ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ለ3ተኛ ዙር ኮማንዶዎችን አስመርቋል ።

ለተከታታይ 6 ወራት በቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ በተመረጡ እና ብቃት ባለቸዉ አሰልጣኞች ስልጠና ሲሰጣቸዉ የቆዩ የ3ተኛ ዙር ኮማንዶዎቸ በዛሬዉ ዕለት በቀን 04/13/17 ዓ/ም ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የክ/ጦር አመራሮች እንዲሁም የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።

በፕሮግራሙ ላይ የቴዎድሮስ ዕዝ የስልጠና መምሪያ ሃላፊ ኮማንዶ ታዬ ብርሃኑ

የቴዎድሮስ ዕዝ ም/ጦር አዛዥ ሻለቃ የኔአለም ዘለቀ

የቴዎድሮስ ዕዝ ም/አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አርበኛ ስለሽ ከበደ

የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ ኮማንዶ ዴቭ እንዲሁም የክ/ጦሩ ፓለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

መመልመል፣ መቀስቀስ፣ ማደራጀት፣ ማሰልጠን፣ማስታጠቅ፣ማቀድ፣ጠላትን ድባቅ መመምታት ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
🙏51🥰1👏1
‎የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክ/ጦር ተስፋ ብርጌድ የኮማንዶ አባላት የአቅመ ደካሞችን እህል አረም በማረም ድጋፍ አደረጉ
‎================
‎የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክ/ጦር የተስፋ ብርጌድ 1ኛ ሺ አለቃ የኮማንዶ አባላት የአቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን አረም በማረም ለህዝብ ያለውን ወገንተኝነት በገሀድ አሳይቷል::
‎የተስፋ ብርጌድ 1ኛ ሺ አለቃ የኮማንዶ አባላት ይህንን መልካም ተግባር የፈጸሙት ራሳቸውን ከማደራጀት ጎን ለጎን ነው::
‎እነዚህ የኮማንዶ አባላት የአቅመ ደካሞችን አረም በማረም እገዛ ያደረጉት በምንጃር ወረዳ 010 ቀበሌ ወሲል በተባለ ልዩ ቦታ ነው::
‎ይህ የተስፋ ብርጌድ አቅመ ደካሞችን የማገዝ ተግባር በሁሉም የብርጌድ አባላቶች በቀጣይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ከደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ እዝ ከሰም ክ/ጦር ዘጋቢያችን የተገኘው መረጃ ያመለክታል::
በሌላ መረጃ "እንመክራለን እንወያያለን እንደራጃለን "በሚል መሪ ቃል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል( አፋብኃ) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ በሆማ ቦነያ ቀበሌ ከሰሞኑ ሕዝባዊ ውይይቶች አድርጓል።
ውይይቱን የአፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ መ/ር በላቸው ዳኘ የመራው ሲሆን ስለ አገዛዙ እና ተልዕኮ ተቀብለው ሰርገው የሚገቡ ኃይሎችን በንቃት ተከታትሎ መያዝ እና በቀጠናው ለሚንቀሳቀሱ ፋኖ አባለት ሪፖርት ማድረግ እናዳለበቸ በአፅንኦት መልክቱን አስተላልፏል።
አየይዞም የሕዝባዊ አስተዳደር ጉዳይን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል።
መረጃውን ያደረሱን የየክፍለጦሮቹ ሪፖርተሮች ናቸው።
‎ " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
‎ ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም
👏2🙏2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ዳ/ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር
ወንድማማቾች ብርጌድ በጠላት ኃይል ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፀመ።
ዛሬ ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር አብራክ የሆነው ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ወንድማማቾች ብርጌድ ከአዘዞ ወደ ቆላደባ ከተማ የእጀባ ተግባርን ፈጽመው ሲመለሱ በነበሩ የሚሊሻ አባላት ላይ ግራርጌ በተባለው ቦታ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽመዋል።
ዉጊያው ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን ከ6 በላይ የሚሊሻ አባላት ሲደመሰሱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የሚሊሻ አባላት ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል።
በመጨረሻም የጠላት ኃይል ከአዘዞና ከቆላደባ በ2 አቅጣጫ ሃይሉን በማንቀሳቀስ አስከሬኑንና ቁስለኛውን ሰብስቦ በተሽከርካሪ በመጫን ወደመጡበት ተመልሰዋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ
ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
👍2🙏1
"ጠላት በወምበርማ ብርጌድ ተደብድቧል " የወምበርማ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴውድሮስ ዕዝ ፭ኛ ክፍለ ጦር የወምበርማ ብርጌድ ከጥዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት የአረመኔው ስርዓት ወንበር ጠባቂዎችን ልዩ ስሙ ኮኪ መገንጠያ ላይ ሲያደባዩት ውለዋል።

አይበገሬዎቹ የወምበርማ ብርጌድ ንስር ሻለቃ፣ ቆምጠው ሻለቃ እና ነበልባል ሻለቃ በጋራ በመሆን ወደ ወገዳድ እንቅስቃሴ ያደረገውን የአረመኔውን ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ስድስት ወንበር ጠባቂዎች ወደ ላይኛዉ ሲሸኙ አንዱ በከባድ ቁሰለኛ በማድረግ ጠላትን ቀጥተውታል።

ዘራፊው እና ጨፍጫፊው በሽንዲ ከተማ መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ቡድን በዓሉን ማህበረሰቡ በሰላም እንዳያከብር ለማወክ ወደ ወገዳድ ከተማ ባደረገው እንቅስቃሴ በክንደ ነበልባሎቹ የወምበርማ ብርጌድ ዕቅዱን ሳያሳካ በመጣበት እግሩ ሰራዊቱን ገብሮ ወደሽንዲ ከተማ ፈርጥጧል።

እንደ ንስር አራሱን አድሶ እና አግዝፎ የመጣው የወምበርማ ብርጌድ ወታደራዊ አቅሙን በማፈርጠም የአረመኔውን ስርዓት ወንበር ጠባቂዎችን እረፍት በማሳጣት ፊት ለፊት እየተዋጋ ይገኛል።

!ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
፲/አ እ/ር ዘመኑ አማረ 5ኛ ክ/ጦር ህ/ግ መምሪያ ኃላፊ
👍31🙏1
ሰበር ዜና

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ እዝ ደጅ አዝማች 4ተኛ ኮር የጎቤ ክፍለ ጦር አካል የሆነው ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌድ ከምዕራብ ጎንደር አብርሃ ጅራ ተነስቶ በእግር በመኪና ዙ 23ም ይዞ ወደ ማዕከላዊ ጎንደር ሶሮቃ ከተማ ይጓዝ የነበረውን 2 ሬጅመንት የጠላት ኃይል እርጎየ ከተማ አቅራቢያ "ማይ ኪጅራ" ላይ ደፈጣ ጥሎ በመቆየት ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ከፊሉ ተመልሶ ወደ መጣበት አቅጣጫ እንዲፈረጥጥ ግማሹ ደግሞ መግቢያ መውጫው ሲጠፋው እንዲበተን አድርጎታል።

ከጠላት 7 ሙት እና 8 ቁስለኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ከወገን በኩል ምንም ጉዳት አልደረሰም።

@ስማቸው ጥላሁን ውብየ(አርበኛ)/
የጎቤ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
3🙏3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ በሁለት ግንባሮች በጠላት ላይ ድል ተቀዳጅቷል ።

1/ የትመን ንዑስ ከተማ እና ማህበርብርሃን ቀበሌ ሰረጎ በመግባት ጥቃት ተሰንዝሯል!!

የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ በየትመን ንዑስ ከተማ የትመን የመጀመረያ ደረጃ ት/ቤት መሽጎ የሚገኜው የአረመኔው አገዛዝ ቅጥረኛ የሚኒሻ አባላት ጳጉሜ 03/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ሰዓት ሰርጎ በመግባት በF1 ቦንብ መድረሻ ሲያሳጣው አድሯል።

አባ ኮስትር ብርጌድ በየትመን ከተማ የመሸገውን የአረመኔው አገዛዝ ይጠቀምበት የነበረውን ሁለት ኮፒውተር እና የተለያዩ ማቴሪያል በማውጣት የአረመኔው አገዛዝ ቅጥረኛ ሰራዊትን ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል። በዚህ የተበሳጨው የአረመኔው ሰራዊት ተጨማሪ ኃይል በማስገባት በእነማይ ወረዳ የፈለገ ሰላም ቀበሌ/ዘብች እየሱስ የንፁሃን አርሶ አደሮችን አንድ በሬ እና አንድ ላም በመዝረፍ እንዲሁም ማህበረሰቡ ይጠቀምበት የቀበሌ ሰነድ አቃጥሎ ወደ መጣበት ቦታ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጦ ሄዶል።

ከደጀን ከተማ ወደ ቢቸና ከተማ የአገዛዙ ካዲሪዎችን በዙ 23፣ብረት ለበስ ፔንፔ እና የቡድን መሳሪያዎች በመያዝ አጅቦ ይንቀሳቀስ የነበር የአረመኔው ሰራዊት ጵጉሜ 04/2017 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ዲቢሳ ቀበሌ አባ ኮስትር ብርጌድ ደፈጣ በመጣል ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል ።

2/ ወምበርማ ብርጌድ የተሳካ ጥቃት ፈፀመ

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴውድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦር የወምበርማ ብርጌድ ከጥዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት የአረመኔው ስርዓት ወንበር ጠባቂዎችን ልዩ ስሙ ኮኪ መገንጠያ ላይ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

አይበገሬዎቹ የወምበርማ ብርጌድ ንስር ሻለቃ፣ ቆምጠው ሻለቃ እና ነበልባል ሻለቃ በጋራ በመሆን ወደ ወገዳድ ኮኪ መገንጠያ ላይ የአረመኔውን ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በርካታ ወንበር ጠባቂዎች ወደ ላይኛዉ ሲሸኙ ቀሪዎችነሰ ቁሰለኛ በማድረግ ቀጥተውታል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
🙏2
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ በልጅ እያሱ ኮር የተሠጠ የአዲስ ዘመን መልዕክት፦
***^^^***^^^*^^^^*

የአዲስ ዘመን ዋዜማ ላይ ሆነን ነገን አሻግረን በተስፋ እያየን ውድ ህይወታችን ሳንሰስት ንፁ ደም ለጋ አጥንት እያፈሰስን እና አየከሰከስን ሦስት አዲስ ዘመኖችን በፅናት ተሻግረን ነገም ለሚከፈለው የትኛውም መስዕዋትነት ራሳችንን አዘጋጅተን አዲሱን ዘመን የህዝባችንን መከራ የምናሳጥርበት የታጋዮችን ተስፋ የምናለመልምበት እንዲሆን እንመኛለን በትጋትም እንሰራለን፡፡

ለመላው የአማራ ህዝብ እና ኢትዮጲያዊያን በሙሉ ሃገሪቷ ላይ ባለው የከፋ የኑሮ ውድነት እና የሰላም እጦት ምክኒያት እንኳን በሰላም አደረሳችሁና በዓሉ የሰላም የፍቅር ይሁንላችሁ ለማለት ሁኔታዎች ባይፈቅዱልንም አዲሱን ዓመት በአንድነት ታግለን ይህን አስከፊ ስርዓት የምናሶግድበት ዘመን እንዲሆን እየተመኘን ሁሉም ብሄር ብሄረሰብች ራሳቸውን ለትግል እንዲያዘጋጁ ከወዲሁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

በዓሉን ተያይዞ ወልዲያን ጨምሮ በሰሜን ወሎ እና በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ስፍራዎች በልጅ እያሱ ኮር ስም የሚደረግ ውንብድና እና ከፍተኛ ዝርፊያ እንዳለ ደርሰንበታል፡፡

ስለሆነም በልጅ እያሱ ኮር ስም ተሠማርተው በተለይ ወልዲያ መርሳ ስሪንቃ እንዲሁም በተለያዩ ዙሪያ ቀበሌዎች ባሉ ባለ ሀብቶች ላይ ኮሩ የማያውቀውን ህገ-ወጥ ደረሰኝ በማሳተም የገንዘብ ማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ ህዝብን የሚያንገላቱ ፀረ ፋኖ እና ፀረ ህዝብ ኀይሎችን ኮሩ እሰከመጨረሻው ይታገላቸዋል፡፡

ህዝባችን ሊያውቅ የሚገባው ነጭ ሃቅ ግን ይህንን አፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙት መንግሥት በፋኖ ስም ያደራጃቸው ዘራፊዎች መሆናቸውን ተረድታችሁ አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት ከጎናችን ተሰልፋችሁ በጋራ ወንጀለኞችን እንድንታገል እያሳሰብን እስካሁን በስማችን በተሰራው ወንጀል ኮሩ ምንም እውቅና እንደሌለው መረዳት ይኖርብናል፡፡

በመጨረሻም ኮሩ ዘመን መለወጫን አስመልክቶ ምንም አይነት ድጋፍ እንዳልጠየቀ ከወዲሁ ማሳሰብ እንፈልጋለን፡፡

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም
🙏6
በቁይ ከተማ በዘመቻ ሰማዕታት ኦፕሬሸን የፋኖን በትር መቆቋም ያቃተው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት እየፈራረሰ ነው።

1ኛ.ናይፍ ጅማ የተባለ ኦሮምያ ክልል የሻሸመኔ ተወላጅ የአረመኔው አገዛዝ የመከላከያ ሰራዊት አባል ከምስራቅ ዕዝ 75ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጂመንት 1ኛ ሻምበል ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም የአ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮሰ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ደባይ ጮቄ ብርጌድን ተቀላቅሏል።

2ኛ. ወንዳወክ ይሁን ሸበል በረንታ ሌዲ ቡይቴ ቀበሌ  እና ማናየ መኩየ ሸበል በረንታ እያሱ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆኑ ከቢቸና ከተማ እና የዕዱውኃ ከተማ መሽጎ ከሚገኜው የሚኒሻ መዋቅር በመክዳት ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ተቀላቅሏል።

በሌላ መረጃ ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም በሸበል በረንታ የዕዱውሃ ከተማ የመሸገው የአብይ አህመድ ዙፍን ጠባቂ ሚኒሻ እርስ በርሱ እየተጋደለ ነው። ሰማይነህ ጌታቸው የተባለ የአገዛዙ ቅጥርኛ የሚኒሻ አባል በእርስ በርስ ተኩስ የተገደለ መሆኑን ተረጋግጦል።

ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም

      ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
  የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
🙏5
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  የአዲስ አመት ዋዜማን  ዘራፊዎችን እና  የብልፅግናን ጥምር ሀይል በማስወገድ አዲስ አመትን በድል ተቀበለ  ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ 5 ኮር   ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  ከአምባጊዮርጊስ እስከ ዳባት ከተማ ድረስ ህብረተሰቡን ሲዘርፋና ሲያግቱ በነበሩ ወሮበሎች ርምጃውን አጠናክሮ ቀጥሏል።ከራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ጋር በመጣመር እየተወሰደ ባለው ስርዓት የማስያዝ ዘመቻ ቀጠናው ከወዲሁ እፎይታ እ ያገኘ ሲሆን ይሄን ተግባር ለማደናቀፍ ዓላማ በማድረግ አገዛዙ ሰራዊት አሰማርቶ ለዘራፊዎች ሽፋን ለመስጠት የሞከረ ቢሆንም የበላይ ዘለቀ ዕዝ አሃዶች ከባድ ምት ደርሶበታል።
ዛሬ ጳጉሜ 5/2017 ዓ/ም ከወርቅ ደቦ እስከ ገደብየ ከተማ ለዘራፊዎች ሽፋን ሊሰጥ የመጣው የዘራፊው አገዛዝ ጥምር   ሀይል በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል በሆኑት  ቴዎድሮስ እና አጥናፋ ብርጌድ  አባላት እና መንገድ በመዝጋት የአገዛዙ ሀይል  ለድጋፍ እንዳይደርስ  ያደረገችውን ይታየው  ብርጌድ አባላትን ጨምሮ  በማስተባበር  ጀኔራል ተዘራ ንጉሴ  እና የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ማርዬ አድማሴ እንዲሁም የብርጌድ አመራሮች በአካል በመሩት ኦፕሬሽን ጠላት ላይ ከፍተኛ ድምሰሳ  ተደርጓል ።
  በቀጠናው ዛሬ የአገዛዙ ሀይል  እንደ ልማዱ በውርደትና በሽንፈት ካባ የተመለሰ ሲሆን አዲስ አመትን በሞትና በመርዶ ተቀብሏል።
ከወርቅ ደሞ እስከ ገደብየ ከተሞች በነበረው  አውደ ውጊያ የአህያ ባል  ከጅብ አያስጥልም ነውና ዘራፊዎችን   ለማዳንና ለሽፋን   ፎክሮ የመጣው   የአገዛዙ ሀይል ይዟቸው የነበሩ  ሁለት  ምሽጎችን ለቆ ሙትና ቁስለኛውን እያንጠባጠበ   እየፈረጠጠ ወደ  አምባጊወርጊስ ከተማ በሀዘንና በእለቅሶ ተመልሷል ።

ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ከመንግስት ጎን የሚሰለፋ ሀይሎችንና ሌቦችን ማጽዳቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በቀጠናው ያሉ  ህብረተሰቡን ቀለበት ፣ ስልክ ፣ብር እና  የተለያዩ ሀብቶችን እንዲሁም እገታ  ጭምር ሲፈፅሙ  የነበሩ ቀማኞች እና አጭበርባሪዎች  በአጭር ጊዜ ውስጥ  ሙሉ ለሙሉ ተወግደው  ቀጠናው ፍፁም ሰላማዊ ይደረጋል ሲሉ የክፍለ ጦሩ ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ወርቁ ዘገየ  አክለው  ገልፀዋል።

           ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን  !!!
           ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
5🙏2
📌ከህሊና እስረኞች የተላከ መልዕክት!

የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ይህንን ማስታወሻ የሰደድንልህ እንደ አባቶቻችን ወግና ልማድ እንኳን አደረሰህ ልንልህ አይደለም። አዲሱ ዓመት እንደ ባለፉት አመታት አገራችን በማያበራ ጦርነት ውስጥ ተነክራ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የማይቻልበት ልጅ ወልዶ ማሳደግ፣ ዘርቶ መቃም ፈፅሞ የማይቻልበት ሆናለች።

ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ከጎረቤት አገራት ተነጥላ እና ተንቃ የቅልውጥ ፖለቲካ በማካሄድ መንግስት የምትመራ ሆናለች።

ሕዝባችን እጅግ አሰቃቂ በሆነ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዬ የአንድ የዩኒቨርስቲ መምህር ደመወዝ አንድ ዳውላ ጤፍ የማይሸምትባት የጉድ አገር ሆናለች። ቤቴ ንብረቴ፣ ካርታዬ ይዞታዬ የማይባልባት በኮሪደር ልማት ስም ከህግ ውጭ በቀላጤ ትዕዛዝ ሙሉ መንደሮች በዶዘር ተጠርገው የሚነሱባት አገር ተደርጋለች።

ከቦታ ቦታ ተንቀሳቀሳቅሶ መስራት የማይቻልባት የንግድ ስራ እንደ ወንጀል የሚቆጠርባት ስልጣን የያዘው ቡድን ገንዘብ እያተመ የሕዝቡን ጥሪት የሚዘርፍባት፣ የውጭ ኃይሎች በቀጥታ እጃቸውን አስገብተው አድራጊ ጀጣሪ፣ ሿሚ ሻሪ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል። በሌላ በኩል " እነ" ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ በሚሊዮን ሚቆጠር ገንዘብ ለአንድ ምሳ የሚከፈልበት፣  እንደ ለሆሊውድ ተዋንያንያን ቅንጡ ሕይዎት የሚመሩበት፣ ሰውነታቸውን በፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና የሚያስውቡበት ነው። አዲሱ ዘመን።

ውዱ የአማራ ሕዝብ ሆይ:- ልጆቻችን የመማር የማደግ መብታቸውን መንግስት ነኝ በሚል አካል የተነጠቁበት፣ በሕዝብ ግብር የሚተዳደሩት የሕዝብ ተቋማት ገንዘብ ላለው ብቻ ትምህርትን ለመሸቀጥ የተስፋፉበት ነው አዲስ ዓመት።

አሁንም 4.9 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝባችን ተፈናቅሎ በካምፕ ውስጥ ይኖራል። አሁንም የዘር ፍጅት የተፈፀመበት የወገናችን ደም የፍትህ ያለህ እያለ እያለ ከመቃብር በላይ ይጣራል።

ዛሬም በአገራችን ተስፋ የቆረጡ ወጣቶቻችን በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩት ድንበር አቋርጠው በመሰደድ ላይ ናቸው። አንዳንዶቹ የበርሀ ሲሳይ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ የባህር አሳ እራት ሆነዋል።

የሕግ በላይነት የሚባለው መርህ ሙሉ በሙሉ ወድቆ  ፣ አቃቢ ሕግ፣ ፖሊስ፣ ማረሚያ ቤት፣ የአንድ ድርጅት አባላት እና የአንድ ብሔር ሰዎች በመሆናቸው በእየለቱ ሰዎችን ያፍናሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ያፍናእንገልፃለን፣ ይሰውራሉ።ሕግን እንደ ማጥቂያ መሳሪያ በመጠቀም ንፁሀንን በማጎሪያ አስረው ያሰቃያሉ።

የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዘመናት ያልተቋረጠ፣ የመንግስት ታሪክ ካላቸው ጥቂት ሕዝቦች መካከል አንዱ የሆነ፣ በተፃፈ ህግ ሲተዳደር የኖረ፣ የራሱ ፊደል እና የዳበረ የስነ ፅሁፍ ታሪክ ያለው እና የራሱን ታሪክ በራሱ ፊደል እና ቋንቋ ፅፎ ያኖረ ሕዝብ ነው።

የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዘመናት ነፃነቱን በደም እና በአጥንት ያስከበረ፣ ለዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምሳሌ የሆነ፣ መዓዛው እንደ መልካም ሽቶ፣ ዓለምን ያወደ፣ የገናና ስም ባለቤት ነው። እንድሁም የአማራ ሕዝብ ፈሪሐ እግዚአብሄር ያለው፣ የመልካም አኗኗር መርሆችን፣ ገንዘቡ ያደረገ፣ ለጠላት ሳይቀር የሚራራ ሕዝብ ነው።

የአማራ ሕዝብ በርእስቱ የማይደራደር፣ ንብረቱን የማያስነካ፣ የሌላውንም የማይነካ ነው። ራሱን በመቻል እንዲሁም ለሌሎች በመትረፍ መርህ የሚመራ ነው። ከሁሉ በላይ የአማራ ህዝብ ለህግ የበላይነት መከበር ቁርጠኝነት ያለው፣ መንግስትን አክብሮ የሚያስከብር ሲሆን፣ ሕግ የማያውቁት ጨካካኝና ዘራፊ ስልጣን ሲይዝ ደግሞ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ዱር ቤቴ የሚልም ነው።

እንደ ሕዝብ የአማራ ሕዝብ ጠላታችን ነው እናጥፋው ያሉ ጠላቶቻችን ተባብረው ተሰልፈዋል። የፖለቲካ ስልጣን ተቆጣጠረው ሕገ ከመንግስት ጀምሮ ፀረ አማራ ሕጎችን ፣ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን በስራ ላይ አውለዋል።

ለዓመታት የዘለቀ የጥላቻ ዘመቻ በአማራ ሕዝብ ላይ አካሂደዋል፣ በዚህም በአማራ ጥላቻ ተኮትኩቶ ያደገ ትውልድ አፍርተዋል።

ከዚህ ዘመቻ በኋላ የአማራን ሕዝብ ንብረት መዝረፍ እና ማውደም። እስር እና ስቃይ ቀጥሎ  የአማራ ሕዝብ በሚሊዮኖች ተፈናቅሏል። የዘር ፍጅት ተፈፅሞበታል። አሁንም በኮሪደር ልማት ስም ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች ሃምሳ አምስት ከተሞች የማፈናቀሉ ስራ ቀን ከሌት እየተሰራ ነው።

የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች የሆኑት እነዚህ ሐይሎች የአማራን ሕዝብ ለማጥቃት ቀን ከሌት በመትጋት ይሰራሉ።
የኢትዮጵያን ሕዝብ  ድልብ ሀብት ጠቅልለን፣ የአማራን ሕዝብ በማፈናቀል ፣ ጠራርጎ በማስወጣት እና በመፍጀት የራሳችንን አዲስ አገር እንመሰርታለን ላሉ ተስፈኞች ቦታ ቦታ ለመልቀቅ ሲባል የአማራን ህዝብ ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ በሆነ ሁኔታ እንዲፈጅ ተፈርዶበታል።

መላው የአማራ ሕዝብ ታጋዮች ለትግሉ በፅናት እና በታማኝነት በመቆማችሁ በዚህ ዘመን ሊደረግ ይችላል ተብሎ በማይታሰብ ደረጃ የማንነት ድምሰሳ እና የዘር ፍጅት እየተፈፀመበት፣ ላለው ሕዝባችን የሕይዎት መስዋትነት በመክፈላችሁ እንድሁም የአንድነት ብስራት እያሰማችሁን በመሆኑ በርቱ ቀጥሉ እንላለን።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ የዘር ፍጅት ለማስቆም የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአፅዕኖት እንጠይቃለን።

እኛ በቂሊንጦ እስር ቤት የምንገኝ  ብዙሃን የአማራ የፖለቲካ እስረኞች በብዙ ስቃይና መከራ ውስጥ እንገኛለን። በተለይ ኮሽ ባለ እና አገዛዙ በደነገጠ ቁጥር ከሰብዓዊነት ውጭ በሆነ ደረጃ ተደራራቢ የሆነ ግፍና በደል ይደርስብናል። የአገዛዙ የቁጣው ሁሉ ማረፊያ እኛ እስር ቤት ውስጥ ያለነውን እስረኞች ቢያደርግም ከተነሳንበት ዓላማ አንፃር የሚደርስብን ሁሉ በፀጋ እንቀበላለን።

በዚህ የሕዝባችን መከራና ስቃይ ባላባራበት እንደውም ተጠናክሮ የቀጠለበትን 2018 ዓ/ም የአዲስ ዓመት መባቻ " ገና ያልጠባው አዲስ ዓመት" ብለን ሰይመነዋል።

ይህን የአዲስ ዓመት ጨለማ እለትም በመከራ እና በስቃይ ውስጥ ያለውን ሕዝባችንን በማሰብ፣ በእኛ ላይ ያለውን ተደጋጋሚ ኢሰብዓዊ ጥቃት በመቃወም እና በአገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ጥቃት ለመቃዎም ስንል  የርሀብ አድማ አድርገን ለማሳለፍ መወሰናችንን ለሕዝባችን እንገልፃለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
ቂሊንጦ ከሚገኙ እስረኞች የተለከ
🙏41