ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሕዝባዊ ውይይት በስናን አባጅሜ ብርጌድ!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር የስናን አባጅሜ ብርጌድ ከሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች ውስጥ አንዱ በሆነው የግድምብል ቀበሌ ማሕበረሰባዊ ውይይቶችን አካሂዷል።
በውይይቱ የትግላችንን የእድገት ደረጃና አሁናዊ ቁመናውን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምሕርት የተሰጠ ሲሆን በቀበሌው ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
በተጨማሪም ሕዝባችን የትግሉ ባለቤት እስከሆነ ድረስ ለቀጣይ ጉዟችን ወሳኝ የሆኑ ነጥቦችም ተነስተዋል።
ድል ለሕዝባችን!
መስከረም 05/2018 ዓ.ም
3
ሰበር መረጃ

በወልድያ ከተማ በነገው ዕለት ሊያካሂድ ላሰበው ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ሰዎችን በጅምላ ማፈኑ ተሰማ።

የሰሜን ወሎ ዞን የወልደያ ከተማ የህዳሴ ግድቡን ምርቃት አስመልክቶ በሚል ሰበብ የብልፅግና ድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ እየተሰናዳ ሲሆን ህዝቡን ለማሸበርና ሰልፍ እንዲወጡ ለማስገደድ በሚል በዛሬው ዕለት ከወጣት እስከ አዋቂ በጅምላ ሲያፍን ውሏል።

የባጃጅ ሾፌሮች ፣ የቀን ሰራተኞች ፣ በመንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ ስለመታሰሩና ተሽከርካሪዎች ላይ በግዳጅ የሰልፍ ባነር እየለጠፉ እንደዋሉ ምንጮቻችን ለአለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ ገልፀዋል። አመሻሹንም ባጃጆችን በማስገደድና የመንግስት መኪኖችና ሞተረኞችን በአንድ መስመር እንዲሄዱ በማድረግና አደባባይ በማዞር የሰልፍ ቅድመ ሙከራ አድርገዋል።

በነገው ዕለት ለሚካሄደው ሰልፍም የሴፍትኔት ተጠቃሚዎችንና ባለባጃጆችን ብሎም የመንግስት ሰራተኞችን በማስገደድ እንዲወጡ መመሪያ በመተላለፉ ለማወቅ ተችሏል።

በነገው ዕለት የሚደረግ ሰልፍ አገዛዙ በአደባባይ ያጣውን የህዝብ ቅቡልነት በአስገዳጅ መልኩ ለማግኘት የሚጥርበት በመሆኑ ህዝቡ እንዳይሳተፍ ጥሪ ቀርቧል።

@አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ
    የፋኖ ድምፅ !
2
ሰበር ዜና!

የአገዛዙ ብልፅግና ኃይል ከበዓል መልስ ወደ ዳባትና ደባርቅ ከተሞች ሲጓዝ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ  ጦር ተመትቶ ተመለሰ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር   ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዛሬ መስከረም 5 /2018 ዓ/ም ከአዘዞ ካምፕ ለበዓልና ለስምሪት በሚል ሰንብተው ዛሬ ወደ  ዳባትና ደባርቅ  ከተሞች ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲጓዝ   ወርቅ ደቦ ላይ በጀግኖች መብረቃዊ ምት ተመትቷል።

በአውደ ውጊያው የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  አሀድ የሆኑት ቴውድሮስ እና  አጥናፋ ብርጌዶች የተሳተፋ ሲሆን የአገዛዙ ሀይል በደረሰበት ደፈጣ  ማሳለፋን ጥሎ ወደ አንባጊወርጊስና ጎንደር ከተሞች አመራሮችና አሽከሮቻቸው ነፍሴ አውጭኝ በእግርና በመኪና እየፈረጠጠ ተመልሷል።

የክፍለ ጦርና እና የብርጌድ አመራሮች በተሳተፋበት አውደ ውጊያ የብርሃኑ ጁላ ሀይል ዛሬም  7  በሙት  4 በቁስል  ተቀንሷል።

ከአምባጊወርጊስ እስከ ገደብየ ከተማ ድረስ ያለው  ጥቁር አስፖልት ዛሬም በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  ጀግኖች ቁጥጥር ስር ሁኖ እንደ ንስር በንቃት እየተጠበቀ ይገኛል።

     ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )።
👍4
የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ የብልፅግናን አስገዳጅ ስብሰባ በተነ።

የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር ከተቆጣጠረባቸው ሶስት ወረዳዎች ማለትም ግሼራቤል ወረዳ ከሚሴ ልዩዞን ዳዋ ጨፌ ወረዳ እና የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሲሆኑ በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ 30 ትምህርትቤቶች ሲኖሩ 27ቱን ትምህር ቤቶች የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በማስተዳደር ተማሪዎችን በ2018 ዓ.ም ትምህርታቸውን እንዲማሩ ከመምህራኖች ጋር ውይይት በማድረግ ምዝገባ እንዲጀመር አድርጓል ።

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲማሩ ምቹ እና አስቻይ ሆኔታዎችን በመፍጠሩ እና የትምህርት ስርዓቱ እንዲቀጥል በፍጥነት እንዲጀመር በቀጠናው የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር ከመምህራኖች ጋር ውይይት አድርጎ የተማሪዎች  ምዝገባ ፋኖ ባለበት ቀጠና እንደሚጀመር ታውቋል።

ይህ ያበሳጨው ብልፅግና የፋኖን ትምህርት የማስጀመርና የመፋቀድ እቅስቃሴ ለማስተጓጉል መምህራንና ወላጆች ላይ ሽብር በመፋጠር  ፀረ ህዝብ መሆኑን አስመስክሯል። 

መምህራን እና ወላጆችን ከሰሞኑ ብልፅግና በሁሉም ሀገራችን ክፋል የያዘውን ለግድቡ ተሰለፉ መልከጥፉን በመልክ ይደግፉ ሰልፋ ህዝባችንን በግዳጅ ጠርቶ ሊያሰልፋ ቢሞክርም የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር የአያሌው መክት ሻለቃ እና የክፋለጦሩ ቃኝዎች በአገዛዙ ወንበር ጠባቂ  ሰራዊት ላይ ተኩስ በመክፈት ብልፅግና በአስገዳጅ ሁኔታ የጠራውን ሰልፍ መበተን ተችሎል።

@የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ድል ለአማራ ፋኖ !!
👍1
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለ ጦር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት አካሄደ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር መስከረም 4/2018 ዓ.ም ደማቅ የተሃድሶ ዝግጅት በማካሄድ በህልውና ትግሉ የተሰው ሰማዕታትን በማሰብ የቆሰሉ ታጋዮችን በማበረታታት ትግሉን እየመሩ ያሉ የሻለቃ የክፍለጦርና የኮር አመራሮችን በመሸለምና በማበረታታት ለአዲስ ድል እንዲዘጋጁ ተልዕኮና አደራ በመስጠት አክብሯል::

ይህ ታላቅ ዝግጅት በክፍለጦሩ አዛዥ አርበኛ ሃብተማርያም መኮነን የ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግርና በኮር 2 ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ረዳ ውበቱ (አባ አዝመራ) የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን ዞብል አምባ ክፍለጦር ከሰሜኑ ጦርነት እስከ አሁኑ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሳላፉት ደማቅ የትግል ጉዞ በክፍለጦሩ የፖለቲካ አመራር አርበኛ ሻምበል አሌ ቀርቧል::

በመጨረሻም በዚህ ከፍተኛ የተሃድሶ ዝግጅት የተገኙ በርካታ የክፍለጦር የኮርና የድርጅት አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው በኮሎኔል ሞገስ ዘገየ እና በኮር 2 ወታደራዊ ዋና አዛዥ አርበኛ አለሙ ገብሩ የቀጣይ የትግል አቅጣጫ ተሰጥቶ በአርበኛ ኪሮስ ደርቤ በሚመራው አምባሰል ባንድ በደማቅ ሁኔታ ተዘግቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 5/2018 ዓ.ም
👍2
ድንቅ ምስሎች !
የአፋብኋ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ አመራሮች እና አሰልጣኞች
🙏1