ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር ዜና!

የአፋብኀ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር የደቡብ ወሎዋን ሰግለን ከተማን ከበባ ውስጥ በማድረግ በርካታ የብልፅግና ቡድን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻና አድማ ብተና በመደምሰስና በማቁሰል ድል ተጎናፀፈ።

ለወራት ከሀይቅ አቅራቢያ ሰግለን ከሚባል ተራራ መሽጎ ማህበረሰቡን ሲያንገላታ፣ሲዘርፍ፣ሴቶችን ካምፕ አድርጎ ከያዘው ተራራ አስገድዶ ሲደፍር የነበረውን የስርዐቱን ጨፍጫፊ ሰራዊት ከሞርተር ጥቃት ጀምሮ እስከ 4:00 በቆየ አውደ ውጊያ ሽርጥ ለበሽ ኮማንዶዎች በከፈቱበት መብረቃዊ ጥቃት በርካታ የአድማ ብተና ሀይልን በመደምሰስ ገሚሱን ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል።

ዛሬ መስከረም 1/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 4:00 በቆየ አውደ ውጊያ በደቡብ ወሎ ዞን ተውለደሬ ወረዳ 017 ቀበሌ ሰግለን ተራራ መሽጎ የነበረውን ሆድ አደር እና የብአደን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻን የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ በአንቡላንሶች ቁጥሩ ያልታወቀ የአድማ ብተና ሀይልን ቁስለኛ ከሰግለን ወደ ሀይቅ ከተማ ሲያጓጉዝ ውሏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መሀመድ ሞገስ አስታውቋል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መስከረም 1/2018 ዓ.ም
👍1
ማንነቱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ መንግስትና ሀገር አልባ የተደረገው አማራ እጣፈንታ በወለጋ- የአገዛዙ ጦር እና ፀራ አማራ እርምጃው

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቢደንጎሮ ወረዳ በአንድ መንደር የሚገኙ አማራዎችን ቤት የጎተራ እህልን ጨምሮ ከእነ ሙሉ ንብረቱ ፋኖን ትቀልባላችሁ በሚል ሰበብ እንዲቃጠል አድርጓል- ፀረ አማራው የዐቢይ አህመድ አገልጋይ ጦር።

ድርጊቱ አስነዋሪ እና ጠያፍ ነው። ለኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ያደረው እና በተለይም ከሁለት ዓመት በላይ ወደ ክልሉ መካናይዝድ ጦር በማዝመት እና በአየር ኃይል እየታገዘ አማራን በከባድ መሳሪያ ጭምር እየገደለ እና እያፈናቀለ ያለው "የመከላከያ ሰራዊት" እየወደቀ ላለው ስርዓት ውግንናውን አሳይቷል ፤ ፀረ አማራነቱንም እንደዚሁ።

ከዳር ድንበር ጠባቂነት ወደ ብጽግና ፓርቲ አገልጋይነት በመውረድ ማንነት እየቆጠረ አማራን በማሳደድ እና በመግደል ላይ ተጠምዷል።

ከክልሉ ውጭ ያሉ የአማራ ተወላጆችንም በፋኖ ስም እየለቀመ ያስራል ፤ ቤታቸውንም በእሳት ያጋያል።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ከወደ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቢደንጎሮ ወረዳ ከሰሞኑ የተሰማው አሳዛኝ መረጃ ነው።

ሎምጫ ቀበሌ ቢጊት በተባለ መንደር ነሃሴ 27/2017 መከላከያ በአማራዎች ላይ የፈፀመው ጥቃት በእርግጥም አሳሳቢ ነው።

ተፈጥሮአዊ ማንነት አማራነት ወንጀል ሆኖ ሕይወትን ጨምሮ ከፍ ላለ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ሲዳርግ መመልከት የተለመደ እና በተለይም የዘረኛው ኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ መገለጫ ከሆነ ከራርሟል።

የተወሰኑ የአካባቢውን ወጣት (ቄሮዎችን) ይዞ ወደ ሎምጫ ቀበሌ ቢጊት መንደር የገባው ይህ የዐቢይ አህመድ አገልጋይ ጦር "ፋኖን ትቀልባላችሁ" የሚል ሰበብ በመፍጠር በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ፈፅሟል።

ይኸውም ነሃሴ 27/2017 ብቻ 2 ገበሬዎችን አቁስሏል ፤ 13 የሚሆኑትን አስሯል ፤ 76 የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የጎተራ እህልና አልባሳቱን ጨምሮ ከእነ ሙሉ ንብረቱ በእሳት አጋይቷል።

እነዚህን ገበሬዎች በጭካኔ በማፈናቀል ሜዳ ላይ እንዲወድቁ እና ለመጠለያ እጦትና ለርሃብ እንዲጋለጡ አድርጓል።

ቤታቸውን በማቃጠል ሜዳ ላይ ከበተናቸው እና ሀገር እና መንግስት አልባ ካደረጋቸው 71 ንጹሃን አማራዎች መካከልም ፦

1) አለባቸው ካሴ፣
2) አንበሳው አባተ፣
3) ዘመኑ ተበጀ፣
4) አይናለም አንባዬ፣
5) ቄስ ይሄነው በላይ፣
6) የኔአለም አበበ እና
7) አባቢል ወንዴ የተባሉ አርሶ አደሮች ይጠቀሳሉ።

"ለአማራ ጋር ትወግናላችሁ" ፣ "አብራችሁ ማህበር ትጠጣላችሁ" እንዲሁም "ፋኖንም ትቀልባላችሁ" በሚልም የአምስት የኦሮሞ ተወላጆችን ቤት በተመሳሳይ ከእነ ጎተራ እህሉ እንዲቃጠል አድርገዋል።

ለአማራ ትወግናላችሁ በሚል ቤታቸው የተቃጠለባቸውም የኦሮሞ ተወላጆችም ፦

1) ተሾመ አበበ፣
2) ታከለ ጉታ እና ወንድሙ፣
3) አዱኛ እና
4) አቢደንጎሮ ላይ ከአማራዎች ጋር ተባብረህ የኦሮሞ ተወላጆችን ቤት አቃጥለሃል በሚል በሽብር ወንጀል ተከሶ 9 ዓመት ተፈርዶበት በዝዋይ ማ/ቤት የሚገኘው የአቶ ታከለ ኃይሉ ናቸው።

ሁለት የኦሮሞ ተወላጆችን ጨምሮ ሰባት አማራዎች ማለትም አባቡ አንለይ እና እንድሪስ አባቡ የተባሉ አባት እና ልጅን ጨምሮ 9 የሚሆኑ የአቢደንጎሮ ነዋሪዎች በሽብር ተከሰው ከ6 ዓመት በላይ ተፈርዶባቸው ወደ ዝዋይ ማ/ቤት ከተጫኑ አንድ ዓመት አልፏቸዋል።

በአገዛዙ ጦር ቤታቸው የወደመባቸውም ሆነ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የአቢደንጎሮ ነዋሪዎች ፍትህ ይፈልጋሉ ፤ አማራነት ወንጀል አይደለም!

የሚመለከታችሁ ሁሉ ስለ ሰው ልጅ ስትሉ ከንጹሃን ጎን በመቆም ኃላፊነታችሁን ተወጡ።

(አውሎግሶን አንድነት ፣ መስከረም 1/2018)
3
አሰደንጋጭ ዜና፦
ፀረ ህዝብ የሆነዉ ብልፅግና በእስቴ መካነየሱስ ከተማ አሰቃቂ ተግባር መፈፀሙ ተሰማ!!

የእስቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማንተፋርዶ ሞላ የተባለ ሆድ አደር ባንዳ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር አንድ ጉና ክፍለጦር አስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ ሁለት ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታርቆ ታመነ ቤትን በቦንብ በመምታት በቤቱ ላይ ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ተደርጓል።

በእስቴ መካነየሱስ ከተማ ቀበሌ01 የሚገኘውን መኖሪያ ቤት ከሌሊቱ 6 :00 ሰአት ቤቱ ውስጥ የሚገኙትን ሰወች እንደተኙ በስከውጭ እንዳይወጡ በመቆለፍ ቤቱን በጋዝ በማርከፍከፍ በቦንብ ጭምር ቤቱ እንዲቃጠል አድርገውታል።

6 ሰው የአርበኛ ቤተሰቦች እብረው እንዲቃጠሉ ከተፈረደባቸው የሞት ፍርድ በእሪታ አካባቢ ሰው ደርሶ አትርፏቸዋል።

በከተማዋ የሚፈፀሙ አሰቃቂ ድርጊቶች ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን የሚፈፀሙ አሰቃቂ ግፎችን በበላይነት የሚፈፅመዉ የወረደው አስተዳዳሪ አቶ ማንተፋርዶ ሞላ ነዉ።
💔42
ሰበር ዜና ምዕራብ አማራ ቀጠና!!
ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ አንድ ካሶኒ ሙሉ የአረመኔዉ አገዛዝ ሰራዊት ደመሰሰ!!

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ ንስሮቹ የአረመኔዉን አገዛዝ በማልዳዉ ረፍርፈዉታል።

የአመኔዉ አገዛዝ ሰራዊት በ 2 አቅጣጫ ወደ ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ ቢያቀናም ንስሮቹ የቀኝ አዝማች ደስታ አናብስቶች  በቲሊሊ ጅባይታ ኢባሎም እንዲሁም ከእንጅባራ የወጣዉን አረመኔዉ አገዛዝ ሻለቃ 3 በሚገባ የቀጠቀጠችዉ ሲሆን በሌላ አቅጣጫ ከሰከላ ወደ ሱርታ የተንቀሳቀሰዉን ሃይል ንስር ሻለቃ (4ተኛ ሻለቃ) ሱርታ ሚካኤል ላይ በብርጌዱ ጦር አዛዥ እና ዘመቻ ድንቅ ጥምረት ለወሬ ነጋሪ እንዳይተርፍ አድርገዉ ደቁሰዉታል ።

ንስር ሻለቃ ዙ_23 ቱን በክላሽ ያናዘዙት ሲሆን የቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ አልሞ ተኳሾች የዙ_23ቱን ተኳሽ ቀንድሸዉ ጥለዉታል።

በዚህም መሰረት:.

1/ ዙ_23ተኳሹ ተደምስሷል።
2/ አንድ ካሶኒ የአረመኔዉ አገዛዝ በቦምብ የጋዬ ሲሆን ከቦንብ የተረፈዉ አረመኔዉ አገዛዝ በአልሞ ተኳሾች ተደምስሷል።

3/ 2 ፓትሮል  ዙ_23 እና ዲሽቃ የጫኑ ፓትሮሎች በጀግኖቹ የቀኛዝማች ስሜነህ ደስታ ልጆች አውድመዋቸዋል።
4/ ዲሽቃ የጫነችዉን ፓትሮል ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ችለዋል ።
5/ 12 ክላሽ ከጠላት ተማርኳል።

አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ !
© አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏52
የአማራ ብሔራዊ ኃይል የሰሜን አማራ ቀጠናም በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ ሁለተኛ ኮር ያጠናው ዋሴ ክፍለ ጦር የሚያደርገውን ትንቅነቅ አጠናክሮ ስለመቀጠሉት ተሰምቷል።

አጠቃላይ በስፍራው ያለውን ሁኔታ በተመለከተም የአጣናው ዋሴ ክፍለ ጦር የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊም አርበኛም አርበኛ እንግዳው ዋኛው ለዓለም አቀፉ ሚዲያ ዝርዝር መረጃ አጋርቷል: በምሽት የዜና እወጃ በመረጃ ቴቪ ይጠብቁን።
👍4
ሸዋ ሜዳ ላይ በደፈጣ ተመታ።
ክንዳቸው የማይዝለው በቅፅል ስማቸው የምድር ድሮኖች የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች ከመሸ ታምር ሰርተዋል።

መነሻውን አዴት አድርጎ በአንድ ኦራልና አንድ ፓትሮል በመሆን የአረመኔው ሰራዊት እሬሽን ለማቀበል ወደ አዳማ ሲንቀሳቀስ ከአዴት እንደወጣ ከቀኑ 11:ሰዓት  ሽዋ ሜዳ ላይ በደፈጣ በተፈፀመ ጥቃት ፓትሮሉ ላይ ዲሽቃ ጠምዶ የነበረውን ተኳሸ እና አራት የአረመኔውን አገዛዝ አባላት ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት የፋሽስቱን ሰራዊት ቅንድቡን በማለት የተሰናበቱ ሲሆን ጀግኖች እቅዱን አክሽፈው መልሰውታል።

የአረመኔው ስርዓት ጦር መፍረሱን  ቀጥሏል።
በስርዓቱ ሲያገለግ የነበረው ወጣት ታፈረ አሰፋ  ተሰባስበው ይዘርፉበት ከነበረው ኬላ ላይ የጓዱን መሳሪያ ነጥቆ ጥቁር ክላሽ በመያዝ የወምበርማ ብርጌድን ተቀላቅሏል።

ወጣት ታፈረ አሰፋ አማራ ሁኜ አማራን አልዋጋም፣ የአማራ ንጹሃን እናቶች ሲደፈሩ፣ ንጹሃን አባቶች ሲታረዱ በአይኔ ሰላየሁ የአርበኛ ዘመነ ካሴን ጥሪ ተቀብዬ ፋኖን ተቀላቅያለሁ ብሏል።

በአረመኔው ስርዓት ውስጥ ሁነው ሚስጥሩ ያልገባቸው የሰላም አስከባሪ ጓዶች ወደፋኖ በመቀላቀል ዕራሳቸሁን እና ማህበረሰቡን ታደጉ ሲልም ታፈረ አሰፋ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ !!
መስከረም 2/2018 ዓ.ም
5
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ

ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ግዮን ብርጌድ ኃይል አድማሱ ሻለቃ ጠላት እሬሽን ተቀብሎ ሲመለስ ከአላይታ እስከ አምቢስ ደፈጣ በመያዝ ጠላት ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

አናብስቶቹ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ያደረሱበት ሲሆን የአረመኔዉ አገዛዝ እግሬ አዉጭኝ በማለት ፈርጥጦ ግሽ ተራራ ላይ ተሰቅሏል።

ክንዳቸው የማይዝለው በቅፅል ስማቸው የምድር ድሮኖች የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች ከመሸ ታምር ሰርተዋል።

መነሻውን አዴት አድርጎ በአንድ ኦራልና አንድ ፓትሮል በመሆን የአረመኔው ሰራዊት እሬሽን ለማቀበል ወደ አዳማ ሲንቀሳቀስ ከአዴት እንደወጣ ከቀኑ 11:ሰዓት ሽዋ ሜዳ ላይ በደፈጣ በተፈፀመ ጥቃት ፓትሮሉ ላይ ዲሽቃ ጠምዶ የነበረውን ተኳሸ እና አራት የአረመኔውን አገዛዝ አባላት  ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት የፋሽስቱን ሰራዊት ቅንድቡን በማለት የተሰናበቱ ሲሆን ጀግኖች እቅዱን አክሽፈው መልሰውታል።

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር  ህዝብ ግንኙነት።
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!

መስከረም 2/2018 ዓ.ም
👍32
እንደ እነ አቦይ ስብአት አልፎም እንደ እነ ጌታቸው ረዳ አልያም እንደ እነ አብዲኢሌ አገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል ወንጅል ሲሰራ እጅ ከፈንጅ ተይዞ ሳይሆን #አማራነቱ ወንጀል ሁኖበት በእስር እየማቀቀ የግፍ ግፍ እየተሰራበት ባጋጠመው ህመም ሁለቱ ኦፕራሲዎን ተደርጓል።

የመጀመሪያውን ኦፕራሲዎን ተደርጎ በወጉ ሳያገግም ደም እያዘነበ ከሆስፒታል ወደ ቂሊንጦ ወረወሩት ከዛም ኢንፊክሽን ተፈጠረ ሰሞኑን መልሶ ኦፕራሲዎን ተሰራ አሁንም መልሰው ወደ እስር ቤት ወረወሩት💔
አማራ መሆን ብዙ ያስደርጋል።
ፍትህ በአማራነታቸው ግፍ ለሚፈጸምባቸው የአማራ ፖለቲካ እስረኞች(ጅል የሆንኩ ያክል ተሰማኝ ፍትህ ከማን ይጠቃል?))
መፍትሄው እንደ አማራ በአንድ ቁሞ በፈርጣማው በተባበረ ክንድ ማሸነፍ ነው።
3👍2
የፋኖ አመራሮችን ለማስገደል ተልዕኮ ተሰጥቶት የነበረው የደህንነት አባል እጅ ከፈንጅ ተያዘ!

የደህንነት አባሉ የፋኖ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ጥቆማ በመስጠት በድሮን ለማስገደል እንዲሁም የፋኖ ሎጅስቲክ ማከማቻ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ቦታዎችን ለድሮን ተኳሾች ጥቆማ በመስጠት የማውደም ተልዕኮ ተሰጥቶት ነበር ተብሏል።

የደህንነት አባሉ፡ በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና አርበኛ በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጃች ኮር ስር የሚገኘው ዋዋ ጎቤ ክ/ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ሲቪል ልብስ በመልበስ በአካባቢው ሲንቀሳቀስ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው ሲሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች አስታውቀዋል።

የደህንነት አባሉ መሐመድ ዋዮ ዎቴ በሚል ስም የሚጠቀም መሆኑንና የመከላከያ ሰራዊት አባል እንደሆነ በኪሱ ከያዘው መታወቂያ ለማረጋገጥ ተችሏል።
5