ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የወጣቶች አፈሳ በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

በክልሉ ዕርሰ መዲና ባህርዳር ፣በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ፣በማርቆስ፣በፍኖተ ሰላም፣በደብረታቦር፣በኮምቦልቻ፣ደሴ፣ወልደያ፣ደብረብርሀን እና በሁሉም የወረዳ ከተሞች እንዲሁም ከመጠለያ ካምፖች ጭምር በርካታ ወጣቶች ታፍሰዉ በሁሉም ፖሊስ ጣቢዎች ታጉረዉ ይገኛሉ።

መረጃዉን በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል!!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2
አፋብሃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ መይሰውካሳ ሁለተኛ ኮር ካራማራ ክ/ጦር ምክትልህ/ግንኙነት ሃላፊ አንተነህ መክብብ ነኝ
አጠር ያለ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ያክል ነው በተለይ ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ሁሉ ማሃበረሰባችን የብር ኖቶችን በጥንቃቄ ሊያውቅ ይገባል ምክንያቱም ሰሞኑን የካራማራ ክፍለጦር መረጃዎች በርካታ ገንዘብ ከ145000 ብር በላይ ፎርጅድ የሁለት መቶ ብር መያዛቸውንና ወንጀለኞችንም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋና አዛዡ አርበኛ ባበይ አምባየ ገልጿል አያይዞም ማህበረሰቡ እንዲጠነቀቅ መልክቱን አስተላልፏል።
ሌላው ከሰሞኑ አሁንም ፋኖ ከተቆጣጠራቸው ቦታዎች በሙሉ ህገወጥ የህክምና ቤቶች መበራከታቸውን ተከትሎ በካራማራ ክ/ጦር የህክምና ቡድን የተመራ ሃይል በለንብረቶችን ሰብስቦካወያየ በኋላ ያላሟሉ ክሊኒኮችንና መዳኒት ቤቶችን በማሸግ አሟልተውና የህክምና ስርአቱን ተከትለው እንዲሰሩ ማስተማሪያ እርምጃዎች ተወከስደዋል
አመሰግናለሁ
👍51
◊◊ የአደረጃጀት ዜና
የአማራ ህዝብ ትግል ዘመን ተሻጋሪ ሁነቶችን እያለፈ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሷል። በእነዚህ ዘመን ተሻጋሪና ተቀያያሪ ሁነቶች ውስጥ የትግሉ እድገትና እመርታ የሚጠቀስ ነው። ሆኖም በዚህ የትግል እድገት ውስጥ የሰው ሃይል፣ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ ፣ ዲኘሎማሲያዊ ብሎም ወታደራዊ አደረጃጀት ቅርጽና ወጥ የሆነ የአሰራር መርሆዎች ተዘርግተውለት ወደ ተሻለ የትግል ምዕራፍ መሸጋገር ላይ እንገኛለን። በዚህም የተነሳ ትግላችን ባሳየው ለውጥና እድገት እንዲሁም በርቀት የምንመለከተውን ትልቁን የአላማችንን ስእል ለማሳካት የአመራር ድልድል / Reform አስፈላጊ ሆኖ ተገንቷል።
በመሆኑም ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር አብራክ የሚጠቀሰው ንስር በለሳ ቅጣው ክ/ጦር የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የክ/ጦሩ አባላት በሙሉ በተገኙበት የአመራር ድልድሉ ተሰርቷል።

1/ ዋና ሰብሳቢ _____ አርበኛ ባንተ ዘለቀ
2/ ም/ሰብሳቢ_____አርበኛ አብራራው ፀጋየ
3/ ወታደራዊ አዛዥ___አርበኛ ይዘዝ ፍቃዴ
4/ ም/ወታደራዊ አዛዥ__አርበኛ ሙሉቀን ዮሃንስ
5/ ዘመቻ ዘርፍ ኃላፊ___አርበኛ አድኖ አስማረ
6/ ም/ዘመቻ ዘርፍ ኃላፊ _አርበኛ ታድሎ ባብየ
7/ ጽ/ቤት ኃላፊ ___አርበኛ ባምላኩ ምህረት
8/ ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ___ አርበኛ ጣማለው ወልዴ
9/ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ_አርበኛ መልከ ጸዴቅ
10/ ፋይናስ ኃላፊ__አርበኛ ቢክስ ተዘራ
11/ ሎጅስቲክ ኃላፊ _____አርበኛ ደሞዝ ማሞ
12/ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ __አርበኛ ማስረሻ አለምነው
13/ ህ/አስተዳደር ኃላፊ _____አርበኛ ሻ/ ኤርሚያስ
14/ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ____አርበኛ አዛናው አሻግሬ
15/ ት/ትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ __አርበኛ ሰፊ መብራት
16/ ህግና ስነምግባር ኃላፊ _አርበኛ አቤሴሎም ተበጀ
17/ መረጃና ደንነት ኃላፊ _+_+**
በስተ መጨረሻም የተመረጡ የክ/ጦሩ አመራሮች ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን የኮሩ የስራ አስፈፃሚ አባላትም መልእክት በማስተላለፍ የእለቱ ኘሮግራም ተቋጭቷል።

➤አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግ/ቴዎ/፭ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ➤አብነት ሞላ
ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም
🙏2
📌የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲምፖዚዬም ዛሬም በደማቅ ዝግጅት ይቀጥላል!

በትላንትናው ዕለት ጷጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም የተካኼደው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲምፖዚዮም በዛሬው ዕለትም ልዩ ዝግጅቶችንና ሰርፕራይዞችን አካቶ ይካሄዳል።

አፋብኃ ድርጅቱን እያስተዋወቀ፣ የቀጣይ የትግል ምዕራፎችን በተጠናከረ ነባራዊ ሁኔታ ለማካሄድ መሠረት እየጣለ ይገኛል።

እናንተም በዚሀወ ዝግጅት ላይ እየተሳተፋችሁ፣ ድጋፍ እያደረጋችሁ አብራችሁን ቆይታ እንድታደርጉ ተጋብዛችኋል።

ዝግጅቱ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ይተላለፋል።

ዝግጅቱ:- በአማራ ሚዲያ ካውንስል አባላት ሚዲያዎች በFree Press; EMS; Anchor Media እና በሌሎች የትግሉ ደጋፊዎች ይተላለፋል።

ድጋፍ ማድረጊያ አማራጮች:- የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን ለመደገፍ

አሜሪካ Zelle 202 528 6749


Canada ላላችሁ e_transfer 780 802 5536

በዌብሳይት ለመርዳት የ ምትፈልጉ https://amharafanonationalforce.org/

የአፋብኃ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች
X - https://x.com/amharafanonf?s=21

Telegram - https://t.me/AmharaFanoNationalForc

ሁላችንም በሰዓቱ እንገናኝ!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል - አፋብኃ!
6🙏1
የተከበራችሁ በውጭው ዓለም የምትኖሩ የኅልውና ትግላችን ደጋፊ ወገኖቻችን፣
የተከበራችሁ በሞት፣ በመፈናቀል፣ በሰቆቃ ላይ የምትገኙ ግፉአን አማራዎች፣
የተከበራችሁ የአማራውን ሥርዓታዊ ግፍ በሃሳብም በግብርም የምትቃወሙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፣ ክቡራትና ክቡራን!!!

ከሁሉ አስቀድሜ ከሠላማዊ ትግል እስከ ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግላችን ውድ ሕይወታቸውን ለከፈሉ የትግሉ ሰማዕታት ያለኝን ታላቅ አክብሮት መግለጽ እፈልጋለሁ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በጽኑ አለት ላይ የተመሠረተ የአማራ ሕዝብን በአራቱም አቅጣጫ አቅፎ የሚያታግል ተቋም መሆኑን እየገለጽኩ ተቋማችን አፋብኃ መሠረቱ የትግሉ ሰማዕታት ደምና አጥንት ባይሆን ኖሮ ከውስጥም ከውጭም በተሰማሩ የጠላት አንጃዎች ፈርሰን፣ ተበትነን ነበር። ቅሉ የያዝነው ትግል መሠረቱ የትግሉ ሰማዕታት የተሰውለትን እውነት፣ የታገሉበትን ዕውቀት፣ የመከሩበትን ሐቀኛ አመክንዮ ያነገበ በመሆኑ ወደፊት ከመወንጨፍ ውጭ አማራጭ ስለሌለው በጽናት ከዛሬ ደርሰናል። የአፋብኃ ሠራዊት የጽናት ምንጩ አንዲት የማትተካ ሕይወታቸውን ለሕዝባቸው፣ ለታሪካቸው፣ ለባሕላቸው፣ ለእምነታቸው በጥቅሉ ለአማራዊ ማንነታቸው አሳልፈው የሰጡት የእነ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ፣ የእነ አርበኛ ዮሐንስ ዓለማየሁ፣ የእነ አርበኛ ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው)፣ የእነ አርበኛ ሃምሳ አለቃ አባይ እንዲሁም የግፍ ግዞተኛው የአርበኛ አሰግድ መኮንንም የአደራ ቃል ነው። ስለሆነም መራብን፣ መቁሰልን፣ ብርድና ሙቀቱን ሁሉ ሕይወትን ከመስጠት በታች ነውና በጽናት ታግሰን፣ ሐቀኛ የመርኅ ተቋም እንድንፈጥር በሕይወት የተለዩን አርበኞች ምኞት ነበራቸውና ለምኞታቸው ማሳኪያ፣ ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ እንዲሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን (አፋብኃ)ን መሠርተን በመታገል ላይ እንገኛለን።

ክቡራትና ክቡራን ወገኖቻችን፦
• አፋብኃ የተሰው የትግሉ ሰማዕታት በደማቸው ቀለምነት ከትበው የሰጡን የአደራ ቤታችን ነው። አፋብኃ በየማጎሪያ ቤቱ በአማራዊ ማንነታቸው በግዞት የሚማቅቁ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች ነጻ መውጫ ተቋም ነው። አፋብኃ በዘር ተኮር ጭፍጨፋ መዋቅራዊ አዋጅ የተጨፈጨፉ ሕጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን የሰቆቃ ድምጽ እረፍት የሚነሳው የትግል ተቋም ነው።
o አፋብኃ ውስጥ ሕጻን አይሻ መሃመድ አለች፣
o አፋብኃ ውስጥ ሃምሳ አለቃ አባይ አለ፣
o አፋብኃ ውስጥ ሜ/ጄ ውባንተ አባተ አለ፣
o አፋብኃ ውስጥ ሳጅን አደም አሊ አለ፣
o አፋብኃ ውስጥ ዮሐንስ ዓለማየሁ አለ።
በመሆኑም አፋብኃ በአርበኝነት የተሰው ጓዶቻችን አደራ፣ ምኞት እንዲሁም በሕይወት የሚገኙ አደራ ተቀባይ ታማኝ አርበኞች የነፍስ ትስስር፣ አማራዊ ተጋምዶ የተሸመኑበት ተቋም መሆኑን አውቃችሁ ለዓላማችን መሳካት የሕይወት ዘመን ባለቤቶች ጭምር እንድትሆኑ ነው ይህ ሲምፖዚዬም የተዘጋጀው።

• አፋብኃ በእውነት፣ ለእውነት፣ ስለእውነት የጀመርነውን ትግል ቅርጽ ፈጥሮ፣ መርኅ ሕግ እና አሠራር አበጅቶ የተገባደደውን ትግላችንን መቋጫ ተቋማችን በመሆኑ በአንድ ጎን እንተኩሳለን፣ በአንድ ጎን እናሰለጥናለን እናደራጃለን፣ በአንድ በኩል ዲፕሎማሲ፣ አድቮኬሲና ፕሮፓጋንዳ እንሠራለን። እነዚህን ሁሉ ሥራዎች ለማከናወን ብዙ የሙያ ስብጥር፣ በርካታ የሰው ኃይል አስፈላጊ ስለሆነ አፋብኃን ከመደገፍ አፋብኃ ወደ መሆን ትሸጋገሩም ዘንድ ጥብቅ ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።
ክቡራትና ክቡራን ወገኖቻችን፦ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ድርጅታዊ መርኅን አክብሮ፣ የሕዝባችንን ኅልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥ አስቻይ የአንድነት መደላድሎችን በሰከነ ውይይት ፈትቶ እንደሚታገል በተደጋጋሚ ገልጸናል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላው ዓለም የምትገግኙ ወገኖቻችን
• የሙያ ተደጋግፎት፣
• የዓላማ ተደጋግፎት፣
• የአማራዊነት ተደጋግፎት ፈጥራችሁ በምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ አንድ እንድትሆኑ፣ ምን እናድርግ በሚል
ሁለትም፣ ሦስትም፣ በርካታም ሆናችሁ በጋራ እንድትመክሩ፣ ስለአንድነት እንድትመክሩና በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በፎክ ሚዲያ፣ በሜንስትሪም ሚዲያ የሚደረጉ መነቃቀፎችን፣ የሚቀርቡ ዘለፋዎችንና ፍረጃዎችን አስወግዳችሁ
• አንድ ዓይነት ጩኸት፣
• አንድ ዓይነት ቋንቋ፣
• አንድ ዓይነት ትንፋሽ፣
• አንድ ዓይነት እርምጃዎችን ልንራመድ የምንችለው ስንቀራረብ፣ ስንነጋገር፣ አንድ ስንሆን ብቻ መሆኑን አውቃችሁ
አንድ ሁኑ፣ አደራ አደራ አደራ አንድ ሁኑ። ያኔ በሁሉም ዘርፍ ተጽእኖ ፈጣሪዎች መሆን እንችላለን።

• ዓለም የተጽእኖ ፈጣሪዎች፣
• ድል አድራጊነትም የተጽእኖ ፈጣሪዎች ስለሆነች ድል አድራጊነታችንን በአጭር ጊዜ እንድናደርገው አንድ እንሁን፣ ዓለም አቀፋዊ ተጽእኖም እንፍጠር። ያኔ በቀናት ውስጥ አይደለም በሰአታት ውስጥ እናሸንፋለን ማለት እፈልጋለሁ።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
አርበኛ ኢንጂኒዬር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ
አመሠግናለሁ!!!!
🙏5
ተከበራችሁ የዚህ ውይይት ተሳታፊዎችና ተከታታዮች
ክቡራን የማሕበራት ተወካዮች
የተወደዳችሁ የመገናኛ ብዙሃን ሙያያተኞችና ድርጅቶች
ውድ የድርጅታችን አፋብኃ አመራሮችና የሠራዊታችን አባላት
ሁላችሁም በመላው ዓለም ያላችሁ አማራዎችና የአማራ ወዳጆች፤

በቅድሚያ የአክብሮት ሠላምታዬ ይድረሳችሁ!!

ከትናንት ጀምሮ እየተካሔደ ያለው ውይይትና እየቀረበ ያለው መልዕክት የአማራ ወገናችን ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ለመታደግ የሚያደርገው የሕልውና እና የፍትሕ ርትዕ ትግል አንድ ሁነኛ መገለጫ ነው።

ዛሬ በዚህ መድረክ ተሰባስበን ስንመክር በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት ለመመከት፡ ከምንግዜውም በላይ ንቃት ፈጥረን፡ አደረጃጀት አበጅተን፡ የትናንትን ጉድለት በዛሬ ጥረት አሟልተን ፡ነጋችንን የተሻለ የማድረግ ቁርጠኝነታችንን የምናድስበት ነው።

ባለፉት ሁለት ዓመታት የአማራነት ንቃትና መሰባሰብ ከእነውስንነቶቹ አመርቂ የሚባል እድገት አሳይቷል። ግዙፍ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም በመፍጠር የመደራጀት ያደረ የቤት ስራችንን መመለስና ማረም ጀምረናል!!

በአማራነት ላይ የተፈጠረው ንቃትና መሰባሰብ የዘመናት የጥቃት አዙሪትን ለመስበር በሚያስችል ግለት ውስጥ ይገኛል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ራሳችንን አጠናክረናል !! ለሕልውናው የሚሰለፍ ሕዝባዊ ኃይል ፈጥረናል!!
ሊያጠፋን የተነሳውን ጠላት በመመከት ማሸነፍ እንደምንችል አረጋግጠናል !!

የዕጣፈንታችን ወሳኞች እኛ ነን ብለን ስንነሳ የመናጆነት፣ የተከታይነት፣ የአጃቢነት ልማዶችን ሰብረን የአማራዊ ማንነታችን እና ፍላጎቶቻችን በአማራ ልጆች የሚወሰንበት ምዕራፍ ለመክፈት ነውና ጀምረነው ብዙ ርቀት ሔደናል።

የተከበራችሁ የዚህ መድረክ ተሳታፊዎች፤

አማራዎች ራሳችንን ብሎም አገራችንን ለማዳን አብዛኛውን የትግል መንገድ ሞክረነዋል።
በዜግነት ፖለቲካና በአገር አንድነት ትግል አልፈናል። ሆኖም በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት አልመከትነውም።
በዚያ መንገድ ኢትዮጵያን ከመስቀለኛ መንገድ መታደግ አልተቻለም።
አሁን ለረጅም ጊዜ ያልሔድንበት በአማራነት ተደራጅቶ ራስን የመታደግ ትግል የጊዜው ቁልፍ ተልዕኮ ነው።

በአማራነት ላይ በተከፈቱ ጥቃቶች ውስጥ ገና ከማለዳው እነደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ የገለጡት የወል ጥቃት መረዳት ተዳፍኖ የቀረ ነበር።

ኋላም እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያነሳሱት የአማራ ንቃት ቅስቀሳ ብዙም ሳይሻገር ቀርቷል።

በረጅሙ ታሪካችን ውስጥ አማራነታችን ላይ ጥቃቶች በቀጠሉበት፥ በአማራነት መሰባሰብ እና የጋራ ተቋም መፍጠር ሳንችል ቀርተን አማራን የሚያሕል ሕዝብ የሕልውና አደጋ ውስጥ ይገኛል።

ተቃርኖው ይገርማል !!
አገር የመሠረተ ሕዝብ ፣ ይብዛም ይነስም የአገሪቱን ተቋማት የመሠረተና የመራ ሕዝብ፣ ለሺህ ዘመን ፀንተው የቆሙ መንፈሳዊ ተቋማትን ያደራጀ ሕዝብ ፣ ለዘመናት አገር የጠበቀ አርበኝነት ያለው ሕዝብ ፥ ራሱን ከሕልውና ጥቃት የሚመክትባቸው ተቋማት አጥቶ ዛሬ ላይ ደረሰ።

አማራዎች ራሳችንን የምንጠብቅበት ሥርዓት፣ ፍላጎታችንን የምንገልጥባቸው አማራዊ ተቋማትን መፍጠር ዳገት ሆኖብን መኖራችን መገታት አለበት።
ይህ ትግል "የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ሕልውና በዘላቂነት የማረጋገጥ ነው" ስንል የሕልውና መሠረቶቻችንን የሚሸከሙ ተቋማትን የመትከል መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።

የፋኖ አንድነት ተቋማዊ ጉዞ የዚያ ምሰሶ ይሆናል!!

በአማራነት ተለይቶ መጠቃት በታወጀበት ዘመን እንኳ አባቶቻችንና እናቶቻችን ስለአገር እንጂ ስለአማራነታቸው አልመከሩም ፡ አልተሰባሰቡም፡ አልተደራጁም።
ስለአገር ዋጋ መክፈላቸው ባልከፋ ፥ ሲከፍሉት የኖሩት ዋጋ ግን በአማራነታቸው ላይ የተከፈተውን የጥፋት ጦርነት ሊያስቆመው አልቻለም።

የትናንት አለመደራጀት ለዛሬ ያወረሰን ምን እንደሆነ በውል ተገንዝበን ተነስተናል !!
ትናንት ያልሠራነው ሥራ ቁጭት ካወረሰንና ለዛሬ ብርቱ ትግል ስንቅ ከሆነን በቂ ነው።
ነጋችንን የምናሳምረው ግን በዛሬ የተባበረ ጥረታችን ነው!!

ይሕ ትውልድ ለነገ የሚያሻግረው የጥቃት ውርስ ሊኖር አይገባም !!
ይሕ የእኛ ትውልድ የቤት ሥራውን ሳይሠራ ቀርቶ የነገው ትውልድ ጥፋትን እና ፈፅሞ መገፋትን ሊወርስ አይገባም!!

ስለዚህ እንሰባሰብ !!
በአማራነታችን እንደራጅ !!

በአማራነት የመደራጀትና የመታገል ጉዳይ ግለሰባዊ እና ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትን መተው ይፈልጋል።
በመካከለችን ያለ ትናንሽና መለስተኛ ቅራኔና ፀብን፥ ኩርፊያና ልዩነትን በመተውና በማቆየት ለወል ፍላጎታችን መሰለፍን ይጠይቃል።
ብሔርተኝነት እንደዚያ ነው !!
ከትናንትም ሆነ ከዛሬ ነገሮቻችን መካከል መርጦ መዘንጋት እና ለይቶ ማንሳትን ይፈልጋል !!
ስለጋራ አማራዊ ፍላጎታችን የመሰለፍ ጥሪ ነው !!

ያን ስናደርግ እንኳን ለአማራ ትውልድ፥ ለኢትዮጵያ እና ለሰው ልጆች ሁሉ የሚተርፍ ቁምነገር እንሠራለን!!

የጋራ ጥቃት አንገሽግሾን የወጣን ታጋዮች ሁሉ እንደአማራ ስንመክር፣ እንደፋኖ ስንነጋገር ከባድ የመሠለን ቀላል እንደሚሆን አይተናል። የራሳችንን ጉዳዮች በራሳችን ለመወሰን "የእብድ ገላጋይ..." አያሻንም። እናም የጀመርነው የአንድነት ጉዞ የተማከለ አማራዊ አታጋይ ተቋም በመመስረት የሚቋጭ ይሆናል።

ይሕ የአዲሱ አመት ድላችን ሆኖ ይመዘገባል!!

የተወደዳችሁ የሕልውና ትግሉ ተሰላፊ ምሑራንና ማሕበራት፤

ያለነው እንቅልፍ አልባ ዘመን ነው። እኛን ለማጥፋት ፍፁም ጭካኔ እና ሙሉ ቆራጥነት ያለው ገዢ ጠላት ነው የገጠመን።
የምናሸንፈው ከአጥፊው ጠላታችን በላይ ስንጨክን፣ ከገጠመን ደመኛ በላይ ስንተጋ፣ ከእነሱ በላይ ስንደራጅና አንድ ስንሆን፣ ከጠላቶቻችን በላይ ቆራጦች ስንሆን ነው።
ከእነሱ በላይ ስንሠራ እንጂ በእነሱ ልክ እየተራመድንም አይደለም።

ስለሆነም በዓለም ዙሪያ ያላችሁ የአማራ ምሑራን፣ የዲያስፖራ ማሕበራት፣ ሰፊው በወጭ አገር ያለህ ወገናችን እንድትሰባሰቡ በአንድ እንድትቆሙ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ።

ስለወገናችን የምንቻቻልበት፣ ስለራሳችን የምንመክርበት፣ የምንተሳሰብበት ፣ በእያንዳንዳችን ላይ ልዩ ተልዕኮ የወደቀብን ወቅት አሁን ነው።
ከዚህ ወቅት በቀር ስለአማራና አማራነት የምንሰለፍበት የምንሠራበት የተለየ ጊዜ የለም። ዛሬ ነው !!

እናም የአማራ ማሕበራት ከተበታተነ ጉዞ ውጡና ተሰባሰቡ!!
በየአሕጉሩ አንድ ጠንካራ ሕብረት አቁሙ!!
ምሳሌ ሁኑ!!
የአንድነት ፤ የዲፕሎማሲ ፣ የአድቮኬሲና ትብብር ምሳሌ ሁኑ!!
በመጨረሻ ግን በዋነኛነት ፥ በመላው ዓለም የምትገኙ ማሕበራት፣ ምሑራንና መገናኛ ብዙሃን ሁሉንአቀፍ አማራዊ ጉዳዮቻችን የሚመከሩበት "የአማራ የምክክር ጉባኤ" በፍጥነት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀርባለሁ።

አርበኛ ዘመነ ካሴ
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል!
🙏4
<<ዘመቻ ሰማዕታት>>

ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ዘመቻ ሰማዕታት የሁለተኛ ዙር ኦፕሬሽን ቢቸና ከተማ አጣና ተራ፣የትመን ከተማ፣ማህበረብርሀን ቀበሌ እና ወይራ ጠልማ ቀበሌ በክፍለ ጦሩ ወታደራዊ ክንፍ እቅድ ውጊያ አካሂዶል።

በዘመቻ ሰማዕታት ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም በተካሄደው ውጊያ አባ ኮስትር ብርጌድ ቢቸና ከተማ እና የትመን ከተማ የታቀደ ውጊያ መደበኛ ማጥቃት ሲያደርግ በየረዝ፣በወይራና ጠለማ ላይ ደግሞ የጠላት ኃይል ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ የደፈጣ ስራ ሰረቷል።

አባ ኮስትር ብርጌድ በየትመን ከተማ መሽጎ የሚገኜውን የአረመኔውን አገዛዝ ይጠቀምበት የነበረውን ካንብ በ9 ቦንብ እና በRPG እንዲሁም የኮስትር ልጆች በታጠቁት ዘመናዊ መሳሪያዎች በየትመን ከተማ መዘጋጃ ቤት የነበሩ የተለያዩ ዶክመቶችን ይዞ በመውጣት እና ከጥቅም ውጭ አድረገዋል።የኮስትር ልጆች ኤፍዋን ቦንብን እና RPG በመጠቀም የትመን ከተማ ተቀምጦ ህዝብን እየዘረፍ የነበረውን ኃይል ሲያሯሩጡት አርፍደዋል፡፡

ደባይ ጮቄ ብርጌድ እና የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ጥምር ኃይል በጋራ በመሆን በማህበረብርሀን ቀበሌ ላይ የሚገኜውን የአረመኔው አገዛዝ አገልጋይ ሰራዊትን ከበባ በማድርግ መውጫ በማሳጣት ሙት እና ቁስለኛ አድርገዋል።ደባይ ጮቄ ብርጌድ በቁይ ከተማ መሽጎ የሚገኜው የአረመኔው ሰራዊት ወደ ማህበረብረሃን ቀበሌ ድጋፍ እንዳያደርግ ሰቅዞ በመያዝ አቅሙን አሳይቷል።

በዘመቻ ሰማዕታት 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር የሁለተኛ ዙር ኦፕሬሽን ባአካሄደው ውጊያ የተገኜ ድል:-
ከ14 በላይ የአረመኔው ሰራዊት እስከወዳኜው ተሸኝቷል።
አበው ሻንበል፣መኳንት ጌታነህ፣አንተነህ ያምራ፣አሸንፍ ይርጋ ፣ወገሽ የሚባል ጋንታ መሪ ጨምሮ ከደብረወርቅ ሽፈሬ ቀበሌ የመጣ ሚኒሻ እና አድማ ብተና ቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን 12 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።

ጠላት ይጠቀምበት የነበረው "ካምፕ" ከፋኖ በተወረወረ ቦንብ እና በRPG መሆኑን
የጠላት ካምፕ ከፋኖ በተወረወረ "ሞርተር" ጥቃት ማድርስ ተችሏል።

በየትመን ከተማ አርሶ አደሩን ከፋኖ ትግል ለመነጠል የአርሶ አደሮች መሬት ተሸንሽኖ ሊሰጥ የነበረበት መሉ ሰነድ ይዞ በመውጣት የጠላት ኃይል ይጠቀምበት የነበረው የቢሮ እቃ እና ሰነድ ማቃጠል ተችሏል።

የአረመኔው አገዛዝ ኃይል በየትመን ከተማ የአንድ አርሶ አደር የቁም ከብት(በሬ) በጠላት ጥይት ተመቶ ሞቷል።

በዘመቻ ሰማዕታት የፋኖ ምት መቋቋም ያልቻለው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት በላይነህ ቸሬ እናርጅ እናውጋ ተወላጅ የሚኒሻ አባል ከደብረ ወርቅ ከተማ በመውጣት አባ ኮስትር ብርጌድ ተቀላቅሏል።3(ሶስት) የመከላከያ አባላት ከማህበረብርሀን 01(አንድ) አድማ ብተና አባል ከጉብያ ከተማ በአጠቃላይ 4(አራት)የአገዛዙ አረመኔው አገዛዝ አባል የነበሩ አካላትን በዘመቻ ሰማዕታት ከካንፖቸው መጥፋታቸው ተረጋግጦል።

ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🙏2
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቲዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ዛሬ ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም በዘመቻ ሰማዕታት ድል አስመዝግበዋል!!!
🙏3