ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በቁይ ከተማ በዘመቻ ሰማዕታት ኦፕሬሸን የፋኖን በትር መቆቋም ያቃተው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት እየፈራረሰ ነው።

1ኛ.ናይፍ ጅማ የተባለ ኦሮምያ ክልል የሻሸመኔ ተወላጅ የአረመኔው አገዛዝ የመከላከያ ሰራዊት አባል ከምስራቅ ዕዝ 75ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጂመንት 1ኛ ሻምበል ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም የአ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮሰ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ደባይ ጮቄ ብርጌድን ተቀላቅሏል።

2ኛ. ወንዳወክ ይሁን ሸበል በረንታ ሌዲ ቡይቴ ቀበሌ  እና ማናየ መኩየ ሸበል በረንታ እያሱ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆኑ ከቢቸና ከተማ እና የዕዱውኃ ከተማ መሽጎ ከሚገኜው የሚኒሻ መዋቅር በመክዳት ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ተቀላቅሏል።

በሌላ መረጃ ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም በሸበል በረንታ የዕዱውሃ ከተማ የመሸገው የአብይ አህመድ ዙፍን ጠባቂ ሚኒሻ እርስ በርሱ እየተጋደለ ነው። ሰማይነህ ጌታቸው የተባለ የአገዛዙ ቅጥርኛ የሚኒሻ አባል በእርስ በርስ ተኩስ የተገደለ መሆኑን ተረጋግጦል።

ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም

      ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
  የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
🙏5
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  የአዲስ አመት ዋዜማን  ዘራፊዎችን እና  የብልፅግናን ጥምር ሀይል በማስወገድ አዲስ አመትን በድል ተቀበለ  ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ 5 ኮር   ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  ከአምባጊዮርጊስ እስከ ዳባት ከተማ ድረስ ህብረተሰቡን ሲዘርፋና ሲያግቱ በነበሩ ወሮበሎች ርምጃውን አጠናክሮ ቀጥሏል።ከራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ጋር በመጣመር እየተወሰደ ባለው ስርዓት የማስያዝ ዘመቻ ቀጠናው ከወዲሁ እፎይታ እ ያገኘ ሲሆን ይሄን ተግባር ለማደናቀፍ ዓላማ በማድረግ አገዛዙ ሰራዊት አሰማርቶ ለዘራፊዎች ሽፋን ለመስጠት የሞከረ ቢሆንም የበላይ ዘለቀ ዕዝ አሃዶች ከባድ ምት ደርሶበታል።
ዛሬ ጳጉሜ 5/2017 ዓ/ም ከወርቅ ደቦ እስከ ገደብየ ከተማ ለዘራፊዎች ሽፋን ሊሰጥ የመጣው የዘራፊው አገዛዝ ጥምር   ሀይል በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል በሆኑት  ቴዎድሮስ እና አጥናፋ ብርጌድ  አባላት እና መንገድ በመዝጋት የአገዛዙ ሀይል  ለድጋፍ እንዳይደርስ  ያደረገችውን ይታየው  ብርጌድ አባላትን ጨምሮ  በማስተባበር  ጀኔራል ተዘራ ንጉሴ  እና የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ማርዬ አድማሴ እንዲሁም የብርጌድ አመራሮች በአካል በመሩት ኦፕሬሽን ጠላት ላይ ከፍተኛ ድምሰሳ  ተደርጓል ።
  በቀጠናው ዛሬ የአገዛዙ ሀይል  እንደ ልማዱ በውርደትና በሽንፈት ካባ የተመለሰ ሲሆን አዲስ አመትን በሞትና በመርዶ ተቀብሏል።
ከወርቅ ደሞ እስከ ገደብየ ከተሞች በነበረው  አውደ ውጊያ የአህያ ባል  ከጅብ አያስጥልም ነውና ዘራፊዎችን   ለማዳንና ለሽፋን   ፎክሮ የመጣው   የአገዛዙ ሀይል ይዟቸው የነበሩ  ሁለት  ምሽጎችን ለቆ ሙትና ቁስለኛውን እያንጠባጠበ   እየፈረጠጠ ወደ  አምባጊወርጊስ ከተማ በሀዘንና በእለቅሶ ተመልሷል ።

ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ከመንግስት ጎን የሚሰለፋ ሀይሎችንና ሌቦችን ማጽዳቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በቀጠናው ያሉ  ህብረተሰቡን ቀለበት ፣ ስልክ ፣ብር እና  የተለያዩ ሀብቶችን እንዲሁም እገታ  ጭምር ሲፈፅሙ  የነበሩ ቀማኞች እና አጭበርባሪዎች  በአጭር ጊዜ ውስጥ  ሙሉ ለሙሉ ተወግደው  ቀጠናው ፍፁም ሰላማዊ ይደረጋል ሲሉ የክፍለ ጦሩ ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ወርቁ ዘገየ  አክለው  ገልፀዋል።

           ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን  !!!
           ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
5🙏2
📌ከህሊና እስረኞች የተላከ መልዕክት!

የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ይህንን ማስታወሻ የሰደድንልህ እንደ አባቶቻችን ወግና ልማድ እንኳን አደረሰህ ልንልህ አይደለም። አዲሱ ዓመት እንደ ባለፉት አመታት አገራችን በማያበራ ጦርነት ውስጥ ተነክራ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የማይቻልበት ልጅ ወልዶ ማሳደግ፣ ዘርቶ መቃም ፈፅሞ የማይቻልበት ሆናለች።

ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ከጎረቤት አገራት ተነጥላ እና ተንቃ የቅልውጥ ፖለቲካ በማካሄድ መንግስት የምትመራ ሆናለች።

ሕዝባችን እጅግ አሰቃቂ በሆነ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዬ የአንድ የዩኒቨርስቲ መምህር ደመወዝ አንድ ዳውላ ጤፍ የማይሸምትባት የጉድ አገር ሆናለች። ቤቴ ንብረቴ፣ ካርታዬ ይዞታዬ የማይባልባት በኮሪደር ልማት ስም ከህግ ውጭ በቀላጤ ትዕዛዝ ሙሉ መንደሮች በዶዘር ተጠርገው የሚነሱባት አገር ተደርጋለች።

ከቦታ ቦታ ተንቀሳቀሳቅሶ መስራት የማይቻልባት የንግድ ስራ እንደ ወንጀል የሚቆጠርባት ስልጣን የያዘው ቡድን ገንዘብ እያተመ የሕዝቡን ጥሪት የሚዘርፍባት፣ የውጭ ኃይሎች በቀጥታ እጃቸውን አስገብተው አድራጊ ጀጣሪ፣ ሿሚ ሻሪ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል። በሌላ በኩል " እነ" ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ በሚሊዮን ሚቆጠር ገንዘብ ለአንድ ምሳ የሚከፈልበት፣  እንደ ለሆሊውድ ተዋንያንያን ቅንጡ ሕይዎት የሚመሩበት፣ ሰውነታቸውን በፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና የሚያስውቡበት ነው። አዲሱ ዘመን።

ውዱ የአማራ ሕዝብ ሆይ:- ልጆቻችን የመማር የማደግ መብታቸውን መንግስት ነኝ በሚል አካል የተነጠቁበት፣ በሕዝብ ግብር የሚተዳደሩት የሕዝብ ተቋማት ገንዘብ ላለው ብቻ ትምህርትን ለመሸቀጥ የተስፋፉበት ነው አዲስ ዓመት።

አሁንም 4.9 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝባችን ተፈናቅሎ በካምፕ ውስጥ ይኖራል። አሁንም የዘር ፍጅት የተፈፀመበት የወገናችን ደም የፍትህ ያለህ እያለ እያለ ከመቃብር በላይ ይጣራል።

ዛሬም በአገራችን ተስፋ የቆረጡ ወጣቶቻችን በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩት ድንበር አቋርጠው በመሰደድ ላይ ናቸው። አንዳንዶቹ የበርሀ ሲሳይ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ የባህር አሳ እራት ሆነዋል።

የሕግ በላይነት የሚባለው መርህ ሙሉ በሙሉ ወድቆ  ፣ አቃቢ ሕግ፣ ፖሊስ፣ ማረሚያ ቤት፣ የአንድ ድርጅት አባላት እና የአንድ ብሔር ሰዎች በመሆናቸው በእየለቱ ሰዎችን ያፍናሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ያፍናእንገልፃለን፣ ይሰውራሉ።ሕግን እንደ ማጥቂያ መሳሪያ በመጠቀም ንፁሀንን በማጎሪያ አስረው ያሰቃያሉ።

የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዘመናት ያልተቋረጠ፣ የመንግስት ታሪክ ካላቸው ጥቂት ሕዝቦች መካከል አንዱ የሆነ፣ በተፃፈ ህግ ሲተዳደር የኖረ፣ የራሱ ፊደል እና የዳበረ የስነ ፅሁፍ ታሪክ ያለው እና የራሱን ታሪክ በራሱ ፊደል እና ቋንቋ ፅፎ ያኖረ ሕዝብ ነው።

የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዘመናት ነፃነቱን በደም እና በአጥንት ያስከበረ፣ ለዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምሳሌ የሆነ፣ መዓዛው እንደ መልካም ሽቶ፣ ዓለምን ያወደ፣ የገናና ስም ባለቤት ነው። እንድሁም የአማራ ሕዝብ ፈሪሐ እግዚአብሄር ያለው፣ የመልካም አኗኗር መርሆችን፣ ገንዘቡ ያደረገ፣ ለጠላት ሳይቀር የሚራራ ሕዝብ ነው።

የአማራ ሕዝብ በርእስቱ የማይደራደር፣ ንብረቱን የማያስነካ፣ የሌላውንም የማይነካ ነው። ራሱን በመቻል እንዲሁም ለሌሎች በመትረፍ መርህ የሚመራ ነው። ከሁሉ በላይ የአማራ ህዝብ ለህግ የበላይነት መከበር ቁርጠኝነት ያለው፣ መንግስትን አክብሮ የሚያስከብር ሲሆን፣ ሕግ የማያውቁት ጨካካኝና ዘራፊ ስልጣን ሲይዝ ደግሞ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ዱር ቤቴ የሚልም ነው።

እንደ ሕዝብ የአማራ ሕዝብ ጠላታችን ነው እናጥፋው ያሉ ጠላቶቻችን ተባብረው ተሰልፈዋል። የፖለቲካ ስልጣን ተቆጣጠረው ሕገ ከመንግስት ጀምሮ ፀረ አማራ ሕጎችን ፣ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን በስራ ላይ አውለዋል።

ለዓመታት የዘለቀ የጥላቻ ዘመቻ በአማራ ሕዝብ ላይ አካሂደዋል፣ በዚህም በአማራ ጥላቻ ተኮትኩቶ ያደገ ትውልድ አፍርተዋል።

ከዚህ ዘመቻ በኋላ የአማራን ሕዝብ ንብረት መዝረፍ እና ማውደም። እስር እና ስቃይ ቀጥሎ  የአማራ ሕዝብ በሚሊዮኖች ተፈናቅሏል። የዘር ፍጅት ተፈፅሞበታል። አሁንም በኮሪደር ልማት ስም ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች ሃምሳ አምስት ከተሞች የማፈናቀሉ ስራ ቀን ከሌት እየተሰራ ነው።

የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች የሆኑት እነዚህ ሐይሎች የአማራን ሕዝብ ለማጥቃት ቀን ከሌት በመትጋት ይሰራሉ።
የኢትዮጵያን ሕዝብ  ድልብ ሀብት ጠቅልለን፣ የአማራን ሕዝብ በማፈናቀል ፣ ጠራርጎ በማስወጣት እና በመፍጀት የራሳችንን አዲስ አገር እንመሰርታለን ላሉ ተስፈኞች ቦታ ቦታ ለመልቀቅ ሲባል የአማራን ህዝብ ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ በሆነ ሁኔታ እንዲፈጅ ተፈርዶበታል።

መላው የአማራ ሕዝብ ታጋዮች ለትግሉ በፅናት እና በታማኝነት በመቆማችሁ በዚህ ዘመን ሊደረግ ይችላል ተብሎ በማይታሰብ ደረጃ የማንነት ድምሰሳ እና የዘር ፍጅት እየተፈፀመበት፣ ላለው ሕዝባችን የሕይዎት መስዋትነት በመክፈላችሁ እንድሁም የአንድነት ብስራት እያሰማችሁን በመሆኑ በርቱ ቀጥሉ እንላለን።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ የዘር ፍጅት ለማስቆም የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአፅዕኖት እንጠይቃለን።

እኛ በቂሊንጦ እስር ቤት የምንገኝ  ብዙሃን የአማራ የፖለቲካ እስረኞች በብዙ ስቃይና መከራ ውስጥ እንገኛለን። በተለይ ኮሽ ባለ እና አገዛዙ በደነገጠ ቁጥር ከሰብዓዊነት ውጭ በሆነ ደረጃ ተደራራቢ የሆነ ግፍና በደል ይደርስብናል። የአገዛዙ የቁጣው ሁሉ ማረፊያ እኛ እስር ቤት ውስጥ ያለነውን እስረኞች ቢያደርግም ከተነሳንበት ዓላማ አንፃር የሚደርስብን ሁሉ በፀጋ እንቀበላለን።

በዚህ የሕዝባችን መከራና ስቃይ ባላባራበት እንደውም ተጠናክሮ የቀጠለበትን 2018 ዓ/ም የአዲስ ዓመት መባቻ " ገና ያልጠባው አዲስ ዓመት" ብለን ሰይመነዋል።

ይህን የአዲስ ዓመት ጨለማ እለትም በመከራ እና በስቃይ ውስጥ ያለውን ሕዝባችንን በማሰብ፣ በእኛ ላይ ያለውን ተደጋጋሚ ኢሰብዓዊ ጥቃት በመቃወም እና በአገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ጥቃት ለመቃዎም ስንል  የርሀብ አድማ አድርገን ለማሳለፍ መወሰናችንን ለሕዝባችን እንገልፃለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
ቂሊንጦ ከሚገኙ እስረኞች የተለከ
🙏41
አንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹህ።

ለመላው የፋኖ ሰራዊታችን፣ለትግሉ ደጋፊዎች፣ለተፈናቃይ ወገኖቻችን እንዲሁም በአገዛዙ ብልፅግና ግፍን ያስተነናገዳቹህ ወገኖቻችን አንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹህ።

አዲሱ አመት የድል ዘመን ይሁንልን!!!
መልካም አዲስ አመት!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ!!!
2
የአፋብኃ ሰሜን ቀጠና በለይ እዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክፍለ ጦር 2018 ዓ.ም ዘመን መለውጫ አከባበር
🙏1
የአፋብኃ ሰሜን ቀጠና በለይ እዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክፍለ ጦር 2018 ዓ.ም ዘመን መለውጫ አከባበር
አንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹህ።

ለመላው የፋኖ ሰራዊታችን፣ለትግሉ ደጋፊዎች፣ለተፈናቃይ ወገኖቻችን እንዲሁም በአገዛዙ ብልፅግና ግፍን ያስተነናገዳቹህ ወገኖቻችን አንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹህ።

አዲሱ አመት የድል ዘመን ይሁንልን!!!
መልካም አዲስ አመት!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ!!!
🙏1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ!!!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏👆🙏
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ እንኳን ለ2018 ዓ.ም በድልና በፅናት አደረሳችሁ አደረሰን በማለት መልካም ምኞቱን ገልጿል።

የአዲሱን አመት አቅጣጫ በጠቆመበት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ከታች ተጨማሪ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
የሻለቃ ዝናቡ የአዲስ ዓመት መልእክት

ለአይበገሬው የአማራ ሕዝብ፤ ሀሩርና ቁሩ፣ ጋራና ሸንተረሩ፣ ገደሉና ዱሩ ሳይበግርህ ለህዝብና ለሀገርህ እየተፋለምህ ያለኸው በየትኛውም ቀጠና ለምትገኙ ጀግናው የፋኖ ሰራዊት እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የተከበርከው የአማራ ህዝብና የትግላችን ደጋፊዎች፤ የተከበራችሁ የፋኖ ሰራዊታችንና አመራሩ በሙሉ ይሄንን አዲስ ዓመት የምናከብረው ሳይሆን የምንቀበለው ከተለመደው የአዲስ ዓመት ዝግጅት በተለየ ሁኔታ አይደለም። ህዝባችንና ተፈጥሮ ያደለን ለሙ መሬታችን ተፈጥሮ የፈጠረውን የክረምቱ ጎርፍና የተናደውን መሬት በሚያስንቅ ሁኔታ በጠላት ከባድ መሳሪያ ድብደባ ሲናፁ በመክረማቸው፤ በውሃ ሙላት ከተጠራረገው አሸዋና ደንጋይ ይልቅ ቀዬና አድባሩ ሁሉ በጠላት የጭካኔ በትር የደም ቦይ ሲፈስበት በመክረሙ፤ የለመለሙ እፅዋትና በአደይ አበባ የፈኩ ተራራዎች ሁሉ ከምንጊዜውም የተለየ ድምቀት የላቸውም። ለማደግ ያልታደሉ ጨቅላ ህፃናት፤ ሩጠው ያልጠገቡና በደንብ ያልሳቁ ታዳጊ ወጣቶች፣ ጦርነት ደስታቸውን የነጠቃቸው እናትና አባቶች በአገዛዙ አረሜናዊ ተግባር በተፈፀመ ከክላሽንኮቭ እስከ ድሮን በተደረገ ድብደባ ነጋቸውን ተነጥቀዋል። የተደረገብንን ሁሉ ለአፍታ አንረሳም። አንዘነጋምም!

የተከበርኸው ህዝባችን የኛ ደስታ የእናንተ ደስታ ነው። በተለመደው የበዓል አከባበር በፍፁም ደስታ ባታከብሩ እንኳን በሰላም እንድታሳልፉት የናንተን ሰላም መዋል በእጅጉ እንሻለን።
እኛ ልጆቻችሁ በዲም ላይት ሳይሆን በጥይት ብልጭታ፣ በሞንታርቦ ባንዘፍን እንኳን በከባድ መሳሪያ ድምፅ ታጅበን፣ በስጋ እና በጠጅ ባይሆንም በምትሰጡን ድንች እና ድርቆሽ ተማምነን፤ ነጭ ባንለብስም “ጥቁር ከለበሰች፣ ማቅ ካሰረች እናት” እና “ገመድ በወገቡ አዙሮ፣ በምርኩዝ ከቤት ደጅ ላይ ለመውጣት ከተቸገረ አባት” ጋር ሁነን ፤ ጦርነቱ “ባህሉንና ገፁን፣ አለባበስና አመጋገቡን” ከለወጠው ወገናችን፤ ድሮንና መድፍ ካፈራረሰው መጠለያ ቤታችን፤ ተዘጋጅተንበት ባይሆንም፣ ተዘጋጅቶ ለሚመጣው አዲስ ዓመት ለማክበር ተገደናል።

መላው ሰራዊታችን “ህዝባችን የሁሉም ነገር መሰረታችን” መሆኑን መናገር ብቻ ሳይሆን በፅኑ እናምንበታለን።ስለሆነም ሰራዊታችን በዓሉን በምናሳልፍበት በየትኛውም ቀጠና ልጇን በጦርነቱ ካጣች ደካማ እናት፣ ቤታቸው ከፈረሰባቸው አዛውንቶች፣ ወላጆቻቸውን ካጡ ህፃናት፣ ተፈናቅለው መጠለያ አጥተው ሜዳ ከሚያድሩ ወገኖቻችን፣ ቆስለው በህክምና ከሚገኙ የሰራዊታችን አባላትና እንዲሁም አካላቸውን አጥተው ክራንች ከጨበጡ አርበኞቻችን ጋር ያላችሁን በማካፈል፤ ምንም ባይኖረንም እንኳን ከጎናቸው መሆናችንንና ችግሮቻቸውን የምንጋራ ልጆቻቸው መሆናችንን በማሳየት፤ በእነሱ ደስታ ተደስታችሁ መዋልን ምርጫ እንድታደርጉ አደራ ማለት እወዳለሁ።

ባዕሉን ለምታከብሩ ኢትዮጵያዊያን መልካም አድስ አመት እመኛለሁ!! 

©የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ ዝናቡ ልንገረው ደለለ
1