሰብ ውይይት አካሂዶል።

በእነማይ ወረዳ ደብረ ገነት ጎተራ ቀበሌ የሻለቃ አመራሮቹ እና የፍትህ አካላት በተገኙበት  የግዚያዊ አስተዳደር እና የቀበሌው የፍትህ አካላት አዋቅሯል። በውይይቱም ላይ ለአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ተነስተው ጥልቅ ውይይት ተካሂዶል።በውይይቱም የብርጌድ እና የሻለቃ አመራር ተገኝተዋል።

የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ደባይ ጮቄ ብርጌድ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች እና የመሰረተ ልማት ጥገናዎችን መስከረም 05/2018 ዓ.ም እያካሄደ ይገኛል።

ደባይ ጮቄ ብርጌድ በደባይ ጥላትግን ወረዳ የባባት ቀበሌ የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በፋኖ እና በህብረተሰቡ ያሉ ግንኙነቶች እንዲሁም የግዚያዊ አሰተዳደሮችን በመገምገም አዲስ የህዝብ አሰተዳደሮችን አስመረጦ የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ አሰቀምጠዎል።

በደባይ ጥላትግን ወረዳ ወደብ እየሱስ ቀበሌ የሚገኘውን በጎርፍ ምክንያት የተጎዱ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን በማህበረሰብ ተሳትፎ አየጠገነ ይገኛል።በውይይቱም የብርጌድ አመራር እና የሻለቃ አመራሮች ተገኝተዋል።

መስከርም 05/2018 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🙏2
የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያው አቶ ሳምሶን ከበደ ከሀገር ተሰደደ።

ለረዥም አመታት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ውስጥ: በተለያዩ የስራ ዘርፎች ሲያገለግል የነበረው ሳምሶን ከበደ ከሀገር መሰደዱን ምንጮች ገለፁ።

ባለሙያው   የአማራን ህዝብ እየጨረሰ ላለው የየብልፅግና ፓርቲ አባል አልሆንም ማለቱን ተከትሎ በብልፅግና መንግስት ጥርስ ተነክሶበታል።  በተያያዘም በስራ ላይ ብልፅግና የሚያስተላልፋቸው የሀሰት መረጃዎችን በመቃወሙ ምክንያት በስውር ደህንነት ተመድቦበት ስራውን ተረጋግቶ እንዳይሰራ ተደርጓል።

በአማራዊ ማንነቱ ምክንያት ልዩ ክትትል: ጫና እና ወከባ ሲፈፀምበት ነበር።

አገዛዙ  በተለይም ፋኖ በሚዲያ የበላይነት በልጦኛል ብሎ መገምገሙን ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥቃት መፈፀሙን ቀጥሏል።

አቶ ሳምሶን: የብልፅግና አባል ያልሆንከው የፋኖ ደጋፊ ስለሆንክ ነው በሚል  ደሞዝ እንዲቀነስ: አላግባብ ከነበረው ሀላፊነት ዝቅ እንዲል በማድረግ የስነልቦና ጉዳት ተፈፅሞበታል።

በከፍተኛ ጫና ስራውን እየሰራ የነበረው ባለሙያው: እንደ አዲስ በአማራ እና በትግራይ ተወላጆች ላይ መፈፀም የተጀመረው ወከባ ተከትሎ አቶ ሳምሶን ማስፈራሪያዎች እና አካለ‍ዊ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል።

አቶ ሳምሶን አሁን ያለበት ቦታ በትክክል እንዳልታወቀ ምንጮች ገልፀው: አለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በ ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ላይ የሚፈፀመውን ማሳደድ ትኩረት እንዲሰጡት ተጠይቋል።

የ ኢትዮጵያ መንግስት በዚህ 2 ወር ውስጥ ብቻ 2 የሪፖርተር ጋዜጠኞችን አፍኖ ደብዛቸውን ያጠፋ ሲሆን የነጋሽ ሚዲያ ባለቤት ጋዜጠኛ ነጋሽ በግፍ ማሰሩ ይታወሳል።
©Black Lion Media
ሰበር ዜና!

ባለ ሽርጡ ክፍለጦር ሰሜን ወሎ ዞን ጃራ ማስልጠኛ ካምፕን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር አሰልጣኞችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠር ሆድ አደር ሚሊሻ አድማ ብተናና መከላከያ በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ 024 ቀበሌ ልዩ ቦታው ጃራ ካምፕ እየተባለ የሚጠራውን አሁን ላይ በፋሽቱ ብልፅግና ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ የሆነ ከበባ ውስጥ በማስገባትና ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር በርካታ የብልፅግና ቡድን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻና አድማ ብተና እንድሁም የስርዐቱን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በመደምሰስ ፣ በማቁሰልና በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ለአመታት ከየጎዳናው፣ከየፑል ቤቱ፣ እንድሁም ከየመኖሪያ ቤታቸው፣ በሀይልና፣በግፍ እያስገደደ ወጣቶችን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ በማሰልጠን ስልጣኔን ያስጠብቁልኛል ብሎ የሚያስበው የአረመኔውና የአማራ ጠሉ የአብይ አህመድ የግል ሰራዊትና የዚህን ጨፍጫፊ እና አገር አፍራሽ ሰራዊት የሚያግዝና መንገድ እየመራ ወገኑን የሚጨፈጭፈውንና የሚያስጨፈጭፈውን ባንዳ ሚሊሻና አድማ ብተና ሃይል መስከረም 5ለ6/2018 ዓ.ም ከለሊቱ 10:00 ጀምሮ ሽርጥ ለባሽ ኮማንዶዎች ጃራ ካምፕ ውስጥ በከፈቱት ድንገቲዊና መብረቃዊ ጥቃት በርካታ የአድማ ብተና የሚሊሻ ፣እንድሁም የስርዐቱን ሀይሎች ገሚሱን በመደምሰስ፣በማቁሰልና በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል።

ከንጋት 10:00 ጀምሮ እስከ ንጋት 12:35 መስከረም 6/2018 በቆየ አውደ ውጊያ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ 024 ቀበሌ ጃራ ማሰልጠኛ ካምፕ መሽጎ የነበረውን ሆድ አደር እና የብአዴን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻን አድማ ብተና ሃይልን የማያዳግም እርምጃ በመወሰዱ ፋሽስቱ አገዛዝ በበርካታ አንቡላንሶች ቁጥሩ ያልታወቀ የአድማ ብተና የሚሊሻ ፣እንድሁም መከላከያ በአምስት ኦራል ወደ አፋር ክልል ጭፍራ ከተማ አጓጉዟል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መሀመድ ሞገስ አስታውቋል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 6/2018 ዓ.ም
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉስ ሚካኤል ኮር አደም አሊ ክፍለጦር ገገለታ ብርጌድ ጥምር የጠላት ጦር ላይ ድል ተቀዳጀ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር አደም አሊ ክፍለጦር ገገለታ ብርጌድ መስከረም 5/2018 ዓ.ም ንጋት 11:00 ለከበባ የመጣን ጥምር የጠላት ጦር በመመከትና መልሶ በማጥቃት እስከ ቀን 5:00 ድረስ ከባድ ትብቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ሁለት ጓድ የጠላት ሃይል በመደምሰስና ከ15 በላይ በማቁሰል ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::

ይህንን ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ አርበኛ ከረም መሃመድ የመራው ሲሆን ጠላት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ ደርሶበታል:: ባለፉት ጊዜያትም ሳጅን እደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለጦር ቦረና ገነቴ ከተማና አካባቢው ላይ በርካታ ተጋድሎዎችን በማድረግ በጠላት ላይ የበላይነትን ወስደው እንደኖሩ ይታወቃል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 6/2018 ዓ.ም
👍2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ

አሳምነው ክፍለጦር ወልድያ ከተማ በምሽት የተሳካ ኦፕረሽን ፈመፈፀም ድል ተጎናፀፉ::

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ መስከረም 5/2018 ዓ.ም ምሽት 5:00 በመግባት አንድ ፓትሮል አድማ ብተና ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስና ሌሎች ጀብዶችንም በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፅፈው አድረዋል::

በአርበኛ ዘውዱ ዘመላክ የሚመራው 5ኛ ሻለቃ በምሽት ወልድያ ከተማ ዘልቆ በመግባት በፓትሮል ይንቀሳቀሱ የነበሩ አድማ ብተናዎችን ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ እና ሌሎች ጀብዶችን በመፈፀም ታልቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በደረሰበት ሽንፈት በመበሳጨት እንደተለመደው የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር አንድ የግለሰብ መኖሪያ ቤት በብሬን በመደብደብ ንፁሃኖች ላይ ጉዳት በማድረስ መኖሪያ ቤቱንም አውድሟል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 6/2018 ዓ.ም
👍2