ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሸዋ ሜዳ ላይ በደፈጣ ተመታ።
ክንዳቸው የማይዝለው በቅፅል ስማቸው የምድር ድሮኖች የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች ከመሸ ታምር ሰርተዋል።

መነሻውን አዴት አድርጎ በአንድ ኦራልና አንድ ፓትሮል በመሆን የአረመኔው ሰራዊት እሬሽን ለማቀበል ወደ አዳማ ሲንቀሳቀስ ከአዴት እንደወጣ ከቀኑ 11:ሰዓት  ሽዋ ሜዳ ላይ በደፈጣ በተፈፀመ ጥቃት ፓትሮሉ ላይ ዲሽቃ ጠምዶ የነበረውን ተኳሸ እና አራት የአረመኔውን አገዛዝ አባላት ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት የፋሽስቱን ሰራዊት ቅንድቡን በማለት የተሰናበቱ ሲሆን ጀግኖች እቅዱን አክሽፈው መልሰውታል።

የአረመኔው ስርዓት ጦር መፍረሱን  ቀጥሏል።
በስርዓቱ ሲያገለግ የነበረው ወጣት ታፈረ አሰፋ  ተሰባስበው ይዘርፉበት ከነበረው ኬላ ላይ የጓዱን መሳሪያ ነጥቆ ጥቁር ክላሽ በመያዝ የወምበርማ ብርጌድን ተቀላቅሏል።

ወጣት ታፈረ አሰፋ አማራ ሁኜ አማራን አልዋጋም፣ የአማራ ንጹሃን እናቶች ሲደፈሩ፣ ንጹሃን አባቶች ሲታረዱ በአይኔ ሰላየሁ የአርበኛ ዘመነ ካሴን ጥሪ ተቀብዬ ፋኖን ተቀላቅያለሁ ብሏል።

በአረመኔው ስርዓት ውስጥ ሁነው ሚስጥሩ ያልገባቸው የሰላም አስከባሪ ጓዶች ወደፋኖ በመቀላቀል ዕራሳቸሁን እና ማህበረሰቡን ታደጉ ሲልም ታፈረ አሰፋ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ !!
መስከረም 2/2018 ዓ.ም
5
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ

ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ግዮን ብርጌድ ኃይል አድማሱ ሻለቃ ጠላት እሬሽን ተቀብሎ ሲመለስ ከአላይታ እስከ አምቢስ ደፈጣ በመያዝ ጠላት ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

አናብስቶቹ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ያደረሱበት ሲሆን የአረመኔዉ አገዛዝ እግሬ አዉጭኝ በማለት ፈርጥጦ ግሽ ተራራ ላይ ተሰቅሏል።

ክንዳቸው የማይዝለው በቅፅል ስማቸው የምድር ድሮኖች የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች ከመሸ ታምር ሰርተዋል።

መነሻውን አዴት አድርጎ በአንድ ኦራልና አንድ ፓትሮል በመሆን የአረመኔው ሰራዊት እሬሽን ለማቀበል ወደ አዳማ ሲንቀሳቀስ ከአዴት እንደወጣ ከቀኑ 11:ሰዓት ሽዋ ሜዳ ላይ በደፈጣ በተፈፀመ ጥቃት ፓትሮሉ ላይ ዲሽቃ ጠምዶ የነበረውን ተኳሸ እና አራት የአረመኔውን አገዛዝ አባላት  ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት የፋሽስቱን ሰራዊት ቅንድቡን በማለት የተሰናበቱ ሲሆን ጀግኖች እቅዱን አክሽፈው መልሰውታል።

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር  ህዝብ ግንኙነት።
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!

መስከረም 2/2018 ዓ.ም
👍32
እንደ እነ አቦይ ስብአት አልፎም እንደ እነ ጌታቸው ረዳ አልያም እንደ እነ አብዲኢሌ አገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል ወንጅል ሲሰራ እጅ ከፈንጅ ተይዞ ሳይሆን #አማራነቱ ወንጀል ሁኖበት በእስር እየማቀቀ የግፍ ግፍ እየተሰራበት ባጋጠመው ህመም ሁለቱ ኦፕራሲዎን ተደርጓል።

የመጀመሪያውን ኦፕራሲዎን ተደርጎ በወጉ ሳያገግም ደም እያዘነበ ከሆስፒታል ወደ ቂሊንጦ ወረወሩት ከዛም ኢንፊክሽን ተፈጠረ ሰሞኑን መልሶ ኦፕራሲዎን ተሰራ አሁንም መልሰው ወደ እስር ቤት ወረወሩት💔
አማራ መሆን ብዙ ያስደርጋል።
ፍትህ በአማራነታቸው ግፍ ለሚፈጸምባቸው የአማራ ፖለቲካ እስረኞች(ጅል የሆንኩ ያክል ተሰማኝ ፍትህ ከማን ይጠቃል?))
መፍትሄው እንደ አማራ በአንድ ቁሞ በፈርጣማው በተባበረ ክንድ ማሸነፍ ነው።
3👍2
የፋኖ አመራሮችን ለማስገደል ተልዕኮ ተሰጥቶት የነበረው የደህንነት አባል እጅ ከፈንጅ ተያዘ!

የደህንነት አባሉ የፋኖ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ጥቆማ በመስጠት በድሮን ለማስገደል እንዲሁም የፋኖ ሎጅስቲክ ማከማቻ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ቦታዎችን ለድሮን ተኳሾች ጥቆማ በመስጠት የማውደም ተልዕኮ ተሰጥቶት ነበር ተብሏል።

የደህንነት አባሉ፡ በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና አርበኛ በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጃች ኮር ስር የሚገኘው ዋዋ ጎቤ ክ/ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ሲቪል ልብስ በመልበስ በአካባቢው ሲንቀሳቀስ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው ሲሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች አስታውቀዋል።

የደህንነት አባሉ መሐመድ ዋዮ ዎቴ በሚል ስም የሚጠቀም መሆኑንና የመከላከያ ሰራዊት አባል እንደሆነ በኪሱ ከያዘው መታወቂያ ለማረጋገጥ ተችሏል።
5
የአዲስአበባ ጎዳናዎች አዲስ ነገር እያስመለከቱን ቀጥለዋል!!!
ሻደይ፣አሸንድየ እና ሶለል እንዳይከበሩ የተከለከሉባት የሀገሪቱ ዋና መዲና አዲስአበባ አዲስ የተፈበረከ በዓል እያስተዋወቁን ይገኛሉ።

ለመሆኑ እነዚህ ጎቤ እና ሸኖየ መቸ መጡ?
በማህበረሰቡ የቆዩ ባህሎች ናቸዉ?
በመንግሥት ጭምር የሚደገፉ እንዲሁም በአገዛዙ ልሳናት በኩል እንዲሰራጩ ተደርገዋል!!!

ነገ በህልዉናችን ፖሮግራም በዝርዝር የምናቀርበዉ ጉዳይ ይሆናል!!
ነገ ምሽት በመረጃ ቴሌቪዥን እና በግሎባል ፋኖ ሚዲያ የዩቲዩብ ገፃችን ይከታተሉን!!
@ ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
በርካታ የጥምር ጦሩ አባላት እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ ተሰማ!!!

ከወለጋ እስከ አርማጭሆ፣ከደብረብርሃን እስከ ራያ አላማጣ በርካታ የጥምር ጦሩ አባላት የፋኖ ሀይሎችን እየተቀላቀሉ ቀጥለዋል።

በአርማጭሆ በተለያዩ ወረዳዎች አገዛዙን ሲያገለግሉ የነበሩ በርካታ የሚሊሻ አባላት በዛሬዉ ዕለት ከነሙሉ ትጥቃቸዉ የፋኖ አደረጃጀትን ሲቀላቀሉ ፋኖን ለመሰለል የገቡ የአገዛዙ የደህንነት ሰዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ዉለዋል።

ሆሮ ጊዱሩ ወለጋ ዞን ከአቤደንጎሮ ወረዳ ቱሉ ጋና ከተማ 8የመከላከያ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ሻምበል መሪው ከነመገናኛ ሬዲዮኑና ከነሙሉ ትጥቁ ፋኖን ሲቀላቀል 3የኦሮሞ ተወላጅና 4 የአማራ ተወላጆች የመከላከያ አባላት ሰሞኑን ጫንጮ ቀበሌ ላይ የአማራው ቤት መቃጠሉን በመቃዎም ፋኖን ተቀላቅለዋል።ቀሪዎቹ ደግሞ ከአገዛዙ አገልጋይነት በመዉጣት ቤተሰቦቻቸዉን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

በክልሉ ዕርሰ መዲና ባህርዳር ክልል ምክርቤት የተሰማሩ እና የብአዴን ባለስልጣን ቪ.አይ.ፒ ጥበቃ ልዩ ሀይል አባላት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቲዎድሮስ ዕዝ አንደኛ ክፍለጦር ባህርዳር ብርጌድን ተቀላቅለዋል።

ከዚህ በፊት ከ20 በላይ የቪ.አይ.ፒ ጥበቃ ልዩ ኃይል አባላት የአፋብኃን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮርን ተቀላቅለዋል!

ከአድማ ብተና ተቋም የአመራ ክልል ምክርቤት ቪአይፒ/VIP/ ጥበቃዎች ጨቋኙን ስርዓት በመክዳት በዛሬዉ ዕለት ፋኖን የተቀላቀሉ ሁለት አባላት
1.ሞገስ አስናቀና
2. አበባየሁ የሻነህ የተባሉ ወንድሞቻችን ከነበሩበት ዘር አጥፊ አማራ ጠል ስርዓት በማፈንገጥ ወደ ትክክለኛ የዐማራ ሕዝብ የነፃነት ትግል ወደ ባህርዳር ብርጌድን ተቀለቅለዋል ሲል የአፋብኃ ምዕራብ ዕዝ ህዝብ ግንኘነት መምሪያ ሀላፊ አስታዉቋል!!!

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
የፋኖ ተቀዳሚ ድምፅ!!
👍1
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ከፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ ለመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ!

እንደሚታወቀው አዲስ ዘመን ይዟቸው ከሚመጣቸው በጎ ቱርፋቶች አንዱ እና ዋናው ቁምነገር ያለፈውን መርሳት የበደሉንን ይቅር ማለት እና ንሰሃቸውን ተቀብሎ ከስህተታቸው ታርመው ወደ እውነተኛ መንገድ እንዲመለሱ እና የበደሉትን እንዲክሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት መንገዶችን መጥረግ መሰናክሎችን ማስወገድ እና ጎርባጣውችን ማደላደል መሆኑን ኮራችን በፅኑ ይገነዘባል።

ስለሆነም አዲሱን ዘመን ምክኒያት በማድረግ ልጅ እያሱ ኮር በዋነኛነት በሚንቀሳቀስባቸው በሰሜን እና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ወረዳዎች ማለትም፦

በደቡብ ወሎ ዞን፦
*^^^*^^^***
1 በአምባሰል ወረዳ
2 በቃሉ ወረዳ
3 በተውለደሬ ወረዳ
4 በወረ ኢሉ ወረዳ
5 በደሴ ዙሪያ ወረዳ
6 በተንታ ወረዳ እና
7 በደላንታ ወረዳ


በሰሜን ወሎ ዞን
*^^^*^^^***
1 በሃብሩ ወረዳ
2 በጉባላፍቶ ወረዳ

በሰሜን ሸዋ ዞን
*^^^*^^^***
ግሽርአቤ ወረዳ

ለምትገኙ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይህ ካለ ጦርነትና ውድመት ሃገር መምራት የማይቻል የሚመስለው ሰነፍ ስርዓተ መንግስት ለሃገር ይበጃል ብላችሁ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እስካሁን ባልገባችሁ መንግሥታዊ ሃገር የማፍረስ አላማ ተሰልፋችሁ ንፁህ ደማችሁን ውድ አካላችሁንና አይተኬ ህይወታችሁን አርክሳችሁ በማይረባ ጥቅም ተደልላችሁ ሞታችሁና ቀብራችሁ እንኳ ክብር አጥቶ እንደ ውሻ የትም ስትጣሉ ከርማችኀል እና ዛሬ ላይ ሊበቃችሁ ይገባል፡፡

ይህ የከረፋና አምባገነናዊ መንግሥታዊ ሥርዓት አሁንም ለ2018 ለቀይ ባህር እና ለአሰብ ዘምታለው በሚል መሪ ቃል ዳግሞ ማለቂያ የሌለው ጦርነት እየጎሰመ እና እየጠነሰሰ ባለው የጦርነት ድግስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ እና ዋጋ ከፋይ አሁንም እናንተ መሆናችሁን እና ለሚነሳው እሳት ለማገዶ የተዘጋጃችሁ ቤንዚን የተርከፈከፈበት ብቻ ሳይሆን የተደፋበት እንደ ደረቅ ግንዲላዎች የቀረባችሁ ከፍማችሁ ወጥ ማጣፈጫ ከሰል ሊያወጣባችሁ እና ዳር ቆሞ ሊሞቃችሁ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ስለመሆኑ ከወዲሁ ተረድታችሁ ልብ ልትሉና አይናችሁን በደንብ ገልጣችሁ ዙሪያ መለሱን በንቃት ልትመለከቱ ይገባል፡፡

ስለሆነም ኮራችን የመንግስትን የተለያዩ የፀጥታ ተቋም ለማገልገል ተሠልፈው ውድ እና አይተኬ አካል እና ነፍሳቸውን ላረከሱ ራስ ጠሎች ማለትም ለመከላከያው ለሚሊሻው ለፖሊሱ እና ለአድማ ብተናው ኀይል አዲሱን አመት 2018 በማስመልከት የንሰሃ ጊዜ አዘጋጅተን እናንተን ወንድሞቻችንን ከነሙሉ ክብራችሁ እና ሞገሳችሁ ለመቀበል የወሰንን ሲሆን ከወንድሞቻችን ጋር እርስ በእርስ የተገፋፋንበት እና የተገዳደልንበት ያ-ክፉ ጊዜ ጥቅም አልባ መሆኑን አምነን ይቅር ተባብለን በፍቅር ያለምንም የሃይል ተፅእኖ ለዚህ ስርዓት ሎሌ መሆናችሁን ወዲያ አሽቀንጥራችሁ ጥላችሁ ወደ ወንድሞቻችሁ እና ልጆቻችሁ እንድትመጡ እኛም በክብር ለመቀበል እና ምርጫችሁን አክብረን ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅታችንን ጨርሰን ይኸው ዛሬ ጥሪ አድርገናል፡፡

ስለዚህ እናንተም የእስካሁኑ ጉዞዋችሁ ትክክል እንዳልነበረ አምናችሁ እና ተፀፅታችሁ በ2017 እና ከዛ ፊት ከወጣችሁበት ህዝብ ላይ ራሳችሁን ፍፁም ጠልታችሁ ከጠላት ጎራ ተሰልፋችሁ ስትፈፅሙት የነበረው ዝርፊያን ጨምሮ አሰቃቂ ግፍና በደል ትክክል እንዳልነበር አምናችሁ እና ከልባችሁ ተፀፅታችሁ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ ጠይቃችሁ ከማህበረሰባችሁ ጋር ዳግም ተቀላቅላችሁ የምትኖሩበት እንዲሁም ፍላጎታችሁ ትግልም ከሆነ ከእኛ ጎን ተሰልፋችሁም ተማምነን በጋራ የምንታገልበት ሁኔታ ፈጥረን አስፈላጊ ነገሮችን እና ድጋፎችን እንደምናመቻች ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

በመሆኑም 2017 ዓም የመጨረሻው የእርስ በእርስ ጦርነት ዘመን እንዲሆንና ዳግም እንደ ጠላት መተያየታችንን አቁመን ለጋራ ዓላማ ለአንድ ህዝብ በአንድ ሰልፍ የምንሰለፍበት እንዲሆን እየተመኘን ጥለነው የመጣነው የአሮጌው ዓመት ክፉ እሳቤን እዛው አሽቀንጥረን በአዲስ ዓመት አዲስ እና በጎ እሳቤ በመፍጠር ያ ክፉ ጥቅም አምላኪነት እና ራስ ጠልነት እንዲሁም ቅርብ አዳሪነት መንፈስ የአሮጌው ዓመት ቆሻሻ እሳቤ እና መጥፎ ጠባሳ ሁኖ የመጨረሻ እንዲሆን በፅኑ እንመኛለን፡፡

በመጨረሻም፦ ለፀጥታ ኃይሉ
*^^^*^^^*^^^*^*^*
ጥሪያችንን አክብራችሁ እኛን አምናችሁ ይህን የከረፋ ስርዓት ጥላችሁ በየአካባቢያችሁ ወይም በቅርበት ካሉ የልጅ እያሱ ኮር ክፍለ ጦር እና ሻለቃ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ኮሮች ጋር በምስጢር በመነጋገር ስርዓቱን ተፀይፋችሁ እንደምትመጡ ባለ ሙሉ ተስፋ ነን::

ለሚመለከተው ሁሉ፦
*^^^*^^^***^*^*
ልጆቻችሁ ወንድሞቻችሁ ባሎቻችሁ አባቶቻችሁ እንዲሁም በጋብቻም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ቤተሰባዊም ዝምድና ወይም ጉርብትና እና አብሮ አደግነት ያላችሁ በሙሉ ይህንን ጥሪ ለሚመለከታቸው ሁሉ በአስቸኳይ በማድረስ አማራዊ ሃላፊነትቻሁን እንድትወጡ እና ወገኖቻችን ከመንግሥት ጋር ተሰልፈው ተቅበዝባዥ ሆነው ሜዳ ላይ ተጥለው እንዳይቀሩ ለወንድሞቻችን እንድረስላቸው እንላለን፡፡

መልካም የድል ዘመን

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር የፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መስከረም 03/2018 ዓ.ም
🙏2
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የተሳካ ድምሰሳ ድል ተቀናጀ!!

ከጉንትር አቦ እስከ ገደብየ ከተማ አስደናቂ ሰርቷል ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዛሬ መስከረም 3/2018 ዓ/ም በጠዋት ሁለት ሰዓት ወደ ወገራ ወረዳ ጉንትር አቦ ቀበሌ በወውጣት ጀግኖች ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተዘጋጀው የአገዛዙ ጥምር ሀይል በጎንደሬ በጋሻው እንደ በዓል ቄጤማ ምድር ላይ ነስንሰውታል ።

የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አመራሮችና አባላትን እንዲሁም የራስ አሞራው (3ተኛ) ኮር አሃድ ተዋጊ ጀግኖች በጥምረት በሰፊ ቀጠና የተደረገውን አውደውጊያ ጠላትን በመረፍረፍ አኩሪ ተጋድሎ ፈፅመዋል።

በአውደ ውጊያው በጎንደሬ በጋሻው በኩል ቴውድሮስ ብርጌድ ፣ አጥናፋ ብርጌድ ፣ ይታየሁ ብርጌድ እንዲሁም ከራስ አሞራው 3 ተኛ ኮር ሁለት ብርጌዶች ከአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ሀይል ጋር ከጉንትር አቦ ቀበሌ እስከ ገደብየ ከተማ ድረስ በተካሄደው እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ ጀግኖች ድል ተጎናፅፈዋል።

የብርሃኑ ጁላው ሰራዊት አስከሬኑን እያንጠባጠበ ሲሄድ በአካል የተቆጠረን ጨምሮ 31 ላይመለሱ የተ*ሸ* ኙ ሲሆን ከ4 በላይ የሚሆኑት ከቀላል እስከ ከባድ ቆስለው በአንቡላንስና በባጃጅ እያመላለሰ የዳባትና የደባርቅ ሆስፒታሎችን አጨናንቋል ።

በአጠቃላይ ውጊያው እስከ አሁን እደቀጠለ ሲሆን ጀግኖቹ አሁን ላይ ገደብየ ከተማን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል።
የብርሃኑ ጁላ ሀይል ከፍተኛ የሆነ ፖለቲካዊና ቁሳዊ ጉዳት አያስተናገደ ሲገኝ ከአምባጊዮርጊስ እስከ ደባርቅ ከተማ ድረስ ያለውም የአገዛዙ ሀይል በፍርሃት እየራደ ይገኛል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
4
የአብን አባል እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ለሁለተኛ ጊዜ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደተደረገላቸዉ ተገለፀ።

የፓርላማ አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በእስር ቤት ከባድ የሚባሉ ፈተናዎችን እያስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብታቸዉ ሳይየሳ በአገዛዙ በግፍ ከታሰሩ እስረኞች መካከል አቶ ክርስቲያን ታደለ በአገዛዙ ብልፅግና ታፍነዉ እስር ቤት ከገቡ ሁለት አመታትን አስቆጥረዋል።

ባለምጡቅ አምዕሮ ባለቤት እንደሆኑ የሚነገርላቸዉ አቶ ክርሰቲያን ታደለ በህዝብ ተመርጠዉ ፓርላማ ከገቡ ጀምሮ የአገዛዙን ገመና በማጋለጥ እና በመሞገት የሚስተካከላቸዉ ሰዉ አልተገኘም።

የህዝብን ጥያቄ ፊት ለፊት በመጠየቅ እና አገዛዙን ፊት ለፊት በመጋፈጥ እንዲሁም የአገዛዙ አገልጋይ ሚንስተሮች የሙስና ቅሌት እና ብልሹ አሰራርን ጭምር በማጋለጥ ቀን ከሌት የሚፈትኗቸዉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በእነዚህ ሰዎች አሻጥር እና ጠቅላይ ሚንስተሩ ባደረበት ፍርሀት ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደርገዋል።

በወቅቱ ለብልፅግና መንግስት ፈተና ይሆናሉ የተባሉ ፖለቲከኞች፣ጋዜጠኞች እና ማህበራዊ አንቂዎች በአገዛዙ ታፍሰዉ ሲታሰሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሀንስ ቧያሌዉ የገፈቱ ቀማሽ ተደርገዋል።

አደገኛ እስር ቤት እንደሆነ በሚነገርበት በአዋሽ አርባ እስር ቤት እንዲታሰሩ ከተደረጉ በኋላ በአገዛዙ ሰራዊት ከፍተኛን ግፍ እና መከራ አስተናግደዋል።በማረሚያ ቤቱ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ያስተናገዱት ሁለቱ የአማራ ሆዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ባሳለፍነው ወር ነበር ቀዶ ህክምና የተደረገላቸዉ።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ቀዶ ህክምና የተደረገላቸዉ ሲሆን አሁን ላይ ጤንነታቸዉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የቅርብ ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በተደረገላቸዉ ቀዶ ህክምና ከፍተኛ እንግልት የተፈፀመባቸዉ እና ቀዶ ህክምና ከተደረጉበት ሆስፒታል ብዙ እንዳይቆዩ በመደረጋቸዉ ደም እየፈሰሳቸዉ ወደ ማረሚያ ቤት ኤንዲመለሱ መደረጋቸዉ ይታወሳል።

እነዚያ የፓርላማው አስፈሪ እና ምጋች እንዲሁም ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤት የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ለአማራ ህዝብ ሲባል ፋትሐዊ ጥያቄ በማቀረባቸዉ በአገዛዙ ፀረ አማራ ኦህዴድ ብልፅግና ማፍያ ቡድን ተይዘዉ ያለ ፍትህ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።

አሁን ላይ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች በከፍተኛ ችግር ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን የተሳሩት የፖለቲካ እስረኞች እስካሁን ድረስ ፍትህ አላገኙም።

የአማራ ህዝብን  በደል እና ግፍ የተረዱ እና መንግስታዊ መዋቅር በሆነ መልኩ አማራ እንደ ህዝብ  እየጠፋ በመሆኑ ጥያቄ በማንሳተቸዉ እና ለህዝብ በማጋለጣቸዉ በእስር ቤት እንዲቀመጡ ተደርገዋል።

የፖለቲካ እስረኞች የታሰሩት የአማራ ህዝብን በደል በማጋለጣቸዉ እና ፍትህ እንዲያገኝ በመጠየቃቸዉ በመሆኑ ሁሉም ለእነዚህ የፖለቲካ እስረኞች ድምፅ ሊሆናቸዉ ይገባል!!!

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
5
በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች የረሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች እንዲሁም ጋዜጠኞች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ በአድማ ላይ የሚገኙት እስረኞች “ለሕይወታቸው እጅጉን አስጊ” በመሆኑ አጣዳፊ እርምጃ በመውሰድ ሕይወታቸውን እንታደግ” ሲል ኢሕአፓ ጥሪውን አቅርቧል።
ተቃዋሚ ፓርቲው ለኢትዮቲዩብ በላከው መግለጫ በማረሚያ ቤቱ የሚገኙት እስረኞች “በደልና ግፍ እየደረሰበት ላለው የአማራና ለቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መብት ነፃነትና ጥቅሞች ከመቆም ውጭ ይህ ነው የሚባል ወንጀል ሳይሰሩ መታሰራቸውን" ገልጿል። እስረኞቹ “ፍትሕ እንዳያገኙ” መደረጋቸውንም ፓርቲው በመግለጫው አስፍሯል።

ኢህአፓ “ወንጀል ሳይሰሩ” በእስር ላይ ይገኛሉ ካላቸው ግለሰቦች መካከል፤የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ አቶ ታዬ ደንደአ፣ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ይገኙበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፣መምህርት መስከረም አበራ፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ ዶ/ር ጫኔ ከበደ፣ መሪጌታ በላይ አዳሙ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር ፓርቲው የጠቀሳቸው ግለሰቦች ናቸው።

ከእስረኞቹ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በሕመም ላይ የቆዩ “በቂና አስፈላጊውን የሕክምና ዕርዳታ የተከለከሉ” መኖራቸውንም ተቃዋሚ ፓርቲው አስታውቋል። በአማራ ክልል እየተካሔደ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም. የአንጀት ድርቀት አጋጥሟቸው በመቅረዝ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረጋቸው አይዘነጋም።
4