ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከውያ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች በየግንባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአፋብኅ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 2ተኛ/ተፈራ ዳምጤ/ክፍለጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በተለያዩ ቀበሌወች ህዝባዊ ውይይቶችን እያደረገ ሲሆን ውይይቱን የብርጌዱ አመራሮች ስምሪት ይዘው ቀበሌወችን በመከፋፈል እያወያዩ ነው።

ህዝቡ ከፋኖ ጋር ያለው ግንኙነት ምን እንደሚመስል፣ አልፎ አልፎ የሚገጥሙ ችግሮችን በተመለከተ፣ ፋኖ የወከለላቸው የጎበዝ አለቆች እንዴት እያስተዳደሩዋቸው እንደሆነ፣ ከትጥቅ ዝግጅትና ከኋላ ደጀንነት አኳያ ፣ በአጠቃላይ ፋኖ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌወች ማህበረሰባችን ቅሬታ እንዳይኖረው እንዲሁም ችግሮችንም ለመፍታትና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል ቀጣይም እንወያያለን ብለዋል።

ከውይይቱ ባገኘነው ሀሳብ መሰረትም ከፋኖ የሚፈጠሩ ችግሮችን ወዲያውኑ የማያዳግም እርምት የሚወሰድ ሲሆን ከጎበዝ አለቆች ጋር የሚከሰቱ ችግሮችን ደግሞ ችግሮችን ለህዝባችን በመዘርጋት የጎበዝ አለቆችን በመቀየር ጭምር የማስተካከል ስራ ይሰራል።

"የትግላችን መሰረት የሆነውን የህዝባችንን ችግሮች በውይይቶች እየፈታን ትግላችንን ዳር እናደርሳለን" ሲል የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ያጋራው መረጃ ያሳያል።
      
  በተመሳሳይ ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከትጥቅ ትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ)  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች አንዱ በዋግኸምራ አስተዳደር ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ላልኪው ቀበሌ አንዱ ሲሆን ከቀበሌው ማህበረሰብ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ተነግሯል።

ጷግሜ 02/2017ዓ.ም የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው ህዝባዊ ውይይት የፋኖ ሰራዊት ከማህብተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት፣የሲቪል አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ  እና ከሰራዊቱ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሁም የፍትህ አሰጣጥን በተመለከተ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በተነሱ የመወያያ ሀሳቦች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መጠናቀቁ ታውቋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ  ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

በሌላ በኩል
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ  ሃይል( አፋበኃ) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው  እዝ በፍቃዱ  በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ በሆማ ቦነያ ቀበሌ  ሕዝባዊ  ውይይቶች  አድርጓል።

ውይይቱን የአፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ ክ/ጦር ፖለቲካ  ዘርፍ ሃላፊ መ/ር አርበኛ ፋኖ በላቸው ዳኘ  የመራው ሲሆን ስለ አገዛዙ እና ተልኮ ተቀብለው ሰርገው የሚገቡ ሃይሎችን በንቃት ተከታትሎ መያዝ እና በቀጠናው ለሚንቀሳቀሰው ለፋኖ አባለት ሪፖርተር  ማድረግ እናዳለበቸ  በጽኑ  መልክቱን አስተላልፏል። አየይዞም ስለሕዝባዊ አስተዳደር ጉዳይ ማብራሪያ  ቷል።

በድርጅት አሰራር እና መርሕ እንጅ ማንም በዘመድ አዝማድ  የሚሰጥ ፍትሕ እንደለለ ለሕዝቡ  አስረድቷል። አክሎም  ትግሉ  ሕዝብን እና ሃገርን የማዳን እስከሆነ ድረስ ሕዝባችን እና  አባት  አርበኞች  እራሳችሁን የትግሉ አካል በማድረግ ጥፋተኛውን በመምከር አለፍ ሲልም ለይታችሁ በመያዝ  ነፃነታችንን በጋራ እንደናሰፍን ሲል በመድረኩ ለተሰበሰቡት አባት አርበኞች እና ሕዝብ መልክቱን አስተላልፏል።
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በአውደ ውጊያ ፣ በስቦ ማስከዳት እና በመልሶ ማደራጀት ከፍተኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ።

በዚህም :-
                1/

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ክፍለጦሮች በጋራ በከፈቱት ጠንካራ ውጊያ የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ውጫሌ ከተማን ተቆጣጥረው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

ዛሬ ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ በልጅ እያሱ ኮር ስር ያሉ ክፍለ ጦሮች የደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ውጫሌ ከተማ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በቀጠለው ተጋድሎ እስከ መሀል ከተማ በመግባት የየጁ ክፍለ ጦር ራስ አሊ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ እና ራምቦ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን በተናበበ ፍፁም በተቀናጀ መልኩ የተሳካ ውጊያ በማድረግ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርጉት ውለዋል ።

እስካሁን ከ10 በላይ ፖሊስ እና ሚሊሻ ሲገደል በቁጥር ያልተረጋገጠ የወራሪው መንግስት ወታደር ሚሊሻ አድማ ብተና አና ፖሊስ ቁስለኛ ሆኗል:: በተጨማሪም ሶስት የሚሊሻ አባላት ምርኮኛ በማድረግ ውጊያው እንደ ተፋፋመ ቀጥሏል::

በዚህ ውጊያ የልጅ እያሱ ኮር የበቀል በትሩን አጠናክሮ በመቀጠል ውጫሌ ከተማ ያለውን የብልፅግና ግብስብሰ የፀጥታ ኀይል እና ካድሬ እያጠራ ይገኛል፡፡

የአብይ ሠራዊት ከወልድያ እና ከደሴ ሁለት ዙ23 እና አንድ መድፍ ያመጣ ቢሆንም ከብዙ ኪ.ሜ ርቀት ቆሞ ከመተኮስ በዘለለ ምንም ፋይዳ ያለው ተግባር ሊፈፅሙ አልቻሉም፡፡

በተጨማሪም በተደረገው ከፍተኛ የከበባ ውጊያ አንድ ከፍተኛ (ኮሎኔል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል) የመከላከያ አመራርም ጭምር ተገድሏል።

ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ውጊያው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከዚህ የተሻለ ጮቤ የሚያስረግጥ ድል እየጠበቅን ከበባውን አጠናክረን ይዘናል፡፡

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

              2/

ተከዜ ክ/ጦር አመራር መልሶ አደራጀ
   የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
መይሳው ካሳ ፬ኛ ኮር

የ4ኛ ኮር አካል የሆነው ተከዜ ክፍለ ጦር የክፍለ ጦሩን አመራር እንደ አዲስ አደራጅቷል።

ወቅቱ የሚዋጅ የክ/ጦር ሁለንተናዊ ቁመና ለመጎናፀፍ እየሰራ የሚገኘው ተከዜ ክ/ጦር አመራሩን በሚከተለው መንገድ አደራጅቷል።

1.አርበኛ መላኩ ነጋ ...የክ/ጦሩ ዋናጨሰብሳቢ
2/... ኃይሉ አስታጠቅ  ም/ሰብሳቢ
3/...  አበባው ወርቁ  ህ/ግንኙነት ኃላፊ
4/...  ዘነበ ገላ    ፖለቲካ ክፍል ኃላፊ
5/... ሀብቴ አስታጠቅ   ዘመቻ
6/... ናቃቸው ጌጡ   ም/ዘመቻ
7/...  በራ ደሳለኝ   ፋይናንስ ኃላፊ
8/...  ባሪያው አየልኝ   የሰው ኃይል ክ/ኃላፊ
9/...  ፍቅሬ ጽጌ   ቀናዊ ትስስር ኃላፊ
10/... አወቀ     ኦርዲናንስ ኃላፊ
11/... አስታጥቄ ጫቅሉ  አስ/ጽ/ቤት ኃላፊ
12/... ኤሪሚያስ ወርቄ   ሎጀስቲክ ኃላፊ
13/ ... የሽነህ ፀጋ   ህግና ስነ ምግባር ክ/ኃላፊ
14/ ... ቴዎድሮስ አለማየሁ  ም/ሎጀስቲክ ክ/ኃላፊ  በመሆን ክ/ጦሩ እንደ  አዲስ ተዋቅሯል።

             3/

የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ   5ኛ ክፍለ ጦር የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ስቦ በማስከዳት የብልፅግናን ዙፋን አስጠባቂ የሚሊሻ እና የመከላከያ አባለትን እየበታተነ ይገኛል።
የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ መ/ወታደር ታደሰ ሞላ ለሚዲያችን እንደገለፁት ወደ ቋሪት ስንገባ ገነት አቦ ከተማ ላይ 28 ጌዜ ሞርተር ተኩሰናል፤  ፋኖ ላይ አንድም ጉዳት አልደረሰም ንፁሀን ነው የጎዳው፤ በዚህ ምክንያት ህዝብን ከሚወጋ  ኃይል ጋር አልዋጋም  ብየ  ስርዓቱን ክጄ ከእነሙሉ ትጥቄ ፋኖን ተቀላቅያለሁ ብሏል።
እየፈራርሰ የመጣው የቋሪት ወረዳ የሚሊሻ አባል የነበረው ጌታሰው ተሰራ እንዳለው  ነሐሴ 3/2017 ዓ.ም  ነበልባሉ የገረመው ወንዳውክ ብርጌድ በገ/ማርያም  ከተማ ባደረገው ውጊያ  በርካታ የሚሊሻ አባል   መበተኑን ገልፆ፤ መጀመሪያም ስገባ  ከወንድሞቸ ጋር ልዋጋ ሳይሆን ትጥቅ ከጠላት ታጥቄ ወይም ነጥቄ ለመውጣት ነበር፤ አላማየና ሀሳቤ ተሳክቶ ከሚሊሻ መሳሪያ ነጥቄ ከፍኖ ወንድሞቼ ጋር ተቀላቅያለሁ ብሏል።
ሌላው የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ የሚሊሻ አባል የነበረ ወጣት ይከበር ጫኔ እንዳለው ወደ ሚሊሻ የገባሁ መሳሪያ ለመታጠቅ ነበር ነገር ግን ፋኖ በነሃሴ 3/2017 ዓ.ም ባደረገው ውጊያ ሚሊሻ ላይ ብቻ ትኩርቱን በማድረጉ በርካታ የሚሊሻ አባላት ላይ ከፍተኛ እርምጃ በመወሰዱ  ሀሳቤ ሳይሳካ ህይወቴን ለማቆየት በጀሌ ወጥቻለሁ ብሏል።
አፋባኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክ/ጦር ነበልባሉን የገረመው ወንዳውክ ብርጌድን ጳጉሜ 02/5017 ዓ.ም የተቀላቀሉ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ የነበሩ የመከላከያና የሚሊሻ አባላት:-
1.መ/ወታደር ዘሪሁን መና   403 ኮር  71ኛ ክ/ጦር  5ኛ ሻለቃ የነበረ
2. መ/ ወታደር ታደሰ ሞላ 403 ኮር 71ኛ ክ/ጦር  5ኛ ሻለቃ የነበረ
3. የሻምበል ንብርት ቀበሌ ግራርማ የሽል ሚሊሻ   ቲም መሪ 
4. ሀይማኖት በለጠ ቀበሌ  ጎምት ድዋሮ ሚሊሻ
5. የቻለ አልፈር  ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
6. ጌታሁን በቀለ ቀበሌ አ/ሌ ገደል  ሚሊሻ
7. ይርጋ አዕምሮ  ቀበሌ አ/ሌባ ገደል ሚሊሻ
8.ይከበር ጫኔ ቀበሌ አ/ሌባ ገደል ሚሊሻ
9. በላይ ደረበው ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
10 ካሳሁን ይታይህ ቀበሌ  አ/ይበርት ሚሊሻ
11. ዘመኑ አየለ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
12. ይናገር ዋለ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
13. ይገርማል ዘርያቆብ ቀበሌ  ጎምት ድዋሮ ሚሊሻ
14. አያና ደርበው ቀበሌ  ወይበይኝ ሚሊሻ
15.  ጌታሰው ተሰራ ቀበሌ ጎምት ድዋሮ ሚሊሻ
16. ደጀኔ ወርቄ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
17. ይልቃል ወረቄ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
18. መኳንንት አንማው ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
19. ፋኖስ ጫኔ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
20. አትንኩት አለምነህ ቀበሌ ቦረዝ በስኮስ ሚሊሻ
22. አብርሃም ጉልማ ቀበሌ አየን ይበርት ሚሊሻ
23. ተስፋሁን ጫኔ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
24. ሀብታሙ ጌታነህ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ  ሻምበል መሪ
25. ደጉ የኔነህ ቀበሌ  ጎሞት ድዋሮ ሚሊሻ
26. ካሳሁን ይታይህ ቀበሌ  አ/ይበረት ሚሊሻ
27. ገደፋው አሸብር ቀበሌ ወይበዬኝ ሚሊሻ ጋንታ መሪ
28. መላክ አያሌው ቀበሌ ወይበይኝሚሊሻ  ቲም መሪ
29. ይከበር ጠብቄ ቀበሌ  ወይበይኝ  የወረዳው ሰላምና ደህንነት  ኃላፊ (ዋሌ ቢተው)   አጃቢ የነበረ
30. መልሰው አወቀ ቀበሌ  ቦረዝ በስኮስ ሚሊሻ
31. እንየው የደሜ ቀበሌ  ቦረዝ በስኮስ ሚሊሻ
32.ካሳሁን እንግዳ ቀበሌ አየን ይበርት ሚሊሻ
#ነሐሴ 04/2017 ዓ.ም ይፋ ያደረግናቸው
33ኛ. እንደግ ጋሻው __  ጀሌ
34ኛ. ይከበር ንጋቱ __ አንድ እግር ክላሽ
35ኛ. አዳነ ውባለም __ ጂንፎ ኤስኬኤስ
35ኛ. መኳንንት ተስፌ __ እንየው ከተባለ ሚኒሻ ክላሽ ነጥቆ የወጣ
36ኛ. እሱባለው መኮነን __ ጀሌ
37ኛ. አጠቃ አልፈር __ ጀሌ
38ኛ. ይግረም አንዷለም __ ጀሌ
39ኛ. በለው ገነት __ ጅንፎ ኤስኬኤስ
40ኛ. ግርማው መሰሉ __  ጀሌ
41ኛ. ጊዜው እውነቱ __ ጀሌ
42ኛ. ሚኪያሰ እንዳሌ __ ጀሌ
43ኛ. ዳንኤል የተባሉ የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት አባላት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን ተቀላቅለዋል ።
🙏3
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ ቀጣና አሳምነው እዝ  ዛሬ ጳጉሜን 3, 2017ዓም ነበልባል ክፈፍለጦር ጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ ሻለቃ አንድ (መብረቁ ሻለቃ) ደማቅ ታሪክ ፈፀመ።

በአረርቲ ከተማ ሸዋ ገነት አካባቢ በሁለት የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂዎች ላይ ሟች ሳጅን ብርሃኑ እና ሌላው ቁስለኛ ለግዜው ስሙ በቅጡ ያልታወቀ በሞተር ሲጓዙ ጀግኖቹ የጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ ጓዶች በወሰዱት የደፈጣ የተሳካ ስራ ተመቶ እያነከሰ ወደ መንደር ሲገባ የሟች መሳርያ ግን በልበሙልነት አንስቷል።

በአከባቢው ተጠግቶ ሲመለከት የነበረው የአረርቲ ከተማ ነዋሪው የጀግኖቹ የፋኖዎች ልበሙልነት ንግግር እንዲህ ሲሉ ነግረውናል። "ማንም ዙፋን አስጠባቂ ባንዳ ከነበልባል እይታ አይሰወርም" እያሉ በተደጋጋሚ "ነበልባል" የሚል ጭሆት ስያሰሙ ነበር። የሚል ከማህበረሰባችን ማረጋገጫ መረጃ ተቀብለናል።

ጀግኖቹ የመብረቁ ሻለቃ 'ምሽናቸው' በተሳካ ጨርሰው የማረኩት መሳርያ ይዘው በሰላም ወደ  ቀጠናቸው እየደረሱ ይገኛሉ።

ድል ለአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል!!!

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ ቀጣና አሳምነው እዝ ነበልባል ክፍለጦር ሚድያ ክፍል።
🙏4
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ አራተኛ ደጃዝማች ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና በተለይ የአገዛዙን ዓላማ ተቀብለው የቅማንትና የአማራን ህዝብ በማጋጨትና ዝርያፊ ያ በመፈጸም የፋኖን ስም ለማጥፋትና ለማጉደፍ እያደረገ በሚገኘውን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን አስታወቀ።

ኮሩ በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ብቻ ሳይሆን የተከዜ ክፍለ ጦርም በቀጣይ አዲስ አመት ይህንን ስራ የሚሰሩት ላይ ትልቅ ትኩረት በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

በመሆኑም በዚህ ተግባር ላይ የሚሳተፉ ማናቸውም አካላት እጃቸውን ለፋኖ እንዲሰጡ ነው ጥሪ ያስተላለፈው።

የአማራ አፈርኖ ብሔራዊ ሰሜን አማራ ቀጠና አራተኛ ደጃዝማች ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ለዓለም አቀፉ ፋኖ ሚዲያ በቀጠናው ያለውን ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በቀጥታ የስልክ መስመር በመገኘት አጋርቶናል፡ ዝርዝሩን በማታው የዜና ዕወጃ በመረጃ ቲቪ እና የዩቱዩብ ቻናላችን ይከታተሉን።
🙏1
የሻምበል አዛዡ የሻለቃ አዛዥ የሆነ የበላይ አመራሩን ገድሎ ፋኖን ተቀላቀለ!

በራያ ቀጠና በርተክላይ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ተመድበው ከነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል ሳጅን ኤፍሬም ከበደ የተባለ የሻምበል አዛዥ የሻለቃ አዛዥ የሆነ የበላይ አመራሩን ገድሎ ፋኖን መቀላቀሉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የሻምበል አዛዡ፡ የሻለቃ አዛዥ በሆነው የበላይ አመራሩ ላይ ግድያውን ከፈፀመ በኋላ ለቀናት በእግሩ ተጉዞ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝን የተቀላቀለ ሲሆን፡ የዕዙ ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ምክትል ኃላፊ በሆነው በአርበኛ ኮማንዶ ጌታቸው ሲሳይ የተመራ ልኡክ ደማቅ አቀባበል እንዳደረገለት ታውቋል።

ግድያው የተፈፀመበት በፌደራል ፖሊስ 5ኛ መምሪያ ስር የ1ኛ ሻለቃ አዛዡ፡ አስከሬኑ ወደ አላማጣ ተወስዶ ስርዓተ ቀብሩ እንዲፈፀም ተደርጓል ነው የተባለው።

የሻምበል አዛዡ ሳጅን ኤፍሬም ከበደ፡ የሻለቃ አዛዡ የሆነው የበላይ አመራሩ "በንፁኋኖች ላይ የሚፈፅመውን ግፍና በደል ቆሜ ማየት ስላልቻልኩ እርምጃውን ወስጄበታለሁ" ሲል ቃል በቃል ተናግሯል።

በ5ኛ መምሪያ ስር የ1ኛ ሻለቃ አዛዡ የአከባቢው ነዋሪዎችን በጅምላ በማሰር ከ50 ሺ ብር ጀምሮ እስከ አንድ መቶ ሺ ብር የሚቀበል ሲሆን፡የተጠየቀባቸውን ገንዘብ መክፈል ያልቻሉትን ደግሞ "የፋኖ ደጋፊ ናቸው" በሚል አንዳንዶቹን ይገድላል፡ አንዳንዶቹን ደግሞ "ለፋኖ ስንቅ ሲያቀብሉ እጅ ከፈንጅ የተያዙ ናቸው" በሚል አላማጣ ከተማ ለሚገኘው ለሪፐብሊካን ኮማንዶ ክ/ጦር አሳልፎ ይሰጣል ሲል ነው እርምጃውን የወሰደው የሻምበል አዛዥ የተናገረው።

የሻለቃ አዛዡ በተጨማሪም፡ በአከባቢው ልጃገረዶችን ጨምሮ የአባወራ ሚስቶችን ወደ ካምፕ እያስመጣ የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ይፈፅም እንደነበር ተነግሯል።

ይሄንን ግፍና በደል ቆሞ መመልከት ያልፈለገው በሻለቃዋ ስር የአንድ ሻምበል አዛዡ ሳጅን ኤፍሬም ከበደ፡ በግፈኛው የሻለቃ አዛዥ ላይ ነፃ እርምጃ በመውሰድ ከነ ሙሉ ትጥቁ ፋኖን መቀላቀሉን ነው ለማረጋገጥ የተቻለው።

የሻምበል አመራሩ ሳጅን ኤፍሬም ከበደ እንደገለፀው፡ "የፅንፈኛ ደጋፊ ናችሁ" በሚል በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ትጥቅ እንዲያወርዱ ተደርገው የተወሰዱበት ደብዛ ጠፍቷል፡ ስለታሰሩ አባሎች የትና እንዴት እንዳሉ የሚጠይቅ ደግሞ "አንተም የፅንፈኛ ደጋፊ ነህ" ተብሎ ለእስር ይደረግና የቀድሞዎቹ እጣ ፈንታ ይደርሰዋል ያለ ሲሆን፡ በርካታ የተቋሙ አባላትም ከእስርና ከእርሸና ለማምለጥ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በገፍ እየከዱ መሆኑን ተናግሯል።

ሳጅን ኤፍሬም ከበደ አክሎም፡ ሰራዊቱ ተመናምኗል፡ የቀረውም በተስፋ መቁረጥ ተሞልቶ ነው ያለው ያለ ሲሆን፡ በአሁን ሰዓት በአንድ ሻምበል ውስጥ ከ20 የማይበልጡ አባላት ብቻ ይገኛሉ፡ በአንድ ሻለቃ ስር ደግሞ የስታፍ አባላትን ጨምሮ 70 የማይሞሉ አባላት ይገኛሉ ሲል የፌደራል ፖሊስ ተቋም ምን ያህል ባዶ ቀፎውን እንደቀረ በዝርዝር አስረድቷል።

@መረብ ሚዲያ
🙏31
በሰሜን ጎንደር ዞን : ምስራቅ ጠለምት ዲማ አካባቢ 6/ስድስት/ቀበሌዎች ማለትም ሜዳ ሐምሾምድር : ደገብራዪ : ፍየልውሀ : ጫጨሬ እና ማይግመሬ የተባሉ ቀበሌዎች በድርቅ ምክንያት ከ 9000 እንስሳት በላይ ለአደጋ ተጋልጠዋል : ብዙም ለሞት ተዳርገዋል።

በነዚህ ቀበሌዎች 50 000 ህዝብ ለከባድ ችግር ተጋላጭ ሁኗል።
🙏2
ሰበር የደፈጣ ድምሰሳ በላይ ዘለቀ ዕዝ !!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ከፍለ ጦር አካል የሆነችው ሻለቃ ዋሴ ተኮላ ብርጌድ አባላት ለበዓል ሲጓዞ የነበረን የአገዛዙን ሀይል መንገድ ላይ በደፈጣ በታትነዋለች ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆችው ሻለቃ ዋሴ ተኮላ ብርጌድ ዛሬ ጳጉሜ 3 /2017 ዓ/ም ከማክሰኝት ከተማ ወደ አዘዞ ካምፕ ለበዓል አመራሮችን አጅቦ ሲጓዝ የነበረ የብርሃኑ ጁላ ቅልብ ሀይል ምንዝሮ ቀበሌ ላይ በጀግኖች ተደምስሷል ።

የአገዛዙ ሀይል በዙ _23 እና በዲሽቃ ታግዞ አመራሮችን አጅቦ ወደ አዘዞ ካምፕ ሲጓዝ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የሻለቃ ዋሴ ተኮላ ብርጌድ ጀግኖች መንገድ ላይ በመጠበቅ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ የተሳካ የደፈጣ ጥቃት ኦፕሬሽን ፈፅመዋል።

በአውደ ውጊያው 4 የብርሃኑ ጁላ ሀይል በሞት ሲሸኙ 6 ቁስለኛ ሲሆኑ 1 እስከ ጥቁር ክላሹ ገቢ ተደርጓል።

ሽምቅ
ደፈጣ
የከበባ ድምሰሳ
ተናጥላዊ ጥቃት
ሐይል ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል !!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
🙏3
‎መልካም ዜና!

‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የኮር ምስረታ አካሄደ
‎================
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አምስት ክ/ጦሮችን ወደ አንድ በማሰባሰብ ግዙፉን የፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር አንድ መስርቷል::

‎ይህንን ኮር አፄይኩኖ አምላክ፥ ሰባት ለሰባ፥ ነጎድጓድ፥ ናደው እና በፍቃዱ በላይ ክ/ጦሮች በአንድ ላይ ሁነው ነው የመሰረቱት ::

‎ይህ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ምስረታ ሥነ ስርዓት የአሳምነው እዝ አመራሮች፥ የየክ/ጦር መሪዎች፥ የፋኖ አባላት፥ አባት አርበኞች፥ የሀይማኖት አባቶች፥ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኤፍራታና ግድም ወረዳ በደራሲና አርበኛ አሰገድ መኮነን መቀመጫ ማጀቴ ተካሄዷል::

‎በዚህ የኮር ምስረታ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ አፄ ይኩኖ አምላክ፥ ሰባት ለሰባ ፥ነጎድጓድ ፥ ናደው እና በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር የፋኖ አባላት በወታደራዊ ሰልፍ ተመው በመምጣት ተሳታፊ ሁነዋል::

‎የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ምስረታ ፕሮግራም ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል እና ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና መሪ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ እስካሁን የገጠሙንን በርካታ ተግዳሮቶች በፋኖ አርበኞቻችን እና በማህበረሰባችን ጥንካሬ ተወጥተን የጋራ መሰባሰቢያ ቤታችንን ከሸንኮራ እስከ ቋራ ተጉዘን ገንብተን በመጣን ማግስት ታላቁን የፄ ዘርያይቆብ ኮር መመስረት መቻላችን ጥንካሬያችን የታየበት በመሆኑ ሁላችንም ደስ ሊለን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል::

‎በኮር ምስረታው የተገኙት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ አባል እና የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ፊት አውራሪ ድርሳን ብረሀኔ ከአሳምነው ዕዝ ጋር በጋራ በመስራት የጥላትን ቅስም የምንሰብርበት ወቅት ሩቅ አይደለም ብለዋል::

‎ይህንን የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ምስረታ በተመለከተ የስም ስያሜ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ አርበኛ አሸናፊ ምንዳ በኩል ማብራሪያ ተሰጥቶ የዕዙ የድርጅት ጉዳዮች  የቀጣይ እቅድ የሚያመላክቱ መልእክቶች ተላልፈዋል::

‎በዚህ የኮር ምስረታ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ ዋና አዛዥ ፊት አውራሪ ባዩ አለባቸው የፋኖ ኃይል ሊከተላቸው የሚገቡ የቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችና ወታደራዊ መመሪያ ምን መምሰል እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል::

‎የኮር ምስረታ ፕሮግራሙም በተለያዩ መጣጥፎች፥ ግጥሞች፥ ሽለላና ቀረርቶ በድምቀት ከተካሄደ በኋላ  የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል እንዲመሰረት ከሸንኮራ እስከ ቋራ ተራራ ሸንተረሩ ቁርና ብርዱ እንዲሁም የጠላት ሀይል ሳይበግራቸው አንድ የአማራ ቤት ሰርተው ለተመለሱት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የቃል ኪዳን ምልክት የሆነችውን የአባቶቻችን የቃል ኪዳን አርማ የሆነችውን ሰንደቅ ዓላማ በማበርከት ለቀጣይ መሪነት ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል::

‎በመጨረሻም የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ም/ል መሪ በአርበኛ ኢሳያስ ደመቀ የአፄ ዘርአያዕቆብ ኮር አንድ መሪ ሁነው የተመደቡ የፋኖ አመራሮች ቃለመሀላ እንዲፈጽሙ ተደርጎ የተመደቡ አመራሮች የአማራ ህዝብ የጣለባቸውን አደራ በብቃት እንዲወጡ ጭምር መልእክት በማስተላለፍ እና ከብልጽግና ጋር ወግነው ለሚሰሩ አመራሮች፥ የአድማ ብተና ፥የሚኒሻ ፥ እና የመከላከያ አባላት የፋኖን ትግል እንዲደግፉ ጥሪ በማስተላለፍ ፕሮግራሙ ተጠናቋል::

‎የኮሩን አመራሮች ዝርዝር ሙሉ መረጃ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

            "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
       ጳጉሜ 03/2017 ዓ.ም
👍2🙏1
የአፋብኃ ምዕራብ ሰማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ር የመንትዮቹ ሁለት ብርጌዶች ልዩ ኦፕሬሽን !!!

ከፋግታ ለኮማ ወረዳ ድማማ ቀበሌ ላይ ተከማችቶ የነበረዉ የእናት ጡት ነካሹ ቡድን አዲሱን 2018 ዓ/ም እንዳያይ ተፈረደበት። 

ሰዉ ሁኖ ተፈጥሮ እራሱ በፈጠረዉ እርካሽ የባንዳነት ስብና ምክኒያት እንደ እብድ ዉሻ እየተሳደደ የዉሻ ሞትን ሙቷታል።

ዛሬ ጳጉሜ 3/2017 ዓ/ም መንትዮቹ የአፋብኅ ምዕራብ ቀጠና ቴዉድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ሻለቃ ፪ እና ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ድማማ ማንጉዳ ላይ ተከማችቶ ከነበረዉ የአድማ ብተና ሚሊሻ እና የፖሊስ ታጣቂ ላይ በወሰደዱት በለሊት ጠላትን የማፅዳት ኦፕሬሽን ከለሊቱ 11:30 ላይ ጠላትን በከበባ ይዘዉ ተሻለ ዳኘዉ የተባለን ከሀዲ ጨምሮ         
_9 የሚሆነዉን በመደምሰስ
_ከ12 በላዩን ቁስለኛ አድርገዉ
_3 ክላሽንኮቭ                                             _1 ሲሶ ክላሽ                                                    _370 የክላሽ ተተኳሽ ተረክበዋል።

ጠላት  ከእንጅባራ ፣ ከአዲስ ቅዳም ፣ ከጎመጅ ተራራ እና  ከጊሳ ከተማ ተነስቶ   ዙ23ን ጨምሮ በከባድ የቡድን መሳሪያ እየታገዘ በገባ ብዛት ያለዉ የብርሀኑ ጁላ ታጣቂ ከጨርሶ መደምሰስ |የለቀማ ፅዳት| ቢተርፍም በደረሰበት ከባድ ኪሳራ ምክኒያት እርስ በእርሱ በሀሳብ መግባባት ተስኖት መሳሪያ ለመማዘዝ በተጠበቅ ላይ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
🙏31
የአፋብሃ ምዕ/አማራ ቲወድሮስ ዕዝ
🕯🕯ግዙፉ 5ኛ ክ/ጦር 🕯🕯
ከሁሉም ብርጌዶች ጋር የጋራ ውይይት አደረገ።
🕯🕯🕯🕯
ግዙፉ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦር ሚያዝያ 9/8/2017ዓ.ም ደባይ ላይ ሪፎርም ተሰርቶ ወደ ስራ ከገባ በኋላ ከፍተኛ የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቲወድሮስ ዕዝ አመራሮች አርበኛ እሸቱ ጌትነት የዕዙ አደረጃጀት መምሪያ ሓላፊ፣አርበኛ ስለሽ ከበደ ም/አደረጃጀት ፣ሻለቃ የኔዓለም ዘለቀ የዕዙ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና ሌሎችም የዕዝ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ጦሩ ሰብሳቢ የሳቱ ጉማጅ አርበኛ ደመላሽ አንድነው ፣የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ ፶/አ ይበልጣል መልካሙ እና ሌሎች የክፍለ ጦሩ አመራሮች በተገኙበት የ4 ወር የስራ ግምገማ አድርጓል።ባፉት አራት ወራቶች
👉በጤና
👉በአደረጃጀት
👉በውጊያ
👉በሚዲያ
👉በፖለቲካ
👉በህግ እና ስነስርዓት እና በሌሎችም በርካታ ስራዎች  ለድጋፍ ከመጡ የድርጅት አመራሮች ጋር በመተባበር ተሰርቷል።እነዚህን ውጤታማ ስራወች በማስቀጠል እና መስተካከል ያለባቸውን ጉድለቶች በማስተካከል ክፍለ ጦሩን የሚመጥን እና ይበልጥ ገዝፎ እንዲወጣ የሚያደርግ ስራ ለመስራት ይበልጥ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ተወያይቷል።
ሁሉም ብርጌዶች ክፍለጦሩ ማስተካከል ያለበትን ከጠቆሙ በኋላ ጠላት ደካማ መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ክፍለ ጦር ከክፍለ ጦር እንዲሁም ብርጌድ ከብርጌድ ከፍተኛ ትስስር በማድረግ አድምተን ልንመታው ይገባል፤ ጠላት ከተሞችን ለቆ ከመውጣቱ በፊት ዝግ በዝግ የጦር መሳሪያዎችን መረከብ አለብን በለዋል።
በጤናው ዘርፍ የሚሰሩ የብርጌድም ሆነ የክፍለ ጦር የጤና ባለሙያዎች እያደረጉት ያለውን ሙያዊ ድጋፍ ሁሉም ብርጌዶች አመስግነው ድርጅቱ ግን አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል አንድነቱ ተመልሶ ወደ አንድ በመምጣቱ ደስ እንዳላቸው ገልፀው ነገር ግን የጋራ የሆነ እና የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ሊያታግል የሚችል የነጠረ እና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ማኒፌስቶ መውጣት አለበት ሲሉ ድርጅታዊ የሆነ ምክረ ሀሳብ ተሰጥተዋል።
በአጠቃላይ ክፍለ ጦሩም ሆነ ድርጅቱ ከብርጌድ አመራሮች የተሰጡትን አስተያየት እና ጥቆማዎች ለወደፊት በዕቅድ አካቶ የሚሰራባቸው መሆኑን በማስመር የትኛውንም ተልዕኮ ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።
በመጨረሻም ትልልቅ የሀይማኖት አባቶች ግጥም ፣ቅኔና ምክረ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን የክፍለ ጦሩ የኪነት ቡድን ሽለላ፣ውዝዋዜ እና ግጥም በማቅረብ መድረኩን እንዲያደምቁት በማድረግ ተሀድሶ ተሀድሶ አድርጓል።

(ጳጉሜ 1/13/2017ዓ.ም)

ዘመኑ አማረ
የ5ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
👍3
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሣይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ብርጌድ በሚንቀሳቀስበት የምዕራብ መሐል ሣይንት ወረዳ ውስጥ የፋሽስቱ አብይ አህመድ በጦር ሜዳ የሚደርስበትን ሽንፈት ለማካካስ በማሰብ በንፁሓን ላይ የሚወስደው እርምጃ ቀጥሎ በዛሬው እለት ማለትም ጳጉሜ 03 ቀን 2017 ዓ.ም 035 ቀበሌ (የረሬ) መምሬ ሀብታሙ ደሳለው የተባሉ የሀይማኖት አባትን ከሌሊቱ 11:00 ስአት ላይ እረሽነዋቸዋል::


ጨለማ ለብሰው ወደ መምሬ ሀብታሙ ደሳለው የመኖሪያ አድራሻ ያመሩት የፋሽስቱ አብይ አህመድ ነፍሰ ገዳዮች በፈፀሙ ግፍ ምክንያት የአትሮንስ ብርጌድ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም መላው የመሐል ሳይንት ወረዳ ህዝብ ቁጣውን የገለፀ ሲሆን መሰል ኢ-ሰብአዊ እርምጃዎች በንፁሓን ላይ ሲወሰዱ ትግሉ የሚቀለበስ የሚመስላቸው አካላት ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር ይበልጥ ቁጭት እና ጉልበት ፈጣሪ እርምጃ መሆኑን ነው የሚል አቋም በወገን በኩል እንደተያዘ ነው ከዛሬው የሀዘን ድባብ እና ከከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ክስተቶች ለመረዳት የተቻለው::

የሀይማኖት አባት እና የሀገር ሽማግሌን መግደል የመጨረሻው ህዝብ ጠልነት ሲሆን አድባር የመቁረጥ እና ፈጣሪን የማስቆጣት የመጨረሻው እርምጃ መሆኑን ሁላችንም እንገነዘባለን:: የዛሬው የግፍ ግፍ የተፈፀመው ተስፋ በቆረጠው ስርዓት ጠባቂዎች ሲሆን የስርዓቱ ውድቀት ማሳያ መሆኑም ገልፅ ነው:: ተስፋ የቆረጠ ስርዓት ወደ ህዝብ እና ወደ ምልክቶቹ ማለትም ወደ ሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ይተኩሳል፤ ዛሬ የሆነውም ይህ ነው::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
👍21
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "የፖለቲካ መኮንኖችን" በድምቀት አስመረቀ::

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ "ፀሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ የፖለቲካ መኮንን ማሰለጠኛ ማዕከል" የሚል ፕሮጀክት በማቋቋም የመጀመሪያ ዙር የፖለቲካ መኮንኖችን ለበርካታ ቀናት ሲያሰለጥን ቆይቶ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የፖለቲካ ዘርፍ ሥር የተቋቋመው የፖለቲካ መኮንኖች ማሰልጠኛ ማዕከል በኢትዮጵያ የፖለቲካና የድፕሎማት ታሪክ ደማቅ አሻራ ባለቤት በሆነው ፀሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ ስም በመታሰቢያነት ተሰይሟል።

ከሁሉም ኮሮች የተመለመሉ ሰልጣኝ የፖለቲካ መኮንኖች በርካታ ዉጣዉረዶችን አልፈው ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለምረቃ በመብቃታቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች የተላለፈ ሲሆን የመኮንን ተመራቂዎቹ በሰለጠኑት መሰረት በአማራ ብሔርተኝነት መስመር ትግሉን በትጋትና በንቃት ለማገልገል፣ ድርጅታችን አፋብኃን ለመጠበቅ፣ ፖለቲካዊ ሥራዎችን ለመስራት ቃል ገብተዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
👍2🙏1