ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለ ጦር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት አካሄደ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር መስከረም 4/2018 ዓ.ም ደማቅ የተሃድሶ ዝግጅት በማካሄድ በህልውና ትግሉ የተሰው ሰማዕታትን በማሰብ የቆሰሉ ታጋዮችን በማበረታታት ትግሉን እየመሩ ያሉ የሻለቃ የክፍለጦርና የኮር አመራሮችን በመሸለምና በማበረታታት ለአዲስ ድል እንዲዘጋጁ ተልዕኮና አደራ በመስጠት አክብሯል::

ይህ ታላቅ ዝግጅት በክፍለጦሩ አዛዥ አርበኛ ሃብተማርያም መኮነን የ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግርና በኮር 2 ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ረዳ ውበቱ (አባ አዝመራ) የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን ዞብል አምባ ክፍለጦር ከሰሜኑ ጦርነት እስከ አሁኑ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሳላፉት ደማቅ የትግል ጉዞ በክፍለጦሩ የፖለቲካ አመራር አርበኛ ሻምበል አሌ ቀርቧል::

በመጨረሻም በዚህ ከፍተኛ የተሃድሶ ዝግጅት የተገኙ በርካታ የክፍለጦር የኮርና የድርጅት አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው በኮሎኔል ሞገስ ዘገየ እና በኮር 2 ወታደራዊ ዋና አዛዥ አርበኛ አለሙ ገብሩ የቀጣይ የትግል አቅጣጫ ተሰጥቶ በአርበኛ ኪሮስ ደርቤ በሚመራው አምባሰል ባንድ በደማቅ ሁኔታ ተዘግቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 5/2018 ዓ.ም
👍2
ድንቅ ምስሎች !
የአፋብኋ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ አመራሮች እና አሰልጣኞች
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ   ‎ሰባት ለሰባ ክ/ጦር ለተከታታይ አራት ቀን ባካሄደው ውይይት የክ/ጦሩን አመራሮች በድጋሚ በመሰየም በሰላም ተጠናቀቀ።
‎=============
‎መስከረም 5/2018 ዓ ም
‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሰባት ለሰባ ክ/ጦር ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው ውይይት ነባር እና አዳዲስ የክ/ጦሩን አመራሮች ገምግሞ ማሻሻያ በማድረግ መድቧል::

‎ክ/ጦሩ የአመራር ምደባ ያካሄደው ወደ እዙ ባደጉ እና የአጼ ዘርዓ ዓዕቆብ ኮር መመስረቱን ተከትሎ ወደ ኮር የሄዱ አመራሮች በመኖራቸው ነው::

‎ይህንን የአማራር ሽግሽግ ክ/ጦሩ ለማሟላት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አመራሮች ባሉበት ለተከታታይ አራት ቀን ግምገማ ካካሄደ በኋላ ነባር እና አዳዲስ አመራሮችን ክ/ጦሩን እንዲመሩ መድቧል::

‎ይህ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ የአፋብኃ ማእከላዊ ኮማንድ አባል እና የዕዙ ዋና መሪ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ፥ የዐሰዙ ም/ል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ እና የአሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ባዩ አለባቸው ባሉበት ተካሄዷል::

‎በዚሁ መሰረት ፥
👉የሰባት ለሰባ  ክፍለጦር ዋና መሪ ........ ፋኖ ደመላሽ ደመቀ
👉ወታደራዊ አዛዥ .......አረጋ ሙሉነህ
👉ምክትል አዛዥ  ኦፕሬሽን...... እሸቱ በቀለ
👉ምክትል አዛዥ አስተዳደር...... እንዳለ ሸዋዬ
👉ዋና ዘመቻ መምሪያ........ነጋ ንጉሴ
👉ምክትል ዘመቻ ............ጌታሁ ንጉሴ
👉ምክትል አዛዥ ሎጀስቲክ...... ታሪኩ አየለ
👉 ኦርዲናንስ.....ታምራት እምሻው
👉ቀልብ እና እደላ.....የምሩ ግዛው
👉 የህክምና ቡድን መሪ ........ይንገስ ከፈለኝ
👉ድርጅት ጉዳይ ....በለጠው ጋሻነህ
👉ፖለቲካ ዘርፍ .......ዳዊት ገ/መስቀል
👉ፋይናንሰ ...........ከበደ ሀብቴ
👉ሪፖርተር  ...........ዝናው በቀለ
👉አስተዳደራዊ ጉዳይ ........አባተ መስፍን
👉አደረጃጀት ............ንጉስ መሰለ
‎ ሆነው ተመርጠው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

‎መረጃውን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያዕቆብ ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል አድርሶናል።

           " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
‎       መስከረም 05/2018 ዓ.ም
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

የአፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክፍለጦር ከስበር ሻለቃ የተውጣጡ ተወርዋሪዎች ከወረኢሉ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ሰኞ ገበያ ከተማ መስከረም 4/2018 ዓ.ም አዳር በመግባት ከተማዋ መሽጎ የነበረው ባንዳ ሚሊሻና ፖሊስ ምንም ሳይተኩስ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ቀሪው ብትንትኑ የወጣ ሲሆን ሶስት የስርዓቱ ገረድ በመሆን ህዝብን የፋኖ ደጋፊ ናቸው እያሉ ሲያግቱ ሲረሽኑ ሲያሰቃዩ የነበሩ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሌላውም ከዚህ በመማር በህዝባችን ላይ ጥፋትና ወንጀል ፈፅሞ ማምለጥ እንደማይቻልና አብይ አህመድና ቡድኑ ሳይገባውም ገብቶትም ከእሱ ጎን የቆመ አካል ቢሞትም ቢቆስልም ደስታው ፋኖ የቆሰለ የተሰዋ ያክል እኩል መሆኑን በአደባባይ እያረጋገጠላችሁ እንደሁ ብዙ ማሳያዎች አሉ ምክናየቱም ሆዳሞች ሆናችሁ ወገናችሁን ለመውጋት ቢዘምቱም እናተም አማራ ስለሆናችሁ መቸም አያምናችሁምና በፍጥነት አስተውሉና ለወንድሞቻችሁ እጅ በመስጠት መታገሉ ቀርቶባችሁ ህይወታችሁን እንድታተርፉ አስቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሱልጣን የሱፍ አፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 5/2017 ዓ.ም
👍1