ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1500 ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሠላም አደረሳችሁ ።

ለአማራ ህዝብ ነፃነት ስትሉ በአራቱ ማዕዘን በዱር በገደሉ እየተዋደቃቹህ ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ #የአማራ ፋኖዎቻችን፣መሪዎቻችን ወገኖቻችን እንኳን አደረሳችሁ ።

መልካም የመውሊድ በዓል 🙏
2
አንድ የአገዛዙ መረጃ ሆድ አደር ፓሊስ ላይ እርምጃ ተወሰደ!

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ካራማራ ክ/ጦ በድጋሚ ነሐሴ 28/2017 በተደረገው ልዩ ኦፕሬሽን በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ አንድ የአገዛዙ አገልጋይ ሆድ አደር ፓሊስ ሳጅን__ ከገንዳውሀ ወደ ኮኪት በባጃጅ ሲቀሳቀስ በተደረገው ክትትል በተኩስ ልውውጥ እስከወዲያኛው ተሸኝቷል።

በተደጋጋሚ በተደረገ ክትትል ንፁሀንን በተለይ ወጣቶችን የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ሰበብ ለአገዛዙ አሳልፎ በመስጠት ብዙዎችን ለግርፋትና ለስቃይ ከመዳረጉ ባሻገር በእስር ቤት ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው እና አላግባብ ከፍተኛ ገንዘብ እየተጠየቁ ለሆድ አደሮች የገቢ ምንጭ ሰለባ እንዲሆኑ አድርጓል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
                              
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ

         ነሐሴ 29/2017
2🙏2
የተዋጊ መሀንዲስ አመራሩ ፋኖን ተቀላቀለ❗️

የአፄ አምደ ጽዮን ኮር ምኒሊክ ክፍለጦር ለተከታታይ ቀናት በሰራው ከፍተኛ የደሕንነት ስራ እራሱን "ልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 104ኛ ክፍለጦር" ብሎ የሚጠራው  ሁለተኛ (2ኛ) ሻለቃ የተዋጊ መሀንዲስ አመራሩ ከነ ሙሉ ትጥቁ ጀግናው ሰራዊታችንን በሰላም ተቀላቅሏል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሐድ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር የምኒሊክ ክፍለጦር ሰሞኑን በተለያዩ ሁለት ግንባሮች ማለትም በመንዝ ቀያ ወረዳ ዘመሮ ከተማ እና በእንሳሮና ዋዩ ወረዳ በበልበሊት ቀጠና በአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ስብስብ ላይ ከፍተኛ ድል ከመቀዳጀቱም በተጨማሪ ከፍተኛ የከተማ ውስጥ የደሕንነት ስራ በመስራት የብርሀኑ ጁላን የሰራዊት ቁመና የሌለውን የዘራፊ ስብስብ እያፈራረሰው ይገኛል።

ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2017ዓ.ም የእምየ ምኒሊክ ልጆችን የተቀላቀለው የተዋጊ መሀንዲስ አመራሩ በቀጣይ እሱ የሚመራው ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ፈርሶ ፋኖን እንደሚቀላቀል የተናገረ ሲሆን እራሱንም ለዝሕ ውሳኔ ያበቃው በተቋሙ ውስጥ የሚታዩ ብሄር ተኮር የሆነ አድሏዊ አሰራሮች በተለይ በደቡብ እና በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ግፍና በደል እየተፈፀመ መሆኑን ለአፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በሰጠው የስልክ ማብራሪያ አረጋግጧል።

ከነ ሙሉ ትጥቁ ፋኖን የተቀላቀለው የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ የልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 104 ኛ ክፍለጦር አባሉ:-
   ~ አንድ ዘመናዊ ጥርጥር ክላሽ (ሞረት ክላሽ)
   ~ 150 የክላሽ ጥይት
   ~ 5 ካዝና 
   ~ በርካታ ምስጥራዊ ዶክመንቶች እና
   ~ የደረት ትጥቅ ለምኒሊክ ክፍለጦር አስረክቧል።

ላለፉት 321 ቀናቶች ቆይታውን ከፋኖ ጋር ያደረገው በጥቅምት 20 ቀን 2017ዓ.ም ከተመሳሳይ የልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 104ኛ ክፍለጦር በመውጣት የምኒሊክ ክፍለጦርን ተቀላቅሎ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ እየታገለ ያለው የደቡብ ኢትዮጵያው ተወላጁ ዛሬ ፋኖን ለተቀላቀለው የአገዛዙ ወታደር አባል በሰላም ወጥቶ ፋኖን እንዲቀላቀል ትልቁን ሚና መወጣቱን በመግልፅ ለቀድሞ የትግል አጋሩና ለምኒሊክ ክፍለጦር የፋኖ አባላትና አመራሮች ላደረጉለት ደማቅ አቀባበል ታላቅ ምስጋናውን አቅርቧል።

በመጨረሻም የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል "ወቅታዊ የአገዛዙ ሰራዊት ቁመና ምን ይመስላል?" በሚል ፋኖን ለተቀላቀለው የሰራዊቱ አባል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን በምላሹም "በተለይ ሰሞኑን በአገዛዙ ቤት ከፍተኛ ትርምስ እና መደናገጥ እንዲሁም አብዛኛው ሰራዊት ከሚቀርበው የትግል ጓዱ  በተናጠል ተቀምጦ እንዴት ተቋሙን ለቆ የሚጠፋበትን መንገድ ብቻ ነው የሚያወራው ሲል ይመልሳል።

ለዝሕ መደናገጥ ዋና ምክነያት የሆነው ደግሞ በዝሕ ሰዓት በሰራዊቱ ውስጥ "የአማራ ፋኖ አንድ ሆኗል!" የሚል አስደንጋጭ ነገር የሰራዊቱን ካምፕ አምሶታል በዝሕ የተነሳ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እየጠፉ ይገኛሉ ሲል በተቋሙ ውስጥ ያለውን አሁናዊ መረጃ አጋርቶናል።

   ════❁✿❁════

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ!!
2🙏1
ተጠናክሮ የቀጠለው የወለጋው ከባድ ጦርነት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ ወረዳ ዛሬ 5ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሀይለኛ ጦርነት እዬተደረገ ይገኛል ትናንትና እስከ ምሽት በቀጠለው ጦርነት ብዛት ያለው የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳርያ ተማርኳል አገዛዙ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ከፍተኛ ሀይል ከዬአካባቢው በማስገባት ሙትና ቁስለኛውን እዬሰበሰበ ወደ ቱሉ ጋናና ደንጎሮ(ቱሉ ዋዩ) ከተሞች እያጋዘ እንደሚገኝ የአካባቢው ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል።

ጦርነቱን ያለ እረፍት በተቀናጀ ሁኔታ ለተከታታይ ቀናት እያደረገ ያለው የአማራ ፋኖ በወለጋ ከአገዛዙ የተቃጣበትን ጥቃት በብቃት እዬመከተ እንደሚገኝና ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን እንዲሁም ትናንትና ማታ ብጅት ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ሚኒሻና መከላከያ አስክሬን ላይ የፋኖ  ሀይሎች እዬተረማመዱ ሲጨፍሩ እንደነበር የአይን እማኞች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል።

ጦርነቱ ዛሬም በጧቱ ምድርና ሰማይ ሲላቀቅ በከባባድ መሳርያ ታጅቦ የቀጠለ ሲሆን አዲስ የገባው የአገዛዙ ሰራዊትም ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገደ እንደሚገኝ የአካባቢው ኗሪዎች ገልጸውልናል።

ነሐሴ 29/2017ዓ.ም
  
1👍1
ደብረኤልያስ የቀጋት ቀበሌ እና  የጁቤ የላምጌጅ  ከተማ ላይ ውጊያዎችን ስናደርግ አርፍደናል። በዚህ ጠላት ላይ ከፍተኛ ማጥቃት የተደረገ ሲሆን በርካታ የአረመኔው ሰራዊት አባላትን መደምሰስና ማቁሰል ያስቻለ ውጊያ አድርገናል።

በተመሳሳይ ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ትናንተና ዛሬ በሰራው የከተማ ኦፕሬሽን ሁለት በብልፅግና ደንነት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ የፖሊስ አባላትን አንቆ ማውጣት ችለዋል። በዚህ መሃል  በተፈጠረው ውጊያ በርካታ የመከላከያ አባላትን መደምሰስ ችለዋል።

በየቀኑ ምሽግ ድረስ በሚደረግ ውጊያ እና ሰርጎገብ ጥቃት  የተማረሩ የአረመኔው ሰራዊት አባላትም እጅ እየሰጡ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለትም  ሶስት የአረመኔው ሰራዊት  አባላት ደብረ ማርቆስና ፈንድቃ ከሚገኘው የአረመኔው ካምፕ በመክዳት  አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
1ኛ/ ጌታሁን ፍሬው ተማረ ከስልጠና ቦታ የከዳ ጀሌ
2ኛ/ ዋለልኝ ሞሴ ሳልለው ሰላም አስከባሪ ከነሙሉ ትጥቁ
3ኛ/ ስላተ አሳየ አስቻለ ሰላም አስከባሪ  ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።
🙏5
የደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ በጠላት ላይ ድልን ተጎናጽፏል።

በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ እዝ  የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ 6ኛ ክ/ጦር  የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች ከደብረ ኤልያስ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው  በየቀጋት ቀበሌ  የመሸገውን የአረመኔ ስብስብ በእሳት አለንጋ ሲገርፉት አርፍደዋል።

ውጊያው ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ላይ የተጀመረ ሲሆን ከተኛበት የደረሱት የተኮሷት ጥይት በከንቱ የማትወድቀው በመሳሪያዎቻቸው የሚራቀቁት ቀስተኞቹ በጠላት ምሽጎች እየተረማመዱ የጠላትን ጭንቅላት እያፈራረሱ እዚያው በምሽጉ ይቀብሩት ጀመሩ።

በኋላም ስራቸውን ጨርሰው ከወጡ በኋላም  ጠላት ተከትሎ እንዲወጣ በተጠቀሙት ዘዴ ጠላትን ወደ ጎፍጭማ  ስቦ በማስገባት በብሬንና በስናይፐር ቅንድቡን እየላጩ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

የሙታን ስብስቡ የጠላት ሠራዊትም እስከ ረፋዱ 5:00 ድረስ በየጢሻውና በየገበሬው አዝመራ የወደቀውን አስከሬን ሲለቃቅም አርፍዷል።

በውጊያውም ከ20 በላይ የተደመሰሰ እና 5 አምቡላንስ ከባድና ቀላል ቁስለኛ  የተነሳ ሲሆን ከዚህ መሀል በርካቶቹ ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈር ተልከዋል።

ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር
🙏31
የአገዛዙ ብልዕግና የጋዜጠኞች አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ ሁለት  ጋዜጠኞች  ታስረዋል።

የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ ሁለት ጋዜጠኞች ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓም ከተላለፈ ዜና ጋር በተያያዘ ትናንት ነሐሴ 28 ቀን 2017ዓም  ተጠርጥረዉ መታሰራቸው ታወቀ።

በተላለፈው ዘገባ ተጠርጥረው የታሰሩት በእለቱ ተረኛ የነበሩት ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ጸጋው ሲሆኑ፣ ታስረው የሚገኙትም በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጣቢያ መሆኑ ታውቋል።የተጠረጠሩበት ዘገባ  ስለ ጤና ባለሙያወች የተሠራ ዜና ከመሆኑ ውጭ ዝርዝር መረጃውን ለማወቅ አልተቻለም።
👍1