ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
<<ዘመቻ ሰማዕታት>>

ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ዘመቻ ሰማዕታት የሁለተኛ ዙር ኦፕሬሽን ቢቸና ከተማ አጣና ተራ፣የትመን ከተማ፣ማህበረብርሀን ቀበሌ እና ወይራ ጠልማ ቀበሌ በክፍለ ጦሩ ወታደራዊ ክንፍ እቅድ ውጊያ አካሂዶል።

በዘመቻ ሰማዕታት ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም በተካሄደው ውጊያ አባ ኮስትር ብርጌድ ቢቸና ከተማ እና የትመን ከተማ የታቀደ ውጊያ መደበኛ ማጥቃት ሲያደርግ በየረዝ፣በወይራና ጠለማ ላይ ደግሞ የጠላት ኃይል ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ የደፈጣ ስራ ሰረቷል።

አባ ኮስትር ብርጌድ በየትመን ከተማ መሽጎ የሚገኜውን የአረመኔውን አገዛዝ ይጠቀምበት የነበረውን ካንብ በ9 ቦንብ እና በRPG እንዲሁም የኮስትር ልጆች በታጠቁት ዘመናዊ መሳሪያዎች በየትመን ከተማ መዘጋጃ ቤት የነበሩ የተለያዩ ዶክመቶችን ይዞ በመውጣት እና ከጥቅም ውጭ አድረገዋል።የኮስትር ልጆች ኤፍዋን ቦንብን እና RPG በመጠቀም የትመን ከተማ ተቀምጦ ህዝብን እየዘረፍ የነበረውን ኃይል ሲያሯሩጡት አርፍደዋል፡፡

ደባይ ጮቄ ብርጌድ እና የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ጥምር ኃይል በጋራ በመሆን በማህበረብርሀን ቀበሌ ላይ የሚገኜውን የአረመኔው አገዛዝ አገልጋይ ሰራዊትን ከበባ በማድርግ መውጫ በማሳጣት ሙት እና ቁስለኛ አድርገዋል።ደባይ ጮቄ ብርጌድ በቁይ ከተማ መሽጎ የሚገኜው የአረመኔው ሰራዊት ወደ ማህበረብረሃን ቀበሌ ድጋፍ እንዳያደርግ ሰቅዞ በመያዝ አቅሙን አሳይቷል።

በዘመቻ ሰማዕታት 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር የሁለተኛ ዙር ኦፕሬሽን ባአካሄደው ውጊያ የተገኜ ድል:-
ከ14 በላይ የአረመኔው ሰራዊት እስከወዳኜው ተሸኝቷል።
አበው ሻንበል፣መኳንት ጌታነህ፣አንተነህ ያምራ፣አሸንፍ ይርጋ ፣ወገሽ የሚባል ጋንታ መሪ ጨምሮ ከደብረወርቅ ሽፈሬ ቀበሌ የመጣ ሚኒሻ እና አድማ ብተና ቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን 12 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።

ጠላት ይጠቀምበት የነበረው "ካምፕ" ከፋኖ በተወረወረ ቦንብ እና በRPG መሆኑን
የጠላት ካምፕ ከፋኖ በተወረወረ "ሞርተር" ጥቃት ማድርስ ተችሏል።

በየትመን ከተማ አርሶ አደሩን ከፋኖ ትግል ለመነጠል የአርሶ አደሮች መሬት ተሸንሽኖ ሊሰጥ የነበረበት መሉ ሰነድ ይዞ በመውጣት የጠላት ኃይል ይጠቀምበት የነበረው የቢሮ እቃ እና ሰነድ ማቃጠል ተችሏል።

የአረመኔው አገዛዝ ኃይል በየትመን ከተማ የአንድ አርሶ አደር የቁም ከብት(በሬ) በጠላት ጥይት ተመቶ ሞቷል።

በዘመቻ ሰማዕታት የፋኖ ምት መቋቋም ያልቻለው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት በላይነህ ቸሬ እናርጅ እናውጋ ተወላጅ የሚኒሻ አባል ከደብረ ወርቅ ከተማ በመውጣት አባ ኮስትር ብርጌድ ተቀላቅሏል።3(ሶስት) የመከላከያ አባላት ከማህበረብርሀን 01(አንድ) አድማ ብተና አባል ከጉብያ ከተማ በአጠቃላይ 4(አራት)የአገዛዙ አረመኔው አገዛዝ አባል የነበሩ አካላትን በዘመቻ ሰማዕታት ከካንፖቸው መጥፋታቸው ተረጋግጦል።

ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🙏2
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቲዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ዛሬ ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም በዘመቻ ሰማዕታት ድል አስመዝግበዋል!!!
🙏3
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ እና የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት አፋህድ በፋኖ አንድነት ጉዳይ እየመከሩ ነዉ ተብሏል።

ከመገፋፋት ወደ አንድ ወንድማዊ ምክክር የገቡት ሁለቱ የፋኖ አደረጃጀቶች ለሰራዊቱ እና ለህዝቡ እፎይታን የሰጡ ይመስላል።በቁጭት እና የህዝብን ፍላጎት በማስቀደም ወደ ታሪካዊ የአንድነት ጉዞ ያቀኑት ሁለቱ አደረጃጀቶች እስካሁን የነበረዉን ክፍተታቸዉን በሙላት ለህዝባቸዉ ደስታን ለጠላት ድንጋጤን እና ፍርሀትን የሚፈጥር የአንድነት ዉይይት ጀምረዋል።

የሁለቱ አመራሮች በአንድነት ጉዳይ ለመደራደር ቁርጠኛ መሆናቸዉን የሰማዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ጀምሯል።አሁን ላይ አንድነት ብቸኛ የማሸነፊያ መንገድ መሆኑን የተረዱት የፋኖ አመራሮቹ ከጣላት የሚወረወሩ ከፋፋይ ሀሳቦች ወደ ጎን በመተዉ የህዝቡን ድምፅ በመስማት ስራቸዉ ላይ ብቻ ማተኮራቸዉ ለአገዛዙ ብልፅግና ዉሀ ቅዳ ዉሀ መልስ ሆኖበታል።

የጠላቶቻችን ሴራ እና በህዝብ ላይ  ያሚያደርሱት ግፍ ለአንድነቱ በቂ የመፍትሄ ሀሳብ መሆኑን የተረዱት የፋኖ አመራሮቹ በራቸዉን ዘግተዉ በመምከር ችግሮችን ለመፍታት ብዙ ተግባራትን አከናዉነዋል።

ከሰሞኑ የቆራ ቃልኪዳንን ያደሰዉ አፋብኃ ለብአዴን ሰዎች ትልቅ የመርዶ ዜና ሆኖባቸዋል።

ወጣቱ ፋኖ ወደ አንድ በመምጣት ያታግለን በሚል በተደጋጋሚ ያቀረበዉ ጥሪ ከጅምሮ መልካም ነገሮችን እያስመለከተን ይገኛል።የወንድሞቻችን ቀና አመለካከት ወደ ተግባር ተለዉጦ አንድ ወጥ ድርጅት ከተመሰረት መላ የኢትዮጵያ ህዝቡ የዚህ አንድነት ደጋፊ እና የትግሉ ተሳታፊ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

የአማራን ህዝብ ለባርነት ለመሸጥ በሆዱ ያደረ ባንዳ የሰራዉ ጥቁር ታሪክ ስህተት መሆኑን የሚያምንበት በአንፃሩ ለነፃነት ሲል ነፋሱን አሳልፎ የሰጠዉ ፋኖ ደማቅ ታሪክ የሚፅፍበት ጊዜዉ እሩቅ እንደማይሆን ከአገዛዙ ብልፅግና ድንጋጤ መገንዝብ በቂ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።

ይህንን ሁሉ ህዝቡ ቆሞ እንዲመለከት ሁለቱ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድ መስመር መምጣት ይገባቸዋል።ለዚህም ህዝቡ ሁለቱ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጊዜ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆይቱ አሁን ለተጀመረዉ መልካም ጅማሮ መነሻ እኔደሆነም ተገልጿል።ፋኖ ኸደ አንድነት እንዲመጣ ላለፉት ሁለት አመታት በአፅኖት ሲጠይቅ የቆየዉ ህዝባችንን ለመካስ አመራርቹ በቁርጠኝነት እና በቁጭት ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።

አንድነቱ የሚያስፈልገው ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የሀገሪቱ ህዝብ አስፈላጊ በመሆኑ መላ የትግሉ ደጋፊ ጉዳዩን በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ ድምፅ!!
4🙏3
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ሸዋንግዛው ክፍለጦር ከላላ ወረዳ ላይ ተጋድሎ በማድረግ ድል ተጎናፀፉ::

አፋብኃ ንጉስ ሚካኤል ኮር ሸዋንግዛው ክፍለጦር ከላላ ወረዳ ሻፊ ቀበሌ እና ቲርቲራ ከተማ በመግባት ጭምር ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ በርካታ የጠላት ጥምር ጦር በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

ተጋድሎው ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም ከጧቱ 2:00-9:30 ድረስ የዋለ ሲሆን ሸዋንግዛው ክፍለጦር ተመም ሻለቃ እና ሁንያለው ሻለቃ ከላላ ወረዳ ዙሪያ ልዩ ስሙ ሻፊ የተባለ ቦታ ላይ በርካታ የጠላት ሃይል በመደምሰስና በማቁሰል ጠላትን ወደመጣበት መልሰውታል::

በተመሳሳይ በዚሁ ተጋድሎ ሸዋንግዛው ክፍለጦር ሁንያለው ሻለቃ ቲርቲራ ከተማ ዘልቆ በመግባት አንድ ጓድ የጠላት ሃይል ላይ ጥቃት በመፈፀምና በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ጠላትን ወደመጣበት በመመለስ ድል ተጎናፅፈዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
🙏41
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ሰበር ዜና

የልጅ እያሱ ኮር ክፍለጦሮች በጋራ በከፈቱት ጠንካራ ውጊያ የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ውጫሌ ከተማን ተቆጣጥረው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

ዛሬ ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ በልጅ እያሱ ኮር ስር ያሉ ክፍለ ጦሮች የደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ውጫሌ ከተማ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በቀጠለው ተጋድሎ እስከ መሀል ከተማ በመግባት የየጁ ክፍለ ጦር ራስ አሊ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ እና ራምቦ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን በተናበበ ፍፁም በተቀናጀ መልኩ የተሳካ ውጊያ በማድረግ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርጉት ውለዋል ።

እስካሁን ከ10 በላይ ፖሊስ እና ሚሊሻ ሲገደል በቁጥር ያልተረጋገጠ የወራሪው መንግስት ወታደር ሚሊሻ አድማ ብተና አና ፖሊስ ቁስለኛ ሆኗል:: በተጨማሪም ሶስት የሚሊሻ አባላት ምርኮኛ በማድረግ ውጊያው እንደ ተፋፋመ ቀጥሏል::

በዚህ ውጊያ የልጅ እያሱ ኮር የበቀል በትሩን አጠናክሮ በመቀጠል ውጫሌ ከተማ ያለውን የብልፅግና ግብስብሰ የፀጥታ ኀይል እና ካድሬ እያጠራ ይገኛል፡፡

የአብይ ሠራዊት ከወልድያ እና ከደሴ ሁለት ዙ23 እና አንድ መድፍ ያመጣ ቢሆንም ከብዙ ኪ.ሜ ርቀት ቆሞ ከመተኮስ በዘለለ ምንም ፋይዳ ያለው ተግባር ሊፈፅሙ አልቻሉም፡፡

በተጨማሪም በተደረገው ከፍተኛ የከበባ ውጊያ አንድ ከፍተኛ (ኮሎኔል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል) የመከላከያ አመራርም ጭምር ተገድሏል።

ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ውጊያው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከዚህ የተሻለ ጮቤ የሚያስረግጥ ድል እየጠበቅን ከበባውን አጠናክረን ይዘናል፡፡

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
3🙏3
የአርበኛ ዘመነ ካሴ፣ የአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ እና የአርበኛ ሔኖክ አዲሴ የአንድነት ጥሪ በአኃብኃ ሲምፖዚየም!!!!
🙏2
የአርበኛ ዘመነ ካሴ፣ የአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ እና የአርበኛ ሔኖክ አዲሴ የአንድነት ጥሪ በአኃብኃ ሲምፖዚየም!!!!
🙏1
ከውያ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች በየግንባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአፋብኅ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 2ተኛ/ተፈራ ዳምጤ/ክፍለጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በተለያዩ ቀበሌወች ህዝባዊ ውይይቶችን እያደረገ ሲሆን ውይይቱን የብርጌዱ አመራሮች ስምሪት ይዘው ቀበሌወችን በመከፋፈል እያወያዩ ነው።

ህዝቡ ከፋኖ ጋር ያለው ግንኙነት ምን እንደሚመስል፣ አልፎ አልፎ የሚገጥሙ ችግሮችን በተመለከተ፣ ፋኖ የወከለላቸው የጎበዝ አለቆች እንዴት እያስተዳደሩዋቸው እንደሆነ፣ ከትጥቅ ዝግጅትና ከኋላ ደጀንነት አኳያ ፣ በአጠቃላይ ፋኖ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌወች ማህበረሰባችን ቅሬታ እንዳይኖረው እንዲሁም ችግሮችንም ለመፍታትና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል ቀጣይም እንወያያለን ብለዋል።

ከውይይቱ ባገኘነው ሀሳብ መሰረትም ከፋኖ የሚፈጠሩ ችግሮችን ወዲያውኑ የማያዳግም እርምት የሚወሰድ ሲሆን ከጎበዝ አለቆች ጋር የሚከሰቱ ችግሮችን ደግሞ ችግሮችን ለህዝባችን በመዘርጋት የጎበዝ አለቆችን በመቀየር ጭምር የማስተካከል ስራ ይሰራል።

"የትግላችን መሰረት የሆነውን የህዝባችንን ችግሮች በውይይቶች እየፈታን ትግላችንን ዳር እናደርሳለን" ሲል የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ያጋራው መረጃ ያሳያል።
      
  በተመሳሳይ ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከትጥቅ ትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ)  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች አንዱ በዋግኸምራ አስተዳደር ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ላልኪው ቀበሌ አንዱ ሲሆን ከቀበሌው ማህበረሰብ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ተነግሯል።

ጷግሜ 02/2017ዓ.ም የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው ህዝባዊ ውይይት የፋኖ ሰራዊት ከማህብተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት፣የሲቪል አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ  እና ከሰራዊቱ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሁም የፍትህ አሰጣጥን በተመለከተ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በተነሱ የመወያያ ሀሳቦች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መጠናቀቁ ታውቋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ  ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

በሌላ በኩል
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ  ሃይል( አፋበኃ) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው  እዝ በፍቃዱ  በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ በሆማ ቦነያ ቀበሌ  ሕዝባዊ  ውይይቶች  አድርጓል።

ውይይቱን የአፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ ክ/ጦር ፖለቲካ  ዘርፍ ሃላፊ መ/ር አርበኛ ፋኖ በላቸው ዳኘ  የመራው ሲሆን ስለ አገዛዙ እና ተልኮ ተቀብለው ሰርገው የሚገቡ ሃይሎችን በንቃት ተከታትሎ መያዝ እና በቀጠናው ለሚንቀሳቀሰው ለፋኖ አባለት ሪፖርተር  ማድረግ እናዳለበቸ  በጽኑ  መልክቱን አስተላልፏል። አየይዞም ስለሕዝባዊ አስተዳደር ጉዳይ ማብራሪያ  ቷል።

በድርጅት አሰራር እና መርሕ እንጅ ማንም በዘመድ አዝማድ  የሚሰጥ ፍትሕ እንደለለ ለሕዝቡ  አስረድቷል። አክሎም  ትግሉ  ሕዝብን እና ሃገርን የማዳን እስከሆነ ድረስ ሕዝባችን እና  አባት  አርበኞች  እራሳችሁን የትግሉ አካል በማድረግ ጥፋተኛውን በመምከር አለፍ ሲልም ለይታችሁ በመያዝ  ነፃነታችንን በጋራ እንደናሰፍን ሲል በመድረኩ ለተሰበሰቡት አባት አርበኞች እና ሕዝብ መልክቱን አስተላልፏል።
🙏1