ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ተከበራችሁ የዚህ ውይይት ተሳታፊዎችና ተከታታዮች
ክቡራን የማሕበራት ተወካዮች
የተወደዳችሁ የመገናኛ ብዙሃን ሙያያተኞችና ድርጅቶች
ውድ የድርጅታችን አፋብኃ አመራሮችና የሠራዊታችን አባላት
ሁላችሁም በመላው ዓለም ያላችሁ አማራዎችና የአማራ ወዳጆች፤

በቅድሚያ የአክብሮት ሠላምታዬ ይድረሳችሁ!!

ከትናንት ጀምሮ እየተካሔደ ያለው ውይይትና እየቀረበ ያለው መልዕክት የአማራ ወገናችን ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ለመታደግ የሚያደርገው የሕልውና እና የፍትሕ ርትዕ ትግል አንድ ሁነኛ መገለጫ ነው።

ዛሬ በዚህ መድረክ ተሰባስበን ስንመክር በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት ለመመከት፡ ከምንግዜውም በላይ ንቃት ፈጥረን፡ አደረጃጀት አበጅተን፡ የትናንትን ጉድለት በዛሬ ጥረት አሟልተን ፡ነጋችንን የተሻለ የማድረግ ቁርጠኝነታችንን የምናድስበት ነው።

ባለፉት ሁለት ዓመታት የአማራነት ንቃትና መሰባሰብ ከእነውስንነቶቹ አመርቂ የሚባል እድገት አሳይቷል። ግዙፍ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም በመፍጠር የመደራጀት ያደረ የቤት ስራችንን መመለስና ማረም ጀምረናል!!

በአማራነት ላይ የተፈጠረው ንቃትና መሰባሰብ የዘመናት የጥቃት አዙሪትን ለመስበር በሚያስችል ግለት ውስጥ ይገኛል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ራሳችንን አጠናክረናል !! ለሕልውናው የሚሰለፍ ሕዝባዊ ኃይል ፈጥረናል!!
ሊያጠፋን የተነሳውን ጠላት በመመከት ማሸነፍ እንደምንችል አረጋግጠናል !!

የዕጣፈንታችን ወሳኞች እኛ ነን ብለን ስንነሳ የመናጆነት፣ የተከታይነት፣ የአጃቢነት ልማዶችን ሰብረን የአማራዊ ማንነታችን እና ፍላጎቶቻችን በአማራ ልጆች የሚወሰንበት ምዕራፍ ለመክፈት ነውና ጀምረነው ብዙ ርቀት ሔደናል።

የተከበራችሁ የዚህ መድረክ ተሳታፊዎች፤

አማራዎች ራሳችንን ብሎም አገራችንን ለማዳን አብዛኛውን የትግል መንገድ ሞክረነዋል።
በዜግነት ፖለቲካና በአገር አንድነት ትግል አልፈናል። ሆኖም በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት አልመከትነውም።
በዚያ መንገድ ኢትዮጵያን ከመስቀለኛ መንገድ መታደግ አልተቻለም።
አሁን ለረጅም ጊዜ ያልሔድንበት በአማራነት ተደራጅቶ ራስን የመታደግ ትግል የጊዜው ቁልፍ ተልዕኮ ነው።

በአማራነት ላይ በተከፈቱ ጥቃቶች ውስጥ ገና ከማለዳው እነደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ የገለጡት የወል ጥቃት መረዳት ተዳፍኖ የቀረ ነበር።

ኋላም እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያነሳሱት የአማራ ንቃት ቅስቀሳ ብዙም ሳይሻገር ቀርቷል።

በረጅሙ ታሪካችን ውስጥ አማራነታችን ላይ ጥቃቶች በቀጠሉበት፥ በአማራነት መሰባሰብ እና የጋራ ተቋም መፍጠር ሳንችል ቀርተን አማራን የሚያሕል ሕዝብ የሕልውና አደጋ ውስጥ ይገኛል።

ተቃርኖው ይገርማል !!
አገር የመሠረተ ሕዝብ ፣ ይብዛም ይነስም የአገሪቱን ተቋማት የመሠረተና የመራ ሕዝብ፣ ለሺህ ዘመን ፀንተው የቆሙ መንፈሳዊ ተቋማትን ያደራጀ ሕዝብ ፣ ለዘመናት አገር የጠበቀ አርበኝነት ያለው ሕዝብ ፥ ራሱን ከሕልውና ጥቃት የሚመክትባቸው ተቋማት አጥቶ ዛሬ ላይ ደረሰ።

አማራዎች ራሳችንን የምንጠብቅበት ሥርዓት፣ ፍላጎታችንን የምንገልጥባቸው አማራዊ ተቋማትን መፍጠር ዳገት ሆኖብን መኖራችን መገታት አለበት።
ይህ ትግል "የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ሕልውና በዘላቂነት የማረጋገጥ ነው" ስንል የሕልውና መሠረቶቻችንን የሚሸከሙ ተቋማትን የመትከል መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።

የፋኖ አንድነት ተቋማዊ ጉዞ የዚያ ምሰሶ ይሆናል!!

በአማራነት ተለይቶ መጠቃት በታወጀበት ዘመን እንኳ አባቶቻችንና እናቶቻችን ስለአገር እንጂ ስለአማራነታቸው አልመከሩም ፡ አልተሰባሰቡም፡ አልተደራጁም።
ስለአገር ዋጋ መክፈላቸው ባልከፋ ፥ ሲከፍሉት የኖሩት ዋጋ ግን በአማራነታቸው ላይ የተከፈተውን የጥፋት ጦርነት ሊያስቆመው አልቻለም።

የትናንት አለመደራጀት ለዛሬ ያወረሰን ምን እንደሆነ በውል ተገንዝበን ተነስተናል !!
ትናንት ያልሠራነው ሥራ ቁጭት ካወረሰንና ለዛሬ ብርቱ ትግል ስንቅ ከሆነን በቂ ነው።
ነጋችንን የምናሳምረው ግን በዛሬ የተባበረ ጥረታችን ነው!!

ይሕ ትውልድ ለነገ የሚያሻግረው የጥቃት ውርስ ሊኖር አይገባም !!
ይሕ የእኛ ትውልድ የቤት ሥራውን ሳይሠራ ቀርቶ የነገው ትውልድ ጥፋትን እና ፈፅሞ መገፋትን ሊወርስ አይገባም!!

ስለዚህ እንሰባሰብ !!
በአማራነታችን እንደራጅ !!

በአማራነት የመደራጀትና የመታገል ጉዳይ ግለሰባዊ እና ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትን መተው ይፈልጋል።
በመካከለችን ያለ ትናንሽና መለስተኛ ቅራኔና ፀብን፥ ኩርፊያና ልዩነትን በመተውና በማቆየት ለወል ፍላጎታችን መሰለፍን ይጠይቃል።
ብሔርተኝነት እንደዚያ ነው !!
ከትናንትም ሆነ ከዛሬ ነገሮቻችን መካከል መርጦ መዘንጋት እና ለይቶ ማንሳትን ይፈልጋል !!
ስለጋራ አማራዊ ፍላጎታችን የመሰለፍ ጥሪ ነው !!

ያን ስናደርግ እንኳን ለአማራ ትውልድ፥ ለኢትዮጵያ እና ለሰው ልጆች ሁሉ የሚተርፍ ቁምነገር እንሠራለን!!

የጋራ ጥቃት አንገሽግሾን የወጣን ታጋዮች ሁሉ እንደአማራ ስንመክር፣ እንደፋኖ ስንነጋገር ከባድ የመሠለን ቀላል እንደሚሆን አይተናል። የራሳችንን ጉዳዮች በራሳችን ለመወሰን "የእብድ ገላጋይ..." አያሻንም። እናም የጀመርነው የአንድነት ጉዞ የተማከለ አማራዊ አታጋይ ተቋም በመመስረት የሚቋጭ ይሆናል።

ይሕ የአዲሱ አመት ድላችን ሆኖ ይመዘገባል!!

የተወደዳችሁ የሕልውና ትግሉ ተሰላፊ ምሑራንና ማሕበራት፤

ያለነው እንቅልፍ አልባ ዘመን ነው። እኛን ለማጥፋት ፍፁም ጭካኔ እና ሙሉ ቆራጥነት ያለው ገዢ ጠላት ነው የገጠመን።
የምናሸንፈው ከአጥፊው ጠላታችን በላይ ስንጨክን፣ ከገጠመን ደመኛ በላይ ስንተጋ፣ ከእነሱ በላይ ስንደራጅና አንድ ስንሆን፣ ከጠላቶቻችን በላይ ቆራጦች ስንሆን ነው።
ከእነሱ በላይ ስንሠራ እንጂ በእነሱ ልክ እየተራመድንም አይደለም።

ስለሆነም በዓለም ዙሪያ ያላችሁ የአማራ ምሑራን፣ የዲያስፖራ ማሕበራት፣ ሰፊው በወጭ አገር ያለህ ወገናችን እንድትሰባሰቡ በአንድ እንድትቆሙ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ።

ስለወገናችን የምንቻቻልበት፣ ስለራሳችን የምንመክርበት፣ የምንተሳሰብበት ፣ በእያንዳንዳችን ላይ ልዩ ተልዕኮ የወደቀብን ወቅት አሁን ነው።
ከዚህ ወቅት በቀር ስለአማራና አማራነት የምንሰለፍበት የምንሠራበት የተለየ ጊዜ የለም። ዛሬ ነው !!

እናም የአማራ ማሕበራት ከተበታተነ ጉዞ ውጡና ተሰባሰቡ!!
በየአሕጉሩ አንድ ጠንካራ ሕብረት አቁሙ!!
ምሳሌ ሁኑ!!
የአንድነት ፤ የዲፕሎማሲ ፣ የአድቮኬሲና ትብብር ምሳሌ ሁኑ!!
በመጨረሻ ግን በዋነኛነት ፥ በመላው ዓለም የምትገኙ ማሕበራት፣ ምሑራንና መገናኛ ብዙሃን ሁሉንአቀፍ አማራዊ ጉዳዮቻችን የሚመከሩበት "የአማራ የምክክር ጉባኤ" በፍጥነት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀርባለሁ።

አርበኛ ዘመነ ካሴ
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል!
🙏4
<<ዘመቻ ሰማዕታት>>

ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ዘመቻ ሰማዕታት የሁለተኛ ዙር ኦፕሬሽን ቢቸና ከተማ አጣና ተራ፣የትመን ከተማ፣ማህበረብርሀን ቀበሌ እና ወይራ ጠልማ ቀበሌ በክፍለ ጦሩ ወታደራዊ ክንፍ እቅድ ውጊያ አካሂዶል።

በዘመቻ ሰማዕታት ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም በተካሄደው ውጊያ አባ ኮስትር ብርጌድ ቢቸና ከተማ እና የትመን ከተማ የታቀደ ውጊያ መደበኛ ማጥቃት ሲያደርግ በየረዝ፣በወይራና ጠለማ ላይ ደግሞ የጠላት ኃይል ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ የደፈጣ ስራ ሰረቷል።

አባ ኮስትር ብርጌድ በየትመን ከተማ መሽጎ የሚገኜውን የአረመኔውን አገዛዝ ይጠቀምበት የነበረውን ካንብ በ9 ቦንብ እና በRPG እንዲሁም የኮስትር ልጆች በታጠቁት ዘመናዊ መሳሪያዎች በየትመን ከተማ መዘጋጃ ቤት የነበሩ የተለያዩ ዶክመቶችን ይዞ በመውጣት እና ከጥቅም ውጭ አድረገዋል።የኮስትር ልጆች ኤፍዋን ቦንብን እና RPG በመጠቀም የትመን ከተማ ተቀምጦ ህዝብን እየዘረፍ የነበረውን ኃይል ሲያሯሩጡት አርፍደዋል፡፡

ደባይ ጮቄ ብርጌድ እና የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ጥምር ኃይል በጋራ በመሆን በማህበረብርሀን ቀበሌ ላይ የሚገኜውን የአረመኔው አገዛዝ አገልጋይ ሰራዊትን ከበባ በማድርግ መውጫ በማሳጣት ሙት እና ቁስለኛ አድርገዋል።ደባይ ጮቄ ብርጌድ በቁይ ከተማ መሽጎ የሚገኜው የአረመኔው ሰራዊት ወደ ማህበረብረሃን ቀበሌ ድጋፍ እንዳያደርግ ሰቅዞ በመያዝ አቅሙን አሳይቷል።

በዘመቻ ሰማዕታት 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር የሁለተኛ ዙር ኦፕሬሽን ባአካሄደው ውጊያ የተገኜ ድል:-
ከ14 በላይ የአረመኔው ሰራዊት እስከወዳኜው ተሸኝቷል።
አበው ሻንበል፣መኳንት ጌታነህ፣አንተነህ ያምራ፣አሸንፍ ይርጋ ፣ወገሽ የሚባል ጋንታ መሪ ጨምሮ ከደብረወርቅ ሽፈሬ ቀበሌ የመጣ ሚኒሻ እና አድማ ብተና ቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን 12 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።

ጠላት ይጠቀምበት የነበረው "ካምፕ" ከፋኖ በተወረወረ ቦንብ እና በRPG መሆኑን
የጠላት ካምፕ ከፋኖ በተወረወረ "ሞርተር" ጥቃት ማድርስ ተችሏል።

በየትመን ከተማ አርሶ አደሩን ከፋኖ ትግል ለመነጠል የአርሶ አደሮች መሬት ተሸንሽኖ ሊሰጥ የነበረበት መሉ ሰነድ ይዞ በመውጣት የጠላት ኃይል ይጠቀምበት የነበረው የቢሮ እቃ እና ሰነድ ማቃጠል ተችሏል።

የአረመኔው አገዛዝ ኃይል በየትመን ከተማ የአንድ አርሶ አደር የቁም ከብት(በሬ) በጠላት ጥይት ተመቶ ሞቷል።

በዘመቻ ሰማዕታት የፋኖ ምት መቋቋም ያልቻለው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት በላይነህ ቸሬ እናርጅ እናውጋ ተወላጅ የሚኒሻ አባል ከደብረ ወርቅ ከተማ በመውጣት አባ ኮስትር ብርጌድ ተቀላቅሏል።3(ሶስት) የመከላከያ አባላት ከማህበረብርሀን 01(አንድ) አድማ ብተና አባል ከጉብያ ከተማ በአጠቃላይ 4(አራት)የአገዛዙ አረመኔው አገዛዝ አባል የነበሩ አካላትን በዘመቻ ሰማዕታት ከካንፖቸው መጥፋታቸው ተረጋግጦል።

ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🙏2
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቲዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ዛሬ ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም በዘመቻ ሰማዕታት ድል አስመዝግበዋል!!!
🙏3
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ እና የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት አፋህድ በፋኖ አንድነት ጉዳይ እየመከሩ ነዉ ተብሏል።

ከመገፋፋት ወደ አንድ ወንድማዊ ምክክር የገቡት ሁለቱ የፋኖ አደረጃጀቶች ለሰራዊቱ እና ለህዝቡ እፎይታን የሰጡ ይመስላል።በቁጭት እና የህዝብን ፍላጎት በማስቀደም ወደ ታሪካዊ የአንድነት ጉዞ ያቀኑት ሁለቱ አደረጃጀቶች እስካሁን የነበረዉን ክፍተታቸዉን በሙላት ለህዝባቸዉ ደስታን ለጠላት ድንጋጤን እና ፍርሀትን የሚፈጥር የአንድነት ዉይይት ጀምረዋል።

የሁለቱ አመራሮች በአንድነት ጉዳይ ለመደራደር ቁርጠኛ መሆናቸዉን የሰማዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ጀምሯል።አሁን ላይ አንድነት ብቸኛ የማሸነፊያ መንገድ መሆኑን የተረዱት የፋኖ አመራሮቹ ከጣላት የሚወረወሩ ከፋፋይ ሀሳቦች ወደ ጎን በመተዉ የህዝቡን ድምፅ በመስማት ስራቸዉ ላይ ብቻ ማተኮራቸዉ ለአገዛዙ ብልፅግና ዉሀ ቅዳ ዉሀ መልስ ሆኖበታል።

የጠላቶቻችን ሴራ እና በህዝብ ላይ  ያሚያደርሱት ግፍ ለአንድነቱ በቂ የመፍትሄ ሀሳብ መሆኑን የተረዱት የፋኖ አመራሮቹ በራቸዉን ዘግተዉ በመምከር ችግሮችን ለመፍታት ብዙ ተግባራትን አከናዉነዋል።

ከሰሞኑ የቆራ ቃልኪዳንን ያደሰዉ አፋብኃ ለብአዴን ሰዎች ትልቅ የመርዶ ዜና ሆኖባቸዋል።

ወጣቱ ፋኖ ወደ አንድ በመምጣት ያታግለን በሚል በተደጋጋሚ ያቀረበዉ ጥሪ ከጅምሮ መልካም ነገሮችን እያስመለከተን ይገኛል።የወንድሞቻችን ቀና አመለካከት ወደ ተግባር ተለዉጦ አንድ ወጥ ድርጅት ከተመሰረት መላ የኢትዮጵያ ህዝቡ የዚህ አንድነት ደጋፊ እና የትግሉ ተሳታፊ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

የአማራን ህዝብ ለባርነት ለመሸጥ በሆዱ ያደረ ባንዳ የሰራዉ ጥቁር ታሪክ ስህተት መሆኑን የሚያምንበት በአንፃሩ ለነፃነት ሲል ነፋሱን አሳልፎ የሰጠዉ ፋኖ ደማቅ ታሪክ የሚፅፍበት ጊዜዉ እሩቅ እንደማይሆን ከአገዛዙ ብልፅግና ድንጋጤ መገንዝብ በቂ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።

ይህንን ሁሉ ህዝቡ ቆሞ እንዲመለከት ሁለቱ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድ መስመር መምጣት ይገባቸዋል።ለዚህም ህዝቡ ሁለቱ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጊዜ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆይቱ አሁን ለተጀመረዉ መልካም ጅማሮ መነሻ እኔደሆነም ተገልጿል።ፋኖ ኸደ አንድነት እንዲመጣ ላለፉት ሁለት አመታት በአፅኖት ሲጠይቅ የቆየዉ ህዝባችንን ለመካስ አመራርቹ በቁርጠኝነት እና በቁጭት ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።

አንድነቱ የሚያስፈልገው ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የሀገሪቱ ህዝብ አስፈላጊ በመሆኑ መላ የትግሉ ደጋፊ ጉዳዩን በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ ድምፅ!!
4🙏3
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ሸዋንግዛው ክፍለጦር ከላላ ወረዳ ላይ ተጋድሎ በማድረግ ድል ተጎናፀፉ::

አፋብኃ ንጉስ ሚካኤል ኮር ሸዋንግዛው ክፍለጦር ከላላ ወረዳ ሻፊ ቀበሌ እና ቲርቲራ ከተማ በመግባት ጭምር ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ በርካታ የጠላት ጥምር ጦር በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

ተጋድሎው ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም ከጧቱ 2:00-9:30 ድረስ የዋለ ሲሆን ሸዋንግዛው ክፍለጦር ተመም ሻለቃ እና ሁንያለው ሻለቃ ከላላ ወረዳ ዙሪያ ልዩ ስሙ ሻፊ የተባለ ቦታ ላይ በርካታ የጠላት ሃይል በመደምሰስና በማቁሰል ጠላትን ወደመጣበት መልሰውታል::

በተመሳሳይ በዚሁ ተጋድሎ ሸዋንግዛው ክፍለጦር ሁንያለው ሻለቃ ቲርቲራ ከተማ ዘልቆ በመግባት አንድ ጓድ የጠላት ሃይል ላይ ጥቃት በመፈፀምና በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ጠላትን ወደመጣበት በመመለስ ድል ተጎናፅፈዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
🙏41
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ሰበር ዜና

የልጅ እያሱ ኮር ክፍለጦሮች በጋራ በከፈቱት ጠንካራ ውጊያ የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ውጫሌ ከተማን ተቆጣጥረው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

ዛሬ ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ በልጅ እያሱ ኮር ስር ያሉ ክፍለ ጦሮች የደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ውጫሌ ከተማ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በቀጠለው ተጋድሎ እስከ መሀል ከተማ በመግባት የየጁ ክፍለ ጦር ራስ አሊ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ እና ራምቦ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን በተናበበ ፍፁም በተቀናጀ መልኩ የተሳካ ውጊያ በማድረግ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርጉት ውለዋል ።

እስካሁን ከ10 በላይ ፖሊስ እና ሚሊሻ ሲገደል በቁጥር ያልተረጋገጠ የወራሪው መንግስት ወታደር ሚሊሻ አድማ ብተና አና ፖሊስ ቁስለኛ ሆኗል:: በተጨማሪም ሶስት የሚሊሻ አባላት ምርኮኛ በማድረግ ውጊያው እንደ ተፋፋመ ቀጥሏል::

በዚህ ውጊያ የልጅ እያሱ ኮር የበቀል በትሩን አጠናክሮ በመቀጠል ውጫሌ ከተማ ያለውን የብልፅግና ግብስብሰ የፀጥታ ኀይል እና ካድሬ እያጠራ ይገኛል፡፡

የአብይ ሠራዊት ከወልድያ እና ከደሴ ሁለት ዙ23 እና አንድ መድፍ ያመጣ ቢሆንም ከብዙ ኪ.ሜ ርቀት ቆሞ ከመተኮስ በዘለለ ምንም ፋይዳ ያለው ተግባር ሊፈፅሙ አልቻሉም፡፡

በተጨማሪም በተደረገው ከፍተኛ የከበባ ውጊያ አንድ ከፍተኛ (ኮሎኔል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል) የመከላከያ አመራርም ጭምር ተገድሏል።

ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ውጊያው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከዚህ የተሻለ ጮቤ የሚያስረግጥ ድል እየጠበቅን ከበባውን አጠናክረን ይዘናል፡፡

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
3🙏3
የአርበኛ ዘመነ ካሴ፣ የአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ እና የአርበኛ ሔኖክ አዲሴ የአንድነት ጥሪ በአኃብኃ ሲምፖዚየም!!!!
🙏2
የአርበኛ ዘመነ ካሴ፣ የአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ እና የአርበኛ ሔኖክ አዲሴ የአንድነት ጥሪ በአኃብኃ ሲምፖዚየም!!!!
🙏1