ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ደብረኤልያስ የቀጋት ቀበሌ እና  የጁቤ የላምጌጅ  ከተማ ላይ ውጊያዎችን ስናደርግ አርፍደናል። በዚህ ጠላት ላይ ከፍተኛ ማጥቃት የተደረገ ሲሆን በርካታ የአረመኔው ሰራዊት አባላትን መደምሰስና ማቁሰል ያስቻለ ውጊያ አድርገናል።

በተመሳሳይ ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ትናንተና ዛሬ በሰራው የከተማ ኦፕሬሽን ሁለት በብልፅግና ደንነት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ የፖሊስ አባላትን አንቆ ማውጣት ችለዋል። በዚህ መሃል  በተፈጠረው ውጊያ በርካታ የመከላከያ አባላትን መደምሰስ ችለዋል።

በየቀኑ ምሽግ ድረስ በሚደረግ ውጊያ እና ሰርጎገብ ጥቃት  የተማረሩ የአረመኔው ሰራዊት አባላትም እጅ እየሰጡ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለትም  ሶስት የአረመኔው ሰራዊት  አባላት ደብረ ማርቆስና ፈንድቃ ከሚገኘው የአረመኔው ካምፕ በመክዳት  አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
1ኛ/ ጌታሁን ፍሬው ተማረ ከስልጠና ቦታ የከዳ ጀሌ
2ኛ/ ዋለልኝ ሞሴ ሳልለው ሰላም አስከባሪ ከነሙሉ ትጥቁ
3ኛ/ ስላተ አሳየ አስቻለ ሰላም አስከባሪ  ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።
🙏5
የደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ በጠላት ላይ ድልን ተጎናጽፏል።

በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ እዝ  የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ 6ኛ ክ/ጦር  የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች ከደብረ ኤልያስ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው  በየቀጋት ቀበሌ  የመሸገውን የአረመኔ ስብስብ በእሳት አለንጋ ሲገርፉት አርፍደዋል።

ውጊያው ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ላይ የተጀመረ ሲሆን ከተኛበት የደረሱት የተኮሷት ጥይት በከንቱ የማትወድቀው በመሳሪያዎቻቸው የሚራቀቁት ቀስተኞቹ በጠላት ምሽጎች እየተረማመዱ የጠላትን ጭንቅላት እያፈራረሱ እዚያው በምሽጉ ይቀብሩት ጀመሩ።

በኋላም ስራቸውን ጨርሰው ከወጡ በኋላም  ጠላት ተከትሎ እንዲወጣ በተጠቀሙት ዘዴ ጠላትን ወደ ጎፍጭማ  ስቦ በማስገባት በብሬንና በስናይፐር ቅንድቡን እየላጩ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

የሙታን ስብስቡ የጠላት ሠራዊትም እስከ ረፋዱ 5:00 ድረስ በየጢሻውና በየገበሬው አዝመራ የወደቀውን አስከሬን ሲለቃቅም አርፍዷል።

በውጊያውም ከ20 በላይ የተደመሰሰ እና 5 አምቡላንስ ከባድና ቀላል ቁስለኛ  የተነሳ ሲሆን ከዚህ መሀል በርካቶቹ ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈር ተልከዋል።

ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር
🙏31
የአገዛዙ ብልዕግና የጋዜጠኞች አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ ሁለት  ጋዜጠኞች  ታስረዋል።

የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ ሁለት ጋዜጠኞች ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓም ከተላለፈ ዜና ጋር በተያያዘ ትናንት ነሐሴ 28 ቀን 2017ዓም  ተጠርጥረዉ መታሰራቸው ታወቀ።

በተላለፈው ዘገባ ተጠርጥረው የታሰሩት በእለቱ ተረኛ የነበሩት ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ጸጋው ሲሆኑ፣ ታስረው የሚገኙትም በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጣቢያ መሆኑ ታውቋል።የተጠረጠሩበት ዘገባ  ስለ ጤና ባለሙያወች የተሠራ ዜና ከመሆኑ ውጭ ዝርዝር መረጃውን ለማወቅ አልተቻለም።
👍1
በ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ከዘመቻ ሰማዕታት ጎን ለጎን የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ኃይል እየፈራረሰ ይገኛል፡፡

1.ጌታቸው ካሲ ይባላል የሸበል ተወላጅ የዱሀ ከተማ ተጠርንፎ አገዛዙን በማገልገል የቆየ ቢሆንም የአረመኔው አገዛዝ በመክዳት ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድን ከእነሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል።

2. ጀማል ኤብሮሺ የፍቸ ሰላሌ ተወላጃ የአረመኔው አገዛዝ ስራዊት አባል ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም አ.ፍ.ብ.ሃ .ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ተቀላቅሏል።

ከዘመቻ ሰማዕታት ጉን ለጎን ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም  የአ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ 4ኛ ሻለቃ የቀብኃና ቀጠና የሆላ ደጀን  ከፋኖው ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ጥልቅ ወይይት በማድረግ የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ አሰቀምጦል።በውይይቱም የ4ኛ ሻለቃ የሆላ ደጀን ሰብሳቢ ም/ል ሰብሳቢ እና ቁጥጥር በተገኙበት ውይይቱን በማድረግ በየቀበሃና ቀበሌ የሆላ ደጀን ሰብሳቢ እና ም/ል ሰብሳቢ በመምርጥ ውይይቱ በሰላም ሲጠናቀቅ፡፡

ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም አ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህግ እና ስነ-ስርዓት ጉባኤ ክፍል ደባይ ጮቄ ብርጌድ ስር በሚገኙ የናብራ 4ኛ ሻለቃና የመቶ አለቃ አደነ ጤነው 3ኛ ሻለቃ የሚያሰተዳድሯቸውን ቀበሌዎች የቀበሌ ጊዜአዊ አሰተዳደሮች የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ሸንጎ አካላት እንዲሁም የብርጌዱ አመራሮች በተገኙበት ስለ ፍትህ አሰጣጥ ስልጠና ተሰጥቷል።

        ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም

   ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
አ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጣና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
2
ከወለጋ ክፍለ ሀገር ቢዛሞ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!!!!
2🙏1
ስብሰባው ተጠናቋል !!

በርካታ መኮንኖች እና ጀኔራሎች የተገኙበት ስብሰባ ተጠናቋል ። በስብሰባው አብይ ብሔራዊ ጉዳይ ያላቸውን የጦር ድግሶች አንድ ሁለት ብሎ ዘረዘረ ።

በመሐል የፋኖ ጉዳይ ምን ይደረግ ? ብለን ጠይቀን ነበር ።
መልሱም :- ፋኖ ያለው እዚህ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው ። እንዲያውም ጨካኙ ፋኖ ያለው እዚህ ውስጥ ነው ብሎ አይኑን ወደሆኑ ሰዎች አፈጠጠ ።

ቴክኖሎጂ ታጥቀናል በማለት ደብረብርሃን እና አዋሽ አካባቢ ያከማቿቸውን ዝንቦች እና ስልታዊ ማፈግፈግ የሚያደርጉ ታንኮችን እንዲሁም የአጭር ርቀት ሚሳኤሎችን በስክሪን አሳይቶናል ።

እሱም እኔ ብቻየን ቀርቻለሁ ፍረዱኝ እናንተ መኮንኖች በማለት መከላከያ ሰራዊቱ ከላይ እስከታች መደማመጥ ፣ መናበብ እንዳልቻለ እና የፈራረሰ ተቋም መሆኑን ሳይሸሽግ ሳይደብቅ ተናገረ ።

በአንድ በኩል ልሞት እችላለሁ በሌላ በኩል እናሸንፋለን የሚል ከራሱ ጋር የተጣላ ሐሳብ ተናገረ ።

በአጠቃላይ በስብሰባው በሚዲያ የማይወጡ በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል ።

አስገራሚው እና በአንደበቱ የተናገረው ነገር :- ከግማሽ በላይ የሚሆነው ጀኔራል እና ሚኒስቴር ለፋኖ በሚሰራበት በዚህ ጊዜ ከጎኔ ቁሙ በማለት መድረክ ላይ አለቀሰ ።

ድጋሜ ሌላ የጦር አዋጅ አውጆ ዛሬ 4:30 ላይ ስብሰባው ተጠናቋል ።

ደሞኮ ፅንፈኛው ምናምን አላለም ። ፋኖ ነው እያለ ነው ሲያወራ የነበረው።
©ፋኖ ማርሸት ፀሐይ
🙏5
~ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የትግሉን አጠቃላይ ገጽታ የተመለከተ ሲምፖዚየም አዘጋጅቷል።

በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልወና አደጋ ለመመከት ላለፉት ሁለት ዓመታት ታላቅ ተጋድሎ እየተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በተበታተነ ሁኔታ የሚደረገውን ተጋድሎ ወጥ በሆነ ድርጅታዊ መዋቅር ስር ለማድረግ በተጀመረው ጥረት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የተወለደና ትግሉን በተሻለ ቁመና እየመራ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል። በጥቂት ታጋዮች ከኋላ ቀር መሳሪያ የተነሳው የአማራ ፋኖ ትግል በሁለት ዓመት ውስጥ ያስመዘገበው ድልና የገነባው ግዙፍ ወታደራዊ ሃይል የተጀመረውን የህልውና አደጋ ለመመከት በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ አድርጎታል። ምንም እንኳን ትግሉ ከሚፈልገው አቅምና ብቃት እንዲሁም የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው መከራና ስቃይ አንጻር የምንገኝበት ምዕራፍ ገና ብዙ እንደሚቀረን የሚያሳይ ቢሆንም በቁርጥኝነትና በተባበረ ሃይል ከቀጠልን በቅርብ ጊዜ የአገዛዙን የጭቆና ቀንበር በጣጥሰን እንደምንጥል ጥርጣሬ የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም።

ለዚህም የተጀመረውን የአንድነት ጉዞ ማፋጠንና ወደኋላ የማንመለስበት የፋኖ ወጥ መዋቅር ለመገንባት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረግን እንገኛለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለዚህ የአንድነት ጉዞ የሚረዳና የተጋረጡብንን ችግሮች በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ታላቅ ሲምፖዚየም ማዘጋጀቱን ሲገልጽ በደስታ ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ከዚህ አቅሙ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆንና የትግሉ ጊዜ ባጠረ መልኩ ለመቋጨት ያስችል ዘንድ እና ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ሂደትና ዓላማ ግልፅ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅ እና በጎ ፈቃደኛ ደጋፊዎችን ለመጨመር ያለመውን ይህን ሲምፖዚየም ጷጉሜ 01 እና 02 ቀን 2017 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ አቆጣጠር September 06,2025 Saturday Starting 12 Noon and September 07,2025 Sunday Starting 12 Noon በቀጥታ ስርጭት የሚያካሂድ መሆኑን ያስታውቃል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አመራሮች በጋዜጠኞች ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል፣ ዝግጅቱም በቴሌቪዥንና በዩቲዩብ፣ ቲክቶክ እና የX (Twitter ) ማህበራዊ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

በዚህ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ሲምፖዚየም ተሳታፊ በመሆን የአማራ ህዝብ የታወጀበትን እልቂት ለመመከት እየታገለ ያለውን የአማራ ፋኖ በመደገፍ፣ ከአማራም አልፎ በየተራ ሁሉንም ብሄሮች በማጥቃት የጭቆናና የባርነት ስርዓቱን ለማስቀጠል እየሰራ ያለውን "ብልፅግና" የተሰኘውን ጸረ ሕዝብ አገዛዝ እንድንታገልና ሀገርን ከመፍረስ እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል - አፋብኃ
🙏4
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

አደም አሊ ክፍለጦር መክት ብርጌድ ቦረና ገነቴ ከተማ አቅራቢያ ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ ድል ተጎናፀፉ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር ሳጅን አደም አሊ ክፍለጦር መክት ብርጌድ ቦረና ገነቴ ከተማ አቅራቢያ አገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ጥምር ጦር ጋር በመፋለም ከአንድ ጓድ በላይ በመደምሰስና በተመሳሳይ ቁጥር በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ተጋድሎው ነሃሴ 29/2017 ዓ.ም ጧት 2:00-8:00 የተደረገ ሲሆን ለስድስት ሰዓት ከተደረገው ፍልሚያ በኋላ ጠላት ሬሳና ቁስለኛውን ታቅፎ ገነቴ ከተማ ገብቷል:: የአባ ናደው አርበኛ ሳጂን አደም አሊ ልጆችም ምሽጉን ለቆ ማጥቃት የመጣን ጠላት በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ሙትና ቁስለኛውን በማስታቀፍ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ነሃሴ 30/2017 ዓ.ም
🙏4