ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ የብልፅግናን አስገዳጅ ስብሰባ በተነ።

የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር ከተቆጣጠረባቸው ሶስት ወረዳዎች ማለትም ግሼራቤል ወረዳ ከሚሴ ልዩዞን ዳዋ ጨፌ ወረዳ እና የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሲሆኑ በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ 30 ትምህርትቤቶች ሲኖሩ 27ቱን ትምህር ቤቶች የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በማስተዳደር ተማሪዎችን በ2018 ዓ.ም ትምህርታቸውን እንዲማሩ ከመምህራኖች ጋር ውይይት በማድረግ ምዝገባ እንዲጀመር አድርጓል ።

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲማሩ ምቹ እና አስቻይ ሆኔታዎችን በመፍጠሩ እና የትምህርት ስርዓቱ እንዲቀጥል በፍጥነት እንዲጀመር በቀጠናው የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር ከመምህራኖች ጋር ውይይት አድርጎ የተማሪዎች  ምዝገባ ፋኖ ባለበት ቀጠና እንደሚጀመር ታውቋል።

ይህ ያበሳጨው ብልፅግና የፋኖን ትምህርት የማስጀመርና የመፋቀድ እቅስቃሴ ለማስተጓጉል መምህራንና ወላጆች ላይ ሽብር በመፋጠር  ፀረ ህዝብ መሆኑን አስመስክሯል። 

መምህራን እና ወላጆችን ከሰሞኑ ብልፅግና በሁሉም ሀገራችን ክፋል የያዘውን ለግድቡ ተሰለፉ መልከጥፉን በመልክ ይደግፉ ሰልፋ ህዝባችንን በግዳጅ ጠርቶ ሊያሰልፋ ቢሞክርም የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር የአያሌው መክት ሻለቃ እና የክፋለጦሩ ቃኝዎች በአገዛዙ ወንበር ጠባቂ  ሰራዊት ላይ ተኩስ በመክፈት ብልፅግና በአስገዳጅ ሁኔታ የጠራውን ሰልፍ መበተን ተችሎል።

@የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ድል ለአማራ ፋኖ !!
👍1
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለ ጦር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት አካሄደ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር መስከረም 4/2018 ዓ.ም ደማቅ የተሃድሶ ዝግጅት በማካሄድ በህልውና ትግሉ የተሰው ሰማዕታትን በማሰብ የቆሰሉ ታጋዮችን በማበረታታት ትግሉን እየመሩ ያሉ የሻለቃ የክፍለጦርና የኮር አመራሮችን በመሸለምና በማበረታታት ለአዲስ ድል እንዲዘጋጁ ተልዕኮና አደራ በመስጠት አክብሯል::

ይህ ታላቅ ዝግጅት በክፍለጦሩ አዛዥ አርበኛ ሃብተማርያም መኮነን የ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግርና በኮር 2 ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ረዳ ውበቱ (አባ አዝመራ) የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን ዞብል አምባ ክፍለጦር ከሰሜኑ ጦርነት እስከ አሁኑ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሳላፉት ደማቅ የትግል ጉዞ በክፍለጦሩ የፖለቲካ አመራር አርበኛ ሻምበል አሌ ቀርቧል::

በመጨረሻም በዚህ ከፍተኛ የተሃድሶ ዝግጅት የተገኙ በርካታ የክፍለጦር የኮርና የድርጅት አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው በኮሎኔል ሞገስ ዘገየ እና በኮር 2 ወታደራዊ ዋና አዛዥ አርበኛ አለሙ ገብሩ የቀጣይ የትግል አቅጣጫ ተሰጥቶ በአርበኛ ኪሮስ ደርቤ በሚመራው አምባሰል ባንድ በደማቅ ሁኔታ ተዘግቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 5/2018 ዓ.ም
👍2
ድንቅ ምስሎች !
የአፋብኋ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ አመራሮች እና አሰልጣኞች
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ   ‎ሰባት ለሰባ ክ/ጦር ለተከታታይ አራት ቀን ባካሄደው ውይይት የክ/ጦሩን አመራሮች በድጋሚ በመሰየም በሰላም ተጠናቀቀ።
‎=============
‎መስከረም 5/2018 ዓ ም
‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሰባት ለሰባ ክ/ጦር ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው ውይይት ነባር እና አዳዲስ የክ/ጦሩን አመራሮች ገምግሞ ማሻሻያ በማድረግ መድቧል::

‎ክ/ጦሩ የአመራር ምደባ ያካሄደው ወደ እዙ ባደጉ እና የአጼ ዘርዓ ዓዕቆብ ኮር መመስረቱን ተከትሎ ወደ ኮር የሄዱ አመራሮች በመኖራቸው ነው::

‎ይህንን የአማራር ሽግሽግ ክ/ጦሩ ለማሟላት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አመራሮች ባሉበት ለተከታታይ አራት ቀን ግምገማ ካካሄደ በኋላ ነባር እና አዳዲስ አመራሮችን ክ/ጦሩን እንዲመሩ መድቧል::

‎ይህ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ የአፋብኃ ማእከላዊ ኮማንድ አባል እና የዕዙ ዋና መሪ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ፥ የዐሰዙ ም/ል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ እና የአሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ባዩ አለባቸው ባሉበት ተካሄዷል::

‎በዚሁ መሰረት ፥
👉የሰባት ለሰባ  ክፍለጦር ዋና መሪ ........ ፋኖ ደመላሽ ደመቀ
👉ወታደራዊ አዛዥ .......አረጋ ሙሉነህ
👉ምክትል አዛዥ  ኦፕሬሽን...... እሸቱ በቀለ
👉ምክትል አዛዥ አስተዳደር...... እንዳለ ሸዋዬ
👉ዋና ዘመቻ መምሪያ........ነጋ ንጉሴ
👉ምክትል ዘመቻ ............ጌታሁ ንጉሴ
👉ምክትል አዛዥ ሎጀስቲክ...... ታሪኩ አየለ
👉 ኦርዲናንስ.....ታምራት እምሻው
👉ቀልብ እና እደላ.....የምሩ ግዛው
👉 የህክምና ቡድን መሪ ........ይንገስ ከፈለኝ
👉ድርጅት ጉዳይ ....በለጠው ጋሻነህ
👉ፖለቲካ ዘርፍ .......ዳዊት ገ/መስቀል
👉ፋይናንሰ ...........ከበደ ሀብቴ
👉ሪፖርተር  ...........ዝናው በቀለ
👉አስተዳደራዊ ጉዳይ ........አባተ መስፍን
👉አደረጃጀት ............ንጉስ መሰለ
‎ ሆነው ተመርጠው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

‎መረጃውን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያዕቆብ ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል አድርሶናል።

           " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
‎       መስከረም 05/2018 ዓ.ም
🙏1