ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ድንቅ ምስሎች !
የአፋብኋ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ አመራሮች እና አሰልጣኞች
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ   ‎ሰባት ለሰባ ክ/ጦር ለተከታታይ አራት ቀን ባካሄደው ውይይት የክ/ጦሩን አመራሮች በድጋሚ በመሰየም በሰላም ተጠናቀቀ።
‎=============
‎መስከረም 5/2018 ዓ ም
‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሰባት ለሰባ ክ/ጦር ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው ውይይት ነባር እና አዳዲስ የክ/ጦሩን አመራሮች ገምግሞ ማሻሻያ በማድረግ መድቧል::

‎ክ/ጦሩ የአመራር ምደባ ያካሄደው ወደ እዙ ባደጉ እና የአጼ ዘርዓ ዓዕቆብ ኮር መመስረቱን ተከትሎ ወደ ኮር የሄዱ አመራሮች በመኖራቸው ነው::

‎ይህንን የአማራር ሽግሽግ ክ/ጦሩ ለማሟላት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አመራሮች ባሉበት ለተከታታይ አራት ቀን ግምገማ ካካሄደ በኋላ ነባር እና አዳዲስ አመራሮችን ክ/ጦሩን እንዲመሩ መድቧል::

‎ይህ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ የአፋብኃ ማእከላዊ ኮማንድ አባል እና የዕዙ ዋና መሪ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ፥ የዐሰዙ ም/ል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ እና የአሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ባዩ አለባቸው ባሉበት ተካሄዷል::

‎በዚሁ መሰረት ፥
👉የሰባት ለሰባ  ክፍለጦር ዋና መሪ ........ ፋኖ ደመላሽ ደመቀ
👉ወታደራዊ አዛዥ .......አረጋ ሙሉነህ
👉ምክትል አዛዥ  ኦፕሬሽን...... እሸቱ በቀለ
👉ምክትል አዛዥ አስተዳደር...... እንዳለ ሸዋዬ
👉ዋና ዘመቻ መምሪያ........ነጋ ንጉሴ
👉ምክትል ዘመቻ ............ጌታሁ ንጉሴ
👉ምክትል አዛዥ ሎጀስቲክ...... ታሪኩ አየለ
👉 ኦርዲናንስ.....ታምራት እምሻው
👉ቀልብ እና እደላ.....የምሩ ግዛው
👉 የህክምና ቡድን መሪ ........ይንገስ ከፈለኝ
👉ድርጅት ጉዳይ ....በለጠው ጋሻነህ
👉ፖለቲካ ዘርፍ .......ዳዊት ገ/መስቀል
👉ፋይናንሰ ...........ከበደ ሀብቴ
👉ሪፖርተር  ...........ዝናው በቀለ
👉አስተዳደራዊ ጉዳይ ........አባተ መስፍን
👉አደረጃጀት ............ንጉስ መሰለ
‎ ሆነው ተመርጠው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

‎መረጃውን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያዕቆብ ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል አድርሶናል።

           " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
‎       መስከረም 05/2018 ዓ.ም
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

የአፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክፍለጦር ከስበር ሻለቃ የተውጣጡ ተወርዋሪዎች ከወረኢሉ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ሰኞ ገበያ ከተማ መስከረም 4/2018 ዓ.ም አዳር በመግባት ከተማዋ መሽጎ የነበረው ባንዳ ሚሊሻና ፖሊስ ምንም ሳይተኩስ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ቀሪው ብትንትኑ የወጣ ሲሆን ሶስት የስርዓቱ ገረድ በመሆን ህዝብን የፋኖ ደጋፊ ናቸው እያሉ ሲያግቱ ሲረሽኑ ሲያሰቃዩ የነበሩ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሌላውም ከዚህ በመማር በህዝባችን ላይ ጥፋትና ወንጀል ፈፅሞ ማምለጥ እንደማይቻልና አብይ አህመድና ቡድኑ ሳይገባውም ገብቶትም ከእሱ ጎን የቆመ አካል ቢሞትም ቢቆስልም ደስታው ፋኖ የቆሰለ የተሰዋ ያክል እኩል መሆኑን በአደባባይ እያረጋገጠላችሁ እንደሁ ብዙ ማሳያዎች አሉ ምክናየቱም ሆዳሞች ሆናችሁ ወገናችሁን ለመውጋት ቢዘምቱም እናተም አማራ ስለሆናችሁ መቸም አያምናችሁምና በፍጥነት አስተውሉና ለወንድሞቻችሁ እጅ በመስጠት መታገሉ ቀርቶባችሁ ህይወታችሁን እንድታተርፉ አስቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሱልጣን የሱፍ አፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 5/2017 ዓ.ም
👍1
መንደር 29 ላይ የተሳካ ደፈጣ በመጣል አመራሩ ተገደለ።

የአ/ፋ/ብ/ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ነበልባሎቹ የአባይ መተከል ብርጌድ የፋኖ አባላት በአረመኔው የአገዛዙ ተላላኪ ሚሊሻ እና አድማ በትን አባላት ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ፈፅሟል። በቀን 05/01/2018 ዓ.ም የበረሃ ፈርጦቹ የአባይ መተከል አባላት
ከወርቅ ሀገር እና መንደር 29 ከተባለ ቦታ መካከል ደፈጣ በመያዝ:-
1.ፈረደ ቸኮል_ የደቅ ሊቀመንበር የነበረ የፋኖ ቤተሰብን የሚያሰቃይ እና የፋኖ ቤቶችን የሚያስፈርስ ባንዳ
2.ሙሉ ታገል_ አድማ በትን
3.ጌትነት አቤ _ አድማ በትን
4.እንዳወቅ አጥናፍ_ አድማ በትን
እንዲሁም 3 የሚሊሻ  አባላትን ጨምሮ በጠቅላላ 7 የጠላት ኃይል መደምሰስ ተችሏል። እንዲሁም 3 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ተማርኳል።

አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ !

አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

        መስከረም 05/2018 ዓ.ም
1
42 ሀገራት በኢትዮጵያ የሲቪክ ምህዳር መጥበብ እንዳሳሰባቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቁ

አርባ ሁለት ሀገራት በኢትዮጵያ በተያዘው አመት ከሚካሄደው ምርጫ ቀደም ብሎ በመሰረታዊ መብቶች ላይ ገደቦች መጣላቸውን በመጥቀስ በሀገሪቱ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቁ።

ሀገራቱ ባሳለፍነው ባወጡት የጋራ መግለጫ “በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ፣ በተለይም ሀሳብን በነፃነት የመናገር፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እና የመደራጀት መብቶች መገደባቸው አሳስቦናል” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፣ “በቅርቡ በሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተፈጸመውን ማስፈራራት እና እገዳን ጨምሮ የሲቪክ ምህዳር መጥበብ እና መዘጋት አሳሳቢ ነው” ብለዋል። ሀገራቱ በገለልተኛ መገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ማስፈራራትም ስጋት እንደፈጠረባቸው በመግለጽ፣ ለእነዚህ ክስተቶች ግልጽ የሆነ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

ፊርማቸውን ያኖሩት ሀገራቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት በ2024 ሪፖርቱ ላይ “በመንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች መፈጸማቸው መገለጹን” ጠቅሰው ይህም አሳሳቢ መሆኑን አመላክተዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ በ2025 በህጻናት እና በትጥቅ ግጭቶች ዙሪያ የቀረበን ሪፖርት በመጥቀስ፣ “የህጻናት መገደልና የአካል ጉዳት ማድረስ፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ እንዲሁም መታገትን ጨምሮ በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ” በእጅጉ እንደሚያሳስባቸውም ገልጸዋል።

በተጨማሪም፤ “የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች ሁሉም ተዋናዮች በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይን ጨምሮ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በደል ለማስቆም ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን” ብሏል መግለጫው።

በተለያዩ አካላት እየተፈጸመ ያለውን “ በንጹሃን ሰዎች ላይ ግድያና ጉዳት ማድረስ፣ ማሰቃየት፣ ኢ_ሰብዓዊ አያያዝ፣ በግዳጅ መሰወር፣ የዘፈቀደ እስር እና ማቆየት፣ በንጹሃን ሰዎች መሰረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን፣ እንዲሁም ከባድ ደረጃ ላይ የደረሰ ወሲባዊ እና ጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት” በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል።

ሀገራቱ ባለስልጣናት በአገር አቀፍ ደረጃ የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ፣ ፍትህና ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል።

የጋራ መግለጫው በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ሂደት ውስጥ መሻሻል ባለመኖሩም ስጋቱን ገልጿል። ተአማኒነት ያለው የሽግግር ፍትህ እና የተጠያቂነት ማዕቀፍ መተግበር “ለተጎጂዎች እና ከጉዳት ለተረፉት ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና እርቅ ለማረጋገጥም ወሳኝ ነው” ሲል አስታውሷል።

ሀገራቱ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት “ከተባበሩት መንግስታት እና ከሌሎች የጥበቃ አካላት ጋር እንዲተባበር እና ገልተኝነታቸውን እንዲያከብር” አሳስበዋል።

ሁሉም ወገኖች ተጨማሪ ጥሰቶች ከመፈጸም እንዲታቀቡ እና መረጋጋትን ለመመለስ በሰላማዊ ውይይት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቴዋል።

(አዲስ ስታንዳርድ- አስ እንደዘገበው)
3
በ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ብርጌዶች የህዝብ ውይይቶች እና የመሰረተ ልማት ስራዎች እንደቀጠሉ ናቸው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ እነማይ ወረዳ አዲስ ዓለም ቀበሌ እና ደብረ ገነት ጎተራ ቀበሌ መስከረም 05/2018 ዓ.ም ህዝባዊ ውይይት አካሂዶል።

አባ ኮስትር ብርጌድ የሰለጠነ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በመገንባት የህዝብ አስተዳደር ስራዎችን በመስራት ትግሉን እያጦጣፈ ይገኛል።አባ ኮስትር ብርጌድ በእነማይ ወረዳ ደብረ ገነት ጎተራ ቀበሌ ግዚያዊ አስተዳደር የቀበሌ የፍትህ አካላትን በመሰብሰብ ውይይት አካሂዶል።

በእነማይ ወረዳ ደብረ ገነት ጎተራ ቀበሌ የሻለቃ አመራሮቹ እና የፍትህ አካላት በተገኙበት  የግዚያዊ አስተዳደር እና የቀበሌው የፍትህ አካላት አዋቅሯል። በውይይቱም ላይ ለአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ተነስተው ጥልቅ ውይይት ተካሂዶል።በውይይቱም የብርጌድ እና የሻለቃ አመራር ተገኝተዋል።

የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ደባይ ጮቄ ብርጌድ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች እና የመሰረተ ልማት ጥገናዎችን መስከረም 05/2018 ዓ.ም እያካሄደ ይገኛል።

ደባይ ጮቄ ብርጌድ በደባይ ጥላትግን ወረዳ የባባት ቀበሌ የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በፋኖ እና በህብረተሰቡ ያሉ ግንኙነቶች እንዲሁም የግዚያዊ አሰተዳደሮችን በመገምገም አዲስ የህዝብ አሰተዳደሮችን አስመረጦ የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ አሰቀምጠዎል።

በደባይ ጥላትግን ወረዳ ወደብ እየሱስ ቀበሌ የሚገኘውን በጎርፍ ምክንያት የተጎዱ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን በማህበረሰብ ተሳትፎ አየጠገነ ይገኛል።በውይይቱም የብርጌድ አመራር እና የሻለቃ አመራሮች ተገኝተዋል።

መስከርም 05/2018 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🙏2