ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር ጥልቅ ግምገማ በማድረግ ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለአዲስ ተጋድሎና ድል መዘጋጀታቸውን አሳወቁ::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር የኮር አመራሮች በተገኙበት ለቀናቶች ጥልቅ ግምገማ በማድረግ ክፍለጦሩ ያለውን ደካማ እና ጠንካራ ጎን በመለየት ከድክመታቸው በመማርና ጠንካራ ጎናቸውን የበለጠ በማጠናከር ለአዲስ ድል እንደተዘጋጁ አሳውቀዋል::

በበርካታ የሰው ሃይል ትልቅ የተኩስ አቅምና በቆራጥና ልምድ ባላቸው አመራሮች የተደራጀው ባለሽርጡ ክፍለጦር ሰፊ ቀጠና በመሸፈን የህልውና ተጋድሎውን በከፍተኛ ደረጃ እየታገለ ያለ ሲሆን ካሁን በፊት የነበሩ ትላልቅ ጀብድና ገድሎችን ለመድገም ብሎም ትግሉን ለድልና ነፃነት ለማብቃት በከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑን ከፍተኛ አመራሮቹ አሳውቀዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጻጉሜ 5 /2017 ዓ.ም
🙏1
ሰበር የድል ዜና!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ የልጅ እያሱ ኮር በድጋሜ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል አማራ ጠል ከሆነው የብልፅግና ስርዓት የከባድ መሣሪያ ግድያ ጠብቆ በፅናት አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት ማለትም ጳጉሜ 05/13/2017ዓ.ም በልጅ እያሱ ኮር ስር ያለችው የቤተ አማራ ክፍለ ጦር ግሽን ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ ሞርተር እና ድሽቃ በማጥመድ መህበረሰቡን መውጫ መግቢያ በማሳጣት ለንግስ እየመጡ ያሉ እንግዶችን በመደብደብ ማንገላታቱን አጠናክሮ የቀጠለውን የወራሪ ጦር ውጊያ ገጥማለች።

የቤተ ክርስቲያኑን ዙሪያ ደግሞ ብሬን ስናይፐር እና የነፍስ ወከፍ መሣሪያ በማጥመድ ሰው በፍርሃት ቆፈን እንድዋጥ አድርጎታል በዚህም ምክንያት የቤተ አማራ ክፍለ ጦር አውሬ የሆነውን የስርዓቱ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ጦር ላይ ውጊያ ለማድረግ ተገዱለች።

እንደ ፋኖ እና እንደ አንድ ጤነኛ ሰው ይህ ቦታ እንኳንስ ኢትዮጵያዊ መላ ዓለም የሚሳሳለት ቅርስ ያለበት እና መነኮሳት ቀሳውስጥ ድያቆናት የሚያገለግሉበት ቦታ በመሆኑ ፋኖ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታውን ለቆ ቢወጣም ፋኖ እግሩ እንደለቀቀ ከ ሶስት በላይ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ኃይል በማስገባት ፋኖ ከወጣ ጀምሮ ቦታውን ይዞት ይገኛል።

ስለሆነም ማህበረሰቡ በሰላም እንዳይኖር በማሳቀቅ እና የቤተ ክርስቲያን አባቶች በነፃነት ቅዳሴም ውዳሴም ማድረስ እንዳይችሉ ተደርጓል።
ይህ ፀረ ህዝብ ፀረ ኦርቶዶክስ ፀረ ሙስሊም የሆነው ስርዓት ከዚህ በላይ እምነቱንም ሲያረክሰው የአካባቢውን ማህበረሰብ እና የሚመጡ እንግዶችን ሲያንገላታ የምናይበት ትግዕስታችን ስላለቀ ተዋግተን ለማስለቀቅ ወስነናል።

በመሆኑም አባቶች ይህ ሰው በላ ስርዓት ከቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ እንድወጣ የማድረግ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ እያልን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን እኛ በጉልበታችን በመጠቀም ያለንን መሣሪያ ሁሉ ተጠቅመን ለመምታት የምንገደድ ሲሆን ለሚደርሰው ጥፋት ሁሉ ፋኖ ተጠያቂ እንደማይሆን ጭምር እያሳወቅን የጀመርነውን ውጊያ አጠናክረን እየቀጠልን መሆኑን ሁሉም ህዝብ እያየ ነው አሁንም እስከ ቀራኒዎ ውጊያችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም
🙏1
የአፋህድ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት---2018 ዓ.ም የተስፋ ዓመት ነው!!!

---ጳጉሜ 5፣ 2017 ዓ.ም

ሰሞኑን የታዘብነውን የጨረቃ ግርዶሽ በጥንታዊ አባቶቻችን ቀደም ብሎ ተተንብዮ የተቀመጠ መሆኑ፣ የዘመን አቆጣጠራችን ልንኮራባቸው ከሚገቡ ታሪካዊ ውርሶቻችን አንዱ መሆኑን በተጨባጭ አሳይቶናል ።

በዘመናት ዑደቶች ውስጥ ከምናከብራቸው በዓላት አንዱ የሆነው ዘመን መለወጫ፣ ከዘመን መለወጫው ዋዜማ ጀምሮ ዕንቁጣጣሽ ተብሎ እንደሚጠራ ኢትዮጰያዊያን አባቶቻችን አስተምረውናል። ዕንቁጣጣሽ "እንኳን መጣሽ" በምትባለው ወርሃ ጳጉሜ በዓለማዊው በባህላዊ ጭፈራዎቻችን እና በቤተ እምነቶቻችን በዜማዎች በተለየ ሁኔታ ይከበራል። ይህ ሁሉ ለሀገራችን የከበረ የባህል ውርስ እና ልዩ መለያ ጌጥ ሆኖ ኖሯል።

“መስከረም ከእነ ሥሩ ለምለም” የሚለው የማህበረሰባችን አነጋገር፣ የተዘሩ አዝርዕት ፍሬ የሚጀምሩበት ፣ውሃ የሚጠራበት ፣ብርሃን የሚገለጥበት ክረምቱ ተግ የሚልበት ጊዜ በመሆኑ፣ በአዲስ ዓመት አዲስ መንፈስ፣ አዲስ እሳቤ፣ አዲስ ውጥን፣ አዲስ ግብ፣ አዲስ ቃል ኪዳን የሚበስርበት የዓመት ዑደት መጀመሪያ ነው።

የባህረ ሀሳብ ሊቃውንቶቻችን እንደሚያስተምሩን፣ መስከረም ቀን እና ሌሊቱ እኩል የሚሆኑበት ነው። ሳይንሱም ፀሐይ በመሬት እኩሌታ የምትስተካከልበት መሆኑን አረጋግጧል። በሀገራችን  “መስከረም ሲጠባ፣ አደይ ሲፈነዳ፣    ሰው  እንኳን ዘመዱን ይጠይቃል ባዕዳ” ይባላል። በመስከረም ውሃዎች ስለሚጎድሉ፣ ሰው  ወንዞችን ተሻግሮ  "ባዕድ ዘመድ" ሳይል የሚጠያየቅበት ጊዜ በመሆኑ፣ አፋህድም አዲሱን ዓመት በዚሁ የተስፋ መንፈስ ሆኖ ይቀበለዋል።

አማራ የ2018ን የዘመን መለወጫ የሚቀበለው ያለፈውን የትግል ዓመት ችግሮች ለመሻገር የሚያስችለው አፋፍ ላይ ቆሞ እና አዲስ የአንድነት ተስፋ ሰንቆ ነው። አፋህድ ህዝባችን በአዲስ መንፈስ በጉጉት የሚጠብቀውን የአንድነት ጥያቄ የመመለስ ግዴታ እንዳለበት ጠንቅቆ የሚረዳ በመሆኑ፣ ለተግባራዊነቱ አመቻች ኮሚቴ አቋቁሞ ከወንድሞቹ ጋር ግንኙነት መጀመሩን የሚገልፀው በታላቅ ደስታ እና ኩራት ነው።

አፋህድ የአዲሱን ዓመት ኃላፊነቱን እና ግዴታውን በቃል ኪዳን ማሰሩ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በትግሉ ውስጥ በቀጥታ እየተሳተፉ ለሚገኙት የአማራ ህዝብ እና የፋኖ አባላት የሚከተሉትን ጥሪዎች እናስተላልፋለን:-

1ኛ---ጄኖሳይድ ታውጆብህ ህልውናህን በትጥቅ ትግል እያስከበርክ የምትገኘው የአማራ ህዝብ :-

የፋኖ አንድነት እውን እንዲሆን ግፊት እንድታደርግ እና ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ለመጨረስ እንዲቻል ትግሉን እንደተለመደው በሙሉ ኃይልህ መደገፉን እንድትቀጥል ጥሪ እናቀርባለን፣

2ኛ--- ጄኖሳይድ ለታወጀበት ለየአማራ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ የምትገኙ  ፋኖዎች ሁሉ፣

በዚህ ዓመት ትግላችን ትላልቅ የውስጥ እና የውጭ ድሎች የምናስመዘግብበት እንዲሆን ሁላችንም ለፋኖ አንድነት ልባችንን እንድንከፍትና እንድንታገል ጥሪ እናቀርባለን።

በተጨማሪም፣ በአምባገነኖች ጭቆና እና በመንግሥታዊ ዘረፋ ፣ በዘረኝነት እየተሰቃየ የሚገኘው ወገናችን የኢትዮጰያ ህዝብ፣ በአዲሱ ዓመት የፋኖን ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ ይደግፋል ብለን በጉጉት እየጠበቅን እንገኛለን። እየተጨፈጨፍንም ቢሆን፣ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን እና ሀገራችንን ለአፍታም ቢሆን ዘንግተን አናውቅም።

እንዲሁም፣ ሁሌም ለወገኑ እና ሀገሩ ተቆርቋሪ የሆነው ዲያስፖራ እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ያለን ግንኙነት በ2018 ዓ.ም እንደ አዲስ የሚታደስበት ዓመት እንዲሆን ቆርጠን ተነስተናል።

በመጨረሻም፣  ባለፉት 2 ዓመታት በነበረው እልህ አስጨራሽ ትግል የተሰው የታጋዮች እና የንፁሃንን ነፍስ ቸሩ ፈጣሪ በአፀደ ገነት ያኑርልን !!!

ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!

ድል ለአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
/
ጳጉሜ 5፣ 2017 ዓ.ም
1
ሰበር የድል ዜና

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ የልጅ እያሱ ኮር የቤተ አማራ ክፍለ ጦር እና የምኒልክ እዝ ልዩ ሻለቃ በመጣመር ባደረጉት ተጋድሎ የብልፅግናን ጥምር ጦር ድባቅ መትተው ድል ተጎናፀፉ::

ትናትና 05/2017 ዓ.ም የቤተ አማራ ክፍለ ጦር አንድ ሻለቃ እና የምኒልክ እዝ ልዩ ሻለቃ ጥምረት በመፍጠር በተደረገ ተጋድሎ በደሴ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል።

በዚህ የተሳካለት ዘመቻ ከደሴ በቅርብ ርቀት የሚገኙ ሀያታ ሞቴ እና ዳባ የሚባሉ የደሴ ዙሪያ ከተሞችን ከእልህ አስጨራሽ ውጊያ በሗላ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል።

የእነዚህ ከተሞች በፋኖ መያዝ ወደ ደሴ ለሚደረገው ግስጋሴ ጉልህ አሰተዋፅኦ እንደሚኖራቸው የፋኖ ከፍተኛ የጦር አማካሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ::

በዚህ ውጊያ በርካታ የጥምር ጦሩ ወታደሮች ሙት እና ቁስለኛ ሲሆኑ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ተተኳሽ እና መሣሪያ በምርኮ ተገኝተዋል። ውጊያው የፋኖ አቅም መጎልበት የታየበት እንደሆንየአካባቢው ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 1/2018 ዓ.ም
2🙏1
የድል ዜና!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 1/2018 ዓ.ም
የልጅ እያሱ ኮር ለአንድ ወር ያህል እራሱን ሲያደረጅ እና ሲመክር ከቆዬ በሗላ ከደቡብ ወሎ የአንባሰል ተራሮች እስከ ተሁለደሪ ከወረባቦ እስከ ደሴ ዙሪያ ወራሪውን ኃይል መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል::

ትላንት ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም ግሽን ላይ የመሸገውን የጠላት ጦር የቤተ አማራ ክፍለ ጦር ሻለቃዎች ሲለበልቡት ወለው ሲያድሩ በተመሳሳይ ቀን የቤተ አማራ ሌላኛዋ ሻለቃ እና የምኒልክ እዝ ልዩ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ያሉ ሶስት ትነነሽ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል::

በሌላ ዜና መስከረም 1/2018ዓ.ም በልጅ እያሱ ኮር ስር ያለችው የራስ አሊ ክፍለ ጦር አራተኛ ሻለቃ በተሁለደሪ ወረዳ ከሀይቅ ከተማ አፍንጫ ስር ቆሎባቄላ የተባለውን ምሽግ ከእልህ አስጨራሽ ውጊያ በሗላ በመቆጣጠር ለአድሱ አመት የደስታ ብስራት እንካችሁ ብላለች።

የራስ አሊ ልጆች የአባታቸው ልጆች መሆናቸውን በተግባር በተደጋጋሚ ያስመሰከሩ ቢሆንም እንደዚህ ግን እረዥም የእግር ጉዞ በመጓዝ የሀይቅ ከተማን ስጋት ውስጥ ማስገባት ከተጋድሎም በላይ ተጋድሎ ነው።

አራተኛ ሻለቃ ባደረገችው ተጋድሎ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ ስታደርግ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የክላሽ ተተኳሽ እና አስር ክላሽ በመማረክ የጠላትን ቅስም ሰብራለች። ይህች ለጠላት የማትያዝ የማትጨበጥ የሆነች ሻለቃ አሁንም ከቆሎባቄላ ወደ ኃይቅ ከተማ በመገስገስ ላይ ትገኛለች።

ኮሩም በዓሉን ወደጎን በመተው የአማራን ህዝብ ነፃ ለማውጣት በየ ዱር ገደሉ ለምትዋደቁ ፋኖዎች በሙሉ ክብር ይገባችሗል 2018 ዓ.ም የአማራ ህዝብ ነፃ የሚወጣበት አመት እንድሆን እየተመኘን ዘገባችንን እዚህ ላይ እንቋጫለን።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የልጅ እያሱ ኮር የህዝብ ግንኙነት
መስከረም 1/2018 ዓ.ም
2🙏1
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሰለሞን አሊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

ዘመን ይመጣል ዘመን ይሄዳል የሰው ልጅ በዚህ የዘመን ዑደት ውስጥ የመነሳት እና የመውደቅ ኩነቶች ሊገጥሙት ይችላል ለዚህም እንደማሳያ የሚሆነው አሁን አማራ የገጠመው መከራ አንዱ ነው ታዳ በዘመኑ የገጠመህን ውጣ ውረድ በብቃት እና በንቃት ተወጥተህ ማለፍ ከቻልክ ለሚቀጥሉት ዘመናት ተሻጋሪ የሆነ ታሪክ እና ዘመንን መሻገር የሚችል ትዉልድ መፍጠር ይቻላል።

በተቃራኒው ይህ ትውልድ ስህተት ከፈጠረ ወደማይወጣበት ቅርቃር ውስጥ ሊገባ ይችላል ስለሆነም እራሱን አሻግሮ አማራን ማሻገር የሚችል ትውልድ መፍጠር አማራጭ የሌለው አማራጭ መሆኑ ግልፅ ነው::

አማራ ሀገሩ ኢትዮጵያን ሲያስከብር የነበረ ትውልድ እንዳለው ሁሉ አሁንም የሰላም መንገዱን እንዳባቶቹ ከተጠቀመ በሗላ ይህን የሚሰማ አካል ከሌለ ደግሞ እምቢ ለሀገሬ እምቢ ለህዝቤ ካለ ማንም አልፎ ሂያጅ አይደለም ታንክ እና የአየር ኃይል ይዞ የመጣው ጣሊያንም በኋለ ቀር መሣሪያ ክንዳችንን ቀምሶ እንደተመለሰ ዓለም ያውቀዋል።

የአማራ ህዝብ አሁን የገጠመውን ችግር ትውልዱ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለው አማራ አንድ ላይ በመቆም ይህን ሰው በላ ስርዓት ግብዓተ መሬቱን ማፋጠን ይጠበቅብናል።ታዳ ይህ አሁን የያዝነው ዘመን አማራ ነፃ የሚወጣበት ዘመን እንዲሆን እየተመኘሁ በዱር በገደል እየተዋደቃችሁ ያላችሁ የአማራ ታጋዮች በሙሉ  እንኳን ለአዲሷ አመት አደረሳችሁ ማለት እወዳለሁ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሰለሞን አሊ!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መስከረም 1/2018 ዓ.ም
👍2🙏1
ሰበር ዜና!

የአፋብኀ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር የደቡብ ወሎዋን ሰግለን ከተማን ከበባ ውስጥ በማድረግ በርካታ የብልፅግና ቡድን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻና አድማ ብተና በመደምሰስና በማቁሰል ድል ተጎናፀፈ።

ለወራት ከሀይቅ አቅራቢያ ሰግለን ከሚባል ተራራ መሽጎ ማህበረሰቡን ሲያንገላታ፣ሲዘርፍ፣ሴቶችን ካምፕ አድርጎ ከያዘው ተራራ አስገድዶ ሲደፍር የነበረውን የስርዐቱን ጨፍጫፊ ሰራዊት ከሞርተር ጥቃት ጀምሮ እስከ 4:00 በቆየ አውደ ውጊያ ሽርጥ ለበሽ ኮማንዶዎች በከፈቱበት መብረቃዊ ጥቃት በርካታ የአድማ ብተና ሀይልን በመደምሰስ ገሚሱን ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል።

ዛሬ መስከረም 1/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 4:00 በቆየ አውደ ውጊያ በደቡብ ወሎ ዞን ተውለደሬ ወረዳ 017 ቀበሌ ሰግለን ተራራ መሽጎ የነበረውን ሆድ አደር እና የብአደን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻን የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ በአንቡላንሶች ቁጥሩ ያልታወቀ የአድማ ብተና ሀይልን ቁስለኛ ከሰግለን ወደ ሀይቅ ከተማ ሲያጓጉዝ ውሏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መሀመድ ሞገስ አስታውቋል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መስከረም 1/2018 ዓ.ም
👍1