ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በአፋብኃ ሲምፖዚየሙ እንዳይቀሩ‼️

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ከዚህ አቅሙ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆንና የትግሉ ጊዜ ባጠረ መልኩ ለመቋጨት ያስችል ዘንድ እና ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ሂደትና ዓላማ ግልፅ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅ እና በጎ ፈቃደኛ ደጋፊዎችን ለመጨመር ያለመውን ይህን ሲምፖዚየም ዛሬ ጷጉሜ 01 እና 02 ቀን 2017 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ አቆጣጠር September 06,2025 Saturday Starting 12 Noon and September 07,2025 Sunday Starting 12 Noon በቀጥታ ስርጭት የሚያካሂድ መሆኑን ያስታውቃል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አመራሮች በጋዜጠኞች ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል፣ ዝግጅቱም በቴሌቪዥንና በዩቲዩብ፣ ቲክቶክ እና የX (Twitter ) ማህበራዊ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እንገናኝ‼️
2🙏2
የለሚ አለም አቀፍ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች በአገዛዙ ወታደሮች ተዘረፉ

የአብይ አህመድ አገዛዝ ወታደሮች ጨለማን ተገን አድርገው በለሚ አለም አቀፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅት እና የተቋሙ ሰራተኞች ላይ የሰሩት አደገኛ ውንብድና አለም አቀፍ ወንጀል መሆኑ ተገለፀ።የለሚ አለም አቀፍ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች 48 ስልክ ሲወሰድ በአገዛዙ ወታደሮች የውጭ ሀገራት ዜጎች ለዘረፋ እና ለአካላዊ ድብደባ ሲዳረጉ የተወሰኑ የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ተደፍረዋል።በዚሕ የውንብድና ተግባር የተሳተፈው እራሱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብሎ የሚጠራው የኦሮሙማው ስርዓት አስጠባቂ የዘራፊ ስብስብ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በእንሳሮና ዋዩ ወረዳ ከአዲስ አበባ ከተማ በ 150ኪ.ሜ ርቀት ላይ በለሚ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በቅርቡ ስራ የጀመረው የለሚ አለም አቀፍ ሲሚንቶ ፋብሪካ (Lemi National Cement Factory) በቀን 28 /12/2017ዓ.ም ከለሊቱ 7:00 ላይ ጨለማን ተገን አድርገው ወደ ድርጅቱ ሰራተኞች መኖሪያ ካምፕ የገቡት የአገዛዙ ወታደሮች ከፈፀሙት የዝርፊያ ወንጀል በተጨማሪ በርካታ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች መፈፀማቸው ተረጋግጧል።

ለመሆኑ ይሕ አለም አቀፍ ድርጅት እንደ ኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ደረጃ በያዘው ግዙፉ የለሚ አለም አቀፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ የተፈፀመውን አስነዋሪ ወንጀል የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር በፅኑ እያወገዘ በጉዳዩ ላይ ወንጀሉ ከተፈፀመ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሰራው ልዩ የማጣራት ስራ የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል መረጃው ለህዝባችንም ሆነ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይደርስ ዘንድ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

ስለጉዳዩ በቂ መረጃ ያላቸው ስማቸው እንዳይገፅ የጠየቁን አምስት (5) የድርጅቱ ሰራተኞች በአገዛዙ ወታደሮች ስለተፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት አስረድተዋል። "ድርጊቱ የተፈፀመው ዕለቱ ረቡዕ ሲሆን ነሐሴ 28 ቀን 2017ዓ.ም ከለሊቱ 7:00 እስከ 9:00 ድረስ መሆኑን በመግለፅ ይጀምራሉ። ቀጥለውም አብዛኛው ሰራተኛ ቀኑን ሙሉ በስራላይ ስለሚያሳልፍ  እስከ ምሽት 5:00 - 6:00 ድረስ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን Wi Fi በመጠቀም አለም እንዴት ዋለች የሚል መረጃ ሲከታተል ይቆይና ከለሊቱ 6:00 ይተኛል ይለናል። ታዳ ይሕን የሰራተኛውን ሁለገብ እንቅስቃሴ በሚገባ የሚያውቀው ወንጀለኛ የማፊያ ስብስብ ቀኑን ሙሉ ሲደክም የዋለ የድርጅቱ ሰራተኞች በተኙበት ከለሊቱ 7:00 ላይ የመኖሪያ ካምፕ ጥበቃዎች በመደብደብ ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት በማድረስ ወደ ውስጥ ገቡ ይላል። የድርጅቱን ጥበቃዎች ደብድበው ወደ ውስጥ እየገቡ ባለበት ወቅት "እኔ ፋኖ ነኝ!፣ እኔ የባዩ ፋኖ ነኝ!፣ እንጨርሳችኋለን!፣ እናጠፋችኋለን!" የሚሉ ድምፆች ከፍ ብለው እየተሰሙ ወደ ውስጥ ዘልቀው በመግባት እያንዳንዱን የሰራተኛ ማረፊያ ቤት እየዞሩ በሩን በማንኳኳት እንዲከፍቱ አዘዙ፣ "በፍጥነት በሩን ካልከፈታችሁት ግን ገንጥለነው እንገባለን!" በሚል አስጠነቀቁን።

ከዛ የተኛው የድርጅቱ ሰራተኛ በፍጥነት ደንግጠን ተነሳን፣ በመጀመሪያ ደረጃ የአስተርጓሚውን ክፍል በመጠየቅ የውጭ ሀገር ቋንቋ አስተርጓሚ ወደሆነው ግለሰብ ቤት ሔዱ። ከዛ መልስ የውጭ ሀገር ዜጎች ቤት ገቡ፣ በመጨረሻም በሁሉም የሰራተኛ ቤት በየተራ እስከ ለሊቱ 9:00 ድረስ ለተከታታይ ሁለት (2) ሰዓታት በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ ዘግናኝ ወንጀል ፈፀሙ ይላሉ የመረጃ ምንጮች።

በመቀጠልም የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በድርጊቱ ለተጎዱ ግለሰቦች አንድ ጥያቄ ያነሳል ፣ወንጀለኞቹ የፈፀሙት ተግባር በዝርዝር እንዲያስረዱት ጠይቋል።የአይን እማኞቹም በድርጊቱ ክፉኛ በማዘን እንዲህ በማለት በምሬት ያስታውሳሉ " በድብደባ ብዛት አካላቸው የጎደለ የድርጅቱ ሰራተኞች አሉ፣ የውጭ ሀገር ዜጎችን በመደብደብ ከፍተኛ ገንዘብ ተዘርፈዋል፣ በርካታ ሴት የድርጅቱ ሰራተኞች በለሊት ተደፍረዋል፣ ከ 48 ስልክ በላይ ተወስዷል፣ በአጠቃላይ ለሊት በተኛንበት በተፈፀመብን ግፍ ለተከታታይ ሁለት ሰዓታት በግቢው ውስጥ ጩኸት እና ዋይታ ብናሰማም እዛው ለሚ ከተማ ውስጥ የነበረው መከላከያ ሊታደገን አልቻለም በማለት ተናግረዋል።

አዳሩን ስለተፈፀመው ጉዳይ ከፍተኛ መነጋገሪያ በመሆኑ ከንጋት ጀምረው ሙሉ የድርጅቱ ሰራተኞች ተቋሙን ለቀው በመውጣታቸው በዕለተ ሀሙስ ሰኔ 29 ቀን 2017ዓ.ም የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ለሚ ከተማ በመምጣት አዳሩን ስለተፈፀመው ወንጀል አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ እንድናብራራ ተጠየቅን ይላሉ ተበዳዮች።

ገና ስብሰባው እንደጀመረ እዛው ለሚ ከተማ የተቀመጠውን መከላከያ የሚመራ አንድ ኮለኔል "እንዲሕ ያደረጋችሁ ፅንፈኛው ነው" በማለት ይጀምራል ፣ ከዛ ሙሉ ሰራተኛው "በማጉረምረሙ" ንግግሩን ያቆማል። ወዲያውኑ አንድ ከአዲስ አበባ ከተማ የመጣ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር "ስለሁኔታው ሁላችንም በጣም አዝነናል! መረጃውን እዛም ሆነን ሰምተናል፤ ነገር ግን እዝሕ ድረስ የመጣነው ስለድርጊቱ ከእናንተው ከተበዳዮች አንደበት በቀጥታ ለመስማት ነውና የመጣሁት ያለምንም ፍርሀት ንገሩኝ ይላል።

በመጀመሪያ "የእውነት እዝሕ የመጡት ፋኖ ናቸውን? ብሎ ጠየቀን ፣ብዙ ሰው በተናጠል ሀሳቡን ገለፀ ፣ ፋኖዎችን እናውቃቸዋለን አዳራቸውን የመጡት ግን በፍፁም ፋኖ አይደሉም! ፋኖ እኮ አንድም ቀን ቀና ብሎ እንኳን አይቶን አያውቅም ብለን የመለስንለት ሲሆን በምላሻችንም የመከላከያ አመራሮች ክፉኛ ተበሳጭተው ነበር ይላሉ ታዳሚዎቹ።

በመቀጠልም በዘራፊዎች አጠቃላይ ስለተፈፀመው ወንጀል እና የተወሰዱ ቁሳቁሶችን አሃዛዊ መረጃ ከተበዳዮች ተቀብለው ወደ አዲስ አበበ ከተማ ሲመለሱ የመከላከያ አመራሮች "በአስቸኳይ ወደ ስራ መመለስ እንዳለብን ሲያስፈራለን እንደ ምክነያት ያነሱት ደግሞ የመከላከያን ስም እንዲጠፋ እየተባበራችሁ ነው ሲሉ በአስገዳጅ ሁኔታ ድርጅቱን ለቀን በለሚ ከተማ ውስጥ ከሰፈርንበት ቦታ ምንም የደሕንነት ዋስትና በለለበት እንድንመለስ ተገደናል ሲሉ መረጃውን አድርሰውናል።

በመሆኑም ይሕን ሁሉ አስነዋሪ ድርጊት በለሚ አለም አቀፍ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች ላይ ጨለማን ተገን አድርገው የፈፀሙት የአገዛዙ ወታደሮች መሆናቸውን የተረጋገጠ ሲሆን፣ የአገዛዙ ዱክማን ካድሬዎች የፋኖን ስም ለማጥፋት የሔዱበት ቀሽም ድራማ በመጋለጡ አገዛዙ በራሱ ጅራፍ እንደተገረፈ የአይን እማኞች ለአፄ አምደ ጽዮን ኮር ተናግረዋል።

በመጨረሻም ይሕን አይነቱን አስነዋሪ ወንጀል የተፈፀመው የሀገር ጠባቂ ነኝ በሚለው እራሱን "የሀገር መከላከያ ሰራዊት" መሆኑ  ድርጊቱን እጅግ አስገራሚ ያደርገዋል፣ በመሆኑም እንደ ተቋም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ግቡን ላልመታ ለርካሽ ፖለቲካ አላማ ሲባል በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ የተፈፀመውን ወንጀል እያወገዘ ወንጀሉ በተፈፀመበት አካባቢ ሰራዊታችን ምንም አይነት ስምሪት እንዳልተሰጠው እና በአካባቢውም እንደሌለ እየገለፅን የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በወንጀለኞች ላይ ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን እንጠይቃለን።

   01/13/2017ዓ.ም
4
በእስር ላይ የሚገኙት ሁለት የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ሲፒጄ ጠየቀ

የዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) የሸገር ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ባልደረባዎች የሆኑት ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው እና አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ ጠየቀ።

የሸገር ኤፍኤም የስራ ባልደረቦች ለሲፒጄ  እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጣቢያው የጤና ባለሙያዎችን አስመልክቶ የተላለፈን ዘገባ ተከትሎ ጣቢያውን “ሁከት በማነሳሳት እና በአድሏዊነት” ወንጅሎ ደብዳቤ ልኳል። ዘገባውም ከሸገር ኤፍኤም የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እንዲወገድ የተደረገ ሲሆን ሲፒጄ ዘገባው ከጣቢያው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ መወገዱን አረጋግጫለሁ ሲል ትናንት ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ “የኢትዮጵያ ህዝብ በጤና ዙሪያ የሚቀርቡ ገለልተኛ ዘገባዎችን ማግኘቱ ወሳኝ ነው” ያሉ ሲሆን አክለውም “ባለሥልጣናት በዚህ ጉዳይ ላይ በሳንሱር እና በቁጥጥር ምላሽ መስጠታቸው እጅግ አሳሳቢ ነው”
3👍1
ኑሯአቸዉን በሸራ ለአራት አመታት የገፉ ተፈናቃይ ወገኖቻችን በአገዛዙ ጥምር ጦር ሀይል የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፅሞባቻዋል ተባለ።

በሰሜን ወሎ ዞን ተወልደሬ ወረዳ ጃራ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ወገኖቻችን ከሚደርስባቸዉ እርሀብ በተጨማሪ በአገዛዙ ሰራዊት በኩል የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል።

ለአራት አመታት በርካታ ግፎችን እና መከራዎችን እያሳለፉ የሚገኙት ተፈናቃይ ወገኖች ከሚደርስባቸዉ የርሀብ እና ሌሎች ችግሮች ባሻገር አገዛዙ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ጭምር መፈፀሙ የሚታወስ ነዉ።ዛሬ ላይ ደግሞ የአገዛዙ ጥምር ጦር  የጃራ መጠለያ ካምፕ በሚገኙ ተፈናቃይ ሴት እህቶቻችን ላይ ከባድ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።ከዚህ በፊት በዚህ መጠለያ ካምፕ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህፃናት፣እናቶች፣አዛዉንቶች እኔዲሁም የከባድ በሽታ ተጠቂዎች በርሀብ አደጋ ለሞት ሲጋለጡ ከሞት የተረፉ ወጣቶችን ደግሞ አገዛዙ አፍሶ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ወስዷቸዋል ተብሏል።

አገዛዙ ብልፅግና በእነዚህ ዜጎች ላይ የሚፈፅመዉ ግፍ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ በሰራዊቱ በኩል እንዲፈፀም ያደረገዉ አሰቃቂ ተግባር የአገዛዙ አመኔነት በግልፅ ያሳየ ነዉም ተብሏል።ይህ ፀረ አማራ ህዝብ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት፣ግፍ እና መከራ ተጠናክሮም ቀጥሏል።አሁን ላይ እነዚህ በሸራ መጠለያ ተጠልለው መከራን እያሳለፉ የሚገኙ ወገኖች የሚሰማቸዉ አተዉ ኑሮአቸውን በመከራ እያሳለፉ ቀጥለዋል።ድምፅ የተነፈጋቸዉ ወገኖቻችን በወሎ፣በሸዋ፣ቨጎጃም እና በጎንደር በርሀብ አደጋ ህይወታቸዉ ሲቀጠፍ ከእነዚህ ተለይተዉ የቀሩት የአማራ ብሄር ተዎላጆች ደግሞ ከሰሞኑ እኔዳዲስ የጀምላ ግድያ ተፈፅሞባቸዋል።ከዛሬ አራት አመት በፊት ከሞት አምልጠዉ ወደ አማራ ክልል የገቡት እነዚህ መከራን እያስተናገዱ ያሉ ወገኖቻችን ድምፅ ተነፍጓቸዉ በከፍተኛ ችግር ዉስጥ ይገኛሉ።ቀሪዎቹ ወገኖቻችን ደግሞ በዛዉ በሲዉል ምድሩ ኦሮሚያ አርሲ፣ሆሮጉድሩ ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ሞትን በፀጋ እየተቀበሉ ቀጥለዋል።

ከሰሞኑ የመካከለኛ እና የከፍተኛ አመራር ስብሰባ በማድረግ የህዝብ ችግር እፈታለሁ ያለዉ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት ብአዴን ከስቀመጣቸዉ የቃል ኪዳን አምስት ነጥቦች ዉስጥ የተፈናቃይ ወገኖቻችን ጉዳይ እንኳን አለማንካቱ ብአዴን በአድር ባይነት ህዝብን እየሸጠ መሆኑን የተመላከተ ነዉ ተብሏል።
4💔1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጉና ክፍለ ጦር/መቅደላ አምባ ብርጌድ/ናደው ሻለቃ
ጳጉሜ 01/2017ዓ.ም

የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት መነሻውን ደብረ ታቦር ከተማ አድርጎ ወደ እሥቴዋ መዳረሻ መካነ ኢየሡሥ ከተማ እየተንቀሳቀሰ እያለ ''አቄቶ'' የተባለ ቦታ ላይ ጥበበኛው የጥበብ ልጅ የታላቁ ጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነው መቅደላ አምባ ብርጌድ/ናደው ሻለቃ በፈጸመችው የታቀደ የደፈጣ ውጊያ በጠላት ላይ ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅታለች። በዚህ የደፈጣ ውጊያ በቁጥር 13 ሢደመሠሥ 07 የሚሆኑት ቁሥለኛ ሆነዋል። ከተደመሰሱት የጠላት አካላት መሐከል አገዛዙን ምሕረት ጠይቀናል ብለው ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተሐድሶ ወሥደው ከጎንደር-ደብረ ታቦር-እሥቴ ሢመለሡ ነው።

ድላችን በተባበረ ክንዳችን👊
ዝንተዓለም ዐምሐራ Forever Amhara
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
🙏41
🔥‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር በባንዳ የፖሊስ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ‼️
‎===============
‎የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር የአስራት ወ/የስ ብርጌድ ቃኝ የሰራዊት አባላት ባደረጉት ልዩ የደፈጣ ጥቃት የብልጽግና ወንበር አስጠባቂ አመራሮች ተሸኝተዋል።

‎የአስራት ወ/የስ ብርጌድ  በኤፍራታና ግድም ወረዳ በቆሪ ሜዳ ቀበሌ ቀርሳ በተባለ ልዩ ቦታ ባደረገችው ደፈጣ ከኦሮሞ ልዩ ዞን ከሚሴ በተነሳ አንድ ፓትሮል የፖሊስ መኪና ላይ በወሰደችው እርምጃ ሦስት አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸው እስከወዳኛው ተሸኝተዋል።

‎የብርጌዱ ቃኚ እርምጃውን የወሰደችው ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጨፋ ሮቢት ተነስተው ወደ አጣዬ ከተማ እየሄዱ ባሉ የባንዳ ስብስብ ላይ ነው።

‎በዚህም እርምጃ የአፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር አስራት ወ/የስ ብርጌድ ቃኝ የፋኖ አባላት በወሰዱት ደፈጣ አንድ ፓትሮል ከጥቅም ውጭ ሲሆን ሦስት አመራሮች እና አምስት አጃቢዎች ወደ ማይቀረው አለም ተልከዋል።
‎  መረጃውን ያደረሰን የክ/ጦሩ ሪፖርተር ነው።
               ‎ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
©አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
      
🙏42
ለንደን ፋኖ እናመስግናለን!!!
2🙏1
🔥የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን ለመደገፍ‼️

👉Zelle = 202 528 6749
👉E transfer (Canada)
708 802 5536

በዌብሳይት https://amharafanonationalforce.org/
🙏2
የወጣቶች አፈሳ በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

በክልሉ ዕርሰ መዲና ባህርዳር ፣በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ፣በማርቆስ፣በፍኖተ ሰላም፣በደብረታቦር፣በኮምቦልቻ፣ደሴ፣ወልደያ፣ደብረብርሀን እና በሁሉም የወረዳ ከተሞች እንዲሁም ከመጠለያ ካምፖች ጭምር በርካታ ወጣቶች ታፍሰዉ በሁሉም ፖሊስ ጣቢዎች ታጉረዉ ይገኛሉ።

መረጃዉን በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል!!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2
አፋብሃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ መይሰውካሳ ሁለተኛ ኮር ካራማራ ክ/ጦር ምክትልህ/ግንኙነት ሃላፊ አንተነህ መክብብ ነኝ
አጠር ያለ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ያክል ነው በተለይ ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ሁሉ ማሃበረሰባችን የብር ኖቶችን በጥንቃቄ ሊያውቅ ይገባል ምክንያቱም ሰሞኑን የካራማራ ክፍለጦር መረጃዎች በርካታ ገንዘብ ከ145000 ብር በላይ ፎርጅድ የሁለት መቶ ብር መያዛቸውንና ወንጀለኞችንም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋና አዛዡ አርበኛ ባበይ አምባየ ገልጿል አያይዞም ማህበረሰቡ እንዲጠነቀቅ መልክቱን አስተላልፏል።
ሌላው ከሰሞኑ አሁንም ፋኖ ከተቆጣጠራቸው ቦታዎች በሙሉ ህገወጥ የህክምና ቤቶች መበራከታቸውን ተከትሎ በካራማራ ክ/ጦር የህክምና ቡድን የተመራ ሃይል በለንብረቶችን ሰብስቦካወያየ በኋላ ያላሟሉ ክሊኒኮችንና መዳኒት ቤቶችን በማሸግ አሟልተውና የህክምና ስርአቱን ተከትለው እንዲሰሩ ማስተማሪያ እርምጃዎች ተወከስደዋል
አመሰግናለሁ
👍51
◊◊ የአደረጃጀት ዜና
የአማራ ህዝብ ትግል ዘመን ተሻጋሪ ሁነቶችን እያለፈ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሷል። በእነዚህ ዘመን ተሻጋሪና ተቀያያሪ ሁነቶች ውስጥ የትግሉ እድገትና እመርታ የሚጠቀስ ነው። ሆኖም በዚህ የትግል እድገት ውስጥ የሰው ሃይል፣ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ ፣ ዲኘሎማሲያዊ ብሎም ወታደራዊ አደረጃጀት ቅርጽና ወጥ የሆነ የአሰራር መርሆዎች ተዘርግተውለት ወደ ተሻለ የትግል ምዕራፍ መሸጋገር ላይ እንገኛለን። በዚህም የተነሳ ትግላችን ባሳየው ለውጥና እድገት እንዲሁም በርቀት የምንመለከተውን ትልቁን የአላማችንን ስእል ለማሳካት የአመራር ድልድል / Reform አስፈላጊ ሆኖ ተገንቷል።
በመሆኑም ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር አብራክ የሚጠቀሰው ንስር በለሳ ቅጣው ክ/ጦር የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የክ/ጦሩ አባላት በሙሉ በተገኙበት የአመራር ድልድሉ ተሰርቷል።

1/ ዋና ሰብሳቢ _____ አርበኛ ባንተ ዘለቀ
2/ ም/ሰብሳቢ_____አርበኛ አብራራው ፀጋየ
3/ ወታደራዊ አዛዥ___አርበኛ ይዘዝ ፍቃዴ
4/ ም/ወታደራዊ አዛዥ__አርበኛ ሙሉቀን ዮሃንስ
5/ ዘመቻ ዘርፍ ኃላፊ___አርበኛ አድኖ አስማረ
6/ ም/ዘመቻ ዘርፍ ኃላፊ _አርበኛ ታድሎ ባብየ
7/ ጽ/ቤት ኃላፊ ___አርበኛ ባምላኩ ምህረት
8/ ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ___ አርበኛ ጣማለው ወልዴ
9/ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ_አርበኛ መልከ ጸዴቅ
10/ ፋይናስ ኃላፊ__አርበኛ ቢክስ ተዘራ
11/ ሎጅስቲክ ኃላፊ _____አርበኛ ደሞዝ ማሞ
12/ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ __አርበኛ ማስረሻ አለምነው
13/ ህ/አስተዳደር ኃላፊ _____አርበኛ ሻ/ ኤርሚያስ
14/ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ____አርበኛ አዛናው አሻግሬ
15/ ት/ትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ __አርበኛ ሰፊ መብራት
16/ ህግና ስነምግባር ኃላፊ _አርበኛ አቤሴሎም ተበጀ
17/ መረጃና ደንነት ኃላፊ _+_+**
በስተ መጨረሻም የተመረጡ የክ/ጦሩ አመራሮች ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን የኮሩ የስራ አስፈፃሚ አባላትም መልእክት በማስተላለፍ የእለቱ ኘሮግራም ተቋጭቷል።

➤አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግ/ቴዎ/፭ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ➤አብነት ሞላ
ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም
🙏2