ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአገዛዙ ብልዕግና የጋዜጠኞች አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ ሁለት  ጋዜጠኞች  ታስረዋል።

የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ ሁለት ጋዜጠኞች ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓም ከተላለፈ ዜና ጋር በተያያዘ ትናንት ነሐሴ 28 ቀን 2017ዓም  ተጠርጥረዉ መታሰራቸው ታወቀ።

በተላለፈው ዘገባ ተጠርጥረው የታሰሩት በእለቱ ተረኛ የነበሩት ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ጸጋው ሲሆኑ፣ ታስረው የሚገኙትም በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጣቢያ መሆኑ ታውቋል።የተጠረጠሩበት ዘገባ  ስለ ጤና ባለሙያወች የተሠራ ዜና ከመሆኑ ውጭ ዝርዝር መረጃውን ለማወቅ አልተቻለም።
👍1
በ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ከዘመቻ ሰማዕታት ጎን ለጎን የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ኃይል እየፈራረሰ ይገኛል፡፡

1.ጌታቸው ካሲ ይባላል የሸበል ተወላጅ የዱሀ ከተማ ተጠርንፎ አገዛዙን በማገልገል የቆየ ቢሆንም የአረመኔው አገዛዝ በመክዳት ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድን ከእነሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል።

2. ጀማል ኤብሮሺ የፍቸ ሰላሌ ተወላጃ የአረመኔው አገዛዝ ስራዊት አባል ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም አ.ፍ.ብ.ሃ .ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ተቀላቅሏል።

ከዘመቻ ሰማዕታት ጉን ለጎን ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም  የአ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ 4ኛ ሻለቃ የቀብኃና ቀጠና የሆላ ደጀን  ከፋኖው ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ጥልቅ ወይይት በማድረግ የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ አሰቀምጦል።በውይይቱም የ4ኛ ሻለቃ የሆላ ደጀን ሰብሳቢ ም/ል ሰብሳቢ እና ቁጥጥር በተገኙበት ውይይቱን በማድረግ በየቀበሃና ቀበሌ የሆላ ደጀን ሰብሳቢ እና ም/ል ሰብሳቢ በመምርጥ ውይይቱ በሰላም ሲጠናቀቅ፡፡

ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም አ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህግ እና ስነ-ስርዓት ጉባኤ ክፍል ደባይ ጮቄ ብርጌድ ስር በሚገኙ የናብራ 4ኛ ሻለቃና የመቶ አለቃ አደነ ጤነው 3ኛ ሻለቃ የሚያሰተዳድሯቸውን ቀበሌዎች የቀበሌ ጊዜአዊ አሰተዳደሮች የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ሸንጎ አካላት እንዲሁም የብርጌዱ አመራሮች በተገኙበት ስለ ፍትህ አሰጣጥ ስልጠና ተሰጥቷል።

        ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም

   ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
አ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጣና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
2
ከወለጋ ክፍለ ሀገር ቢዛሞ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!!!!
2🙏1
ስብሰባው ተጠናቋል !!

በርካታ መኮንኖች እና ጀኔራሎች የተገኙበት ስብሰባ ተጠናቋል ። በስብሰባው አብይ ብሔራዊ ጉዳይ ያላቸውን የጦር ድግሶች አንድ ሁለት ብሎ ዘረዘረ ።

በመሐል የፋኖ ጉዳይ ምን ይደረግ ? ብለን ጠይቀን ነበር ።
መልሱም :- ፋኖ ያለው እዚህ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው ። እንዲያውም ጨካኙ ፋኖ ያለው እዚህ ውስጥ ነው ብሎ አይኑን ወደሆኑ ሰዎች አፈጠጠ ።

ቴክኖሎጂ ታጥቀናል በማለት ደብረብርሃን እና አዋሽ አካባቢ ያከማቿቸውን ዝንቦች እና ስልታዊ ማፈግፈግ የሚያደርጉ ታንኮችን እንዲሁም የአጭር ርቀት ሚሳኤሎችን በስክሪን አሳይቶናል ።

እሱም እኔ ብቻየን ቀርቻለሁ ፍረዱኝ እናንተ መኮንኖች በማለት መከላከያ ሰራዊቱ ከላይ እስከታች መደማመጥ ፣ መናበብ እንዳልቻለ እና የፈራረሰ ተቋም መሆኑን ሳይሸሽግ ሳይደብቅ ተናገረ ።

በአንድ በኩል ልሞት እችላለሁ በሌላ በኩል እናሸንፋለን የሚል ከራሱ ጋር የተጣላ ሐሳብ ተናገረ ።

በአጠቃላይ በስብሰባው በሚዲያ የማይወጡ በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል ።

አስገራሚው እና በአንደበቱ የተናገረው ነገር :- ከግማሽ በላይ የሚሆነው ጀኔራል እና ሚኒስቴር ለፋኖ በሚሰራበት በዚህ ጊዜ ከጎኔ ቁሙ በማለት መድረክ ላይ አለቀሰ ።

ድጋሜ ሌላ የጦር አዋጅ አውጆ ዛሬ 4:30 ላይ ስብሰባው ተጠናቋል ።

ደሞኮ ፅንፈኛው ምናምን አላለም ። ፋኖ ነው እያለ ነው ሲያወራ የነበረው።
©ፋኖ ማርሸት ፀሐይ
🙏5
~ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የትግሉን አጠቃላይ ገጽታ የተመለከተ ሲምፖዚየም አዘጋጅቷል።

በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልወና አደጋ ለመመከት ላለፉት ሁለት ዓመታት ታላቅ ተጋድሎ እየተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በተበታተነ ሁኔታ የሚደረገውን ተጋድሎ ወጥ በሆነ ድርጅታዊ መዋቅር ስር ለማድረግ በተጀመረው ጥረት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የተወለደና ትግሉን በተሻለ ቁመና እየመራ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል። በጥቂት ታጋዮች ከኋላ ቀር መሳሪያ የተነሳው የአማራ ፋኖ ትግል በሁለት ዓመት ውስጥ ያስመዘገበው ድልና የገነባው ግዙፍ ወታደራዊ ሃይል የተጀመረውን የህልውና አደጋ ለመመከት በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ አድርጎታል። ምንም እንኳን ትግሉ ከሚፈልገው አቅምና ብቃት እንዲሁም የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው መከራና ስቃይ አንጻር የምንገኝበት ምዕራፍ ገና ብዙ እንደሚቀረን የሚያሳይ ቢሆንም በቁርጥኝነትና በተባበረ ሃይል ከቀጠልን በቅርብ ጊዜ የአገዛዙን የጭቆና ቀንበር በጣጥሰን እንደምንጥል ጥርጣሬ የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም።

ለዚህም የተጀመረውን የአንድነት ጉዞ ማፋጠንና ወደኋላ የማንመለስበት የፋኖ ወጥ መዋቅር ለመገንባት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረግን እንገኛለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለዚህ የአንድነት ጉዞ የሚረዳና የተጋረጡብንን ችግሮች በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ታላቅ ሲምፖዚየም ማዘጋጀቱን ሲገልጽ በደስታ ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ከዚህ አቅሙ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆንና የትግሉ ጊዜ ባጠረ መልኩ ለመቋጨት ያስችል ዘንድ እና ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ሂደትና ዓላማ ግልፅ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅ እና በጎ ፈቃደኛ ደጋፊዎችን ለመጨመር ያለመውን ይህን ሲምፖዚየም ጷጉሜ 01 እና 02 ቀን 2017 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ አቆጣጠር September 06,2025 Saturday Starting 12 Noon and September 07,2025 Sunday Starting 12 Noon በቀጥታ ስርጭት የሚያካሂድ መሆኑን ያስታውቃል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አመራሮች በጋዜጠኞች ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል፣ ዝግጅቱም በቴሌቪዥንና በዩቲዩብ፣ ቲክቶክ እና የX (Twitter ) ማህበራዊ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

በዚህ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ሲምፖዚየም ተሳታፊ በመሆን የአማራ ህዝብ የታወጀበትን እልቂት ለመመከት እየታገለ ያለውን የአማራ ፋኖ በመደገፍ፣ ከአማራም አልፎ በየተራ ሁሉንም ብሄሮች በማጥቃት የጭቆናና የባርነት ስርዓቱን ለማስቀጠል እየሰራ ያለውን "ብልፅግና" የተሰኘውን ጸረ ሕዝብ አገዛዝ እንድንታገልና ሀገርን ከመፍረስ እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል - አፋብኃ
🙏4
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

አደም አሊ ክፍለጦር መክት ብርጌድ ቦረና ገነቴ ከተማ አቅራቢያ ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ ድል ተጎናፀፉ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር ሳጅን አደም አሊ ክፍለጦር መክት ብርጌድ ቦረና ገነቴ ከተማ አቅራቢያ አገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ጥምር ጦር ጋር በመፋለም ከአንድ ጓድ በላይ በመደምሰስና በተመሳሳይ ቁጥር በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ተጋድሎው ነሃሴ 29/2017 ዓ.ም ጧት 2:00-8:00 የተደረገ ሲሆን ለስድስት ሰዓት ከተደረገው ፍልሚያ በኋላ ጠላት ሬሳና ቁስለኛውን ታቅፎ ገነቴ ከተማ ገብቷል:: የአባ ናደው አርበኛ ሳጂን አደም አሊ ልጆችም ምሽጉን ለቆ ማጥቃት የመጣን ጠላት በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ሙትና ቁስለኛውን በማስታቀፍ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ነሃሴ 30/2017 ዓ.ም
🙏4
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም


1.ነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር
ወጂ ከተማ
ነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር የተጠኑና የታቀዱ ውጤታማ ውጊያዎችን አድርጓል። ወጂ ከተማ ላይ ውጊያ ለመፈጸም አለም በር መውጫና ወረታ መውጫዎችን ቀድሞ በመዝጋት ጠላት አጋዥ ኃይል እንዳያገኝ በማቀድ ''ወጂ አርባ አምባ'' ላይ መሽጎ የነበረውን የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በደምብ ገርፎታል። የጠላት ምሽግ ከባድና የቁም ምሽግ ሥለነበር ከቡድን መሣሪያ እሥከ ጨበጣ ድረሥ ውጊያ ተደርጎበታል። ጥበበኞቹ የጥበብ ልጆች የጠላትን 03 ምሽጎች በRPG-7 መሣሪያ አፈራርሰዋቸዋል። ከድምሠሣ የተረፉት የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ቅጥረኞች እግሬ አውጭኝ ሢሉ ተበታትነዋል። ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎችም፦ ወጂ፣ አጓት ውኋ፣ አረጋዊ፣ ውኃ ልማት፣ አውራምባ መገንጠያ፣ ወምበር ተራራና ጋዞ ናቸው። በዚህ አውደ ውጊያ ወጂ ከተማን ሙሉ በሙሉ የአማራ ፋኖዎች ሊቆጣጠሩት ችለዋል።

በዚህ አውደ ውጊያ ከ20+ በላይ የጠላት ኃይል ሢደመሠሥ ቁጥሩ ያልታወቀ ቁሥለኛ መኖሩ ሢረጋገጥ የአድማ ብተና ዘመቻ ኃላፊውም መሠዋቱ ተረጋግጧል። በዚህ ሠዓት ወረታ ሆሥፒታል ንጹሐን ታማሚዎች መግባት እንዳይችሉ ተደርጓል።

በውጊያው ከፍተኛ ውርደትን የተከናነበው የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በብሥጭትና በበቀል ንጹሐንን ወጂ ከተማ ላይ ከቤታቸው አውጥቶ ረሽኗቸዋል። ከተረሸኑት ንጹሐን መሐከል ቄሥ ገብረ ማርያም ይገኝበታል። እንስሶችም ሕዝብ እያዬ በጥይት ተመትተዋል።


አለም በር
ነጻነታቸውን በደማቸው እየጻፉ ያሉት የነበልባሉ ፎገራ አብራኮች የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ለሆድ ዘመዱ አራዊት ሠራዊት ወጂ ከተማ እንዳይደርሥ ለማድረግ አለም በር ከተማ በመግባት ውጊያ ከፍተውበታል። በዚህ ውጊያ ተበታትኖ የነበረው የጠላት ኃይል ወደ አንድ ተሰባስቦ ወደ ቀድሞው አማራ ልዩ ኃይል ካምፕ ሊመሽግ ችሏል። በአለም በር ከተማ፣ በአሥራት ተራራ፣ ማደያ፣ ሥንኳ፣ ቁሥቋም እና ሌሎች መዳረሻዎች ላይ ውጊያ ተደርጓል። በዚህ ውጊያ 07 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ወደ 13 የሚሆኑት ቁሥለኛ ሆነዋል።

02ኛ ዙር ከወርቅ ሜዳ እሥከ አጓት ውኋ እና አሸዋ መገንጠያ የተደረገ ውጊያ
የአገዛዙ ኮንዶምና የብአዴን ተከፋይ የሆነው ፀዳሉ ደሤና የአገዛዙ ቅጥረኛ ከጎንደር ወደ ደብረ ታቦር እየተንቀሣቀሠ እያለ ብርቱ ፍልሚያ ከአማራ ፋኖዎች ከቀኑ 09:00 ላይ ገጥሞታል። የነበልባሉ ክፍለ ጦር አካል የሆነው አሣምነው ብርጌድ/ንሥር ሻለቃ እና የክፍለ ጦሩ ቃኝና መሐንዲሥ የአገዛዙን ኮንዶሞችና ቅጥረኞችን አሥጨንቀው ገርፈዋቸዋል። በዚህ ውጊያ ባንዳነት መለያቸው፣ ክህደት ግብራቸው፣ ተላላኪነት መገለጫቸው፣ ብአዴናዊነት ሕይወታቸው የሆኑት እነ ፀዳሉ ደሤ በሐሰት መንገድ ሥለቆሙ የአማራ ፋኖን መቋቋም አልቻሉም። በዚህ ውጊያም ፀዳሉን አጅበው ሲጓዙ የነበሩ የጠላት ቅጥረኞች ሢደመሠሡ ቁጥራቸው ያልታወቀ ቁሥለኞች መኖራቸው ተረጋግጧል።


2. ጉና ክፍለ ጦር/ገብረ መሥቀል ብርጌድ
የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ከአለም በር እሥከ ወጂ ከተማ በጥበበኛው የጥበብ ልጅ የአማራ ፋኖ መገረፍን ተከትሎ ለሆድ ዘመዱ ድጋፍ ለመሥጠት በማቀድ መነሻውን ደብረ ታቦር ከተማ ያደረገው የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በሜካናይዝድና 05 ፓትሮል፣ 06 ካሶኒ የተጫነ እና በእግረኛ ወደ አለም ሣጋ በሌሊት እንቅሥቃሤ ጀምሯል። መረጃው ቀድሞ የደረሳቸው የአማራ ፋኖዎች በተጠና ተልዕኮ አለም ሣጋ ጫካ ''አረሙ'' የተባለ ቦታ ላይ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እሥከ ረፋድ በወሰዱት ርምጃ ጠላት ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን ተከናንቧል።
የገብረ መሥቀል ብርጌድ የጦር መሐንዲሶች በሌሊቱ ዕንቁ ድልን ሲጎናጸፉ በጠላት ላይ ቁሳዊ፣ አካላዊና ሞራላዊ ኪሣራን አድርሰውባቸዋል። 15 የጠላት ጥምር ኃይል ሢደመሠሥ 20 የሚሆኑት ደግሞ ቁሥለኛ ሆነዋል።


ድላችን በተባበረ ክንዳችን👊
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ
ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
🙏5
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ነሐሴ 30/2017ዓ.ም

12 የአገዛዙ አድማ ብተናና ሚሊሻ ሲደመሰሱ አራቱ ተማረኩ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለጦር እና አንሻ ሰይድ ብርጌድ በጥምረት በመቄት ወረዳ ፍላቂትና ገረገራ ከተማ አስተዳደር ባደረጉት የተጠና ኦፕሬሽን በጠላት ላይ ሰብዓዊ ና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዋል።

ነሐሴ 29/12/2017 ከቀኑ 8:30 እስከ ምሽት 3:00 በተደረገ አውደ ውጊያ 12 የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ማኒሻ እና አድማ ብተና ሲደመሰሱ 22 መቁሰላቸውን እንዲሁም አራት መማረካቸውን ከግንባር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ነሐሴ 30 / 2017 ዓ.ም
4🙏3
ከአማራ ማሕበር በሰሜን አሜሪካ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
🙏2
ከዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን)
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የአንድነት ስምምነት ላይ በመድረሱ የተሰጠ የደስታ መግለጫ።

የአፋብኃ ነሀሴ ፳ ፰ ቀን ፪ሽ፲ ፯ ዓመተምህረት በጽሁፍ አንዲሁም አመራሮቹ ነሀሴ ፳ ፱ ቀን ፪ሽ፲ ፯ በድምጽ የሰጡትን የጋራ መግለጫዎች ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በታላቅ ደስታ በመቀበል ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት ዝጝጁነቱን ያረጋግጣል።

በቋራ ቃል ኪዳን የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ያጋጠሙትን የውስጥ ልዩነቶች በትእግስት አና በጥበብ በመፍታት በአንድነት ለመጓዝ ስምምነት ላይ መድረሱ ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል አሸናፊነት ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ዓለም አቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በጽኑ ያምናል። አፋብኃ ዳግም አንድነታቸውን አድሰው የአማራ ህዝብን ህልውና በአሰተማማኝ እና በቀጣይነት ለማስጠበቅ የጋራ ቃልኪዳናቸውን ጽፈዋል።

በውጪ ለሚኖረው አማራ በአማራ ማህበራት ውስጥ በአባልነት በመሳተፍ፣ ማህበራቱም በአስቸኳይ ዓየንን በመቀላቀል የትግል ዋናኛ ድርሻዎች በሆኑት ፈጣን እና ቀጣይ የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የድምፅ ማሰማትና የውጭውን ማህበረሰብ እና መንግስታት ድጋፍ ለማግኘት በአፋብኃ መንፈስ እና አማራዊ ስሜት ተግተን እንድንስራ ወገናዊ ጥሪችን እያቀረብን፣ በተመሳሳይ አፋብኃን ያልተቀላቀሉ ፋኖዎችም አፋብኃን እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን።

በዚህ አጋጣሚ ለቋራ ቃልኪዳን መታደስ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋና እያቀረብን ከአፋብኃ መሪዎች በቀረበው ጥሪ መሰረት ዓየን የአማራ ተቋማትን ለማሰባሰብና ተቋማቱም ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የበኩላቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ ለማስተባበር የምንችለውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን። ለአማራ ህዝባችን፣ ለፋኖ ሰራዊት፣ ለአማራ እና አጋር የህዝብ መገናኛዎች፣ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እና በተለይም በውጭ ለሚኖረው አማራ በግልፅ ያቀረባችሁትን የትግል ጥሪዎች ተግባራዊነት ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በፍፀም የአማራ ብሄርተኝነት፣ በአላማና በመርህ ላይ ተመርኩዞ፣ ህብረቱን አጠናክሮ፣ አቅሙን አጎልብቶና ተግቶ እንደሚሰራ ዳግም ያረጋግጣል።

ድል ለአፋብኃ!
ድል ለአማራ!
ድል ለኢትዬጵያ!

ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን)
🙏31
በወቅታዊ ጉዳዮች ከአማራ ፋኖ በወለጋ ጽናት ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ከአርበኛ አደም ተፈራ የተሰጠ መግለጫ።

የዘመናዊ አኗኗር ዘይቤ ያስተማረው ታታሪውና ስራ ወዳዱ የአማራ ማህበረሰብ ወለጋ ምድር ላይ  እንደ መጤና ወራሪ ታይቶ መንግስት መር ጭፍጨፋ ከታዎጀበትና መጨፍጨፍ፣መሳድና ንብረቱን መዘረፍ ከጀመረ ድፍን 7አመታትን አስቆጥሯል።ይህ እንዲጠፋ የተፈረደበት ማህበረሰባችን ባለፉት አመታት ከተለያዩ የወለጋ ዞኖች እድል የቀናቸው በአሁኑ ስዓት አማራ ክልል የተለያዩ መጠለያ ጣብያዎች የሚጣልላቸውን ፍርፋሪ እዬቀመሱ የስቃይ ኑሯቸውን እዬገፉ ሲገኙ ይችን እድል ያላገኙ ወገኖቻችን ስጋቸው የዱር አራዊት ቀለብ ሁኖ አጽማቸው በዬጫካው ወድቆ ይገኛል።

ወለጋ  ምድር ላይ ከሞት የተረፍን ነገደ አማራውያን ከፈጣሪ በታች ከዝህ መንግስት መር ጭፍጨፋ ማንም ደርሶ ሊታደገን  እንደማይችል ተረድተን እራሳችንን በማደራጀት መከላከል ከጀመርን አመታቶችን አስቆጥረናል።

ይሁን እንጅ እኛ ከወለጋ ምድር ከነዘር ማንዘራችን ተነቅለን አለመጥፋታችን ያንገበገባቸው ሀይሎች በዬግዜው እራሳቸው ባደራጇቸው ሀይሎች የኦሮሞ ንጹሃን ወገኖቻችንን በመጨፍጨፍ  ጅራፍ እራሷን ገርፋ እራሷ ትጮሃለች እንደሚባለው ብሂል ወለጋ ምድር ሲያሻቸው የመንግስት ፋኖ ደስ ሲላቸው ጽንፈኛው ፋኖ ህዝባችን ጨፈጨፈ በሚል ህዝባችን ላይ የተቀናጀ ጭፍጨፋ ያውጁበታል።

እኛ ብሶት የወለደን የጭቁኑ የወለጋ አማራ ማህጸን ያፈራን የአማራ ፋኖ በወለጋ ህዝባችን ከሁለንተናዊ ጥፋት ለመታደግ የወጣን ከመላው ብሔር ብሔረሰብ ጋር እኩል ሁነን የመኖር መብታችን ተከብሮ እኛም የሌላውን አክብረን እንኑር እንጅ ያልነው ከማንም እንብለጥ አላልንምና መላው ኢትዮጵያውያን እንዲያውቁልን የምንፈልገው ይህ በዬግዜው ወለጋ ምድር ላይ የሚደረገውን የሁለቱንም ብሔሮች ጭፍጨፋ ገለልተኛ አካል ወደ አካባቢው በመግባት አጣርቶ እውነታውን ለህዝብ እንዲያሳውቅልን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ድል የመጥፋት አደጋ ለተደቀነበት ህዝባችን

ጳግሜ 01/2017ዓ.ም
የአማራ ፋኖ በወለጋ
ጽናት ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ
አርበኛ አደም ተፈራ
4🙏2