ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram

‎አስደንጋጭ ዜና
‎የብልጽግና የጥፋት ቡድን የአንድ ቀን አራስ ከአምቡላስ በማስወረድ አንቡላንሷንን አቃጠለ
‎=============
‎ወንበደው እና በአማራ ጥላቻ የታወረው የብልጽግና ስርዓት የአንድ ቀን ህጻን ይዛ ከወረኢሉ ተነስታ ወደ ግሸራቤ የምትጓዝ አምቡላስ አቃጥሏል ።

‎ንብረትነቷ የግሸራቤ ወረዳ የራቤል ጤና ጣቢያ የሆነች አምቡላስ ከወረኢሉ ተነስታ የአንድ ቀን ህጻን ይዛ ወደ ራቤል ከተማ እየተጓዘች እያለ ብልጽግና መልምሎ ባሰማራቸው የጥፋት ቡድን በወረኢሉና ግሸራቤ ወረዳ አዋሳኝ ቦታ ላይ ተቃጥላለች።

‎የአምቡላንስ ቃጠሎው የተፈጸመው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን ፋኖን ከአማራ ህዝብ ለመነጠል በፋኖ ስም አደራጅቶ ባሰማራቸው የሚኒሻ አባላት ነው።

‎የስርዓቱ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በግሸ ራቤ እና ወረኢሉ አካባቢ ያለውን ጠንካራ የፋኖ ይዞታ በሀይል ለማስለቀቅ አቅም ሲያጥረው የአንድ ቀን ህጻን ከአምቡላስ አውርዶ አምቡላንስ በማቃጠል ፋኖን ከህዝብ ለመለየት የሄደበት ሴራ የራሱን የመንግስት እኩይ ተግባር በአደባባይ አስጥቶለታል።

‎ይሕንን እኩይ ሴራ ለመፈጸም የተገደደው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን ፋኖ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ተቀባይነት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ከርችሞት ሲሆን ስርዓቱ ከገባበት የፍረሃት አሮንቃ ውስጥ ለመውጣት ሲል ለወራት በጀት በጂቶ ስልጠና ሰጥቶ በፋኖ ስም ባሰማራቸው የሚኒሻ አባላት ይህን በአለም አቀፍ ህግ የተከለከለ ፅዩፍ ድርጊት ፈጽሞታል።

‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር የብሩኬ ደምሴ ብርጌድ ቃጠሎው በተፈጸመበት ቦታ በመንቀሳቀስ ባደረጉት ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ካዋሏቸው ተላላኪ የብልጽግና የጥፋት ቡድን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አገዛዙ በጀት መድቦ ስልጠና ሰጥቶ ያደራጃቸው መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

‎ይህንን እኩይ ተግባር የአፋብኅ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ አጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር የብሩኬ ደምሴ ብርጌድ ቃጠሎውን የፈጸሙትን አካላት ይዞ እያካሄደ ያለውን ዝርዝር ምርመራ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ከወድሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም
3👍1
ሰበር ዜና !!!
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

“..... አንድ ሁኑ!" ብ/ጀኔራል አሳምነው ፅጌ

ትግላችንን አንድ ቅርጽ' አንድ መዋቅር፤ አንድ ደርጅት፤ አንድ መርኅና የአሠራር መልክ ማስያዝ የኅልውና ትግላችን የማሸነፊያ ቁልፍን እንደመጨበጥ መሆኑን ሕዝባችን፤ ስራዊታችን እንዲሁም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በጽኑ የሚያምንበት ጉዳይ ነው፡፡

አማራነትን የሚጸየፍ ኢትዮጵያዊነትንና አማራነት የጎደለውን አውራጃዊነትን እንደምንጸየፈው ሁሉ ልዩነትን የማይታገስ አንድነትን እንዲሁም አንድነትን የማይቀበል ልዩነትንም እናወግዛለን: የአማራን ሕዝብ ትግል በአንድ ድርጅት ጥላ ሥርየማንበር፤ በእንድ መዋቅር የመሰብሰብ እንዲሁም በተመሳሳይ መርሀና አስራር እንዲመራ ማድረግ በብዝኃ ሀሳብ የሚሰራውን ያክል በብዝኃ ሀሳቦች መካከልም ልዩነት እና ልዩነትን መቻቻል የሚጠበቁ ጉዳዮች ናቸው:: ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው፡ ልዩነትን መግራት ደግሞ ብስለት ነው፡፡

በመሆኑም በቋራ ቃል ኪዳን ድርጅታችንን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን ከመሰረትን በኋላ በአማራ ፋኖ በጎጃም በኩል የተነሱ የልዩነት ሀሳቦች ነበሩ፣ እነዚህ የልዩነት ሀሳቦች በውስጥና በውጭ ገፊ ምክንያቶች መልካቸውንና ዓይነታቸውን እየቀያየሩ ቢቆይም በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች በዛሬው ዕለት ማለትም ነሃሴ 27/2017 ዓ.ም መቋጫ አግኝቷል፤ በመካከላችን የተፈጠሩ ልዩነቶችን ፈትተን አንድ ሆነናል፣ በውይይታችንም የቋራ ቃል ኪዳንን አድሰናል፡፡ በዛሬው ዕለትም ሙሉ የአፋብኃ የኮማንድ አባላት በተገኘንበት የድርጅታችንን ጉዞ ገምግመን ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠናል፡፡ ስለሆነም የአማራ ፋኖ በጎጃምም እንደሌሎቹ ቀጠናዎች ሁሉ ከዚህ ቀደም በቀን 18/10/2017 ዓ.ም በድርጅታችን በተገለጸው መግለጫ መሰረት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና - ቴዎድሮስ ዕዝ ተበሎ የሚጠራ ይሆናል፡፡

በመጨረሻም መላው የአማራ ሕዝብ፣ ደጋፊዎቻችን፤ የሚዲያ አካላት እንዲሁም ሰራዊታችን በስትራቴጅ፣ በእውቀት፣ በእውነት፣ በወንድማዊና ጓዳዊ መስተጋብር የድርጅታችንን አንድነት ጠብቀን እንድንጓዝ እያሳሰብን በመካከላችን በነበሩ ልዩነቶች ምክንያት ለተፈጠሩ ችግሮች በሙሉ የድርጅታችን ማዕከላዊ ኮማንድ ሕዝባችንንና ስራዊታችንን ከልባችን ይቅርታ እንጠይቃለን!! ትግላችንን በውስጣዊ ዴሞክራሲ፤ በመርህና በድርጅታዊ አሰራሮች ለመምራት እና የውስጥ ጉዳዮቻችንን በውስጥ ለመፍታትም ቃል እንገባለን!!!

ጎልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል
7🙏2
ሰበር ዜና
በፋኖ ድል የተበሳጩት የአገዛዙ ወታደራዊ መኮነኖች!!
አዲሱ የብልፅግና ሰራዊት ኩብለላ!!
አደገኛ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በኦሮሚያ !!!
1
ሰበር ዜና
በፋኖ ድል የተበሳጩት የአገዛዙ ወታደራዊ መኮነኖች!!
አዲሱ የብልፅግና ሰራዊት ኩብለላ!!
አደገኛ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በኦሮሚያ !!!
1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
አራት ዕዞች አሉት ።ሙሉ መጠሪያቸውም እንደሚመለከተው ነው!!
፩ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
፪ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ
፫ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ
፬ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ናቸው።

ድርጅቱ ከዛሬ ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስራ የጀመረ ስለሆነ ማንኛውም አይነት ውስጣዊና ውጫዊ ጥያቄዎቹን ለመመለስና ያባከነውን ጊዜ የሚያካክስ ተግባራትን ለመፈፀም ቀንና ለሊት እንደሚተጋ የወሰነ ስለሆነ በቀጣይ ጊዜያት ትግሉን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ ዛሬ አስፈንጣሪ ውሳኔ በመወሰን የቋራ ቃልኪዳንን አድሷል።

ተፈጥሮ ለሰነበተው ክፍተትና ተከትለው ለመጡ ማንኛውም አይነት ጥፋቶች ይቅርታ የጠየቀው አፋብኃ በቀጣይ ወገን በነቂስ ከጎኑ እንዲቆምም ጥሪ በማስተላለፍ የአንድነት ብስራት አውጇል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
🙏6👍1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲምፖዚየም - ጷጉሜ 1 እና 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ከምሽቱ 1 ሰዓት
👍2
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 2ኛ /ተፈራ ዳምጤ/ ክፍለ ጦር ከመዝገበ ጮቄ ብርጌድ ለሰዴ ከተማና አካባቢው ማህበረሰብ  የተላለፈ መልዕክት

ድሮ ተናግረናል፣ ዘንድሮም እየተናገርን ነው ግን ደግሞ ነገም በተመሳሳይ እንደ ድሮውና እንደ ዘንድሮው ብልሹ የሆነ አሰራር መቀጠሉ አይቀሬ ነው ።ስለዚህ ነገችንን ዛሬ ላይ ሁነን አሰራሮችን ለማስተካከል ትልቅ ትግል ላይ ነን።  ይህንን ደግሞ ከሰልፍ አልፈን ሰይፍ አንስተን እየታገልነው መሆኑን ሁሉም ያውቃል ። ሁኖም ግን ከሞት አፋፍ ላይ ያለው ተስፋ ቆራጩ የብልፅግና መንግስት ነኝ ባዩ አሸባሪ ቡድን እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚል ህዝባችንንና የህዝባችንን ንብረት በእራሱ እንዲሁም በዘመዶቹና በሚቀርባቸው  ስዎች ሀብት እያካበተ ይገኛል።

ገንዘብ ከሚሰበስብባቸው መንገዶች አንዱ የከተማ መሬትን በሊዝ መልኩ ማለትም ውስብስብ በሆነ የማጭበርበር ዘዴ አንድም ለሆዳም የብልፅግና አሽከር አልፎም ለዘመዳ አዝማድ እያስረከበ እንደሚገኝ ደርሰንበታል።

እናም ከሀምሌ 27/11/2015 ዓ.ም ወዲህ በሰዴ ከተማ በየትኛውም መንገድ የሊዝም ሆነ የምራታ መሬት የሚቀበል ግለሰብ ካለ በብርጌዳችንም ሆነ በድርጅቱ  ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እያሳወቅን ከላይ በጠቀስነው መንገድ ቦታ ለመቀበል ሂደት የጀመረ ካላችሁ እንድታቆሙ እናሳስባለን። ይህንን መመሪያ ጥሶ የተገኘ ግለሰብ የገዛውን መሬት ከመነጠቅ አልፎ ተጨማሪ ቅጣት እንደሚጠብቀው ማሳወቅ እንደወዳለን።

መዝገበ ጮቄ ብርጌድ

ድል ለአማራ ፋኖ
ክብር በጀግንነት ለተሰው ሰማዕታት
👍1
ዘመቻ ሰማዕታት እንደቀጠለ ነው።
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ  ሀዲስ አለማየሁ ክፍለጦር አብራጅት ብርጌድ ከየጁቤ ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው የላምጌጅ ከተማ ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመፈፀም የአረመኔው ሰራዋት ጠርናፊ የነበረውን አበበን ጨምሮ በርካታ ሰራዊት መደምሰስ ችሏል።
ከጥዋቱ የጀመረው ውጊያ እስካሁን የቆየ ሲሆን በጠላት ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራን ማድረስ ችለዋል። 

በተመሳሳይ ቀኝጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ዛሬም ቸርተከል መገንጠያ ሞሰቢት ተራራ ላይ  በሌሊት ጥቃት ፈፅሟል።
አረመኔው ሰራዊት በተኛበት የደረሱት አይበገሬዎቹ የጎዛምን አንበሶች ጠላትን ሲረፈርፉት አድረዋል።

አረመኔው ሰራዊትን እረፍት በመንሳት ፣በመጠዝጠዝ ፣በማዋከብ መድረሻ እንዳያጣ በማድረግ እየተደመሰሰ  ይገኛል።በዚህ የተማረረው እና የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው ለፋኖ እጅ እየሰጠ ይገኛል።

በትናትናው እለት  ሁለት የአረመኔው ሰራዊት አባላት ከእነማይ ወረዳ ጠልማ ቀበሌ ከሚገኘው የአረመኔው አገዛዝ ካንፕ  በሐክዳት  የፋብኃ ምዕራብ  አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል፡፡
ይደርሳል ካሳሁን  እና አማኒኤል አሰፋ አድማ ብተና  የነበሩ ፋኖን ከነሙሉ ትጥቃቸው ሲቀላቀሉ ደማቅ አቀባብል ተደርጎላቸዋል።

አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ነሀሴ 28/2017ዓ.ም
👍2
መራሩ የአማራ ህዝብ ሀዘን በኦሮሚያ !!!

በርካታ ንፁሀን አማራዎች በኦሮሚያ እና መተከልበ ብልፅግና ሀይሎች ተገደሉ።

ዛሬ በጥዋቱ መተከል ዞን ወደ ድባጤና ቡለን ወረዳዎች የገባው የአገዛዙ ዘራፊ ታጣቂ 12 ንፁሃን አማራዎችን ገድሎ ከ60 በላይ ሰዎችን አግቶ ሲወስድ በርካታ የቁም እንስሳትን ዘርፏል ሀብት ንብረት አውድሟል ሲሉ የአካባቢው ኗሪዎች ገልጸውልናል።

ነሐሴ 28/2017ዓ.ም
1
ከሰሞኑ በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች ያሰለጠናቸዉ ወታደሮችን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ማስማራቱ ተገለፀ።

ዛሬ ነሀሴ 27/2017 ዓ.ም 79 ታታ ባስ ወደ ጎንደር ቀጠና ተሰማርቷል።ወደ ጎንደር ከተሰማረዉ ሰራዊት አብዛኛዎቹ ህፃናት መሆናቸዉም ታዉቋል።አገዛዙ ብልፅግና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በአስገዳጅ ሁኔታ ያፈሳቸዉን ህፃናት በለብለብ ስልጠና አስመርቆ ወደ አማራ ክልል እያሰማራ ይገኛል።ትናንት ከብርሸለቆ ወተ ወደ ጎጃም ቀጠና ሲሰማሩ በነበሩ መሰረታዊ ወታደሮች ላይ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ ዉድመት ተፈፅሟል።የድሀ ልጅን በመገብር ስልጣኑን እየራዘመ የሚገኘው አገዛዙ ትናንትም ከብርሸለቆ ያስወጣቸዉ ወታደሮች በአቸፈር በደርዘን የሚቆጠሩ የሰራዊት አባላት ስለመገደላቸዉ ነዉ የታወቀው ።

ዛሬም ወደ ጎንደር ቀጠና ከገቡ 70 የሰራዊት አባላት በቦታዉ ከመድረሳቸዉ መፈጥፋታቸዉ የብልፅግናዉን መንግስት አስደንግጧል።በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት ብቻ ከብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ወተዉ ወደ ጎጃምና ጎንደር የገቡት አብዛኞቹ መኮብለላቸዉን ተከትሎ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ ብርሀኑ በቀለ ሀገር ጠል ባንዳዎች ሲል ሰራዊቱን ወርፏል።በሁለት ቀን ብቻ በመቶዎች የማቆጠሩ አባላት ከመዉጣታቸዉ መኮብለላቸዉን ተከትሎ የዕዙ አዛዥ የፋኖ ግልገሎች ሲል ወቅሷል።

ከወርሶ እና ጦላይ የሰለጠኑ የድሀ ልጆችም በበርካታ ባስ ተጭነዉ ወደ አማራ ክልል እየገቡ ነዉ መሆናቸው ተገልጿል።ጦርነትን አጀንዳዉ ያደረገዉ አገዛዙ የድሀ ልጆችን እያፈሰ በለብ ለብ ስልጠና ወደ አማራ ክልል በማስገባት ጦርነት ከከፈተ ሁለት አመታትን እያሳለፈ ወደ ሶሴተኛዉ አመት ተዘዋዉሯል።ዛሬም እንደ አዲስ ሰልጣኞችን ወደ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለማስገባት ወጣቶችን በየከተሞች እያፈሱ ወደ ማጎሪያ ቤት ማስገባት ጀምረዋል።በአዲስአበባ፣በጅማ፣በሀረሬጌ፣በወለጋ፣በአርሲ፣በመቱ እና በአማራ ክልል ሁሉም የዞን እና የወረዳ ከተሞች አፈሳዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ወጣቶች በአስገዳጅ ታፍሰዉ የአገዛዙ ስልጣን ማራዘሚያ ዋና መሳሪያ ከመሆናቸዉ በፊት ወደ ፋኖ ቀጠና በመሄድ ሀገራቸዉን ከመፈራረስ መታደግ እንደሚገባቸዉም ተጠቁሟል።
2🙏1