ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሣይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ብርጌድ በሚንቀሳቀስበት የምዕራብ መሐል ሣይንት ወረዳ ውስጥ የፋሽስቱ አብይ አህመድ በጦር ሜዳ የሚደርስበትን ሽንፈት ለማካካስ በማሰብ በንፁሓን ላይ የሚወስደው እርምጃ ቀጥሎ በዛሬው እለት ማለትም ጳጉሜ 03 ቀን 2017 ዓ.ም 035 ቀበሌ (የረሬ) መምሬ ሀብታሙ ደሳለው የተባሉ የሀይማኖት አባትን ከሌሊቱ 11:00 ስአት ላይ እረሽነዋቸዋል::


ጨለማ ለብሰው ወደ መምሬ ሀብታሙ ደሳለው የመኖሪያ አድራሻ ያመሩት የፋሽስቱ አብይ አህመድ ነፍሰ ገዳዮች በፈፀሙ ግፍ ምክንያት የአትሮንስ ብርጌድ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም መላው የመሐል ሳይንት ወረዳ ህዝብ ቁጣውን የገለፀ ሲሆን መሰል ኢ-ሰብአዊ እርምጃዎች በንፁሓን ላይ ሲወሰዱ ትግሉ የሚቀለበስ የሚመስላቸው አካላት ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር ይበልጥ ቁጭት እና ጉልበት ፈጣሪ እርምጃ መሆኑን ነው የሚል አቋም በወገን በኩል እንደተያዘ ነው ከዛሬው የሀዘን ድባብ እና ከከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ክስተቶች ለመረዳት የተቻለው::

የሀይማኖት አባት እና የሀገር ሽማግሌን መግደል የመጨረሻው ህዝብ ጠልነት ሲሆን አድባር የመቁረጥ እና ፈጣሪን የማስቆጣት የመጨረሻው እርምጃ መሆኑን ሁላችንም እንገነዘባለን:: የዛሬው የግፍ ግፍ የተፈፀመው ተስፋ በቆረጠው ስርዓት ጠባቂዎች ሲሆን የስርዓቱ ውድቀት ማሳያ መሆኑም ገልፅ ነው:: ተስፋ የቆረጠ ስርዓት ወደ ህዝብ እና ወደ ምልክቶቹ ማለትም ወደ ሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ይተኩሳል፤ ዛሬ የሆነውም ይህ ነው::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
👍21
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "የፖለቲካ መኮንኖችን" በድምቀት አስመረቀ::

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "ፀሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ የፖለቲካ መኮንን ማሰለጠኛ ማዕከል" የሚል ፕሮጀክት በማቋቋም የመጀመሪያ ዙር የፖለቲካ መኮንኖችን ለበርካታ ቀናት ሲያሰለጥን ቆይቶ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የፖለቲካ ዘርፍ ሥር የተቋቋመው የፖለቲካ መኮንኖች ማሰልጠኛ ማዕከል በኢትዮጵያ የፖለቲካና የድፕሎማት ታሪክ ደማቅ አሻራ ባለቤት በሆነው ፀሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ ስም በመታሰቢያነት ተሰይሟል።

ከሁሉም ኮሮች የተመለመሉ ሰልጣኝ የፖለቲካ መኮንኖች በርካታ ዉጣዉረዶችን አልፈው ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለምረቃ በመብቃታቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች የተላለፈ ሲሆን የመኮንን ተመራቂዎቹ በሰለጠኑት መሰረት በአማራ ብሔርተኝነት መስመር ትግሉን በትጋትና በንቃት ለማገልገል፣ ድርጅታችን አፋብኃን ለመጠበቅ፣ ፖለቲካዊ ሥራዎችን ለመስራት ቃል ገብተዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
👍2🙏1
ሰበር ዜና - ኮለኔሉ የተሸኘበት አው- ደ ግ-ንባር | ፋኖ አዲስ ኮር መሰረተ - ድል ተመዘገበ | በሁሉም ግንባር ህዝባዊ ውይይት
ሰበር ዜና - ኮለኔሉ የተሸኘበት አው- ደ ግ-ንባር | ፋኖ አዲስ ኮር መሰረተ - ድል ተመዘገበ | በሁሉም ግንባር ህዝባዊ ውይይት
🙏2
ታሪካዊው ዲማማ ዲክላሬሽን በተፈፀመባት ታሪካዊቷ ዲማማ ቀበሌ ላይ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ተሰማ!

በምዕራብ አማራ ቀጠና ፋግታ ለኮማ ወረዳ ስር በምትገኘው ድማማ ቀበሌ ማዘዣ ጣቢያቸውን አድርገው በነበሩ የአገዛዙ ወታደርች ላይ ዛሬ ጳጉሜ 03/2017 ከንጋት ጀምሮ በተወሰደ እርምጃ በርካታ ወታደሮች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን መረብ ሚዲያ ከዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ስር የሚገኙት የአሥር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ እና ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ አባላት ዛሬ ከንጋት ጀምሮ በወሰዱት እርምጃ ዘጠኝ ወታደሮች ሲገደሉ ከ12 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተረጋግጧል።

በጥቃቱ በተለይ በዲማማ ቀበሌ ልዩ ስሙ ማንጉዳት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ የነበረው የጠላት ማዘዣ ካምፕ የወደመ ሲሆን በርካታ የጦር መሣሪያዎችም በፋኖ እጅ መግባታቸው ታውቋል።

የፋግታ ለኮማ ወረዳዋ ዲማማ ቀበሌ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ኃይል እና የአማራ ፋኖ ጎጃም ዕዝ ውህደት የፈፀሙባት፣ የጎጃም ፋኖ አንድነት ማሰሪያ ገመድ የተቋጠረበት ዲማማ ዲክላሬሽን የተፈፀመባት ታሪካዊት ቦታ ናት።

የጎጃም ፋኖ አንድነት ፅንስ ተፀንሶ በተወለደባት በዚች ታሪካዊት ስፍራ ሰፍረው በነበሩ የፀረ አማራው አገዛዝ ተላላኪ ወታደሮች ላይ እርምጃው የተወሰደው።

ዲማማ ለሚገኘው ኃይል እገዛ ለማድረግ መነሻቸውን ከእንጅባራ፣ ከአዲስ ቅዳም፣ ከጎመጅ ተራራ እና  ከጊሳ ከተማ ያደረጉ ዙ23ና ሌሎች ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቁ የአገዛዙ ኃይሎች ካሰቡበት ሳይደርሱ ከወደ ፋኖ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ብትንትናቸው ወጥቶ እርስ በእርሳቸው ሲታኮሱ መዋላቸው ታውቋል።

@መረብ ሚዲያ
3🙏3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኀ)
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ዙሪያ በፈፀመዉ ኦፕሬሽን ታላቅ ድል መፈፀሙን አስታዉቋል።

የኮሩ አካል የሆነዉ ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ጅባስራ ብርጌድ እና ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ፋሲለደስ ብርጌድ ዘጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከባህሪ ግንብ እስከ ብርቧክስ እና አርሴማ ድረስ የሸፈነ ከጠላት ጋር ውጊያ በማድረግ በጠላት ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ማድረስ ችለዋል።

   በዙሪያዋ በተደረገዉ አዉደዉጊያ ከ10 በላይ ሙትና ቁስለኛ የሆነው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ሸሽቶ ወደ ጎንደር ከተማ እንዲገባ ተገዷል።

   

በሌላ መረጃ በህዝብ ላይ ዘረፋ ሲፈፅሙ በነበሩ ዘራፊ ሀይሎች ላይ ዕርምጃ ተወስዷል።

ከጎንደር ደባርቅ ዋና አውራ ጎዳና አሽከርካሪዎችንና መንገደኞችን በመዝረፍ የውንብድና ተግባር ተሰማርተው በነበሩ ዘራፊ ሀይሎች ላይ ዛሬ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ርምጃ ተወስዷባቸዋል።

በተለይም ከአምባጊዮርጊስ ደባርቅ መስመሮች ላይ ሲዘርፉ፣ሲያግቱ እና የውንብድና እኩይ ድርጊት ለመፈፀም ተሰማርተው በነበሩ ስርዓት አልበኞች ላይ እየተወሰደ በሚገኘው የተጠና ኦፕሬሽን መስመሩን ለጊዜው ከወሮበሎች ማፅዳት የተቻለ ሲሆን በዘላቂነት ችግሩን ለመቅረፍ ጠላት በሰፈረባቸው አካባቢዎች ድረስ ዘልቆ ማፅዳት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል።

    ተበትነው የተሰወሩ ወንበዴዎች እጅ እየሰጡ ሲሆን ህዝቡ እየተወሰደ ለሚገኘው ስርዓት የማስያዝ ርምጃ እየተሳተፈ ይገኛል።

በሌላ መረጃ የአፋብኃ ሰሜን አመራ ቀጠና በላይ ዕዝ ራስ አመራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር የአደረጃጀት ሪፎርም ማድረጉን አስታዉቋል።

ዘራይ አዝመራው ክፍለ ጦር አዲስ ዓመትን”ውስጣዊ ችግር በመፍታት ሃይል እንገንባ!መሪ እንፍጠር” በሚል መሪቃል ለሁለት ዓመታት  በአርበኛ ኢንጅነር በየነ አለማው እና አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ ሲመራ የቆየው ዘራይ ክፍለ ጦር ሙሉ ሪፎርም አድርጓል።

አውናዊ የክፍለ ጦሩ ቁመና መደበኛ የብርጌድ ስታዳርድ ባሞሉ አምስት ብርጌዶች የተዋቀረ ነው።

እነዚሁ ብርጌዶች፦
1. ቆራጡ ገብሬ አቡሃይ ፩ኛ ብርጌድ
2. ሸጋው ውበት ፪ኛ ብርጌድ
3. ሃይሌ ማሞ ፫ኛ ብርጌድ
4. ንግስቷ ሰላም ጥላሁን ፬ኛ ብርጌድ
5. ሞላ ደጀን ማይካድራ ብርጌድ ሲሆኑ የዘራይ ክፍለ ጦር እንደሚከተለው ሁኖ ተዋቅሯል።

1. የዘራይ ክፍለ ጦር ሰብሳቢ-አርበኛ እሱባለው ይርጋ
2. ወታደራዊ አዛዥ-አርበኛ ፻ዓለቃ የሽበር አስማማው
3. ም/ል ወታደራዊ አዛዥ-አርበኛ አምሳሉ ዘሪሁን
4. ዘመቻ-አርበኛ ሙሉቀን ያለው
5. ም/ል ዘመቻ-አርበኛ አማኑኤል አጥናፉ
6. አስተዳደር-አርበኛ ፶ዓለቃ ትግስት ተረፈ
7. ሎጅስቲክ አስተዳደር-አርበኛ ጋሻው መሰለ
8. ልዩ ተልዕኮ-አርበኛ ገብሬ ሸቴ
9. ስለጠና-አርበኛ አሜሪካው አለባ
10. ኦርዲናስ-አርበኛ ይበልጣል ጌታቸው
11. ገንዘብ አስተዳደር-አርበኛ ጌታቸው ዘሪሁን
12. ፖለቲከ ዘርፍ-አርበኛ ላቀው ፈረደ
13. ህዝብ ግንኙነት-አርበኛ ፍቅሩ የማታው
14. መረጃ እና ደህንነት———-
15. ህዝባዊ አስተዳደር-አርበኛ ቃቀይ ጌትነት
16. ህግ እና ስነ-ምግባር-መምህር አስቻለው አግንቸ
     በመሆን ዘራይ ክ/ጦር አመራር አዋቅሯል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ቃል አቀባይ ማርሸት ፀሃው
🙏31
በማስመሰል እንባ ሀዘንን ላይገልጡ፣
ዛሬም 'ሰዉ እና አዞ' ተመሳስለው መጡ።

የዚች ሀገር ጉዳይ ምነው ድንግርግሯ፣
የመጋረጃዉ ጉድ ላይደበቅ ግብሯ።

ከጀርባዋ ፅልመት ከፊት ብልጭልጭታ፣
እየሳቁ ሙሾ እያነቡ እስክስታ፣
ሆነና ነገሩ የሁላችን ህመም፣
ላይቀር መወለዱ ምነው ምጧ ባይረዝም።

ተፃፈ... በአፋብኃ አፄ ምኒልክ ዕዝ ፖለቲካ መምሪያ ም/ኃላፊ ፋኖ ሞገስ አባራው ወዳጆ!
ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም
👍63
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ለ3ተኛ ዙር ኮማንዶዎችን አስመርቋል ።

ለተከታታይ 6 ወራት በቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ በተመረጡ እና ብቃት ባለቸዉ አሰልጣኞች ስልጠና ሲሰጣቸዉ የቆዩ የ3ተኛ ዙር ኮማንዶዎቸ በዛሬዉ ዕለት በቀን 04/13/17 ዓ/ም ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የክ/ጦር አመራሮች እንዲሁም የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።

በፕሮግራሙ ላይ የቴዎድሮስ ዕዝ የስልጠና መምሪያ ሃላፊ ኮማንዶ ታዬ ብርሃኑ

የቴዎድሮስ ዕዝ ም/ጦር አዛዥ ሻለቃ የኔአለም ዘለቀ

የቴዎድሮስ ዕዝ ም/አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አርበኛ ስለሽ ከበደ

የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ ኮማንዶ ዴቭ እንዲሁም የክ/ጦሩ ፓለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

መመልመል፣ መቀስቀስ፣ ማደራጀት፣ ማሰልጠን፣ማስታጠቅ፣ማቀድ፣ጠላትን ድባቅ መመምታት ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
🙏51🥰1👏1