አንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹህ።
ለመላው የፋኖ ሰራዊታችን፣ለትግሉ ደጋፊዎች፣ለተፈናቃይ ወገኖቻችን እንዲሁም በአገዛዙ ብልፅግና ግፍን ያስተነናገዳቹህ ወገኖቻችን አንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹህ።
አዲሱ አመት የድል ዘመን ይሁንልን!!!
መልካም አዲስ አመት!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ!!!

❤2
የአፋብኃ ሰሜን ቀጠና በለይ እዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክፍለ ጦር 2018 ዓ.ም ዘመን መለውጫ አከባበር
🙏1

የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ እንኳን ለ2018 ዓ.ም በድልና በፅናት አደረሳችሁ አደረሰን በማለት መልካም ምኞቱን ገልጿል።
የአዲሱን አመት አቅጣጫ በጠቆመበት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ከታች ተጨማሪ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

የሻለቃ ዝናቡ የአዲስ ዓመት መልእክት
ለአይበገሬው የአማራ ሕዝብ፤ ሀሩርና ቁሩ፣ ጋራና ሸንተረሩ፣ ገደሉና ዱሩ ሳይበግርህ ለህዝብና ለሀገርህ እየተፋለምህ ያለኸው በየትኛውም ቀጠና ለምትገኙ ጀግናው የፋኖ ሰራዊት እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
፤
የተከበርከው የአማራ ህዝብና የትግላችን ደጋፊዎች፤ የተከበራችሁ የፋኖ ሰራዊታችንና አመራሩ በሙሉ ይሄንን አዲስ ዓመት የምናከብረው ሳይሆን የምንቀበለው ከተለመደው የአዲስ ዓመት ዝግጅት በተለየ ሁኔታ አይደለም። ህዝባችንና ተፈጥሮ ያደለን ለሙ መሬታችን ተፈጥሮ የፈጠረውን የክረምቱ ጎርፍና የተናደውን መሬት በሚያስንቅ ሁኔታ በጠላት ከባድ መሳሪያ ድብደባ ሲናፁ በመክረማቸው፤ በውሃ ሙላት ከተጠራረገው አሸዋና ደንጋይ ይልቅ ቀዬና አድባሩ ሁሉ በጠላት የጭካኔ በትር የደም ቦይ ሲፈስበት በመክረሙ፤ የለመለሙ እፅዋትና በአደይ አበባ የፈኩ ተራራዎች ሁሉ ከምንጊዜውም የተለየ ድምቀት የላቸውም። ለማደግ ያልታደሉ ጨቅላ ህፃናት፤ ሩጠው ያልጠገቡና በደንብ ያልሳቁ ታዳጊ ወጣቶች፣ ጦርነት ደስታቸውን የነጠቃቸው እናትና አባቶች በአገዛዙ አረሜናዊ ተግባር በተፈፀመ ከክላሽንኮቭ እስከ ድሮን በተደረገ ድብደባ ነጋቸውን ተነጥቀዋል። የተደረገብንን ሁሉ ለአፍታ አንረሳም። አንዘነጋምም!
፤
የተከበርኸው ህዝባችን የኛ ደስታ የእናንተ ደስታ ነው። በተለመደው የበዓል አከባበር በፍፁም ደስታ ባታከብሩ እንኳን በሰላም እንድታሳልፉት የናንተን ሰላም መዋል በእጅጉ እንሻለን።
እኛ ልጆቻችሁ በዲም ላይት ሳይሆን በጥይት ብልጭታ፣ በሞንታርቦ ባንዘፍን እንኳን በከባድ መሳሪያ ድምፅ ታጅበን፣ በስጋ እና በጠጅ ባይሆንም በምትሰጡን ድንች እና ድርቆሽ ተማምነን፤ ነጭ ባንለብስም “ጥቁር ከለበሰች፣ ማቅ ካሰረች እናት” እና “ገመድ በወገቡ አዙሮ፣ በምርኩዝ ከቤት ደጅ ላይ ለመውጣት ከተቸገረ አባት” ጋር ሁነን ፤ ጦርነቱ “ባህሉንና ገፁን፣ አለባበስና አመጋገቡን” ከለወጠው ወገናችን፤ ድሮንና መድፍ ካፈራረሰው መጠለያ ቤታችን፤ ተዘጋጅተንበት ባይሆንም፣ ተዘጋጅቶ ለሚመጣው አዲስ ዓመት ለማክበር ተገደናል።
፤
መላው ሰራዊታችን “ህዝባችን የሁሉም ነገር መሰረታችን” መሆኑን መናገር ብቻ ሳይሆን በፅኑ እናምንበታለን።ስለሆነም ሰራዊታችን በዓሉን በምናሳልፍበት በየትኛውም ቀጠና ልጇን በጦርነቱ ካጣች ደካማ እናት፣ ቤታቸው ከፈረሰባቸው አዛውንቶች፣ ወላጆቻቸውን ካጡ ህፃናት፣ ተፈናቅለው መጠለያ አጥተው ሜዳ ከሚያድሩ ወገኖቻችን፣ ቆስለው በህክምና ከሚገኙ የሰራዊታችን አባላትና እንዲሁም አካላቸውን አጥተው ክራንች ከጨበጡ አርበኞቻችን ጋር ያላችሁን በማካፈል፤ ምንም ባይኖረንም እንኳን ከጎናቸው መሆናችንንና ችግሮቻቸውን የምንጋራ ልጆቻቸው መሆናችንን በማሳየት፤ በእነሱ ደስታ ተደስታችሁ መዋልን ምርጫ እንድታደርጉ አደራ ማለት እወዳለሁ።
ባዕሉን ለምታከብሩ ኢትዮጵያዊያን መልካም አድስ አመት እመኛለሁ!!
©የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ ዝናቡ ልንገረው ደለለ

❤1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር ጥልቅ ግምገማ በማድረግ ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለአዲስ ተጋድሎና ድል መዘጋጀታቸውን አሳወቁ::
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር የኮር አመራሮች በተገኙበት ለቀናቶች ጥልቅ ግምገማ በማድረግ ክፍለጦሩ ያለውን ደካማ እና ጠንካራ ጎን በመለየት ከድክመታቸው በመማርና ጠንካራ ጎናቸውን የበለጠ በማጠናከር ለአዲስ ድል እንደተዘጋጁ አሳውቀዋል::
በበርካታ የሰው ሃይል ትልቅ የተኩስ አቅምና በቆራጥና ልምድ ባላቸው አመራሮች የተደራጀው ባለሽርጡ ክፍለጦር ሰፊ ቀጠና በመሸፈን የህልውና ተጋድሎውን በከፍተኛ ደረጃ እየታገለ ያለ ሲሆን ካሁን በፊት የነበሩ ትላልቅ ጀብድና ገድሎችን ለመድገም ብሎም ትግሉን ለድልና ነፃነት ለማብቃት በከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑን ከፍተኛ አመራሮቹ አሳውቀዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጻጉሜ 5 /2017 ዓ.ም